ቤተክርስቲያን እና የሞት ፍርድ ህግ መጽደቅ
አንድ ነገር ዛሬ ላያቸው የፈለኩት ነገር ቢኖር አንዱ እግዚአብሄር መሪዎች
ወይም ገዢ ፓርቲዎች መጥፎም ቢሆኑ አትንቀፉአቸው የሚለው ትእዛዝ ነው፡፡ እንግዲሕ እዚህ ላይ እኔ እንደተረዳሁት፤ እግዚአብሄር
ይህንን ነገር ያስተላለፈልን አድሎ ባላቸው ሰዎች ጋር ስለተስማማ ወይም ስላበረ ሳይሆን፤ ብንቃወማቸው ሊያንገላቱ፣ ሊያሳድዱ አልያም
ሊገሉህ ስለሚችሉ ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ለእኛ በማዘን እንጂ ሌላውን በማበር አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በአንተ የሚሰራው ስራ
ስላለ ማንም ሰው በቶሎ እንዲሞት የሚፈልግ አምላክ አይደለም፡፡ ትእግስትም ካለህ የክፉ ሰውን መጨረሻውን ሊመሰክርልህ ስለሚፈልግ
በትእግስት እንድትጠብቅ ይፈልጋል፡፡ ውሻ ባለቤቱን ይበላል፡፡ ደግሞም መሪዎችም በገዛ ወታደራቸው ሲበሉ ማየታችን የቅርብ ግዜ ታሪክ
ነው፡፡ እግዚአብሄርንም „የበቀል አምላክ“ ዳዊት ብሎታል እና፡፡ ይህ ትክክል ምክር ነው፡፡ ክፉ መሪዎች ተቃውሞ የሚስማማቸው አይደለም፡፤ ተግሳጽም
የሚቀበሉእና የሚያርሙም እንዳልሆነ በአለም ሁሉ ታይቶአል፡፡ ሂትለርን የተቃወሙ ጀርመኖች፤ ጀርመኖችን በሚወደው በእራሱ ሂትለር
ተገለዋል፤ ድምጥማጣቸው ጠፍቶአል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄርም ይህን
ተመርኩዞ እንጂ በምንም አይነት መጥፎ መሪዎችን እንዲቆዩ ፈልጎ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በቀኑ ሊፈርድ ይነሳል፡፡ ታአምረኛ መሆኑን የኤርትራ ባሕር የፈረኦንን ወታደር ሁሉ እንዳሰመጠው ተመስክሮልናል፡፡ እኛም ሞኝነትም ሆኖ ቢቆጠርብን አምነን ተቀብለነዋል፡፡
በጣም የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር፣ መሪዎች ድክመታቸውን
እንዳያዩ አይናቸው እንዲሸፈን፤ ምእመናኑን እግዚአብሄር እንደለለ ወይም እንደማይሰራ የሚያሳይ ምግባር አንዳንድ የቤተክርስቲያን
ቅርቦች እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ ይህንን መሪዎችን አትቃወሙ የሚለውን ሁኔታ
ለግል ጥቅም ሲጠቀሙበት ይታያል፡፡ የፖለቲካ መሪዎችንም ይሸነግሉበታል እንጂ መነቃቃት እና በህዝብ እሚያስወደድዳቸውን ስራ እንኩዋን
ለመናገር አይደፍሩም፡፡ ይህ ሁኔታ እግዚአብሄር ከሚለው ጋር ፍጹም የተለያዬ እና ግብዝነትን የሚያሳይ ነው፡፡ ሰው ባይቃወምም፤
መጥፎን ግን መደገፍ ወይም መጥፎ እንደለለ መሸፈን ከእግዚአብሄር እውነት ልትደበቅ አለመቻሉዋን ዘንግተዋል ማለት ነው፡፡ መጥፎን
የመደገፍ ሁኔታ ግን በጭራሽ የሚበረታታ አይደለም፡፡ የኢትዮጲያን ፖለቲካ ጠቀስ ለማድረግ የምፈልግበት ምክናያቶችም አሉኝ፡፡ እሱም
ከዘመኑ ጋር ሊሄድ ይችላል ወይ የሚለውን ነው፡፡ ይህ የአገራችን ሰላም ጉዳይ ህዝብን ውስጡን የሚቦረቡር እና መደነጋገር እየፈጠሩ
መሆናቸውን እያየን ነው፡፡ የአንድ አገርፖለቲካ ካለተቃዋሚ ሊጉዋዝ አይችልም፡፡ ይህ ከሆነ ግን አመጽ እና ጥላቻን ያባብሳል፡፤
ይህንን ቤተክርስቲያን ልትሸፍን አትችልም፡፡ምንም እንከን የለለበት፤
እግዚአብሄር እንኩዋን ተቃዋሚ አለው፤ የቤተክርስቲያን መሪዎች እራሳቸውን ካላስተካከሉ እና የእግዚአብሄርን ውነት ካልተረዱ፤ ቤተክርስቲያን
እያደር ባዶ እየሆነች እንደምትሄድ ከአንዳንድ የውጭ አገሮች ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ የውጭ አገር ቤተክርስቲያን በምእመናን ያልታደለችው፤
ሰው በሀጢያት ስለተዘፈቀ ሳይሆን፤ ሀጢያት ቤተክርስቲያን ውስጥ እየገባች የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስን ባህሪ አንዳንድ የምእመናኑ
አስተማሪዎችን እንዳያሳዩ አይናቸውን ስለጋረደች ነው፡፡ የሰው ጥራት
እንጂ ፤ የቤተክርስቲያን ብዛት ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄደውን የምእመናን ብዛት ሊያበዛ አይችልም፡፡ ቁምሳጥን ውስጥ ያለህ ልብስ
ብዛት የሚመችህን አያሳየንም፡፡
እኔ በበኩሌ በግልጽ መናገር የምፈልገው ነገር ቢኖር፤ ማንኛውም ቤተክርስቲያን በኢትዮጲያ ውስጥ ያሉ ፖለቲካ ፓርቲዎችን
ሁሉ፤ ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ተግሳጽ፣ እርቅ አልያም ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ ምንም አይነት ደፋር የሆነ መጋፈጥን፤ እግዚአብሄር
እንዳለው ለማድረግ አልቻሉም፡፡ ከቶም እየደመቀ እና እየገነነ የሄደው፤ በየአቅጣጫው አለማዊ የሆነ ወገናዊነት በኢትዮጲያም ቤተክርስቲያን ውስጥ እየታዬ
በመሆኑ ወደእግዚአብሄር እውነት መመለስ ጥሩ ነው፡፡ ለእኔ ተቃዋሚ ቢኖርም በእነሱም ግዜም ቢሆን የተሸለ ዴሞክራሲ ይመጣል ብዬ
ባላምንም ግን አንድ ገዢ ፓርቲ እረጅም ግዜ መግዛቱ በእራሱ እግዚአብሄርን መናቅ እንዳይሆን መፍራት ነው፡፡ ይህ በእራሱ ህዝብን
መናቅ እና ወደሌላ ጥላቻ እንዲሄድ መገፋፋት ነው፡፡ ምንም አይነት ወንጀልም ይስራ፤ እግዚአብሄር እስረኞችን ጠይቁ ያለውን የጅምላ
ንግግር ተረድተን፤ ቤተክርስቲያን በእንዲሕ አይነት ነገር ላይ ብትነቃቃ መልካም ነው፡፡ ይህም ሊረዳ የሚችለው ገዢው ፓርቲ በንዴት
እና በብስጭት የሞት ፍርድን እውን እንዳያደርግ መታገል ቤተክርስቲያን ግዴታ አለባት፡፡ አንዳንድ አገሮች የሞት ፍርድን እውን ሲያደርጉ
አንዳንድ እንደማያደርጉት ከህጋቸው ላይ እንደሰረዙት ይታወቃል፡፡ ይህ የሆነው በብዛት በበቤተክርስቲያን ምእመናን፣ ቀሳውስት እና
በሰበአዊ መብት ተሙዋጋቾች ነው፡፡ ኢትዮጲያ ግን ምድራችንን ሊያስረግም በሚችል የሞት ፍርድ ወይም ለሚደረጉ ማንኛውም ግድያ ሁሉ
አንድም ቀን በድፍረት ምእመናኑ በሰብአዊ መብት ላይ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጣ ህግን እንዲሰረዝ ወይም እንዲሻሻል የማድረግ ነገር
ስታደርግ አትታይም፡፡ ይህንን የምለው ኦርቶዶክስን፣ ካቶሊክን ደግሞም ፔንጤን ነው፡፡ ሁሉም መጽሃፍ ቅዱስን ወይም ወንጌል ከሆነ
አላማው፤ ደም የሚፈስበት አገር ምንም አይነት ሰላም ስለማያመጣ የሞት ፍርድ በሕግ ተደንግጎ ተፈጻሚ እንዳይሆን ድምጽ ማሰማት አለብን፡፡ ይህንን እኔ ትናንትም
ወያኔ ኢሕአዴግ ጫካ በነበረበት ግዜ፤ ሰዎችም በሚሰቃዩበት ነገር ሁሉ ላይ በዛም ዘመን በሚታሰሩ እስረኞች ላይ ሰቆቃ እንዳይፈጸምባቸው
የሞት ፍርድ እንዳይፈረድባቸው አጥብቄ እንደተቃወምኩት ሁሉ፤ ዛሬም የምለው በታሰሩ ሰዎች ላይ የሚደረጉ ማንኛውም የሰቆቃ ምርመራ
ካለ እና የሞት ፍርድ እንዳይደረግ፤ በጌታዬ በእየሱስ ክርስቶስ ስም በጾም እና በጾሎት ጸጉሬንም በመንጨት በማልቀስ እና በመድፈር
እጠይቃለሁ፡፡ ሌላ ሰው እስኪነሳ ድረስ እና ገዢውፓርቲ የምድራችንን በረከት እንዳያዘጋ ከማንኛውም ግፍ መሰል ነገሮች እንዲቆጠብ
እማጸናለሁ፡፡ የሞት ፍርድ መልካም ሰውንም በስህተት፤ በሀሰተኛ ምክር
ስትበላ ታይታለች እና የሞት ፍርድ በሕግ ተደንግጎ ከሆነ እንዲነሳ እና እንዲሻሻል ማንኛውም ምእመናን ጥረት እና ጸሎት ማድረግ
አለበት፡፡ ዛሬ የሞት ፍርድንም የደነገጉት፤ እንደአፍሪካ አይነት አገር ላይ እነሱ እራሳቸውንም ሊበላ ችላል እና፤ ነግ በእኔ ብሎ
ሰው ይህንን የሚመጣውን መከራ ከወዲሁ ማስተዋል ነው፡፡ እግዚአብሄር ፊተኞች ወደሁዋላ ይሆናሉ ተብሎ ተጽፎአል እና፡፡ ጌታ ከሁላችሁ
ጋር ይሁን፡፡ ባዩሽ
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen