ከአፉ የሚሮጠውን አንተ እየተጣልክም አስተምረው፡፡
ደንቆሮ ነህ እንግሊዘኛ አትችልም ብሎ የሚሰድብህ ያገርህ ሰው፤ በእንግሊዘኛ የጻፍከው ጽሁፍ ጭንቅላቱን መቶታል ማለት
ነው፡፡ ምክናያቱም ቁዋንቁዋ አለመቻል አያሰድብም እና፤ ሁልግዜ እየተንተባተብክም በሁሉም ቁዋንቁዋ ጻፍ፡፡ አያችሁ፤ መሰረቱ ዘሩ እንግሊዝ የሆነ ፈረንጅ፤ ሰበር ያለ እንግሊዘኛ ብትናገር፤ እንግሊዘኛህ
ጥሩ ነው የት ተማርከው ብሎ እንድትደፍር ያበረታታሃል፡፡ ያገርህ ሰው ግን ኦሪጅናል ቁዋንቁዋው እንግሊዘኛ ያልሆነ ፌስ ቡክ ላይ
ይመጣና እንግሊዘኛህ ጥሩ አይደለም ብሎ ሊሰባበርህ ብዙ ተቀጥያ ቃል ያወጣል፡፡ ይህ እንግዲህ አይምሮውን ሚዛን ላይ ያስቀመጠ ሁዋላ
ቀር ነው፡፡ ቁም ነገሩ ቁዋንቁዋ አለማወቅህ ሳይሆን የሚያሰድበው አላማህ ነው፡፡ እናውቀዋለን ሰም እና ወርቁን፡፡ ብቻ እንደምንም
ብለው ሞራል አድቀው ሊያባርሩህ የሚፈልጉ አንዳንድ ሰዎችን እንድትነቃባቸው ብዬ ነው ወዳጄ ይህን ጽሁፍ የማቀርብልህ፡፡ በቃ የማይጭሩት
ጉድጉዋድ የለም፡፡
ዋናው ነገር ማንም ሰው ቁዋንቁዋ አወቀ አላወቀ የሰው ልጅ ፈጽሞ ማለፍ ለሚገባው ነገር ሁሉ፤ እንደአስተሳሰብ መስጠት
መንቀፍ እና ተካፍሎ መኖር መብቱ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር ፈጥመህ ለማለፍ የግድ ቄስ መሆን ይጠበቃል እንዴ? እንግሊዘኛ አወክ አላወክ ደግሞ ድምጽህን ለመስጠት ማነው ከልካዩ፡፡ የአለም
ትምህርት ተማርክ አልተማርክ ማነው ከልካዩ፡፡ የመጀመሪያው አስተማሪ እኮ ያስተማረው እግዚአብሄር እንጂ ሰው አይደለም፡፡ መብቴ
ነው ብለህ መጋፈጥ ነው እንጂ የምን መሸሽ ነው፡፡ በጀርመን አገር ብዙ የጀርመን ምሁሮች አሉ፤ ወ;ሮ
አንጀላ መርክል አይምሮ ያላት እውቀቱዋ የላቀ አገሩን በደንብ የምታስተዳድር ሆና እያለች፤ እንግሊዘኛዋ ግን በቂ አይደለም ተብላ
እውቀቱዋን እውን እንዳታደርግ አልተከለከለችም፡፡ የእሱዋ ቁዋንቁዋ ጀርመነኛ ነውአሃ፡፡ እንግሊዘኛ የማይችሉ፤ እና ከማወቅ የከለከላቸው
ነገር ምንድን ነው? ቁዋንቁዋ መቻል የመጨረሻው የእውቀት ደረጃ ነው ላችው ማን ይሆን እነዚህ የሞራል ላጲሶች? አንዳንድ የቁዋንቁዋ ባሪያ ወይም ዝም ብሎ ተገዢ የሆነ ሰው ብቅ ይልና ትንሹዋን
ችሎታውን ለማሳየት እንግሊዘኛህ ብሎ ሊተች ይነሳል፡፡ የቁዋንቁዋ ችሎታ የአንተን አይምሮ መመዘኛ ሊሆን አይችልም፡፡ በቃ ቁዋንቁዋ
የአካባቢው ሰው መገናኛ መገላላጫ ብቻ ነው፡፡ በቁዋንቁዋ አነስተኛነት እራስህን መግለጥ ሊያቅት ይችላል እንጂ፤ ለአንተ መሰደቢያ
እና መዘለፊያ መሆን የለበትም፡፡ ቁዋንቁዋ የአይምሮ መመዘኛ ቢሆን ኖሮ ቁዋንቁዋ ባለማወቅ ተሳዳቢው ባልተቸህ ነበር፡፡እሱ ችሎታውን
ቁዋንቁዋ በደንብ በመቻሉ ደምድሞታል፡፡ እድገቱ በዚህ ተወስኖአል፡፡ ከዛ ማለፍ አይችልም፡፡
ስለዚህ ቁም ነገሩ አካባቢን እና አገርን ወገንን በሚለውጥ ነገር ላይ መነጋገሩ ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ እኔ ለእራሱ የሚገርመኝ
የተለያየው የአካባቢያችን ቁዋንቁዋ የዘር መለያ እና መጫኛ ሆኖ ሲቀርብ እንኩዋን ያስቀኛል፡፡በቃ ቁዋንቁዋ የአካባቢ መለያ ሳይሆን
መግባቢያ ነው፡፡ ሌላውን ቁዋንቁዋ ተሰባብሮም ይሁን ተጣሞ ማወቅ እንዴት ጠቃሚ ይመስላችሁዋል፡፡ ምንው ሰባብሬም ቢሆን ሁሉንም
የአለም ቁዋንቁዋ በቻልኩ፡፡ እኔ ከአለም ሰው ሁሉ ጋር ተግባብቸ ለመኖር አይምሮዬ እያስገደደኝ ነው፡፡
ሌላው ውጭ አገር የምትኖሩ ሳሃን አጣቢ እያለ የሚሳደብ አለ፡፡ ፈረንጅ አገር ኮቢሊስቶን ተነጥፎ ካለቀ ብዙ አስርተ አመታቶች አልፈዋል፡፡ ስለዚህ እዚህ ኮቢሊስቶን ማንጠፍ
የለም፡፡ ታዲያ ምን እንስራ፡፡ ለነገሩ እውጭ የሚኖር ሰው በፖለቲካው
አለም የሚነቅፍ ነገር ሲፈጽም፤ አልያም ደግሞ የሚጻፉ ጽሁፎች አንዳንዱን ጭንቅላቱን ሲመታው እና ማንነቱን ለእራሱ ሲገልጽለት፤
አንጀቱን የሚያቃጥለው ይመስለኛል፡፡ ይህንን ሰሃን አጣቢ የሚል ተቀጥያ
የሚናገረው ማለቴ ነው፡፡ ኮብሊስቶንም ማንጠፍ ስራ ነው፤ ሳሃንም ማጠብ ስራ ነው፡፡ ዛሬ እኮ ሳሃን
ለማጠብ ባገኝ ብሎ ነው አብዛኛው የውጭ እድል የናፈቀው ባገኘበት አገር እየለቀቀ የሚወጣው፡፡ ሳሃን እንዳያትብ እዛ ሰላም ስጡታ፡፡
ስራ ስጡታ፡፡ የት ሊደርስ መሰለህ ታዲያ፡፡ በሰላም አጥቦ ለመኖር ነው፡፡ ዶክተር ሆነህ ሰላም እና እኩልነት በለለበት ስፍራ ከመኖር
፤ሳሃን አጥቦ ስብእናህን ሲከበር ማየት ደስ ይላል፡፡ ያስደስታል፡፡ ፊት ያፈካል፡፡ እዚህ እኮ ሳሃን አጣቢ እና የታወቀ ሳይንቲስት
እኩል የሚኖርበት አገር ነው፡፡ ቁጭ ብሎ አስተያየት የሚሰጣጥበት ደግሞ አስተሳሰብ የሚደማመጥበት አገር ነው፡፡ ግን ሳሃንም አጥበሕ
ቂጡ ያበጠ ደላር ይከፈልሃል፡፡ አገሬ ሀኪሙ ከሚያገኘው በላይ እዚህ ሳሀን አጣቢው ያገኘዋል፡፡ ስለዚህ ሳሃን አጣቢ ስድብ እንደማይሆን
ልንገራችሁ እና ግንዛቤያችሁን አሳድጉ፡፡ ሳሃን አጣቢ የአገሩ ሁኔታ አይመለከተውም የሚል ማነው ለመሆኑ? ለምንድን ነው ሰው የዋሕ የሚሆነው? ስራ ክቡር ነው፡፡ እንኩዋን እኛ ፈረንጁ ለእራሱ ተወልዶ ባደገበት አገር ሳሃን
ያጣባል፡፡ እቤቱ የበላበትን ለማጠብ እናቱን አይደለም የሚያሳጥበው፡፡ ደግሞም ሰራተኛ ቀጥሮ አይደለም የሚያሳጥበው፡፡ እንደአገራችን
ወይ በዘመድ ስም ከገጠር አንዲቱን አስመጥቶ አልያም እርካሽ ጉልበት ቀጥሮ አይደለም፡፡ እዚሕ ጉልበት እንደአገራችን እርካሽ አይደለም፡፡
የሰው ጉልባት ዋጋ ያለው አገር ሆኖአል፡፡ ስለዚህ እንደአገርህ እየመሰለሕ ሳሃን አጣቢ አትበል፡፡ ይህን ቃል ከአፉ የሚያወጣ መቸም፤
ያደገው በደሃ ገጠር ቤትሰብ የሆነች አስጠግቶ፤ በእናቱ እና በእህቱ፤ በርካሽ ሰራተኛ ጉልበት የኖረ አውደልዳይ ነው፡፡ እሱ እኮ
ይህን ቢያገኝ የእናቱን ቤት አሲዞ ተበድሮ ለደላላ ከፍሎ ልውጣ የሚል ነው እንዲሕ የሚለው፡፡ ምንድን ነው ሳሃን ማጠብ የሚያሰድበው፡፡
ቢሆንስ፤ ሰርቶ መብላት ያሰድባል? ወይስ ሳሃን ማጠብ ፤በአገርህ
ጉዳይ አስተሳሰብ መስጠት ይገደባል? እንዴ የተማረ ብቻ ነው እንዴ
አስተያየቱን መስጠት የሚችለው? ማነው ይህን ያስተማረህ? ደሞም እንዲሕ ስልህ ሁሉም ሳሃን እሚጥብ አይምሰልህ፡፡ ናዛ ብትገባ ሀበሻ
አለልህ፤ ሳይንቲስት ብትፈለግ ሀበሻ አለልህ፤ ሜዲካል ዶክተር ብትፈልግ ሀበሻ አለልህ፡፡ፊልም አክተር ብትፈልግ ሀበሻ አለልህ፡፡ ፖለቲከኛ ብትፈልግ ሀበሻ አለልህ፡፡ ፓይለት
ብትፈልግ ሀበሻ አለልህ፤ ወታደር ብትፈልግ ሀበሻ አለልህ፡፡ ሌባም ብትፈልግ አለልህ፡፡ ቦዘኔም ብትፈልግ አለልህ፡፡ ተማሪ አለልህ፤
ሴት አዳሪም አይጠፋም፡፡ በቃ አቃጥሮም የሚበላ አይጠፋም፡፡ በቃ የሰው ባህሪ ሁሉ በማንኛውም ስፍራ በማንኛውም ዘር አለልሕ፡፡
ወይኔ የምታሰኘውስ የምትጣጠብ ሳህን የጠፋች ለታ ነው፡፡ በጠቅላላው፤ ለአለም ፖለቲካ ሁሉ አማካሪ የሚሆኑም ኢትዮጲያውያኖች ከወደአሜሪካ፤
ካናዳ“ እና እንግሊዝ አገርም እኮ ሞልተዋል፡፡ ምነው በታደልክ እና ወደአንተም በመጡልህ እና በረከትን በበላሕ፡፡ ለመሆኑ የተማረው
መናሀሪያ የት ሆነእና ሳሃን አጣቢ ትላለህ፡፡ ግን እኔ አልተማርኩም፡፡ አይዞአችሁ፤ ላስተዳድር አልመጣም፡፡ ግን ግን አስተሳሰቤን
ለመስጠት የሚገድበኝ ድንቁርእና ግን እኔ ጋር ከጠፋች ዘመናት አስቆጥሮአል፡፡ እራስህን ለውጥ እና ስብእናን ተማር፤ ለእኩልነት
እና ለዲሞክራሲ ተናገር እንጂ አፍን ለማሰር አትሩጥ፡፡ አስተሳሰብ አንድ ከእግዚአብሄር አንድ ከሰይጣን ነውእና ማንነቱን ለይ፡፡
ሰላም ይብዛላችሁ የምላችሁ እማማ ባዩሽ ነኝ፡፡
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen