ከየት ወደየት
ወደፊት ወይስ ወደሁዋላ፡፡ ማንኛው ይሻላል፡፡ የመረዳትን ጎዞ እንጂ የእግርን
እርምጃ አይደለም የምመለከተው፡፡ ደፋር እፈሪ መሃል ቀውስ ነው፡፡ ፈሪ ግን ፈሪ የሚሆነው ላለመሞት የተመኘ ነው፡፡ እንግዲሕ ይህን ስላችሁ መድፈሬም
መፍራቴም አልቀረም፡፡ ለመሞት ብዬ አይደለም የምናገረው፡፡ ለአገሬ መኖሬ እንጄ መሞቴ አይጠቅማትም እና፡፡ በሰው ልጅ ሕይወት የሚደሰት
ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ለምን ቢባል የእግዚአብሄር አላማ በዛ ሰው እንዳይገለጥ ስለሚፈልግ ነው፡፡ ብቻ ስለፖለቲካ ባይመለከተኝም ግን
ፖለቲካ በማንነቴ ላይ ጥሎ ጥሎ የሚሄደው ጠባሳ እንድነጋገርበት ያደርገኛል፡፡
ፖለቲካን እንዳመጣላቸው በይምሰል፣ በወኔ፣ በእልክ እና በብቀላ የሚወስዱት ከሆነ፤ ሕዝብ ሁሉ ላይ የአይምሮ ጥላሸት ጥሎ ያልፋል፡፡
ማነው ጤነኛው በኢትዮጲያ ምድር፤ ግፈኛው ወይስ የእሱ ተቃራኒው? ተረሻኙ ወይስ እረሻኙ፣ ተከሳሹ ወይስ ከሻሹ፣ መስካሪው ወይስ
የተመሰከረበት፣ ወንጀል ፈጻሚው ወይስ ተመልካቹ ሕዝብ፡፡ ብቻ ልናገር ልጽፈው ስፈልግ እንደታፈነ የንፍሮ ቶፋ ጉሮሮዬ ላይ ይሰማኛል፡፡ ገባችሁ ቶፋ እሳት ላይ ከተጣደ እውስጡ ያለው በቆሎ
ወይ ባቄላ ከፍላቱ ለማምለጥ ይታገላል፡፡ ግን የሚወጣው በቆሎው ሳይሆን የፈላው ውሀ ነው፡፡ እኔም እንግዲሕ ላወጣው ያልኩትን ለማውጣት
ስል ከእራሴ ጋር የማደርገው ትግል ከዛ ጋር ተመሳሰለብኝ፡፡ ወገኔን ይመቸው ይሆን ወይስ አይመቸው እያልኩ ትግል ግብ ግብ ያዝኩላችሁ፡፡
ስለዚህ ታፍኖ የኖረ እንደልቡ የሚሆንበት ወቅት ፈንቅሎ ከእራሱ የወጣል እና፤ ጥቂት ልበላችሁ፡፡
ደርግ የሚባለው የኮለኔል መንግስቱ ቡድን የተነሳው አዎ ግፍን ለማስቀረት ለውጥን ለማምጣት መሆኑ በሕዝቡ ውስጥ ተዳፍኖ የነበረው
ግን ሊወጣ ያልቻለው ብሶት ይናገራል፡፡ ትልቅ ነገሩ፤ ደርግ ትልቅ ባሕል ትልቅ ነገር ገርስሶ እንደጣለ አንድእና ሁለት የለውም፡፡
ንጉስ እና ባላባት አምላኩ የሆነውን ፤ ሰው ሰው እንጂ አምላኩ እንዳልሆነ አሳይቶታል፡፡ ከባርነትም የወጣ እኮ አለ፡፡ ለዘመናት
የማይደፈረውን ደፍሮአል፡፡ የፖለቲካ ለውጥ ጅማሮ ሀ ያለ ይመስለኛል፡፡ እምነትን ሊያጠፋ የተነሳው ደርግ፤ የጥላቻው አዋጅ ጭራሽ
የመጽሀፍ ቅዱስን ምንነት ያወጀ አስመስሎታል፡፡ የማያቀው ለማወቅ ምሽግ እረድቶታል እና፡፡ እምነትን ለማጥፋት ስትታገል፤ ወደመንፈሳዊ
ምሽግ ትገባለሕ፡፡ እምታምነው እምነት ምሽግ ውስጥ የመግባት አቅም አለውእና፡፡ ግን አንድእና ትልቁ ነገር ዛሬ ዛሬ ሊዘነጋ ያለው
ነገር ያ ደርግ ምሁር በላ ተብሎአል፣ ሰው በላው ተብሎአል፡፡ አንዲት
ዛሬ ከኔ እድሜ መለስ ያለች ሴት እንዲሕ ስትል አጫወተችኝ፡፡ አዳምጡ
“ደርግ መምጣቱ ለውጥ ለማምጣት እንደሆነ አውቃለሁ፡፡
ግን በዚህ በደርግ ሰው በላ መንግስት፤ ሚያዚያ 21 ቀን 1969 ዓ.ም ያየሁትን ልንገርሽ፡፡ ጉዋደኞቼ ጋር ተቀምጠን ጨዋታ እየተጫወትን፤
የብዙ ሰው ድምጽ ሰማን፡፡ ዋካታ ነበር፡፡ እኛም ድምጹ ወደሚተንበት ልንሄድ ብንል ቤተሰብ ከለከለን፡፡ የሚሰማው ድምጽ“ አትነሳም
ወይ አትነሳም ወይ የግፍ አገዛዝ አይበቃሕም ወይ ይሚል ነበር፡፡ ወዳውም የማያቁዋርጥ የጥይት ጩሀት ተሰማ፡፡ ሁሉም እየሮጠ በየቤቱ
ገባ፡፡ እኔም አልጋ ውስጥ ተደበኩ፡፡ ከትንሽ ግዜ በሁዋላ ብንወጣ እሬሳው ወደ 27 ነበር፡፡ ከሞቱትም ውስጥ መንገደኛውንም አግኝቶታል፡፡
እኔ በበኩሌ ደርግ ደርግ እያሉ እያሞጋገሱ ነውእና፡፡ ይህ አሁን ያለው ይሻለኛል፡፡“ ገባሽ ብላ እንደማንቀጥቀጥና እንደፍርሀት
ሆና አየሁዋት፡፡ „አዎ አልፈልግም አለች“፡፡ እየተናደደች „እስኪ ይታይሽ ምን አይነት ህሊና ነው፣ ከሚኒስተር ጀምሮ አንድ ሁለት
እያለ እና ስም እየጠቀሰ የፍየል ወጠጤ እያለ የረሸነ መንግስት፡፡ ንገሪኝ እስኪ 20 አመት ያልገባ ወጣት የሚረሽን ደሃ የሚረሽን፡፡
እኔ በበኩሌ አማራ ነኝ ግን ያንን ደርግ የሚባል ሰው ስሙንም ማንሳት አልፈልግም፡፡ ሕሊና የለውም እንዴ ሰው፡፡ እኛ እኮ ከምንጫወትበት
ሄደን ነው እሬሳ የቆጠርነው፡፡ እስከዛሬ ድረስ በስመአብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ከአይኔ አልጠፋም፡፡ መግደል ያላስፈራው መንግስት
ማነው መሰለሽ ደርግ እኮ ነው፡፡ እንዲሕ አይነት ሰው በሰበአዊ አገሮች በየአገሩ ለፍርድ ይቅረብ ይባላል ወንጀል የሰራ ሰው፡፡
እንዳው ህሊና የለውም ሰው እንደገና ጀግና ነው የሚሉን፡፡ በስመአብ፡፡ እረ እኔ ወያኔ ይሻለኛል፡፡ እነሱ ችግራቸው አማራ ትግሬ
እያሉ ያመጡብን ጦስ ነው እንጂ የሚያሳዝነን፡፡ በእርግጥ ደርግ አማራው ላይ ባይብስ እርሸናው፤ ግን
እሱ ለመግደልም ለመሾምም ዘር አልመረጠም፡፡“ እኔ የሚገርመኝ አለችኝ ከእኔ መልስ የሚጠብቅ መስላ፤ „መለስ የሞተው በሀጢያት ደግሞ
መንግስቱ የተረፈው በጽድቅ መሆኑ ማን መልስ መስጠት ይችላል ካለእግዚአብሄር፡፡ እኔ ግን ከመለስ እና ከመንግስቱ ብትይኝ መለስን
ነው የምመርጠው፡፡ አንቺስ? በአይኔ ያየሁት ያ የወጣት እሬሳ አይረሳኝም፡፡ ያየሁትን ነው እንጂ የምነግርሽ የሰማሁትንእማ ተይው
ታውቂው የለ፡፡ እናቴ እኔ እንዲሕ ስልሽ ከእኛ ዘር ውስጥ ደርግ የገደለብንም የሾመልንም የለም፡፡ እኛ ያልተማርን ነን፡፡ ግን
የቀበሌ ቤት አግኝተናል ቢሆንም ግን ቤቱ ውስጥ ኖረን ከተጠቀምነው በአይምሮአችን ይዘን እስከዛሬ የምንጉዋዘው ጎድቶናል፡፡ የፍርሀት
ድባብ ድር ያደራብን ካልሽ ደርግ ነው፡፡ ወይ ጉድ መንግስቱ ጻዲቁ
ሳይባሉ ይቀራሉ ብለሽ ነው እየቆዩ ቢሄዱ፡፡ እኒህ የግመል ሽንት
ነው የሚባሉት ወደሁዋላ የሚመለሱ ሰዎች፡፡ ወይጉድ ደሞ አማራ ናቸው አትበሉኝ፡፡ እነሱ የሰይጣን መልክተኞች እንጂ፡፡ ሀይማኖትን
እንኩዋን የከለከለ ደሞ እሱ፡፡ እኔ እስከማህተሜ ቆይቻለሁ፡፡ “
በማለት
ዘጋች፡፡ እኔም የነገረችኝን ዘገብኩ፡፡ ይቅር በሉኝ፡፡ ወደሁዋላ
ማየት ቁስል መቀስቀስ? በቸር እላለሁ፡፡
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen