ድባቅ የሚከት ድምጽ ካልተጠበቀ አፍ
ሲወጣ ንቃ፡፡
„እናንተ የእፍኝት ልጆች ከሚመጣው ቁጣ እንድትሸሹ ማን
አመለከታችሁ፡፡ እንግዲሕ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፡፡ በልባችሁም አብርሃም አባት አለኝ እንደምትሉት አይምሰላችሁ“ ይህ የመጥመቁ ይሁዋንስ ንግግር አይናችንን ሊከፍተው ይገባል፡፡ ገና ያልመጣው ግን ለመምጣት ዳር ዳር እያለ
ያለውን ዘመን አስከፊነት፣ መራራነት፣ አሰቃቂነት የሚናገር እንጂ እስከዛሬ የሆነውን አይደለም፡፡ የሁሉም ሀይማኖት አንድ ቀን አለም እንደምታልፍ ይናገራል፡፡ ያንንም በጉጉት
በናፍቆት የሚጠብቅ ሲኖር፤ አንዳንዱ ደግሞ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ እንኩዋን አለም እሱም እንደማያልፍ መስሎት በመርሳት ይኖራል፡፡
መርሳት የሚያመጣብን ሁኔታ ደግሞ የሕመም ምልክት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ሰው እንግዲሕ እግዚአብሄርን ካልፈራ ማንን ይፈራል፡፡
ነገ ሁሉንም ነገር ትተን እንደምንሄድ የረሳነው እኛ አለም አንድ ቀን ትጠፋለች ብሎ ለማሰብ ከባድ ነው፡፡ ጭራሽ ለነገር ፍለጋ
ነገር ከየቦታው እየቆፈርን እየመዘዝን ሰው በመልካም አምልኮ የአምላኩን መምጣት እንዳይጠባበቅ አካባቢያችንን በነገር ቆሻሻ ሞልተን
ትውልዱን እናጨናንቃለን፡፡ በእምነት ከሄድን የየአንዳንዳችን ፍርድ ከፈጣሪ የሚመጣ እንጂ ከአንድ ሰው ወይም ከአንድ ግሩፕ የሚመጣ
አይደለም፡፡ ምንአልባት አይናችንን ብንከፍት አጠገባችን ስንት ሰው እግዚአብሄር ልኮልን በሀጢያት የተሸፈነው አይናችን ሳይመለከት
አሳልፈናቸው ይሆናል፡፡ ወይም ደግሞ በሀይማኖት የታወረው ልባችን ብርሀን አጥቶ እየወነጀልን አባረናቸው ይሆናል፡፡ እግዚአብሄር
አንድም ቀን የሰውን ልጅ ብቻውን ጥሎት እንደማያውቅ መረዳት አለብን፡፡
ምንም እንኩዋን የመጀመሪያው የክርስትና ሀይማኖት ኦርቶዶክስ መሆኑ አለም የመሰከረለትም ቢሆን፤ ግን እግዚአብሄር አሁንም ቢሆን
ስራ አላቆመም፡፡ እግዚአብሄር አብርሀምን ሲመርጠው አብራሀምን ብቻውን ለማዳን ሳይሆን የፈጠረውን ሕዝብ ለማዳን ያደረገው አንዱ
የመገናኛ መንገድ ነው፡፡ እግዚአብሄር ዘወትር ለማያውቁት ሁሉ እንዲያውቁት ጥረት የሚያደርግ እሩህሩህ አምላክ ነው፡፡ አብራሀምን
ብቻ ለማዳን ቢሆን ኖሮ እሱን እስከቤተሰቡ እንደእነ ኤልያስ መንጠቅ ባላቃተው ነበር፡፡ ባለችሎታ አምላክ መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን፡፡
ባይሆን በአንድ ክፉ የሆነ የፖለቲካ መሪ ዘላለም አለም ታልፈን በተሰጠን ነበር፡፡ አስቸጋሪ መሪዎች ምን ልግባ ብለው ሲሽመደመዱ
ሰምተናል አይተናል፡፡ ክፉ መሪዎች ደዝባቸው የሚጠፋው የእግዚአብሄር ጣት ጣልቃ ሲገባ ብቻ ነው፡፡ መጥፎ መሪዎችም ልባቸው እንደፈርኦን
የደነደነ ይሆናል፡፡ እርግጠኛ ሆኘ በእምነቴ የምነግራችሁ በመሪዎች ላይ
ተግሳጽ፣ ምክር እና ወንበሩንም እንዲያስተካክሉ አልያም እንዲለቁ ዘወትር መልእክት ይመጣል፡፡ይህንንም ካልሰሙ በሕልም
ብሎም በራእይ የእግዚአብሄር ተግሳጽ ለመሪዎች ለእራሳቸው እንደሚያስከትል ነው፡፡ ሁሉ መልእክት የሚደርሳቸው ወይም የሚመጣባቸው
እነሱ ስላመኑ ሳይሆን ሕዝብን የፈጠረው እራሱ ስለሆነ ሕዝብን ሲታደግ
ብቻ ነው፡፡ እንደእውነቱ የእግዚአብሄር ስራ ተሰርቶ ያበቃ ሳይሆን ያንኑ ያንኑ የሚደጋግም ነው፡፡ ይህንም የምለው፤ ያንኑ ትምህርት
ዘወትር በተለያዩ ሰዎች እና በአዲስ መንገድ ያስተምራል ያሳያል፡፡ የእግዚአብሄር ህግ ሲነሳም አንድ ነው መደምደሚያውም ያው ነው፡፡
ዛሬ አስተማሪ ቢበዛ አይድነቅህ፡፡ እግዚአብሄር አንድም ሰው እንዲጠፋበት የማይፈልግ በመሆኑ ሁሉን ለማዳረስ የሚፈልግበት ግዜ ላይ
ደርሰናል፡፡ የምስራቹን ሁሉ መስማት አለበት፡፡ ስለዚህ ወገኔ ሆይ የምስራቹን አብሳሪ ወንጌላዊ ቢበዛ አይድነቅህ፤ አያስደንግጥህ፡፡
ማመን ግን የየግልህ ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ሰው ሌላውን የሚያንገላታው፤
እግዚአብሄር ስለፈረደበት ሳይሆን የአንተ ሀጢያት ልብህን ስላሳወረው ብቻ ነው፡፡ ሁሉንም ተግሳጽ መሪ ካልሰማ እንደአክቲቪስት አይነት ድምጽ ከየቦታው ያስነሳበታል፡፡ ከመካከልህም የወደድከውን
ያመንከውን ማንነትህን እንዲዋጋ ሙሴን የሚያስነሳብህ አምላክ ለፈጠረው ህዝብ እንደሚጥር እመን፡፡ ድባቅ የሚከት ንግግርም ካልጠበቀው
አፍ እንደሚወጣ ማየት እና መጠበቅ ነው፡፡ እግዚአብሄር እንኩን ሰውን ከአህያዋ መልእክት ያወጣል እና፡፡ ባላባት እና ቄስ የመረጠው ሳይሆን ዳዊት እግዚአብሄር የቀባው ነበር፡፡ አንተ የናከው፣ አንተ
ያንቁዋሸሽከው፣ አንተ እብድ ያልከው፣ አንተ ተቀዋሚ ያልከው በየቤቱ
እና በየአደባባዩ በየእስርቤቱ ስንት የተቀባ እንዳለ ወገኔ ሆይ እምነህ
አይንህን ክፈት፡፡ መሪን የደፈረ እብድ ነው እንጂ ለአንተስ መቼ
እግዚአብሄርን ለማየት የተሰጠህ ነገር አለእና፡፡ መንፈስን ሁሉ የመመርመር ችሎታስ እንዲኖረው ማን ይሰጣል እና፡፡ እግዚአብሄር
የሚሰራው፤ እሱ በመረጠው እንጂ መቺ አንተ ወይስ ቡድን የመረጠው ሆነና፡፡ ሁሉም ሆኖ ግን ተግሳጽን ያልሰማ እምቢተኛ የተናገረውን በመግደል በማሰር በማሳደድ እጁን
በሀጢያት የበለጠ እየነከረ ይሄዳል እንጂ ለማያቀው አምላክ መች ይታዘዛል፡፡
እግዚአብሄር ስለእኛ ሕዝብ ጥረት ያደርጋል፡፡ ለእኛ ለምናምን
እግዚአብሄር የፈጠረን እንድንጠፋ ሳይሆን እየተደሰትን እንድንኖር መሆኑ ይታወቃል፡፡ ግን ሕግን ለመጠበቅ ከመጀመሪያውም የተቸገርን
በመሆናችን በአዳም እና በሒይዋን ምክናያት ከገነት ውጭ እንድንጣል ሆነናል፡፡ እንግዲህ ከገነት ውጭ ከተጣልን ምን ያህል አሰቃቂ
እና አሳዛኝ የሚያሰቃይ ቦታ ላይ ዛሬ እንዳለን እንረዳለን፡፡ እኛ ወደእዛ ለመግባት ለመታገል አቅም እንዲኖረን ዘወትር እግዚአብሄር
በተለያየ መንገድ የሰውን ልጅ ሲገናኝ ሰምተናል አይተናል፤ አለም እስከአለፈችም እግዚአብሄር እኛን መገናኘቱ ይቀጥላል፡፡ ጥረቱም ከወጣንበት እንድንመለስ ለመታደግ እና ወደእሱ የሰው ልጅ እንዲመለስ
ብዙ አዳዲስ መንገዶችን ለመፍጠር የሚሳነው አምላክ እንዳልሆነ መዘንጋት የለብንም፡፡ አይናችንን ከከፈትን እግዚአብሄር የታምራት
አምላክ ነው፡፡ ለምናምን የዘር ልዩነት ቴማችን ሊሆን የሚገባው አይደለም፡፡ አንዱ የባብልን ታሪክ ሰው እግዚአብሄርን የተወዳደረበት
ወቅት ቁዋንቁዋን መደበላለቁን እናስታውስ፡፡ ሌላው ደግሞ እኛ የእግዚአብሄር ጥበብ ማሳያ እንጂ ሰው በተፈላሰፈ ቁጥር ለሚያወጣው
ህግ ቀለማችንም ሆነ ቁዋንቁዋችን መግለጫ እና መለያያ እንዲሆን አታድርጉ፡፡
አንድ ነገር ልንገርህ ወዳጀ፤ ሀብትን የሚመኝ የሚያሰርቀውን መንገድም ይመርጣል፡፡ እኛ ግን የእለት እንጀራችንን ስንመኝ
እግዚአብሄርን እናያለን፡፡ ዛሬ አንተ ሀብታም ብትሆን የነገውን የልጅህን እጣ ፋንታ ግን በአንተ ሀብት እጅ መሆኑ ምንም ዋስትና
የለሕም፡፡ ደሀም ብትሆን ለምን ተስፋ ትቆርጣለህ የነገውስ በእግዚአብሄር እጅ አይደለም እን? በራእይ ከእግዚአብሄር መላእክ ጋር
ተገናኘሁ ብሎ ሰው ቢነግርህ አትደንግጥ፡፡ የአንተም ነፍስህ እግዚአብሄርን ታውቀዋለች እና፡፡ ነጭ ይሁን ጥቁር፤ አማራ ይሁን ትግሬ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር አምሳል
እንጂ መች በሰው ነው እና፡፤ ጥበብ ከሁሉም በኩል ተሰጥቶአል እና፤ በሀሉም ዘር ደግሞም ጽድቅ እና ኩነኔ አለች እና የአገሬ ሰው
ሆይ አይንህን እራቅ አድርጎ እንዲያይ አድርገው፡፡ አሕያ ብቻ ናት ከአምስት መቶ ሜትር በላይ የማታየው፡፡ አንተ ግን በእግዚአብሄር
አምሳል የተፈጠርክ ሰው ነህእና ትግሬው አሻግሮ ይይ፤ ኦሮሞውም ማዶውን ይይ፤ አማራውም እንዲያው፡፡
ንብ ከየት አምጥታ ማር እንደምትተፋ ሳታውቅ ንብ ነኝ
አትበል፡፡ ንብ አበባ መርጣ ትቀስማለችእን? ደግሞስ ከአፍዋ መራራ ትትፋለችእን? ነኝ እንዳለክው ወገኔ ሆይ ሁን፡፡ ቃልን የሚጠብቅ
የአምላክህ ክንድ በአንተ ላይ አለች እና፡፡ ካጠፋሁ እና ከደፈርኩ በጌታዬ በእየሱስ ክርስቶስ ስም ወገኔ ሆይ ይቅር እንድትሉኝ
እማጸናለሁ፡፡ ሰይጣንን የካድኩ ስለሆነ ከሰይጣንስ አልናገርም እና፡፡ በቸር እላለሁ፡፡
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen