ብዙው ችግር በገዢው ፓርቲ ብቻ አይፈታም
ብዙው የኢትዮጲያ ሕዝብ ችግር በመንግስት የሚፈታ ሳይሆን የሞራል ጉዳይ ነው፡፡ ብዙ
ሰው የሚሰደደው የኢኮኖሚው ሁኔታን ለማሻሻል ሲሆን ማለትም የስራ ማጣት ጉዳይ ሲሆን ፤ አዛም አገር ውስጥ የሚንገላታው በግለሰቦች ጥላቻ
እና አሉባልታ ነው፡፡ ይህን ደግሞ ለማስከበር ለአንድ ሰው አንድ ጠባቂ ማቆም አይቻለም፡፡ እውነቱን ብናውቀውም መጋፈጥ
ስለሚያቅተን ሁሉንም ሸፋፍነን እናልፋለን፡፡ ኢትዮጲያ ውስጥ ይህ ነው የማይባል የሞራል ውድቀት አለ፡፡ በጣም የሚገርመው ግን በአሁኑ
ሰአት በማንኛውም እምነት ነጻነት ቢኖርም እና ሞራል የሚጠብቀው ስብከትም ቢሰበክ ግን ከመቼውም ዘመን የበለጠ ስግብግብነት እና
ማንአለብኝነት በሕብረተሰብ ውስጥ ብሶበት ይገኛል፡፡ ይህ የመጣው ከአገዛዙ ግድፈት ሳይሆን አለም የደረሰችበት የማተርያል አቅርቦት
ነው፡፡ ሰው ያያል፣ ለሚያየው ነገር ምኞት ይዳረጋል፡፡ ኢትዮጲያ የሚታዩ የገባያ አቅርቦት ከአለም ቢበልጥ እንጂ የሚተናነስበት
ጉዳይ የለም፡፡ ይህም እይታ ሁሉም ተጠቃሚ የመሆን ፍላጎትን ያሳድራል፡፡ ድንገትም ካለስራ ተነስተው ሀብት የሚያካብቱ ሰዎች ሌላውን
ተመልካች እሱ ከቻለ እኔም እችላለሁ የሚለውን አስተሳሰብ እንዲይዝ እንዲነሳሳ ያደርጋሉ፡፡ በእርግጥ ሙስናን እና አለአግባብ መበልጸግን
ዛሬ ባለው አገራችን የ ፖለቲካ ደረጃ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ነው፡፡ ግብር ሰው ሁሉ እኩል የማይከፍልበት አገርን ያለው ገዢ ፓርቲ
100% ተጠያቂ ማድረግ ይከብዳል፡፡ ምክናያቱም መሰረት ያልነበረው ጅማሮ ግብር ከፍሎ የማያውቀውንም ነጋዴ እጅግ ሊያስቆጣ የሚችል
ስለሆነ እነሱም ሙስናን እንዳይጠፋ የማድረግ አቅም ይኖራቸዋል፡፡ ወደህጉ ከመሄድ ህጉ ሊፈርስ የሚችልበትን ነገር ሊሄዱ ይችላሉ
እና፡፡ ትክክለኛ ግብር ከፋይ የመንግስት ደመወዝተኛ ብቻ ነው፡፡ ብዙው ሕዝብ ግብር መክፈሉ እየተላመደው የመጣ ቢሆንም፤ ግን የግብር
አተማመን ሁኔታው ብዙው በአድሎእና በሙስና የተተበተበ በመሆኑ ግብር ከፋዩን እሚያበሳጭ እና ተስፋ አስቆራጭ ሆኖአል፡፡ የግብር
ጉዳይ አድሎ፤ በዘመድ በጉቦእና በጥላቻ ተመን ነው፡፡ ልንቃወም የሚገባን ይህንን ነው፡፡ ማለትም ጥያቄያችን እኩል የምንስተናገድበትን
ሞራል ሲቪል ሰረቫንቱ እንዲይዝ ማድረግ ነው፡፡ አልያም መቅጣት ነው፡፡ አንዳንዶች ለመንግስት ግብርን በትክክል መክፈል ስላልተላመዱት
በጉቦ እናስቀንሳለን እያሉ የምንግስትን ባለስልጣናት በማባለግ እራሳቸውንም በመጉዳት ይገኛሉ፡፡ ምንም እንኩዋን ኢሕአዴግ ይበቃዋል
ይነሳ ቢባልም ግን እውነቱን ጠቃሚውን እና የአገር እድገትን ዲሲፒሊንን የሚያመጣውን ለማበረታታት ተቃዋሚዎች ሊደግፉት ይገባል፡፡
ተቃዋሚውን ማብዛት ማለት ለውጥ ማምጣት አይደለም፡፡ እነዚሕ እንዝላል የሆኑ ባለስልጣንን የማባለግ እና በስንጥቅ ትርፍ መኖርን፤
እነሱም ሊወጡት የማይችሉት ነገር ውስጥ እንደሚገቡ አልተረዱትም፡፡ ጉቦ ከፋይ ዜጋ ምንግዜም ከሚከፍላቸው ሰዎች ነጻ ሊሆን አይችልም፡፡
ይህ የመንግስት ገባሪ ሳይሆን የግለሰብ ኪስ አክባሪ ሞኝ ነው፡፡ ብዙው ነገር በሞራል የምናየው እንጂ ሕግን ለማስፈጸም ለአንድ ሰው አንድ ሌላ
ሰው የምንቀጥርበት አቅሙም የለም፡፡ምንአልባት እራሳቸውን ያልገዙ የመንግስት ባለስልጣኖች ቢኖሩ ይህ የፖለቲካ ግድፈት ሳይሆን የሞራል
ውድቀት ነው፡፡ እነዚህ ካሉ ገዢው ፓርቲ እራሱ ወደሕግ አምጥቶ የሚያስቀጣበት ዘዴ ካልፈጠረ ወዳቂ የሚሆነው እራሱ ነው፡፡ የፖሊስ
ቁጥርን የሚያበዛው የወንጀል ብዛት ስለሆነ፤ ግን ምን አይነት ወንጀል እንዳለ እና ውነት ይህንን ወንጀል የፖሊስ ብዛት ወይስ የአይምሮ
ንቃት ይቀንሰው ይሆን ብሎ የፖለቲካ ሳይንሱን ከተማረው ሕግ አውጭ ክፍል ጋር መነጋገር አለበት፡፡ በጭፍን በእልክ የምንጉዋዘው
ሁሉ የህዝብን ግንዛቤ የበለጠ ይዘጋዋል፡፡ በእርግጥም መንግስትን የጎዱም እየመሰላቸው ይህ መንግስት ከሚበላው የእነእከሌ ኪስ ቢዳብር
ይሻላል ወደሚለው የሚገቡም እልከኞች እንደማይጠፉ ግልጥ ነው፡፡ ይህ ለሌላው ከማሰብ የተነሳ ሳይሆን ተነክቶ የማያውቅ ሲነካ ጉድ
ፈላ ነው፡፡ ስለዚህ ህገመንግስት ወደሚተገበርበት መማማር እንዲቻል ጉቦ መቀባበል የአገሪቱን ባጀት ከመጉዳቱም በላይ፤ በሰው ልጅ
መካከል እኩልነት እንዳይሰፍን የሚያደርግ ነቀርሳ በመሆኑ የአገር ገቢ ላይ ሁሉም ትኩረት በመስጠት ቅጣቱ ጫን ያለ ቢሆን መልካም
ነው፡፡ መምጣት መነጋገር ግንዛቤ መስጠት መልካም ነው፡፡ በቸር
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen