Freitag, 4. Juli 2014

የግንቦት 7 እና የወያኔ ኢሕአዴግ ፍጥጫ እስከመቼ ይዘልቅ ይሆን?



የግንቦት 7 እና የወያኔ ኢሕአዴግ ፍጥጫ እስከመቼ ይዘልቅ ይሆን?

እውነቱ እኔ ስለግንቦት 7 እጅግም የማውቀው ነገር የለኝም፡፡ ይህን ስል ፈርተሸ ነው የሚለውን ነገር ወደጎን ተወት፤ አድርጉት፡፡ ፍርሃት ካላችሁ፤ ነፍስ ካወኩ ጀምሮ አብሮኝ የኖረእና ያረጀብኝ ስለሆነ በአባባላችሁ እውነትንት እደነቃለሁ፡፡  ብዙ በማላቀው ነገር መጨናነቅ ሲደርስብኝ እና፤ ያለውም ገዢ ፓርቲ ብዙ ነገሮቹ ከቁጥጥር ውጭ በሆነበት ሁኔታ፤ እንደአብዛኛው ሰርቶ ለፍቶ አዳሪ እንደሚፈልገው ሰው የሚደርስብኝ የስራ አፈጻጸም ሁኔታ፤ ወደአንድነት ቢሮ ሄጃለሁ፡፡ የሴት የመጀመሪያ ትግሉዋ ከኢኮኖሚ ጥገኝነት መውጣት እንደሆነ ስለማውቅ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ትግሌ ላይ ነበር ትኩረቴ፡፡ ምክናያቱም በኢኮኖሚ መዳከም ማለት መራብ ነው፡፡ ሴት ከተራበች አካሉዋን ወደመሸጥ ካለመሄድ በቀር ሌላ አማራጭ የላትም፡፡ ስለዚህ ለምን የመጀመሪያ ደረጃ ትግልሽ ይህን አደረግሽ ብላችሁ ልትወቅሱኝ አትችሉም፡፡ ግን ይህን የአላማዬን ድል የሚያቀናጀኝ ለእኔ እይታ የተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ አላያሁም ነበር፡፡ ወደአንድነትም ሄጀ የነበረው አንድ ግዜ በጋዜጣ ላይ ስብሰባ ጠርቶ በድንገት ስላየሁት ነበር፡፡ እስኪ ልይ ልስማ ብዬ ሄድኩ፡፡ መስራት ባለመቻሌ ስራ አቁሜ ነበርእና፡፡ ግን እንደእውነቱ በንግግራቸው ሁሉ ከመመሰጤ ቀደም ብዬ፤ ችግር የደረሰባቸው ሰዎች እየተነሱ የእርዳታ ጥሪ ያሰሙ ነበር፡፡ እኔም ብሶተኛ ስለነበርኩ ነገሩ ሁሉ ለግዜው የመንፈስን መጽናናት አገኘሁበት፡፡ የሚገርመው በየቤተክርስቲያኑ ሄጄ ያላገኘሁትን የሰው መጽናናት እዛ ቦታ ላይ ግን ትንሽ በነጻ መተንፈስ አይነት ነገር ስላየሁበት አይምሮዬን ቀለል አለው፡፡ በዚህ የተነሳ፤ ሰው ከመሰሉ ተበዳይ ጋር ባይጀግንም ይጽናናል ብዬ ገመትኩ፡፡ ለካስ ብቻዬን ተበዳይ አይደለሁም ለካ፤ የሚያስብል ስሜት ገነባሁ፡፡ ግን አንድ ነገር ደግሞ ተገነዘብኩ ስሜታዊ ሆኖ የፖለቲካ ፓርቲን መደገፍ ይሻላል ወይስ በግንዛቤ ብዬ ገመትኩ፡፡  ግን በበደሉ መካካል ልዩነት ሊኖር ይችላል፡፡ እንደተረዳሁት በፓርቲ አባልነቱ የተነሳ የሚንገላታ እና ደግሞ ዝምብሎ በስግብግብ ስራ አስፈጻሚዎች የተጎዳ አንድ ቤት ውስጥ ማየት ነበር፡፡
ለማንኛውም ሁልግዜ በግልጽ የምናገረው ነገር አለ፡፡ እኔ ፈሪ ነኝ፡፡ አስተዳደጌም ቢሆን ፈሪ ተደርጌ እንጂ ጀግና እንድሆን ተደርጌ አላደኩም፡፡ ሴት በመሆኔም ሴት በዘመኑ ልታድግበት የምትችለውን በአባት በወንድም ሁልግዜ መኮርኮም፤ እንዳዳምጥ እንጂ እንዳልናገር፣ ከወንዶች መካከል እንዳልገኝ፣ እንዳልስቅ የመሳሰሉ ወግ አጥባቂ የሆኑ እድገቶችን አልፌበታለሁ፡፡ የሚገርመው በእኛ ግዜ እንደእውነቱ ከሆነ አጥፍተን ሳይሆን ሌላዋ ባደረገችው ድርጊት እንኩዋን ለመቀጣጫ መቀጥቀጥ ነበር፡፡ አዎ ዛሬ ይህንን ሁሉም ቢጋፈጠው፤  አስተዳደግ ባህል ምንያህል እንደሚያሽ እና ስነልቦና ለይ ተጽእኖ እንዳለው፡፡ ዛሬ ቢሆን በፖለቲካ ውስጥ እንኩዋን ሚስቶቻቸውን የማያሰልፉ ብዙ ፖለቲከኞች እናያለን፡፡ ጨዋ ሴት ድምጹዋ የማይሰማ የሚል የሙገሳ ቃል ውርሳለች እና፡፡  እስከዛሬ ያለቀቀኝ ተፈጥሮአዊ ሳቄ፤ የዛን ግዜ ምን ያህል እንዳስገረፈኝ አስታውሳለሁ፡፡ የሳቀ ሁሉ ግን ደስተኛ ነው ማለት እንዳልሆነ ተረዱልኝ፡፡ በአንዳንድ ቦታ ላይ ያሰማሁት ድምጽ ለብዙዎች የቀለለው „ቀውስ ወይም እብድ“ የሚል በመሆኑ፤ ይህ ቃል ዝም ብሎ ለፍርድ እንዳልወጣ አውቃለሁ፡፡ ሴት ከተናገረች ጤነኛ እንዳልሆነች የሚያሳይ አስተዳደግ ያደጉ የወግ አጥባቂ እርዝራዦች ናቸው እላለሁ፡፡ ይህንም ብዙ ሴት ስለሚፈራው እስከዛሬ ድረስ ሴት የታገለቸውን ያህል ብትታገል ስሙዋ ድብቅ ሆኖ ያልፋል፡፡ በወያኔ ኢህአዲግም ገናና ሴት አልሰማሁም እና፡፡ ሁሉም ድል የሚሉት በተወሰነ ወንዶች የተጠናቀቀ መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ስለፓርቲዎች አላውቅም ብል ውሸት እንዳልሆነ እንድትረዱ እፈልጋለሁ፡፡ ያም ሆነ ይህ አለማወቅም የሚያስኬደው መንገድ የምትወደውን ልጅህን አይምሮ ሰባብሮ መጣል ነው፡፡ ስለዚህ እኔ ለፖለቲካ ሕይወት የማላገለግል መሆኔን አውቀዋለሁ፡፡ በዚህም የተነሳ ዝንባሌዬ ወደእምነት እና ብሎም ወደሰብአዊ መብት ሙሉ ለሙሉ ሆኖአል፡፡ አስተዳደጉ እንደዛ ሆኖ ያደገ ልጅ ልበል ልተው እያለ የሚኖር ለመወሰን የሚቸገር እና ፈሪ ይሆናል፡፡ የኢትዮጲያ ፖለቲካ ሀይለኛ ውሳኔን የሚጠይቅ መሆኑ በዲሞክራሲው አካሄድ እያየነው ነው፡፡ ወይ ተዋጊ ነህ አልያም አይደለህም፡፡  እንግዲሕ መቀጣት ማለት አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቻለሁ፡፡ ተሰርቄ እንጂ ሰርቄ እንድመጣ ማን ይፈልጋል? በታማኝነት ማደግ የሚተወው ጥሩ ነገር ቢኖርም ተሰርቀህም ግን ወደሙግት፣ ወደማሳመን፣ አልያም ጉዳይህን ለመግለጽ የሚከብድ ይሆናል፡፡ እንግዲሕ በዚህም የተነሳ ፖለቲካ መፍተሄ አገኛለሁ ብዬ ስለማልገምት ወያኔ ኢሕአዴግም በሉኝ ተቃዋሚ ጋር ምንም ትስስር የለኝም፡፡ ግን የባህሪ ለውጥ የሚያመጣልኝን ነገር ለመገንባት ዘወትር በመጣሪ ዛሬ ዛሬ የደረስኩበት ነገር አትንኩኝ፤ የእኔ የሆነን ነገር አትንኩ ባይነትን አምጥቻለሁ፡፡ ልናገር እንጂ ግን ህግ የማይከበርበት አገር መብቴንም እውን ማስደረግ፤ „ላም አለኝ በሰማይ ወተቱዋንም አላይ“ ይሆናል፡፡ በቃኝ መገፋት ማለትን ግን አምጥቻለሁ፡፡ ይህ አስተዳደግ ባህሪዬ በእራሴ ላይ የሚደረጉ ግፎችን ለመቃወም የሚያስችል ጥንካሬን አልሰጠኝም ነበር፡፡ ያደረገኝ ሁልንም ነገር ለመቀበል እና ማልቀስ ብቻ ነበር፡፡ ስለዚህ አንዳንድ ስራ አስፈጻሚዎች የሚያደርጉት አድሎእና ግፍ በገዢው ፓርቲ ተስፋ እንድቆርጥ አድርጎኛል፡፡ ይህም የሆነበት ምክናያት ምንም እውነት እና ውሸቱን መለየት አቅቶአቸው መሰለኝ፤ ሕግን የበላይነት እንዲኖረው የሚያደርጉት ምንም አይነት እርምጃ ባለማየቴ ነው፡፡
እንግዲሕ እኔ የምናገረው በአማራው ክልል በኖርኩበት አካባቢ የኖርኩትን እና ያየሁትን ነው፡፡ በተለይ ሴትን ካሬጅ ሳይሆን ዳሜጅ የሚያደርግ ሁኔታ በሰፊው የሚታይበት ነው፡፡ ማንም ይህንን ለመለወጥ የሚያደርጉት ፖለቲካም ሆነ ሶሻል እንቅስቃሴ የለም፡፡ በሌላ መልኩ አንድም ተቃዋሚ አልያም ወያኔ ኢሕአዴግ የሚያስብል ትችትም የሚመጣብኝ ግንዛቤዬ በብዛት ያተኮረው ፖለቲካው ላይ ሳይሆን የሶሻል ችግሩ ወይም የባህል ተጽእኖ ያመጣው ችግር ላይ ብቻ ስለነበር ነው፡፡ ወደአንድ ጎን እንድትሆን የሚያስገድድህ የፖለቲካ ባህል ያለበት አገር ኢትዮጲያ መኖር እውነትን ደብቀህ መሸንገል መኖር ያለማምድሃል፡፡ ገዢውን ፓርቲ ሳትወድ እንደምትወደው መሸንገል አልያም ተቃዋሚን ሳትጠላ እንደጠላህ መናገር፡፡ ሀሰት እና ፍርድ የተተናወጠው እና ለሙስና እራሱን ያዘጋጀ፤ጉዳይንም ቶሎ በጉቦ በመለማመጥ የሚያስጨርስን ሰው የፖለቲካ ንቃተ ህሊና ያመጣል እና ለፖለቲካው ለውጥ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብዬ ስላልገመትኩ ውስጤ በብዛት በሀዘን ስሜት ይሞላል፡፡ ምክናያቱም የአስተሳሰብ ለውጥ ከሌለ ዲሞክራሲን ፖለቲካ ፓርቲ ብቻ እውን ያደርጋል ብዬ ስለማልገምት ነው፡፡ በዚህም መልኩ የኢትዮጲያ ፖለቲካ ፓርቲዎችን በሙሉ ፈተና እንደሚገጥማቸው ተረድቻለሁ፡፡ መጀመሪያ እራሴን ከተጫነኝ የፍርሀት አስተዳደግ ካላወጣሁ ለአገሬ እድገት አስባለሁ ማለት ይቸግረኛል፡፡ የምንናገረውን መርጠን ያስቀይም ይሆን፤ ያስጠይቀኝ ይሆን ብለን በመቆዘም የምንኖር ነንና፡፡ ብቻ በመጠኑም ቢሆን እንደተረዳሁት ግንቦት 7 የሚባለው ፓርቲ በትጥቅ ትግል ውስጥ የገባ ነው ተብሎ እንደሽብርተኛ በገዢው ፓርቲ ተቆጥሮአል እና በኢትዮጲያ ውስጥ እንደማይፈቀድለት እንደእነ አንድነት ፓርቲ ያልሆነ ነው ሲባል፤ መረጃ አገኘሁ፡፡ ይሁንና ይህ እንግዲሕ በኢሕአዴግ እና በግንቦት 7 መካከል ትልቅ ልዩነት የፈጠረ ውጊያ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ይሁንና ግን ዛሬ አቶ አንዳርጋቸው የሚባሉት የግንቦት 7 ዋና ሰው፤ ከየመን ተላልፈው ለኢትዮጲያ ተሰጥተዋል በመባሉ በአንዳንድ ሚዲያዎች ሰማሁ፡፡ እውን ከሆነ እንግዲህ ሁኔታው ብዙም የሚደንቅ አይሆንም፡፡ ምክናያቱም በሁለት ተዋጊዎች ወይም ተቀናቃኞች መካከል ምንግዜም የሚጠቀሙት መንገድ እረቂቅም ቢሆን ለማሸነፍ እና ለመሸነፍ ተፋጠዋል እና፡፡ የፖለቲካ አኪያሄድ አደጋው እንዲህ ስለሚሆን፤ ለማንኛውም ትግል በሉት ጦርነት፤ ዘመንን መገንዘብ ደግሞም ቦታን መምረጥ ደንብ ነው፡፡ ብቻ እኔ ምኞቴ አሁንም ቢሆን እርቅ ነውእና እግዚአብሄር በወንድማማቾች መካካል ያለውን ሁኔታ ይፈታ ዘንድ ጸሎቴ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ግንቦት 7ስ እድሉ ቀንቶት ከወያኔ ኢሕአዴግ አንድ ሰው እጁ ቢገባ ይለቅ ነበር ወይ ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ፡፡ እኔ በበኩሌ የምለው በኢትዮጲያ ችግር እንዳለ ሁሉም ያውቃል ችግሩ ግን የሚፈታው የመንን አቁዋርጦ በመሄድ ነው ወይስ እዛው አገር ውስጥ በመሆን? በመጨረሻ የምለው ነገር ቢኖር፤ እራስን ወዳድ በበዛበት አገር፤ ጉቦ ሰቶ ነገርን ማጣመም ጤነኛ ሆኖ በሰው አይምሮ በተቀመጠበት ሁኔታ፤  አንዱ ደስታውን ላለማጣት ገዢውን ፓርቲ በሚያታልልበት እና በሚሸነግልበት አገር፤ ፖለቲከኞችን ተጠያቂ እያደረጉ ምሁሮች እንዲንከራተቱ ማድረግ እስከመቼ ይሄድ ይቀጥል ይሆን?  በሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በገዢው ፓርቲም ቢሆን ቀናነት ያላቸው ለአገር ለወገን ልባቸው የተቃጠለ ይኖራል፡፡ ግን አለመታደል ሆኖ የምንኖርባት ኢትዮጲያ ህዝቦቹዋ፤ ለውጥ ፈላጊ ግን ለለውጡ ምንም አይነት እርምጃ መሄድ የማይፈልጉ እንደእኔ አይነት በመሆናቸው ነው፡፡ አያችሁ ዘወትር የምለው እውነትስ የገዢው ፓርቲ አባልስ የሆነው መልካም ለአገሪቱ ለመስራት ዝግጁ ነውእን? ወይስ እንዳው ዝም ብሎ እየሸነገሉ የራስ ህይወትን ማሰብ፡፡ ምክናያቱም ጥፋቱ ሁሉ መጨረሻ ላይ በአንድ መሪ አልያም በጥቂት ሚኒስተሮች ማሳበብ ተለምዶአል እና፡፡ በቸር፡፡ ባዩሽ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen