የታጠከውን ሳታጠብቅ፤
ቸኩለህ አትሩጥ
አንድ ሰው አስተያየቱን በነጻ የማይሰጥበት ባህል አለው አገር፤ ሰው አንድ
ጎን ብቻ እንዲይዝ የሚገፋፋበት አገር፤ ሰው ይረሸን እና ይገደል የነበረበት አገር፣ የሰው ልጅ እኩል በልቶ ለብሶ የማይኖርበት
አገር፣ ባህልና ታሪክ ተብትቦ የያዘው አገር፣ ትምህርት ገና እኩል ባልተዳረሰበት አገር፤ የሚኖር አንድ ግፍን ያልቻለ ሰው አይምሮው ቢታመም ምን ይደንቃል? የአንድ ሰው አስተያየት
ወደዚች ጹሁፍ እንድመጣ አደረገኝ፡፡ ውነት ነው እኔ ከብዙዎች አይምሮ ጋር የሚመሳሰል የለኝም፡፡ የደነዘ ስሜት አልባ፤ የሌላው
ህይወት ዴንታ የሌለው፡፡ ኑሮው ወረቀት ከመሰብሰብእና ገንዘብ ከመሰብሰብ ውጪ ሌላ የማያውቅ፡፡ ነገሮችን እያጣመመ ከሚያፌዝ ሌላ
ምንም ውል የማይሰራ፣ በሕብረተሰብ መካከል መለያየትን የሚፈጥር ሰው ፤ ማይንዱ ያለውን ያላጣራውን የቆሸሸ ነገር ለሌላውም አስተላልፎ
ሌላውን የሚነዳ፤ አስተሳሰቡን ለመለወጥ የማይጥር ሰው፣ ባህሪው ያልተለወጠ ቢሳደብ ምን ይገደኛል፡፡ እኔ እንግዲህ ልንገራችሁ፤
የሰዎችን ክፋት፣ ሸር እና ማንአለብኝነት ሁሉ አሳምመውኝ ይሆናል፡፡ግን
ለመዳን እየጣርኩ ነው፡፡ መንገዱም ይህ የያዝኩት መንገድ ነው፡፡እራሴን መሆን፡፡ ገባችሁ እራስን መሆን፡፡ እራስን ግልጽ ማድረግ፡፡
አስተሳሰቤን የሚታረመውን ማረም የሚይዘውን መያዝ፡፡እንደአለፈው ዘመኔ ማንም አይምሮየን እንዳይነዳው መጠንቀቅ፡፡ ሰው የሚነዳው
አይምሮ ይዠ በህሊና ቁስል ከመጨማለቅ፤ የእራሴን አይምሮ ተጠቅሜ እብድ ብባል ይሻለኛል፡፡ ያሳዝናል የሰው ሞራል ሊያስነካቸው የሚቸኩሉ
ሰዎች፡፡ እራሳቸውን ያልሆኑ፤ በአለም ሲስተም እና በባህል እጅ የወደቁ፣ ወደሁዋላ እንጂ ወደፊት የማያዩ፣ አይምሮአቸው የማያድግ፣
ባህሪያቸው የማይቀየር፡፡እነዚህ ስሜታዊ የሆኑ ሰዎች የአገር እንቅፋት ናቸው፡፡ እራሱን የሆነ ሰው ሌላውን ለመረዳት ጥረት ያደርጋል እንጂ ቶሎ ወደዘለፋ ባልገባ
ነበር፡፡ ግን እንዲሕ አይነት ሰዎች አይምሮአቸው የሌላው ተገዢ የሆኑ ናቸው፡፡ ያልኩትም ይህንን ነው፡፡ አዎ እኔ የምጽፈውን እነዚህ
ሰዎች ማንበብ ይገባቸዋል፡፡ እኔ የምጽፈው ተፈጥሮን መሰረት አድርጌ የተገነዘብኩትን እንጂ ትምህርት ቤት ገብቼ የተማርኩትን ወይም
ፎቶ ኮፒ አድርጌ የወጣሁትን አይደለም፡፡ ተፈጥሮአዊ የሆነውን የሌላ ሰው አስተሳሰብ እንዳይወጣ ለማድረግ የሚታገሉ ሙሊታቸው ሰይጣናዊ
ነው፡፡ የምሁር ደንቆሮን ያልተማረ ብልህ ይመክረዋል፡፡ በእድሜዬ ጸሎት አድርገሽ ዝም ብለሽ ተቀመጪ ያለኝ ይህ ሰው፡፡ ትልቅ ነገር
አስታወሰኝ፡፡ እሱም በእድሜ ጾሎት ኢትዮጲያን መለወጥ ቢቻል ኖሮ
መች እስከዛሬስ ባለእድሜ ጠፋ እና፡፡ ብዙ አልፎበት ግን በእጃችን የነበረው ያልተለወጠ ኢትዮጲያ ነው፡፡ እኔን አዎ ግፍን ማየትም
መካፈልም አሳምሞኛል፡፡ ስነልቦናዬን ጎድቶታል፡፡ እግዚአብሄር ይማረኝ አሜን፡፡ እናንተንም የተዘጋውን አይምሮአችሁን ይክፈትላችሁ፡፡
አይምሮው የተዘጋ ሰው ሌላውን የመረዳት አቅም የለውም፡፡ ለመዝለፍ አትቸኩል እራስህን ታጋልጣለሕ፡፡ እውቀትህም ሚዛን ላይ ይወድቃል፡፡
የአስተያየትን ነጻነት የሚጠብቅ አይምሮ እንደሚያድግ ያገናዘበ ብቻ ነው፡፡ አገርህን መለወጥ ትፈልጋለሕ? በቸር እላለሁ፡፡
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen