Montag, 17. März 2014

መባበል እና መሸንገልን አንጠብቅ




                                        መባበል እና መሸንገልን አንጠብቅ
ቡና እንደወረደ ስትጠጣው ያነቃሀል፡፡ ደግሞም ጣሙም የቡና ይሆንልሀል፡፡ ሱስህን ያረከዋል፡፡  ስለዚህ እኔም እንደወረደልኝ ነው መጻፍ የምፈልገው፡፡ የለም ጉረኛም አይደለሁም ግን እኔም የፖለቲካ ቅራሪ አስጠልቶኛል፡፡ አልጣፈጠኝም፡፡  የፖለቲካችን እድገትን በተመለከተ የአይምሮ ብስለትን በተመለከተ የግድ ሁሉም እንደወረደለት መነጋገር አለበት፡፡ ሳይሸማቀቅ፡፡ እኔም እራሴን መለወጥ እፈልጋለሁ፤ ማነኝ እና የእናንተው ወገን፣ የእናንተው ባህል ተካፋይ ነኝ እኮ፡፡ ግን መለወጥ አለብን፡፡ እኔ ልንለውጠው ያለብንን ነገር ላይ አተኩሬአለሁ፡፡ወደሁዋላ ይጎትተናል የሚለው ነገር ላይ አተኩሬአለሁ፡፡ ካልሆነ አርሙኝ፡፡ እኔ የመነጋገሪያ አጀንዳ አቅራቢ ነኝ እንጂ ወሳኔው የእናንተው ነው፡፡ አባባሌ ሁሉም በሕሊናው ይጠይቃል ይመልሳል፡፡ የህሊና አጀንዳ ነው ያቀረብኩት፡፡  ፡፡ የቆሸሸ ነገር ከእኔ ውስጥ እንዲወጣ እፈልጋለሁ፡፡ ቆርጫለሁ፡፡ እናንተስ?  በአገሬ ዲሞክራሲን እውን የሚያደርግ ባህሪ መለማመድ አለብን፡፡ ፖለቲከኞች ካለእኛ አጋዥነት ምንም አይሆንላቸውም፡፡ እኛስ ምን ያህል ዝግጁ ነን ለዲሞክራሲ፡፡ ይህ በፍቃደኝነት የሚፈጸም እንጂ በግዳጅ ሊሆን የሚችል ነገር አይደለም፡፡ እኛ ዲሞክራሲ እንፈልጋለን ስንል፤ ገዢው ፓርቲ ደግሞ ዲሞክራሲ አለ ይለናል፡፡ ታዲያ ማንኛው ነው ውሸታሙ፡፡ ምንአልባት ዲሞክራሲ ይኖር ይሆን? እኛ መተግበር አቅቶን ይሆን?  ማንም በአስተያየቴ ላይ ክሪቲክ መስጠት ይችላል፡፡ ስድብ ግን ለእኔ ትምህርት የሚሰጥ ሳይሆን የተሳዳቢውን ኢዲሞክራቲክነት ይገልጻል፡፡ ተሰደብኩ ብዬ ደግሞ አላፈገፍግም፡፡ ምስጋናም አያሞቀኝ ነቀፌታም ስድብም አያቀዘቅዘኝ፡፡  እኔ ከህዝቡ ውስጥ አንዱዋ ነኝ እንጂ፤ ከፖለቲከኞች ውስጥ አንዱዋ አይደለሁም፡፡ እንደሕዝብ አስተያየቴን የመስጠት፤ የመጻፍ መብት መለማመድ እፈልጋለሁ፡፡
ማሕበራዊ ኑሮ
የማህበራዊ ኑሮ ትርጉሙ በሚበላ ድግስ ብቻ የምትለዋወጠው አይደለም፡፡ ብዙ  ያበላ  ሲሰገድለት እና ጥሩ ሰው ሲባል ያላበላው ግን ማሕበራዊ ኑሮ  እንደማያቅ ይሆናል፡፡ አልያም እስከመኖሩም የሚያውቀው የለም፡፡ ብዙውን ግዜ ክፉ ሰዎችም ማንነታቸውን የሚደብቁት በዚህ መሰረት ነው፡፡ ማሕበራዊ ኑሮ ለታይታ፣ ለመመሳሰል እየሆነ በዛው በኖረበት እንዳይቀጥል የሚያስፈራ ነው፡፡ ብዙውን ግዜ በአንድ ግሩፕ  የሆነ ይቁዋቁዋም እና፣ ማሕበራዊ ይሆናል፡፡ አንዱ አንዱን ይስባል ሰውም ሊበዛ ይችላል፡፡ ግን የሚገርመው የሚኖረው በትንሽ ሰዎች አስተሳሰብ ነው፡፡ በቃ ይጠለፋል፡፡ ሁሉም በዛ ሰው ግሩፕ ስር ይሽከረከራል፡፡ እነዛም ሰዎች በስውር ያለው መሪያቸው በግል የጠላውን ሰው ሕይወት ለማበላሽት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ይህን ስል በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ ገብቶ የሚያምሰው በሬ ማንነቱ ግን ለሁሉም ግልጽ የሆነ አይደለም፡፡ በቃ የባሕሪ ጉዳይ እንጂ በስጋ ስሙንም የሚሰጥ አይደለም፡፡ በጥላቻ በቅናት እና በግል ጠብ የተነሳ፤ ዘመቻ ማካሄጃ የጦርነት ሜዳ ያደርገዋል፡፡ እያደርም ውስጡ እነእከሌ እነ እከሌ ይባባል እና ውስጡ በባህሪው የፈራረሰ ማሕበራዊ ኑሮ ግን በድግስ የተያያዘ ሆኖ ይቀራል፡፡ አስተሳሰብም እድገት አያመጣም፡፡ ሁሉም እርስ በእርሱ በባህሪ የተወራረሰበት ጉዳይ አለ፤፤ እሱም ግልጽነት የጎደለው በመሆኑ ነው፡፡ ግልጽነት የፈለገ እና አስተሳሰቡ የተለወጠ ብዙውን ግዜ ማህበራዊ የሚለው ነገር ያስፈራዋል፡፡ ምክናያቱም ይህ ሰው ግንዛቤው ያደገ በመሆኑ፤ እዚህ ጣጣ ውስጥ ምን አስገባኝ ብሎ ይቀራል፡፡ ይለያል፡፡ ይደበቃል፡፡ በተለይ በዚህ ነገር የተጋለጡት በይበልጥ በእምነታቸው የጠነከሩ ሰዎች እና በከፍተኛ ትምህርት እውቀታቸውን ያዳበሩ ሰዎች ማህበራዊ ሕይወት አይኖራቸውም፡፡ ይህም የሚሆንበት ጉዳይ በኢትዮጲያውያኖች ስብስብ ብዙውን ግዜ ሙግትእና ክርክር አለመግባባት ስለሚበዛ ነው፡፡ ከነቀፍከው ሰደብከኝ ብሎ ዱላ የሚያነሳ ነው፡፡ ሴቱም ያው ያለውን ጉልበት ይዘረጋል፡፡ ጭራሽ „ አንቺ ደግሞ ተማርኩ ብለሽ ነው ይባለል፡፡ እረ ከማን ትበልጫለሽ ይከተላል፡፡ መጥፎውን በነቀፍክ ተሰድበህ ወይ ተፈንክተህ ትመለሳለሕ፡፡ ይሕ ካለአርእስት የሚደረግ ክርክርም እያመዘነ የሚሄደው ታሪካችን፤ ባህላችን እያለ እያደገ ይሰፋእና በመጩዋጩዋሕ ያልቃል፡፡ ትምህርት አስጨባጭነት እንኩዋን የለውም፡፡ በመጨረሻም ተቃዋሚ ነሕ ደጋፊ ነሕ የሚል የጥርጣሬ ነገር ይዞ እያጉመተመተ ወደቤቱ ይሄዳል፡፡ ያሰበውን ሳይናገር ሁሉም እርስ በእርሱ ተዛዝቦ ይለያያል፡፡ የየሉኝታ ባሕል አለና ደግሞ መልሶ ደግሶ ይገናኛል፡፡ ግን ያለፈው ይደገማል፡፡“ውሀ ቅዳ፤ ውሃ መልስ“  ወይም በጎሪጥ ተያይቶ ይለያያል፡፡ ግልጽነት የሌለው ያልተፈታ ነገር በውስጣችን አመርቅዞ የሞተው ማንነት ሕይወት እንዳለው ለዘመናት በዚህ መልኩ ይቀጥላል፡፡ የሚገርመው ሁሉም ፖለቲከኛ አይደለሁም አያገባኝም ይላል፡፡ ተቃዋሚ መስለሕ የታየሐውን፤ ስምህን ወደገዢው ፓርቲ ባለስልጣን በመውሰድ እጅ መንሻ ያደርገዋል፡፡ ደግሞ የገዥው ፓርቲ ደጋፊ የመሰልከው ስምህን ወስዶ ይባዝተዋል፡፡ በቃ ሁሉም ግን ያንን አንስቶ ሳይቆዛዘም አይለያይም፡፡ በመካከሉ እኮ ሁሉንም በቁም ነገር የሚረዳ የለም፡፡


         እኔ ምን ያህል ለዲሞክራሲ አስተዋጽኦ አድርጌአለሁ የሚል የለም፡፡ ፖለቲከኞችን እናማለን፡፡ መለስ እንዲህ አድርጎ ወይም ብርሀኑ፡፡ እንላለን፡፡ ግን ወንድሜ፣ ጉዋደኛዬ፣ ጎረቤቴ፣ አበልጄ……የሚያደርጉትን ነውር ግን በለውጥ ላይ ምን ያህል ተጽእኖ እንደሚያመጣ ሊረዳ የሚችል የለም፡፡ እረ ማን ደፍሮስ ይገስጻል፡፡ እንዳውም ቶሎ ጠጋ ነው እንጂ፡፡ እጎንህ ያለውን ገበና ደብቀህ ፖለቲከኛ ታማለሕ፡፡ እኔም ነኝ አይዞአችሁ፡፡ ከእናንተ በአንድ እጅ ልለይ አልችልም፡፡ አጭበርብሮ አምጥቶ ቢያበላሕ ትበላለህ ግን ፖለቲከኛ ጥሩ ነው ወይም መጥፎ ነሕ እያልክ ጉሮሮህ አስከሚነቃ ትሙዋጉታለሕ፡፡ የፖለቲካ መድረክ የለ፡፡ የወጣቱ መድረክ ጫት ሆኖዋል፡፡ የመንግስት እና የተቃዋሚ ማሚያ፡፡ እናንተ የእኔ ወጣቶች ግን ብታሙም ጫት አትቅሙም አይደል? ደሞ በሰል ያለው ሌላው ቢራቤትም ቢሆን ፖለቲከኛን ማማት ይጀምራል፤ በዛው በልዩነቱ ወይ ጠረንጴዛ ሰብሮ አልያም ተፈናክቶ ይለያያል፡፡  ግንዛቤው ያደገው  ከዘመዱ አንዱ ሞራል የለለው ነገር ቢሰራ የሚለው“ አንተ አፈርኩብህ፣“ ይለዋል፡፡ ይንቀዋል፡፡ ይለየዋል፡፡ እኛ ግን መጥፎ እየሰራ እያየነው፤ ደግሶ እስከአበላን ድረስ ትልቁ ጨዋው ብለን እናውጅለታለን፡፡  ለዲሞክራሲ ለውጥ ያልረዳነው ፖለቲከኛን ወንጅለን ወንጅለን ጥግ አውጥተን እንጥለዋለን፡፡ ከአገር ሲወጣ ተገላገልን ወይ ሲሞት እሰይ እንላለን፡፡ የነገዎቹንም እንደማንላቸው ምን ዋስትና አለን፡፡ የዲሞክራሲ ጉዞአችን ከባድ እና አስቸጋሪ ነው፡፡ ቢሆንም ግን እሁሉ መገናኛ ቦታ ላይ የሚደበለቀውን የፖለቲካ ንግግር እንተው፤ አልያም ካልተውን በልዩነት መቀባበል እና መነጋገር አንጂ መጣላት እና መለያየት ይቅር፡፡ በአስተሳሰብ ልዩነት አንድ አገር ላይ በሳቅ መኖር፡፡  በማለት በቸር እላለሁ፡፡
ባዩሽ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen