Samstag, 22. März 2014

እኔ ውርድ ከራሴ




እኔ ውርድ ከራሴ

የዘመድ ጥልእና የወይራ ስናባጭ
ሲሉ ሰምቻለሁ እንኩዋን በወረንጦ አይወጣም በምላጭ፡፡
እቤትህ ያለውን ሳታስተካክለው
ጎረቤትህ  ሄደህ የምታማስለው
ምን  እንደሚያመጣ ቆም ብለሕ አስብ
አትሩጥ አትብረር ምላስህን ሰብስብ
እኔ ውርድ ከራሴ እኔ እነግርሃለሁ
የአንተ መቀስፈት አልፎ በልጅ አይቻለሁ፡፡
ምንድነው ጥላቻ ብቀላ መንገር
ይቅርባይ የሆነው እያለልን ፍቅር፡፡
እኔ ውርድ ከራሴ
በእግዚአብሄር ፊት ቆሜ ልናገር ለነፍሴ
ይህ ሁሉ ጋጋታ የምላስ ጅራፍ
እግዜርን አትፈትን ይብቃህእና እረፍ
ኢትዮጲያ አገሬ ስትል አምላክ አላት
ምን ብትበድልህ ነው ጥለሕ የሸሻሀት፡፡
ደክቶሩም አልቀረ የቤት ሰራተኛ
ሀሰተኛው አይል ወይም እውነተኛ
የታመናት አይቀር ወይስ ያ ቀማኛ
ምን ያህል ሰርተሕ ነው አርፈሕ የምትተኛ፡፡
አንተም  እዛው ያለሕ የምትኖር በውስጥ
ልብህ ወደማዶ እግርህ በአገር ውስጥ
ሻንጣህንም ቁዋጥረህ የሚታይህ ስደት
ቀልብህን የአሻውን ምን ልታገኝበት
በረሀው አይብለሕ አይንህን ክፈት
አገር ሰው ትላለች እዛው ሁንላት
አንተ አንተ ቀና ብለሕ ስማኝ
አይን አይኔንም እየኝ አንገት አትድፋብኝ
እኔ ውርድ ከራሴ
ለስጋዬም አይደል ልናገር ለነፍሴ
የአረብ መከዳ አይደል ድንጊያ ነው ትራሴ
ለምነግርህ ነገር ክርስቶስ ነው ዋሴ፡፡
ትግሬው አማራውን፤ አማራውን ሌላውን
ኦሮሞው እንደዛው በዘር ያነሳውን
ለጆሮ የሚቀፍ አንስተሕ ስትለጥፍ
መርገም አይሁንብን ይሻልሀል ማረፍ፡፡
አንተ ግን፤ አንተ ግን በልተሕ የምትክድ
ምን ይውጥህ ይሆን ስትመጣ ያቺ ፍርድ፡፡
እኔ ውርድ ከእራሴ
እናገርሀለሁ በእኔ ላለች ነፍሴ፡፡
አታስብ አትቸኩል ነፍሴን ልትወስዳት
ሆና ተሰርታለች ምንም ላታገኛት፡፡
ውሰደው እንዳሸህ ይህን ስጋየን
ጥምብ ከወደደልህ የሚገማውን፡፡

ባዩሽ



Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen