በኢትዮጲያ አስከፊው ገጽታ ምዕ/2
እኔ እና ኮኮቤ እራስን ወዳድነት
አገሬን እንዳልወድ የሚያደርግ አንድ የማላውቀውና
ያልተረዳሁት አካል እንዳለ ተረዳሁ፡፡ ከአገሬ ስወጣ በልጅነት እና በአዋቂ መካከል ያለ እድሜ ላይ ነበርኩ፡፡ ወደአገሬ ስመለስ
ግን አዋቂነቴን በማወቅ ልደሰትበት ያልኩት እድሜ ላይ ደርሻለሁ፡፡ በልጅነት ወደተለየሁት አገሬ መመለስ፤ ብዙውን የሚያውቀኝን ሰውም
ሆነ መንግስቴንም ጭምር ያስደስታል ብዬ ገምቸ ነበር፡፡ ግን ሆኖ አላገኘሁትም፡፡ መንግስቴንም ሆነ ማንንም ዘመድ አዝማድ ስለረዳሁእና
ስለጠቀምኩ ወይም የተለዬ ስጦታ ስለያዝኩ አይደለም የኔ ወደአገሬ
መመለስ ሊያስደስታቸው ይገባል ብዬ የገመትኩት፤ ግን የእነሱ ስለሆንኩ ኪሴን ሳይሆን በሕይወት መመለሴን ያስደስታቸዋል የሚል የልጅነት
መንፈስ ስለተላበስኩ ነበር፡፡ የአገር ሰው የአገር ሰው፡፡ የጠበቀኝ ግን ፍርሀትን እና ድንዛዜን የሚያስከትል የህይወት ልምድ ሆነ፡፡
ብዙው የሚጠይቀኝ ማተርያል ይዠ ተመልሽ እንደሆን እንጂ ምን ልምድ እንደተሸከምኩ ማወቅም የሚፈልግ የለም፡፡ ብዙው በውጩ አለም
ላይ ያለው አመለካከት ሀብት ትምህርት እና እድገት ብቻ ነው፡፡ ሌላውን እንቅፋት ስለዘረኝነትም ሆነ ስለሌላው ፖለቲካ አካሄድ ሊያውቅ
የሚፈልግ የለም፡፡ ማወቅ የሚፈልግ መሰረታዊ የሆነ እውቀት የያዘ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ የኢትዮጲያ መሰረታዊ እውቀት በፈረንጆቹ
አለም ላይ እጅግ በጣም ጥሩ ሆኖ ስለቀረበ በላጩ ሰው ጥረቱ እኔ ትቼ ተመልሸ ወደነበረው አለም ለመሄድ እንጂ አገሩ ለመቀመጥ አይደለም፡፡ እንደጉድ የምጠየቀው የመውጫ መንገድ
እንዳለ እንድረዳቸው ነበር፡፡ አንዳንዱ ቤቱንሽጦም አሜሪካ እና ኢይሮፕ ለመግባት እንደሚከፍለኝ እንድወስደው ይማጸነኝ ነበር፡፡
ምነው እኔ ያለኝን ሁሉ ሰጥቼ አገሬ በሰላም በኖርኩ፡፡ እኔን ግን ሕይወቴ እንዴት እንደሆነ የሚጠይቀኝ አንድም አልገጠመኝም፡፡
ቀንቶኝ ልመለስ ሳይቀኛኝ ማን ማወቅ ፈለገእና እናገራለሁ፡፡ ምንአልባት የራስን ወዳድነት ባሕሪ ተላብሶን ይሆን? ስለሕዝብ ለማውራት
አልደፍርም፡፡ የምናገረው ግን እኔና በእኔ አካባቢ ወጣ ገባ የሚለውን ሰው በመቀንጨብ ነው፡፡ የኢትዮጲያን መሰረት እንዲናጋ ያደረጉት
የኢትዮጲያ መሪዎች ይሆኑ ብዬ እራሴን የጠየኩበት ግዜ ብዙ ነው፡፡ ስለውጩ አለም እየሰማን ያደግነው ኮሎኒ የጣለብንን ጠባሳ እንድንረሳው ወይም
እንዳናስተውል አድርጎናል፡፡ ተምታቶብናል፡፡ ኮሎኒውን ስናስብ የነጮች ጥላቻ፤ ማተርያል ስናስብ የፈረንጁ አለም ውዴታ፡፡ አውቃለሁ፤
በማተርያል ሳይቀናው የተመለሰ እንዳማይረባ ይታያል፡፡ ለነገሩ ጥሩ አገር ተብሎ እንደመላአክ የቀረበልህን የፈረንጁን አገር ገብተህ
ሳይቀናህ ብትመለስ እና እማይረባ ተብለህ ስም ቢሰጥህ የአገርህ የፖለቲካ ታሪክ ብልሹነትን የሚያስረዳህ ነው፡፡ ብሄራዊ ፍቅር ከልጅነት
ግዜ የምትማረው እንጂ በከፋህ ግዜ የምትፈልገው አይደለም፡፡ የአገር ፍቅር እንጂ አገርህ የሚስቀምጥህ የማተርያል ጋጋታ መሆን አልነበረበትም፡፡
በአይምሮህ የምትገነባው እውቀት ከማገኘት ጋር የተሳሳረ ሆኖ አድጎአል፡፡ የእኔን ደህንነት ሳታውቅ የአንተን ሕመም ብትነግረኝ ያስደነግጠኛል፡፡
ይህ በዚህ መንግስት የመጣ ችግር ነው ብል ምንአልባት የማይወደውን አካል ላስደስት እችላለሁ፡፡ ዛሬ እኔ የማወራው አንዱን ማስደሰት
እና ሌላውን ማሳዘን አይደለም፡፡ፖለቲከኞች በሕይወታችን ላይ የሚጫወቱት ሚና ግን ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው የፖለቲካል
ቀውስ ያስከተለው ችግር ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ መሰረት ያለውን ነገር ሊያናጋው የሚችል የለም፡፡ ያ አገር የሚለው ስሜቴ እና ናፍቆቴ
በቅዝቃዜ ተሞላ፡፡ አገራችንን በሚጠቅማት ነገር ላይ ከምናተኩር ፈረንጆች የደረሱበትን ሄደን መቁዋረስ እንፈልጋለን፡፡ ግን ማስተዋል
የተሳነን ፈረንጆች ያለፉበትን ሳይሆን የደረሱበትን መመልከታችን ነው፡፡ ያልተከልከውን አትክልት ፍሬውን ለመብላት መጉዋጉዋት ይሆናል፡፡
አገሬን ታዲያ ማን ይርዳት፤ ያ ፈረንጆች ያለፉበትን የቴክኖሎጂ እድገት እንዴት አልፋ ትድረስ፡፡ አንተ ትተሕ የምትወጣውን አገር
አንድ የፈረንጅ ኢንቬስተር ታዲያ ቢገባ ምን ያስደነግጥሀል፡፡ ሕይወት ይህን ይመስላል፡፡ ዛሬ በአሕያ ጭኖ የሚነግደውም፤ ወይም
በኮንቴነር መርከብ ላይ ጭኖ የሚነግደውም የሙባይል ተጠቃሚ ያደረገው የፈረንጁ ኢንቬስተር መሆኑን አትዘንጋ፡፡ ዛሬ እኛ ዘለን የገባንበት
ቴክኖሎጂ ፤ በፈረንጆች ያልተቁዋረጠ የረጅም ጊዜ ጥረት ግረት ስራ ነው፡፡ እኛስ ምን እንፈጥር ይሆን፤ ወይስ ተስፋ ቆርጠን ወደፈረንጁ
አገር እየሄዱ ቴክኖሎጂ ያፈራውን ማተርያል መግዣ ብር መፈለግ? አዎ ስለተረጋጋው ፖለቲካቸው፣ ስለሰብአዊነት አስተሳሰባቸው፣ ስለትምህርታቸው
፣ ስለእኩልነታቸው እና ስለሰላማቸው ያደረሳቸውን እድገት እና መንገድ መስማትም መካፈልም ለምድም መለዋወጥን አንፈልገውም፡፡ ስለዚህ
በአገራችን ተስፋ መቁረጥ አብሮ የተወለደን ይመስል ካለመሸሽ በስተቀር ሌላ አማራጭ አጥተናል፡፡ የፖለቲካ እውቀታችንም በአስተዳደጋችን
ላይ የተጫወተው ሚና እንደምንም እራስን ማውጣት ነው፡፡ ግን ደግሞ በፈረንጁ አገር ሁሉም እራሱን ማውጣት እንደማይችል መስማት ስለማንፈልግ
ጠይቀን ለመረዳት አይተን ለመፍረድ አልቻልንም፡፡ ዛሬ ጭራሽ የውጭ አገር ዜጋ ሁሉም ወደማይፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ዘወትር
የምንሰማው ባህር ገባ ባቡር ውስጥ ገብቶ ሞተ ሆኖአል፡፡ ምን የዠ ልግባ የሚለው ይዠ እመለሳለሁ ብሎ የወጣ መሆኑን አንዘንጋ፡፡
ምንይዠ ልግባ ያለ ሳይገባ ቀልጦ ይቀራል፡፡ ደግሞም ይዞ የገባው እንዴት ይዞ እንደገባ የመከራውን መንገድ ሊያስረዳም አይፈልግም፡፡
የሚፈልገውም አዳማጭ አያገኝም፡፡
አዎ የምትላወስውን ኮኮቤን በኢትዮጲያ ሰማይ ላይ
ማየት ግድ ያለኝ ምክናያት ወደሰማይ እንዳጋጥጥ ያደረገኝ የጨለማው ምድር እይታዬ ነው፡፡ ጨለማ የአስተሳሰብ ጨለማም ይሆናል፡፡
ጨለማ የጠቆረው ለሊትም ይሆናል፡፡ ጨለማ የወደፊቱን አይቶ የማይዘጋጅ አለም ይመሰላል፡፡ አዎ አይግረማችሁ በፈለኩት ሰአት ለሊት
ብነሳ አንዲት የምትንቀሳቀስ ወይም የምትሄድ ኮኮብ አያለሁ፡፡ መቸም በሰማይ በለሊት ለእኔ የሚያብረቀርቅ ኮኮብ ነውእና፡፡ እኔም
ልቤ ይረካል፡፡ ምንአልባት ማየት የፈለግነውን የማየት ተሰጥትኦ ይኖረን ይሆን? ወይስ እግዚአብሄር አንተን ወደእሱ የማቅረብ ሁኔታ
ያመቻች ይሆን? ግን የምታየው ነገር ለእራስህ እውነት አድርገው እንጂ ለሌላው እውነትነት አይኖረውም፡፡ ይህ ጥሩና መጥፎ እንድንለይ
ተደርገን የተፈጠርንበት አፈጣጠር ግን በእራሳችን ውስጥ አለ፡፡ እይታሕ የሚወሰነው እንደውስጥህ አስተሳሰብ ነው፡፡ መልካም ማየት
የፈለገ መልካሙን ያያል፡፡ የአንዱዋ ኮኮቤንም ስራ ስትሰራ ማየት ማንም ካልሰራ ለሌላው ምንም ተስፋ ሊሆን እንደማይችል ተረድቸበታለሁ፡፡
የምትሄደው ኮኮቤ እንደሌላው ኮኮብ ሁሉ ዝም ብላ አንድ ቦታ ብትቀመጥ ኖሮ ተስፋ ልትሆነኝ ባልቻለች ነበር፡፡ ሁሉም የተፈጠረው ለሌላው መደሰቻ ነው፡፡ አንዳንድ የሚያስቸግሩኝን ሰዎች
ሳይ፤ እርግጥ ነው ለእኔ መበሳጫ ይሆን የተፈጠሩት ብዬ እጠይቃለሁ፡፡
ይህም አለ፡፡
ውድ ወገኖቼ ገንዘብ ምንግዜም ከሀይል ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ማግኘት ደግሞ ከመግዛት
ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ገንዘብ ማግኘት ያማረህን ሁሉ ያስገዝሀል፡፡ ስልጣን ማግኘት ደግሞ ህዝብን እንድትገዛ ያደርገሀል፡፡ ስለዚህ
ገንዘብ እና ስልጣን በማግኘት ውስጥ የሚኖሩ ሀይል ናቸው፡፡ ሀይልን ለምን እንድትጠቀም የሚመራሕ እይታህ ነው፡፡ እይታህ ህልም
ከሌለው ባለራእይ ልትሆን አትችልም፡፡ ሀይል ለሁሉ የተሰጠ አይደለም፡፡ ግን እኛ ሁላችን ለሀይል ታልፈን የተሰጠን መሆናችንን አንዘንጋ፡፡
መጠየቅ ግን የሚገባን በእኛ ላይ ያለው ሃይል ምን ይሆን? ጨለማ
ወይስ ብርሀን? እኔ ሳልቀየር አካባቢዬን እቀይራለሁ ማለት አልችልም፡፡ አካባቢዬ ሳይቀየር አገሬንም መቀየር አልችልም፡፡ እራስን
መቀየርም የሚቻለው የሌላውን ልምድ ጠይቆ ሲረዳእና እራሱም ልምዱን ሲያካፍል ብቻ ነው፡፡ ብዙ ሰው ፈረንጅ አገር ያለውን ውድን
ሽቶና ውዱን ካሜራ እንዳለኝ ይጠይቁኛል፡፡ ግን እኔ ይዠ የተመለስኩትን የሕይወት ልምድ እንደሚጠቅም ስለማያውቁ አልጠየቅም፡፡ በዚህም የተነሳ ሁሉም ውዱን ያለሙትን
ቆሳቁስ ለመፈለግ ከአገር ለመውጣት የማይቆረቁሩት በር የለም፡፡ ያንን እኔ ያላገኘሁትን ወይ ያገኘሁትን ያገኙ ይሆን? ፖለቲከኞችስ
በአገር ውስጥ ታግሎ መኖርን ማስተማሩን ለምን ፈሩት? ኮኮቤ ኮኮቤ አንቺ ባትኖሪስ በአገሬ ምድር ምን እመለከት ነበር? ስደት እንደድል
ለማውራት የሚከብደኝ ሴት፤ እኔ ባዩሽ አበበ
እኔና ኮኮቤን በምእራፍ ሶስት ይዠ እስክቀርብ በቸር ልበላችሁ፡፡
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen