Freitag, 7. März 2014

ምእራፍ 4 ኮኮቤ ኮኮቤ ---የሕግ የበላይነት



ምእራፍ 4
 ኮኮቤ ኮኮቤ ---የሕግ የበላይነት
ማንም ሰው ሳይሸማቀቅ እንዲኖር የሚያደርገው የህግ የበላይነት በመካከላችን ሲኖር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ነው ህጋችን የሚሉ ሰዎች ደግሞ፤ እግዚአብሄርን በደንብ ያልተረዱ ሰዎች ናቸው፡፡ ምክናያቱም የሰው ልጅ እግዚአብሄር ለሰጠው ሕግ መተዳደር ስላቃተው ለዚህ አለም ህግ ተላልፎ ተሰጥቶአል፡፡ የእግዚአብሄር ህግ መተግበር ብንችል ኖሮ ፖለቲከኞችም ባላስፈለጉን ነበር፡፡ ስለዚህ  ትክክለኛ ዲሞክራሲን ስናስተውለው የእግዚአብሄርን ሕግ በመከላካያ ሚንስተር እንደማስፈጸም  ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ እንዳትሳሳቱ ለትክክለኛ ዲሞክራሲ ነው ያልኩት እንጂ የተመሳሰለ ዲሞክራሲ አይደለም፡፡ ጥሩ ዲሞክራሲ መነሻው የእግዚአብሄር ህግ  ነው፡፡ እሱ አስቀድሞ ሰብአዊ መብትን ቁልጭ አድርጎታል፡፡ ስለዚህ የምድር ህግ መከበር በሰላም ለመኖር መነሻ ዋስትና ነው፡፡ የምድር ህግም ለሰብአዊ መበት ገደብ የለለው አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ የሰውን ልጅ አላግባብ ማንገላታት ሕግም ውስጥ ባይደነገግ የሚፈጸመው ሕገ መንግስትን በመናቅ ነው፡፡ ወሳኙ በሕግ የበላይነት ህዝብ በደንብ እንደሚኖር ካወቀ፤ ከመካከሉም ጥሩ ፖለቲከኞች ይወጡለታል፡፡ አንድ ሰው በነጻነት ለመኖር የግድ አንድ ወንጀልን የሚከላከልለት ሰው በአጠገቡ መኖር የለበትም፡፡ መተማመን ያለበት የሕግን የበላይነት  መሆን አለበት፡፡ ይህ በኢትዮጲያ ከድሮ ጀምሮ መተግበር ያቃተው፤  ስለህግ የበላይነት ያለን ግንዛቤ በጣም ዝቅ ያለ በመሆኑ ነው፡፡ የኢትዮጲያ ሰላም እና ነጻነት የሚከበረው የሕግ የበላይነትን እኩል ሁላችንም ስናውቅ ብቻ ነው፡፡ ሁልግዜ ለሕግ የበላይነት የሚጮሕ ተጎጂ ብቻ ከሆነ፤ ነገ አንተ በተራህ ደግሞ ትጮሃለሕ ማለት ነው፡፡ ሁሉንም ነገር ፖለቲከኞች ላይ ብቻ እያሳበብን ብናልፍ ዋጋ የለውም፡፡ እኔ ማነኝ ?የማስበው ምንድን ነው? የሌላውን መበደል እንዴት አያለሁ? የመሳሰሉ ሕሊናችን የሚጠይቀንን ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት መድፈር አለብን፡፡ ለምሳሌ ብዙ ሰው በየአጋጣሚው የሚደርስበት ችግር ሕግን በናቁ እነጂ ሕግ ያንን ሰው ብቻ አናሳ ለማድረግ ስለተደነገገበት ወይም ስለተጻፈ አይደለም፡፡ እራሳችንን ስናውቅ እርግጠኛ በዳይ ወይም ተበዳይ መሆናችንን ለይተን ማወቅ ይረዳናል፡፡ አንዱ ሊናገር የፈለገውን ሌላው እንዲናገርለት መፈለግ በእራሱ የህግ የበላይነትን አውቆ መጋፈጥ የማይፈልግ ነው፡፡ አንዱ ለሌላው የሚሞትበት ምክናያት የለም፡፡ በኢትዮጲያ አስቸጋሪ ሁኔታ የፈጠረብን ለሕግ ተገዢ የመሆን ብቃት ስለሚያንሰን ብቻ ነው፡፡ ይህ በሕብረተሰቡ ውስጥ የኖረ ያለ እና ላልተወሰነ ግዜ ወደፊትም የሚኖር ነው፡፡ ሁሉም አጥፊው ፖለቲካኛው ነው ብለን ውርጅብኝ እናወርዳለን፡፡ አይደለም ይህ ዞር ብለን ማሰብ እና መጋፈጥ የሚገባን ጉዳይ ነው፡፡ እስከመቸስ እራሳችንን አታለን እና ተሸነጋግለን እናልፋለን፡፡ ሕግ እየተጎዳ የሚሄደው በእራሱ በህዝቡ ነው፡፡ የህግን የበላይነት ያላወቀ አኑዋኑዋሩ እንደልቡ ሌላውን በመጉዳት ነው፡፡ ይህ ተፈጽሞአል እየተፈጸመም ያለ ነገር ነው፡፡ ፖለቲከኞችም እርስበእርሳቸው የሚናቆሩት የህግ የበላይነት በመካከላቸው እንደማይታወቅ እንደማይፈጸም ስለሚያውቁት ነው፡፡ ምንአልባት በጉልበት መኖር የማይፈልግ ሰው አቅም የሌለው ብቻ ነው፡፡ እርግጥ ነው አቅም ቢኖረው ማንም በማንም መጎዳት የሚፈልግ የለም፡፡ ማንም መብት የለውም ማጭበርበርም ሆነ ሌላውን መጫን፡፡ ይህ ግን በኢትዮጲያ በሕብረተሰቡ መካከል ይፈጸማል፡፡ ፖለቲከኞችን የምንወቅሰው በህዝብ መካከልም ባይፈጸም ነበር፡፡ ግን ግፍ በመካከላችን ሲኖር እያየን ነው፡፡ እጅግ በጣም ደካማ የሚጠቃበት አገር ነው፡፡ በውሸት ወይም ነገሮች እንደለሉ በማድረግ ኢትዮጲያን ልንለውጥ አንችልም፡፡ አዎ ኢሕአዴግም ቢለወጥ የማይለወጥ ነገር ይኖራል ፤ ግን ፖለቲከኛ ሊለውጠው የማይችል አሁንም ሊደገም የሚችል ስግብግብነት እና እራስን ወዳድነት እንደማይነሳ  ከወዲሁ ልታውቁት ይገባል፡፡ ይህ በሕግ የተደነገገ ሳይሆን የባሕሪ ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ብልሹ ባሕሪ በመካከላችን አለ፡፡
ማንም ሰው ይህንን አገናዝቦ የህግ ጠባቂ መሆን ያለበትን መንገድ መረዳት አለበት፡፡ ፐለቲከኞችም እርስ በእርሳቸው የሚያናቁራቸው ነገር ላይ ብቻ ትኩረት ከመስጠት የህግ የበላይነት እንዲታወቅ ሕብረተሰብ ውስጥ ገብተው መስራት ማነቃቃት አለባቸው፡፡ ገዢውም ሆነ ተቃዋሚው ማለቴ ነው፡፡ ሕግን አውቆ ማሳወቅ፡፡ እራስህ የማታደርገውን ከመጠበቅ እራስህ መጀመሪያ እያደረክ ህግን እያከበርክ ማሳየት ነው፡፡ እኔ መኖር የምፈልገው የሕግ የበላይነት አለበት አገር ላይ ነው፡፡ ግን ግን አገሬ ላይ የህግ የበላይነት የለም ግን አገሬ መኖር እፈልጋለሁ፡፡ ለዚህም የሕግ የበላይነት በአገሬ ላይ እንዲኖር እታገላለሁ እንጂ ለእኔ አበበ ገዛ ገብረእግዚአብሄር የሚያመጣልኝ ለውጥ የለም፡፡ ምንም የለም፡፡ የሕግ የበላይነት እስካልታወቀ ድረስ ሌላውስ ምን ያመጣል፡፡ ለምሳሌ ጀርመን አገር ጥቁር ማየት የማይፈልጉ ሰዎች አሉ፡፡ ግን እያኖረኝ ያለው ፖሊስ ጠብቆኝ ሳይሆን  ሕግ ነው፡፡ ይሕ ጥቁር የሚጠላው ሰው የሕግ ተገዢ ነው፡፡ በቃ የተቃጠለውን ያሕል ቢቃጠል የህግ ተገዢ የሚያደርገውን እውቀት ይዞአል፡፡ ለምሳሌ አንድ ትግሬ ወይም አማራ ተነስቶ በአማራነቴ ቢሰድበኝ፤ ሁሉ ሰደበኝ ማለት እንዳልሆነ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ ያ የሰደበኝ ሰው ያደረገው ምንድን ነው፤ የሚችለውን ችሎታው ጥላቻ ብቻ መሆኑን እና  ደግሞም ሕግ የደረሰበትን ደረጃ አለማወቁን  ግንዛቤውን አሳይቶኛል፡፡ ይህን እንዲያደርግ የሚፈቅድለት የተደነገገው ህግ ሳይሆን፤ የሕግን የበላይነት የማያውቁ ግለሰቦችን አመኔታ ሊሆን ይችላል፡፡ አንድን ሰው ህግን እንዲንቅ እና ህግን እንዲጎዳ የሚያደርገው ሕግን የሚያስፈጽመው ደካማው ጥቂት ግለሰብ ይሆናል፡፡ ሰው ሰውን እና ንዋይን ሲተማመን ያጠፋል፡፡ ሕግ፤ የሚጠላሕ እና የሚቀናብህ ሰው መካከል እንድትኖር የማድረግ ሀይል ያለው ነው፡፡ ጠበንጃ አይደለም ሕግን የበላይ እንዲያደርግ የሚያደርገው፤ ህግን የበላይ ሊያደርግ የሚችለው ነገር ግንዛቤ ብቻ ነው፡፡  ህግ በግድ ተቀብለሕ የምትኖረው ነገር ነው፡፡ ለነገሩ በባህል ትስስር እና በመቻቻል መኖር ትልቅ የሆነ የዲሞክራሲ ቀውስ የሚያመጣ ነው፡፡ ጥንት የተጠቀምህበትን ባህላዊ ሕግ ይዘህ መጉዋዝ አንዱን ተጠቃሚ አንዱን የሚያፍን ይሆናል፡፡ የጥንቱ ጥሎልን የሄደው የሕግ የበላይነትን ሳይሆን ተሸነጋግሎ መኖርን ብቻ ነው፡፡ ይቅርታ ላይመቻችሁ ይችላል፡፡ እኔ በበኩሌ ሁልግዜ ፖለቲከኞችን በመክሰስ መኖር አልፈልግም፡፡ ፖለቲከኞች የእኛን ባሕሪ የሚያንጸባርቁ  መስታወት ናቸው ብዬ እገምታለሁ፡፡
ኮኮቤን ለምሳሌ የእኔ የምላት ሌላ የሚፈልጋት እስከሚመጣ ድረስ ነው፡፡ ሰማይ ላይ ያለች ነገር ለሁላችንም አይን የተፈጠረ መሆኑን ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ አይደለም ቀውስ መሆን አይደለም ወደሰማይ አንጋጦ ኮኮብን እንድከታተል ያደረገኝ፡፡ አንድ ነገርን በደንብ መመልከት የሚያመጣውን  ለውጥ ስላየሁ ነው ዘወትር የማየው፡፡ ሕግንም አይቸ አይቸ የህግ የበላይነት ባለማወቅ ህግን እንዴት እንደምንጎዳው ገርሞኛል፡፡ ለምንድን ነው ተለማምጨ መኖር ያለብኝ? ለምንድን ነው ሰው ሰውን ፈርቶት የሚኖረው? ይህ ሁሉ መለወጥ ያለበት ነገር ነው፡፡ እኛ አይምሮ ለኝ ሰዎች እንጂ ከሌላው ያነስን አይደለም፡፡ ሌላው የቻለውን እንችላለን፡፡ ሰብአዊመብትም የሚከበረው አንድ በእግዚአብሄር ሌላው ከእግዚአብሄር መነሻነት በምድር ሳለን የተደነገገ የምድር ሕገመንግስት ነው፡፡ ሰው ከመሬት የሚበልጥ ነውእና በሰላም የመኖር መብት አለው፡፡ በቸር እላለሁ፡፡
ባዩሽ



Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen