Mittwoch, 19. März 2014

ጆሮ ያለው ካለ ይስማ






               ጆሮ ያለው ካለ ይስማ

ከሰዎች መካከል እግዚአብሄር ሰው ይመርጣል፡፡ ስራውን የሚሰራው በሰው ነውእና፡፡ ግን እየሱስ ከተጠበቀበት አልተወለደም፡፡ እንዳውም ካልታሰበ ቦታም በበረት ተወለደ፡፡ ጆሮ ያለው ካለ ይስማ፡፡ አሁንም እኔ ጻድቅ ነኝ ብለሕ የምትኮፈስ ሁሉ እግዚአብሄር እፍረትን እንደሚያመጣብህ እመን፡፡ አንተ 100 አመት በሱ ውስጥ ነኝ ብትልም፡፡ እሱ ግን በአንተ ውስጥ ከለለ ከንቱ መሆኑን እወቅ፡፡    
ዲሞክራሲ አለ ይባል ወይም  የለም፤ ጉዳዩ ግን ሰበአዊ እርህራሄ ገደል እየገባ የሚሄድበት ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡ ሕጻናቶች ይበደላሉ፡፡ በየበረንዳው ይወድቃሉ፡፡ ለጉድፈቻ ይሰጣሉ፣ ሴቶች ደግሞ በየአገሩ ይሰደዳሉ፡፡ ይገደላሉ፡፡ በየበረሀው ሬፕ ይደረጋሉ፡፡ ደግሞም ለአሰቃቂው የሴት አዳሪ ስራ በእጅግ ተጋልጠዋል፡፡ ወጣቱ አቅጣጫው ጠፍቶበት ከፊሉ ሲሰደድ ደግሞ ከፊሉ ለጫት፣ለድራግ እና ለስደት ተዳርጎአል፡፡ አዛውንቱ እና በሰል ያለው ይህን ማየት ተስኖትእና መልሰ መስጠት ስላልቻለ፤ ያለፈው ይሻል ነበር እያለ ፊቱን ወደሁዋላ እግሩን ግን ወደፊት አድርጎ ቁጭ ብሎ ይተክዛል፡፡ አዎ ይህ የኢትዮጲያ የየቀኑ ሕይወት ሆኖአል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም በአለም ላይ ይህ እንደባህል እየሆነ መጥቶአል፡፡ ዳቦ ፍለጋ፣ የተሻለ ኑሮ ፍለጋ፣ የእውቀት እድገት ፍለጋ፤ እግር አውጭኝ በአለም ላይ ተጡዋጡፋል፡፡ ይገርማል፡፡ ይህን አንዱ በጉጉት ሌላው በምኞት ከዘሩ ተወልዶ ካደገበት አገር አቅጣጫውን ስቶ ወደማያውቀው አለም ያራውጠው ይዞአል፡፡ የሰው ልጅ ተስፋው እግዚአብሄር እንዳይሆን የሰውን ልጅ አይን ከፈጣሪው ላይ እንዲያነሳው ያደረገው ፖለቲካ ጉልበት አጥቶ  በመንገዳገድ  ላይ ቆሞአል፡፡  
ፖለቲካ በፖለቲካ ለመለወጥ የሚደረገው ጥረት በሰላም መንገድ የማይቻልበት ኢትዮጲያ የፖለቲካ መሪዎች ክህዝብ ስልጣንን ወንበርን የሙጥኝ ብለው ተያይዘውታል፡፡ እርስ በእርስ ተፋጠው አንዱ አንዱን የሚረዳበት ሁኔታ ከመፍጠር ሁሉም የሚያብረቀርቀውን ሱፉን እየለበሰ፤ አቅጣጫ ያጣውን የተደናገረውን ህዝብ ገንዘብ እየቆመቆመ በዛው ቀጥሎአል፡፡ የዚህአለም የሰይጣንን ሕግ ሀግ የሚለውም ነብይ በኢትዮጲያ ሊገኝ፡፡ አልቻለም፡፡ ጭራሽ ሀይማኖት መሪዎችም የፖለቲከኞች ደጋፊእና ነቃፊ ሁነው በጎሪጥ ካለመተያየት በስተቀር የእግዚአብሄርን ድምጽ የሚያሰማን መንፈሳዊ አጥተናል፡፡ የሰው ልጅ ወንጌልንም በእጁ ይዞ መሰደድ ሆኖአል፡፡ የተሰደደውም በስደቱ አለም ቆንጆ ልብሱን ለብሶ አገር ሰላም ይለናል፡፡ ወጣቱ በባህርም በቦሌም ብሎ የአባት የእናቱን ቤት አሲዞ ለከበርቴዎች ክፍሎ ባህርን ይሻገራል፡፡ አገር ጥሎ የወጣውም ለምን እንደዋጣ ሳያውቀው ወጥቶአል፤ ገንዘብ ለማግኘት ደፋ ቀና ይላል፡፡ አልያም ተቆዝሞ የአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚ ሆኖአል፡፡  የወንጌልን ጉልበት ያሳጣው አንዱእና ዋንኛው እራሱ አማኙ ነው፡፡ የእምነትን ጉልበት ያሳጣው እራሱ አማኙ ነው፡፡ ለምን ቢባል አላመነም እና፡፡ የወንጌል ሰው ሕልሙን ቢያይ አይናገርም፤ መልክትም ቢመጣለት አይናገርም፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ሲወጣ የሚያሳርድ እንጂ በዚህ አለም ላይ መች የሚያስኖር ነውእና፡፡  
ኢሕአዴግን አንድ የማመሰግነው ነገር አለ፡፡ እሱም ወንጌል እንዲገለጥ ፈቃዱን ሰጥቶታል፡፡ ግን ወንጌል እንዲሰራ ገድቦአል እና ዋ ለእራሴ ቢል ይሻለል፡፡ ይቅር በሉኝ፡፡ የጌታዬ የእየሱስ እምነት ተሸክመህ አፊን እይዛለሁ ማለት አይቻለም፡፡ አኔ ሳልሆን የምናገረው መረዳቴ ነው፡፡ ያስፈራል፡፡ እንኩዋን እኔ እየሱስ ያቺን ለሊት ተጨንቆባት ነበር እና፡፡ በሰው እጅ መጥፋት ያስፈራል፡፡ አይቸዋለሁ፡፡ ለሊቱን ሰዎች ሲያስፈራሩኝ፣ ሲያስጨንቁኝ፣ አይቸዋለሁ እንኩዋን ሴት ናት ብለው ሊረዱኝ ሲዘርፉኝ፣ አውቃለሁ ምንም ያላደረኩዋቸው ሰዎች በሀሰት ሲመሰክሩብኝ፣ ሲተፉብኝ ሲመቱኝ፡፡ አይቻለሁ ፊትለፊት አይኔን የሚያየኝ ሰው ያጣሁበትን ግዜ፡፡ ግን ከውስጤ ያለው ሙላቱ ሊገድበው የሚችል አልተገኘም፡፡ እየሸሸሁም እናገራለሁ፡፡ ከእንግዲሕ እኔን እግዚአብሄር ካልረዳኝ አንድ ሰው የማላገኘበት ደረጃ ደርሻለሁ፡፡ ግማሹ እንደወጭት ውሃ ወዲያ ወዲሕ ሲል፤ ግማሹ ሳንወድ በግድ በተገደድንበት ንግግር እንደእብድ ሲያየን፤ ቤተክርስቲያንም አዩን አላዩን ብለን ስንቀመጥ፡፡ አዎ የውስጥህ የእየሱስ ፍቅር ያስወጣሀል፡፡ ድምጽ ለለለው ድምጽ አድርጎ ያስነስሀል፡፡ ከተናገርክ በሁዋላ ምንልግባ ትላለሕ፡፡ ምን ይዋጠኝ ትላላሕ፡፡ እጣ ፋንታዬ ይህ ሆኖአል፡፡ መለስ ስል እና ሰዋዊ ሳስብ፤ አሁን ምንሆኜ ነው የተናገርኩት እላለሁ፡፡ አዎ ቀበሌውም ፖሊሱም እንደነብር አይኑን ያጉረጠርጥብኛል፤ የዝሆን ጡንቻ ይልክብኛል፤ የእባብ መርዙን በከተማው ይነዛብኛል፤ እንደጅብ ዘራፊ እንደውሻ ተናካሽ በጥጉ ያስቀምጥብኛል፡፡ ግን እግዚአብሄር ሊነሳበት እንዳለ አይገባውም፡፡ ዛሬ የሚታየው በወገኑ ላይ እየዋሸ ፖለቲከኞችን እያሳሳተ የሚያካብተው ጥቃቅን ነገር አይኑን ሸፍኖታል፡፡ ሀብታም ቤቱን በዲንጋ ሲሰራ እሱ ለጭራሮ ቤቱ ያሳድደኛል፡፡ ግን እውነቱ የእግዚአብሄር እውነት ይህ ነው፡፤ እኔ በክርስቶስ ነኝ፡፡ እሩህሩሁ አዛኙ ክርስቶስ በውስጤ ገብቶአል፡፤ የማየውም እሱ ሊያየው የፈለገውን እንጂ የእኔ ስጋ ሊያይ የፈለገውን ከቶም ሊሆን አልቻለም፡፡ ብፈልግም አልመጣም፡፡ እኔስ እንደፍርሀቴ ጀግኜ ባየሁት ነበር፡፡ ግን ሊሆን አልቻለም፡፤ የስጋ ጀግንነት ከእኔ አዲዎ ብሎ መንፈሳዊ ማንነቴ አየለብኝ፡፡ ለመናገርም የሚቸኩልብኝ መንፈሳዊ ማንነቴ እንጂ መች እኔ ሆንኩእና፡፡ የነፍስ ጉዳይ ነው፡፤ ነፍሴ ወደእግዚአብሄር ተጠማች፡፡ ወንጌልን ይዞ ክርስቶስ ገብቶት መጥፎውን ጥሩ ነው የሚል ሌላውን ያስታል፡፡ አንተ የወንጌል ሰው ከክፉ አታብር የአምላክህን አደራ የሰጠህን ሕግ አታፍርስ፡፡ አንተ ንጉስህ በሰማይ ያለው የማያዳላው፣ ሁሉን በግልጽ የሚያየው እና የማይተኛው የማያንቀላፋው እግዚአብሄር ነው፡፡ ልብ በል ዛሬ ወንጌልን ካልሰራህባት ኢትዮጲያን ለሪቮሊሽን አሳልፈሕ ትሰጣታለሕ፡፡ ምክናያቱም የህዝብን ብሶትን የሚፈነቅለውም እግዚአብሄር ነውእና፡፡ እግዚአብሄር ነውር አለበት ቦታ እንደማይገኝ ታውቃለሕ እና፡፡ እግዚአብሄርን በስጋዊ ሽፋን በለበስከው ሱፍ፣ በምትነዳው መኪና፣ በምታውቀው ባለስልጣን በምትመካበት አገር ልታቆመው አትችልም፡፡ በክርስቶስ አምናለሁ፡፡ በእግዚአብሄር እመካለሁ፡፡ ብፈራም በመንፈስ ቅዱስ እጽናናለሁ፡፡ ለነውር አንተ ካልወጣህ ነውርንስ ማን ያውቀዋል፡፡ አገርህስ እምነት ቢኖር ኖሮ ትግሬው አማራውን፤ አማራው ሌላውን… እያለ የአጸያፊ ስድብ ከአፍ ባልወጣ ነበር፡፡ ወዳጄ ሆይ ልብ በል፡፡ ዘርስ የእግዚአብሄር ጥበብ ማሳያ ካልሆነልህ፤ የፈካስ አበባ እንዴትስ ታያለሕ፡፡ ተነስ ውጣ ተናገር፡፡ ዘር የእግዚአብሄር ጥበብ ማሳያ እንጂ መቺ የፖለቲከኞች መሳሪያ ነውእና፡፡ በቸር እላለሁ፡፡
ባዩሽ



Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen