የተቃዋሚን ስም መጥራት ወንጀል እና አስፈሪ በሆነበት ኢትዮጲያ
የተቃዋሚን ስም መጥራት ወንጀል እና አስፈሪ በሆነበት ኢትዮጲያ ደፍሬ ትንሽ ለማለት ኢትዮጲዊነት ወይም የማንነት መዳን አስገደደኝ፡፡ ብዙ
ስለተቃዋሚ ማወቅ ይቸግራል፡፤ ይህ ማለት ግን ሰው ችግር የለውም ከችግሩም መላቀቅ አይፈልግም ማለት አይደለም፡፡ የሰው ልጅ እግር
አውጭኝ ከአንዱ አገር ወደ አንዱ አገር ይንከራተታል፡፡ ይህንም በከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ኢትዮጲያዊያኖች የምናየው ነው፡፡ እለት
ከእለት ደግሞ የሚሰደደው ስደተኛ የዲሞክራሲን ምንንት አንዲረዳ ሆኖአል፡፡ የሰውን ልጅ መብት ምንያህል እንደሆነ እያየው፤ እያወዳደረ
አሁን ያለውን አስተዳዳር እየጠላ ነው፡፡ የድሮውን ለማወቅ ገና ልጅ
ነበርእና፡፡ ኦሮሞውም በሰማው እየተጠራጠረ ትግሬውም እኔ የለሁበትም ብሎ ጸጥ ብሎአል፡፡ ግን ግን ደግሞ፤ እዲሞክራሲውም አገር
ካለመረዳት እግር አውጪኝ ብሎ የመጣውን ስደተኛ ኢሒአዴግን ቢጠላውም እንደወደደው ሆኖ ዝም ያለበት ምክናያት አለ፡፡ እሱም ከዛሬ
ነገ ሊመልሱት በእንጥልጥል የያዘውን አገር የመኖሪያ ፍቃድ መከልከል
ጉዳይ ነው፡፡ አለመረጋጋት ልበለው፡፡ የተቃዋሚን ስም መጥራት ወንጀል እና አስፈሪ በሆነበት ኢትዮጲያ ድንገት ብመለስ የት እኖራለሁ እያለ እኮ ነው፡፡ ልብ በሉ ድንገት ብመለስ?
ባይቀናኝ ብሎ መንግስትን መውደድ ?ያም
ሆነ ይህ አሁንም እንደትናንትናው ልያዛችሁ የሚል ሞኝነት ነው፡፡
የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ይዛ አግታለች የሚለውን ነገር ስሰማው፤ ከግንቦት
7 ከሚባለው ድርጅት ጋር አያይዠው ትኩረቴ ወደእዛ ተስቦ፤ ማነው እንዴት የሚለውን ማሰላሰል ጀምሬ ነበር፡፡ ልብ በሉልኝ እነዶክተር
ብርሃኑን አላውቃቸውም፤ ወይም አቶ አንዳርጋቸውን አላውቃቸውም ማለቴ አይደለም፡፡ እንኩዋን እኔ የከተማዋ ሰው እና ዛሬ ወረቀት
እንኩዋን ትውር የማይልባቸው፤ ቢያገኙትም ማንበብ የተሳናቸው ሰዎች እንኩዋን፤ እነዶክተር ብርሃኑን ያውቁዋቸዋል፡፡ እርግጥም ነው
መምጣታቸውን ይጠባበቁአቸዋል፡፡ እንዳውም ዛሬ ዛሬ ሳስበው፤ ሰላማዊ ትግል የሚዳከምበት ምክናያት ብዙዎቹ የሚጠባበቁት ሌላ ወይም
የእኛ የሚሉትን እነ ዶክተር ብርሃኑን ይሆን ብዬ መጠራጠር ይዣለሁ፡፡ ምንም እንኩዋን እኔ መራጭም ሆኘ ባልሳተፍም፤ በወቅቱ ቅንጅት
የሚባለው ጉዳይ የኢትዮጲን ህዝብ አቅጣጫውን ያሳዬ መሆኑን ገዢውም ፓርቲ የሚክደው አይሆንም፡፡ እኔ በበኩሌ የትጥቅ ትግል፤ አለም
እራሱዋ በታመሰችበት ወቅትእና የኢትዮጲያ ህዝብ ኤርትራን እምነት ባጣበት ወቅት፤ ለውጥ ካለብዙ ደጋፊ ሊመጣ አይችልም የሚል ግምት
አሳድሮብኛል፡፡ ማንኛውም የትጥቅ ትግል ድሮ ድሮ ካለ አሜሪካ ወይም ካለራሽያ ድል መቶ አየውቅምእና፡፡ ዛሬስ የትጥቅ ትግልን የሚረዳ
አለወይ ነው፡፡ ካለስ ኢሕአዴግ በሀያላኖች ተጠልቶአል ወይ ነው ? ጥያቄዬ፡፡ በዚህም የተነሳ እንደእውነቱ ከሆነ የትጥቅ ትግል የሚለውን ነገር ሁሉ ትኩረት ሰጥቼ
ተከታታየ ባለማወቄ የግንቦት 7 ጉዳይ ከወሬ የማያልፍ ብዬ ገምቼ ስለሆነ ነበር አላውቃቸውም ያልኩት፡፡ ይህ ሆኖ ደግሞ ኤርትራ
የኢትዮጲያ መንግስት ወዳጅ ነው እየተባለ ታዲያ እንዴት ተቃዋሚ ሊምናቸው ቻለ የሚለው፤ ህዝባችን ይበላል የሚለው ሌላውን ክፍል
ስሰማ በቃ አይኔን ትጥቅ ትግል ላይ አላደረኩም ነበር፡፡
እንዳውም ኢትዮጲያ
ጠንካራ ሰው አላት እንጂ ጠንካራ ተቃዋሚ የላትም ለማለት ያበቃኝም፤ እንደእነ ዶክተር ብርሃኑ እና አቶ አንዳርጋቸው ያሉ በምቾት
የሚያስኖራቸው ትምህርት እና ደመወዝ እያላቸው በወሰዱት ቆራጥ እርምጃ ነው፡፡ ጠንካሮች ናቸው ይህ አንድእና ሁለት የለውም፡፡ ለምን
ቢባል መበላትም እንዳለ እያወቁት ምቾታቸውን ጥለው ወደትግል ገብተውበታል እና፡፡ እንደኔ አይነት ግን፤ ችግር፣ በደል፣ ግፍ እና
መከራ እነኩዋን እያንገላታን ለዚህ ለውጥ ለማድረግ የማናሳየው ጥረት አንድ ሳይኖር ተቃዋሚ አይረባም ወይም እንዲሕ ነው እንዲያ
ነው እያልን በመቆዘም እንኖራለን፡፡ የትግል አጋርነት የለንም፡፡ ይህ ሁሉ ያሳፍረኛል፡፡ እንዳውም እኔ እረዳሁት የምለው ወያኔ
ኢሕአዴግን ነው ብል የሚያሳፍረን አይሆንም፡፡ ብትፈልጉ እንደኑዛዜ ውሰዱት፡፡ ምክናያቱም በራሱ በመረጣቸው በሾማቸው ሰዎች ወይም
ፖሊሶች ለሚደርስብኝ መገፋት እንኩዋን እንደሕጉ ሊረዱኝ ቀርቶ እንዳውም የግፈኞች ተባባሪ ሆነው እዳ ፍዳዬን ሲያሳዩኝ፤ እኔ ከእነሱ
ስር በተስፋ ዘመኔን በእንባ መግፋቴ ነው፡፡ አዎ 20 ዓመት ሙሉ ማልቀስ በተስፋ መኖር፤ ለእኔ ኢሕአዴግ ምድራዊ እየሱስ ሆኖብኝ
ቆይቶአል፡፡
አንድ ደስ የሚለኝ ነገር አለ፤ ኢሕአዴግን እንደመንግስት ቆጥሬ ለሰራሁት እንቅስቃሴዬ
ሁሉ፤ በስርአት እና በሕጉ መኖሬን፤ አንድ የህግ ጥሰት ሳላሳይ መኖሬን እና ለሕገመንግስቱ ተገዢ ሆኜ መቆየቴ፤ አመጸኛ ወይም ሽብርተኛ
ሳልባል ወጥቻለሁ፡፡ እንዳውም አንድ ግዜ በጀርመን አገር አድሱልኝ ብዬ የሰጥሁዋቸውን ፓስፖርት „ኢትዮጲያዊነትሽን አናውቅም“ ብለው
የቀሙኝን አልረሳውም፡፡በዛም የተነሳ ጀርመን ዜግነት እንድወስድ ሆኛለሁ፡፡ አዎ ይህ እውነተኛ ታሪክ እንጂ ቅዠት አይደለም፡፡ ድምጼን
ለዲሞክራሲ ማሰማት የጀመርኩት ከቅንጅትም ከግንቦት 7ም በፊት መሆኑን እንድታውቁት ይገባል፡፡ ግን ያልተሰማው የእኔን መሰል ድምጽ
ተጠራቅሞ እኮ ነው፤ ቅንጅት ወይም ግንቦት 7 የሚሆነው ለካ፡፡ ከ ማንም እንደእኔ በኢሕአዴግ ጊዜ አገሩ ለመኖር የጣረ ደግሞም
በማያውቀው ጉዳይ ሁሉ የተገፋ ያለ መስሎ እስከማይታየኝ ድረስ የደም እንባ አልቅሻለሁ፡፡ እንዳው እናንተው ስም አውጥቼ ቀረሁ „
ዲያስፖራ“ ፡፡ አገሬን እንዳለቅ ያደረኩት ጥረት ሁሉ ሳይሳካ መቅረቱ እና ዛሬ እንደገና በኢይሮፕ መገኘቴ ይገርመኛል? ዛሬም አገሬን ስለምፈልግ፤ አገሬን እንዳይከለክሉኝ ብዬ ከአንድም
ተቃዋሚ ጋር አልወገንኩም፡፡ ለመወገኑም በቂ ምክናያት ባካብትም እንኩዋን ፡፡ ግን ይህ ሁኔታዬ ምንአልባት ላሳደዱኝ ሰዎች እንደድል
ሲሆን ለእኔ ግን እንደሽንፈት መሆኑን ዛሬ አየሁት፡፡ ዞሮ ዞሮ አገሬን ለማግኘት አልቻልኩም እና፡፡ ይህን ልበል እንጂ፤ ለኢሕአዴግ
አባልም ሆነ ወይም ልዩ ተላላኪ ሆኜ የፈጸምኩለትም ጉዳይም የለም፡፡ እንደእውነቱ ዲሞክራሲ ሳይኖር እንደአለ ለመኖር ያደረኩት ጥረት
ምንአልባት እራሴን አንገላትቼ ሊሆን ይችላል፡፡ የሚገርመው በይፋ ስንገላታ እና በጠራራ ጸሃይ ስዘረፍ ፖሊስ ያላገጠብኝን ነገር
አልረሳውም፡፡ ሁሉም የሜንታል ቶርች ነበር ለካ፡፡ ሰቆቃ፡፡ ለዛውም
ደግሞ እራሴም ወደእስር እንድወረወር መደረጌ፤ ሕግ እንዴት መጨዋቻ ለግለሰቦች አገልግሎት ጥቅም ብቻ እንዲውል መደረጉ፤ ኢሕአዲግ
ዞሮ ያጤነው አልመሰለኝም፡፡ እንደእውነቱ የምወዳትን አገር ለመኖር
ብዬ እንጂ እኔ ከኢህአዴግ ጋር ያገኘሁት አምስት ሳንቲም ጥቅም የለም፡፡ 20 አመት የከንቱ ተስፋ፤ 20 ኣመት ማንነትን ማጣት
እና መንከራተት፡፡ ሁሉንም እግዚአብሄር ይመልከተው፡፡
ያም ሆነ ይህ አሁን
የግንቦት ሰባት ጉዳይ እና የእኔ ጉዳይ ሳይሆን ይህን እንድጽፍ ያደረገኝ፤ የአቶ አንዳርጋቸው በአረቦች መታገት ወይም ሌላ እርምጃ
ማስወሰድ ነው፡፡ ትናንት አረቦች ኢትዮጲውያኖችን የሚያንገላቱት ማንገላታታ ምንአልባትም ዛሬም ያላቆመ ነገር በግርምት የማልፈው
አልሆነም፡፡ እነዚህ አካባቢዎች፤ ለምስኪን ዳቦ ፈላጊ ሴት እንኩዋን የማይመለሱ መሆናቸውን፤ እራሱ አለም የሚያውቀው ነው፡፡ ግን
የሚገርመው ዛራ ኢትዮጲያዊው ምንም ከነሱ ዳቦም ሆነ ሹመት የማፈልግ አንድ ምሁር ለምን ተደፈረ? ነው የእኔ ጥያቄ፡፡ ደግሞስ በአቶ አንዳርጋቸው ምንአገባቸው እና እንዲህ ዓይነት ጨዋታ ውስጥ ገቡ የሚለው ነው፡፡
እንግዲሕ ነገ የሌላውስ ኢትዮጲያዊ እጣ ፋንታ በዚህ አካባቢ ምን ይመስላል? እስከመቸስ በአረብ ተጠልቶ እና ተወግዞ ይኖራል? ስለእኛስ
የሚያስቡት ምንድን ነው? ምንድን ነው የሚነገራቸው? ትናንት ያልደፈሩትን ዛሬ እንዴት ኢትዮጲያን ናቁ የሚለው እረፍት የለሽ ጥያቄ በውስጤ አስተጋባ፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ኢትዮጲያዊ ናቸው፡፡
ይህ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊውን የሚነካ እንጂ የአንድ ሰው ጉዳይ አይደለም፡፡ ነገስ? ሌላው አገር በሌሎችስ ላይ ምን ያደርጋል?
ስለዚህ አቶ አንዳርጋቸውን የመን ከሆኑ ያሉት አንድም ቀን ማሰር አይገባትም፡፡ ምንአልባት እዛ ታግተው ከሆነ፡፡ ታልፈውም ከተሰጡ፤
ምንአልባት ያልተረጋገጠ ወሬ በመሆኑ ይቅርታ፡፡ የኢትዮጲ መንግስት አሁንም የተሳሳተ ስራ ሰርቶ የበለጠ በሕዝብ ጥላች እንዳይጠላ፤
በምኑም በምኑም እየተጎሰመ ያለውን የተቃዋሚውን ህዝብ ቁጥር መቁጠሩ መልካም ነው እላለሁ፡፡ በቸር
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen