ቁዋንቁዋ ስለሚገባህ ሳይሆን መረዳትን ይዘህ አንብብ
ቁዋንቁዋ
ስለሚገባህ ሳይሆን መረዳትን ይዘህ አንብብ
እኔ
እምጽፈውን እያነበበ የሚናደድ ሰው፤ አቁሚ እያለ ይሰድበኛል፡፡ ቢያገኙኝ ምን እንደሚያደርጉኝ ክርስቶስ ያውቃል፡፡ የሚያስቀኝ ስድብ ግን አሮጊት የሚለው ነው፡፡ ተሳድቦ ሞቶ ነው በእሱ ቤት፡፡ እኔ ግን በአሮጊትነቴ
የምኮራ እና፤ ምንም አይነት የማጎብጉብም ሆነ የአድርባይነት ባህሪ የለለኝ አሮጊት ነኝ፡፡ በዚህ ባህሪዬ እኮራለሁ፡፡ አብሮ
አረጀብኝ፡፡ አጎብጉቤ አልበላም፡፡ መንግስትንም የለለሁትን አለሁልህ እያልኩ አልሸነግለውም፡፡ አልበላውም አልጠቀምበትም፡፡ የኢሕአዴግ
ገንዘብ የሕዝብ ነውእና፡፡ የእኔ ነውእና፡፡ የእናንተ ነውእና፡፡ እንደሚሳደቡት ማለቴ ነው፡፡ እውነቱን እውነት እያልኩ እዚህ
ደርሻለሁ፡፡ ለማንኛውም ይህ እናቱን እየተሳደበ ያደገ አንዳንድ ሰው ምንም አይገባውም፡፡ የባህሪ ለውጥ ካላመጣ በስተቀር፡፡ ፖለቲከኛም
ደግሞ ያደርጋቸዋል፡፡ ከአንጀቴ ብስቅበት ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ግን አገርን ወገንን አለምን ይዞ የሚሞት ድንቁርናን ስለተሸከሙ
በእነዚህ ሰዎች መሳቅ ሳይሆን መጸለይ ነው፤ ኮስተር ብሎ መንገር እና ማስተማር ነው፡፡ እንዳውም መንግስትን የጠቀሙ መስሎዋቸው
ገደል የሚከቱት እነዚህ እንደ ክረምት ጻሀይ ብልጭ ድርግም ዕያሉ አንድ ቃላት ወርወር አድርገው የሚሄዱ ናቸው፡፡ እዛም አለንልህ
ይሉታል፡፡ አድርባይ የትም ቦታ ግን ተገኝቶ የማያውቅ የማይጨበጠው ንፋስ ነው፡፡ አድርባይን እጠላለሁ፡፡ እናንተም ጥሉ፡፡
ለምድራችን አሳች ነው፡፡ ለማንም አይጠቅምም፡፡
ግን
ዲሞክራሲ ማለት ፤ከዚህ ጀምሮ እኔንም ነጻነቴን አለመንፈግ መሆኑን እንኩዋን የማያውቅ አለ፡፡ ይገርማል፡፡ አቁሚ አትጻፊም የሚለኝ
ወንድ መሳይ ሴትም ሊሆን ይችላል፤ ያው የፌስ ቡክ ነገር አይታወቅም፡፡ ያም ሆነ ይህ አንዳንዱ ጽሁፍ ማንነትን የሚነካ፣
የሚያስታውስ በመሆኑ ውስጡ ሲነካ የሚናደድ ይኖራል፡፡ እዚህ ላይ ጹሁፌ ታርጌቴን መታ እላለሁ፡፡ በሚሰድቡኝ እስቃለሁ፡፡ እኔ
ምንም ማድረግ አልችልም፡፡አንድ ሰውን አነጻጽሬ አልጽፍም፡፡ በናታችሁ እዛው እንደለመደ እናቱን እና ሚስቱን ያፍን እንጂ፤ እኔ ጋር
ምን አለው? እሱ መንግስት ነውን? አንዳንዱ እኮ የፖለቲካ ፓርቲን
የሚረዳው፤ ሌላውን በመሳደብ ነው፡፡ አያስቅም? ወይ ግንዛቤ? 23 ዓመት እድሉ እያለ ዲሞክራሲን ለማስተማር ሳይጠቀሙበት፤ ሹል
ምላስ አሲይዘው አፍ ጠባቂ ማስኮልኮል እና ሞራልን ለመግደል ማሰማራት ምን ትርፍ አመጣ፡፡ በአጠቃላይ ስድብ ከፖለቲካ ጋር፤
ከአገር ፍቅር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም፡፡ የሰውን የእራሱን የወደቀእና ያዘቀጠ ባህሪ የሚያስረዳ ነው፡፡ ገዢውን
ፓርቲም ሆነ ተቀዋሚን ደጋፊ ነን ወይም አጃቢ ነን የምትሉ እርስ በእርሳችሁም አትሰዳደቡ፡፡ ልብ በሉ ስድብ ይዞ የሚሰለፈውን
መልስ አትስጡት፡፡ ቁም ነገር የምትለዋወጡበትን ግዜ ሊያቃጥል የገባ ቦዘኔ ነው፡፡ ዝም ብሎ ያለችውን ያልታደለች የኢንተርኔት
ገንዘብ ገደል እየከተተ ያለ፡፡ ወይም ያገኘውን የነጻ የኢንተርኔት መጠቀሚያ እድል በከንቱ የሚያቃጥል፡፡ ስድብ ክርቲክ አይደለም፡፡
ስድብ የእራስህን ማይንድ የእድገት ደረጃ የሚያሳይ ነው፡፡ ጥቂት
ሰዎች ዲሞክራሲ እንዴት እንደሚሄድ ተማሩ፡፡ ሰውን ለማፈን አትሞክሩ፡፡በምታነቡት አትናደዱ፡፡ በተለይ ስለእራሴ የምናገረው በእኔ ጹሁፍ የሚናደድ
አያንብብ፡፡ እኔ አስተያየቴን ከመጻፍ ስለማልቆጠብ ጨርሳችሁ እንዳትቀውሱ ብዬ ነው፡፡ ጠንከር ለክርቲክ፤ አስተያየቴን መቃወም መብት ነው፡፡ እኔም መማር እፈልጋለሁ፡፡
ጎበዝ ወይም ጀግና አልያም ሰነፍ እና ፈሪ ስለሆንኩ አይደለም የምጽፈው፤ መብቴ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ ማመዛዘን የሚችል መሆን አለበት
የተጻፈን ማንበብ የሚችል፡፡ እንዳው ቁዋንቁው ስለሚገባህ ብቻ አይደለም የሚነበበው፡፡ መረዳትህንም ይዘህ ነው፡፡ ክሪቲክ እና
ስድብ ለዩ፡፡ ለነገሩ ተመስገን ነው ለዛሬ እድሜ ያደረሰኝ፡፡ ስንቱን አየሁት፡፡ አሮጊት ሹመት መስሎ እስከሚታየኝ ደስ
ይለኛል፡፡ አያሳፍርም፡፡ ዛሬ ስንቱ በለጋ እድሜ እየተቀጨ አይደል? ለሊቱን በጫት፤ በዲስኮ እና በልቅነት የሚያሳልፈው አላማ
የለሹ አሮጊት እናቱን የሚሳደበው፤ አገሩን የረሳው እረ ስንቱ፡፡ ለዛሬ እድሜ በቅተህ ታዝበህ የምትተች የምትነቅፍ ደግሞም
ዘመንን የምትመሰክር ሽሜ እና አሮጊቴ ደስ ይበልህ፡፡ ሽበት ማየትህ፤
እፊትህ ላይ የተጣጠፈው ጨምድድ ያለው ቆዳሕ ደስታ ነው፡፡ በውስጡ
ብዙ ልምድ እና ተመክሮ አለእና፡፡ ስለዚህ አሮጊት መባሌን ወድጀዋለሁ፡፡ አይግረማችሁ እና፤ ሽበቴን ቀለም ደግሞም ጨምዳዳውን ቆዳየን ልጅ ለመምሰል ሜክአፕ አልቀባውም፡፡ እግዚአብሄር የሠጠኝን ነገር ሁሉ ተቀብዬ ተመስገን ብዬ
እደሰትበታለሁ፡፡ ወዳጄ ሆይ፤ ገና አገራችን በዛ ደረጃ ስለማትገኝ፤ የመልክህ ማንነት ላይ ብዙም ኢንቭስት አታድርግ፡፡
የውስጥህ ማንነት ነው ለአገርህ ወሳኙ፡፡ ለለውጥ ወሳኙ፡፡ ለዲሞክራሲ ወሳኙ፡፡ ለመብትህ ወሳኙ፡፡ ለእኩልነት ወሳኙ፡፡ ለሰላም
ወሳኙ፡፡ ለእርህራሄ ወሳኙ፡፡ ሌላውን ዘር ለመቀበል ወሳኙ፡፡ ለቆዳህ ሳይሆን ለህሊናህ ኑር፡፡ ቆዳን መልሰህ ብትለጥጠውም ነገ
ማንነቱን አይክድም፡፡ ያው ታረጃለሕ ትሞታለሕ፡፡ በቸር የምላችሁ This is me Bayush Abebe.
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen