ከቅንጅት በፊት ኢትዮጲያ የምትመስለው፡፡
ጉዋደኛ ያልኩዋቸው ከአጠገቤ የሉም፤ ቤተክርስቲያንም ብሄድ የሚያስፈራራቸው እንዳለ ጉዋደኛ አላገኘሁም፡፡ዛሬ ከነአካቴው
ከቤተክርስቲያን ተለይቻለሁ፡፡ ዘመዶቸም ከአጠገቤ እርቀዋል፡፡ ሁልግዜ
የሚመጣብኝ ክስ እና ወቀሳ አሉባልታ ብቻ ነው፡፡ በሰፈርም የተደራጁ ሁለት ሰዎች በሀሰት ከሰው ፖሊስ ጣቢያ ያመላልሱኝ ነበር፡፡
ክሱም፤“ ህጻን ልጆቻችንን በፈረፈንጎ ግጭቼ እገላለሁ“ ብላለች ነበር፡፡ እኔ ግን ፈረፈንጎ ምን እንደሁ እንኩዋን ሳላውቅ ለምን
ይህ ውሸት እንደተነሳብኝ አልገባኝም ነበር፡፡ ውሸት ነው አልኩ፡፡ አለች ያሉኝ የአንድ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተመራጭ ሽማግሌ
ነበሩ፡፡ እኔም አላልኩም፡፡ ፈረፈንጎስ ምንድን ነው ብዬ ፖሊስ አዛዡን ጠየኩ፡፡ የምነዳት መኪና አንዱ ክፍል በጎን በኩል ነው
ብሎ አስረዳኝ፡፡ እምወደው የኢትዮጲያን ሕጻን፤ ወገኔን ቀርቶ ጥላቴ ላይ ይህንም አላስብም፡፡ ነገሩ ሁሉ እኔን ለመቀወስ ሆን ብሎ
የተጠነሰሰ ሴራ መሆኑ አልገባኝም፡፡ „ እነሱ እኔ ለማለቴ ምስክር አቀረቡ፤ የምትታመን ሴት የቀበሌው ተመራጭ ናት ሌላዋ መስካሪ፡፡
እኔ ግን የሚመሰክርልኝ የለም፡፡ አለማለቴን የሚመሰክር ጌታ ብቻ ነው አልኩ፤ አለቀስኩ፡፡ „ከሕብረተሰቡ ጋር መኖር አትችይም“
ብሎ ፖሊስ አዣዡ ከሳሾቼን አስደሰተ፡፡ አንድ ወገንተኛ የሆነው አዛዥ እንዳውም እነሱን ያደራጃቸው መሰለኝ፡፡ ሁሉም እንዲርቀኝ
እንዲፈራኝ፤ እንዳያምነኝ የሚያደርግ ያልገባኝ እና የማላውቀው ሀይል ለምን እንደተነሳብኝ ግራ ገብቶኛል፡፡ ግን የቤተክርስቲያኑ
ሽማግሌ እሳቸውም፤ ብለሻል ብለው ደመደሙ፡፡ እንግዲህ በዚህ አፈዎ ስለተናሩ እግዚአብሄር ሰምቶአል እና እኔንም ሰምቶአልእና በማለቴ
ቅር በሉኝ ብዬ ተደፋሁ፡፡ እርቁን የፈለኩት መሳደዱ እንዲቀርልኝ ብዬ ነው፡፡ የዛን ግዜ ያልወላወልኩ ኦርቶዶክስ ነበርኩ፡፡ በዚህም በማስጠንቀቂያ ከፖሊስ
ጣቢያ ተለየሁ፡፡ እቤትም ገብቼ አለቀስኩ፡፡ አልበቃኝም ወደእምወደው ደሴ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አመራሁ፡፡ ከከተማ የወጣው ቤተክርስቲያን
የዛን ግዜ በአካባቢው ብዙ ቤት አልነበረም፡፡ ብቻዬን ነበርኩ፡፡
ቤተክርስቲያኑም ዝግ ነበር፡፡ እኔ ግን እግቢው ገብቼ ቤተክርስቲያኑን ተደግፌ ተኛሁ፡፡ እንቅልፍም ወሰደኝ፡፡ ባንኔ ስነቃ ግን
ሰአቱ ሄድዋል፡፡ ወደመኪናዬ ስሄድ፤ አንድ እርግብ አፍንጫዋ ላይ ተቀምጣ ነበር፡፡ ግን አልሸሸችም፡፡ ትኩር ብዬም አየሁዋት፡፡
አንድ ነገር ግን ገረመኝ፡፡ ሁሉ ሰው ሸሽቶኝ፤ ሰው በናፈቀብኝ ወቅት፤ ይህቺ እርግብ ከእኔ አለመሸሽዋ ነበር፡፡ ልቤም በድንገት
መጽናናትን ጀመረ፡፡ ያለመድኩት መረጋጋትም ውስጤ ውስጥ ሲፈልቅ ተሰማኝ፡፡
እኔም መኪና መንዳት ለጊዜው አቆምኩ፤ ፈራሁ፤ ደግሞ ልጅ ገፍትረው ያስገጩኝ እና ያሳበብብኛል ብዬ፡፡የ20
አመቱ ልምዴ የሚገርም ትእይንት ነበር፡፡ ሳስበው ተረት ተረት የማወራ
ይመስለኛል፡፡ አይደለም ግን እውነቱን ነው የምነግራችሁ፡፡ በኢሕአዴግ ዘመን አገሬ ለመኖር ያደረኩት ጥረት የህልም እሩጫ የማይደረስበት
መደረጉ አልገባኝም ነበር፡፡ ተወልጄ ያደኩበት አገር፡፡“ ነገረኛ ናት፤ ውሸታም ናት“ እየተባልኩ እንድገለል ወሬ የሚያናፍሱ ግሩፖች
እንደተፈጠሩብኝ አወኩ፡፡ መረዳት ከእግዚአብሄር እንጂ ከየትም አይመጣም፡፡ „ሺህ ጦር ቢሰለፍ አምላክ ከእኔ ጋር ነው ማን ይቃወመኛል“.
ይላልእና ዳዊት፡፡ ሰፈሩ ሁሉ ያውቃል“ ቀውሱዋ ባዩሽ“ ዳዊትን በመጮህ መድገምዋ፡፡ አይገደኝም የሰጡኝ ስም፡፡ የሰፈሩ አንዳንድ
ስራ የማይሰሩ እና ለአንዳንድ ሰዎች በመላላክ የሚያሳልፉ“ ቀውሱዋ፣ ቀውሱዋ“ እያሉ ይጠሩኛል፡፡ ያሳዝናል፡፡ የአገር ትርፍ ይህ ይሆን?
ፖለስ ጣቢያ በተከሰስኩ እና በተመሰከረብኝ ቀን ሶስት ቀን ቆይቶ፤ አንድ የተገረመች
ሴት እንዲሕ አለችኝ፡፡ „ አንቺ እኒያ ከትናንት ወዲያ የመሰከሩብሽ
ሰው እኮ አፋቸው ተጣሞ አደረ፤ የሰፈሩም ሰው ሄዶ ጉድ ጉድ እለ ነው“፡፡ አላመንኩዋትም፡፡ ቢሆንም ከእኔ ጋር የተያያዘ አየሆንም
ብዬ ገመትኩ፡፡ እግዚአብሄር የታምራት አምላክ ቢሆንም እንዲሕ በአፋጣኝ የሚመሰክር አልመሰለኝም፡፡ ግን አዎ፤ በአራተኛው ቀን ጡዋት
ተነስቼ ወደ ቤተክርስቲያን ስሄድ ሰውየውን ተደግፈው ሲሄዱ አገኘሁ፡፡ አይን አሰይኔን አዩኝ፡፡ እኔ ሰላም አላልኩም ፈርቼ፤ ግን
ደመኛ የሚባለውንም ማኩረፍ አልወድም፡፡ ተፈጥሮዬ ሞኛ ሞኝ ነኝ፡፡ ለእግዚአብሄር ብዬ አይደለም የማደርገው፤ አብሮኝ የተፈጠረ ባህሪ
ነው፡፡ ይህ መሰል ነገሬ ለድግግሞሽ ጥቃትእና መታለል ዳርጎኛል፡፡
ሰውየው ግን በደገፉዋቸው ሴትዮ ጠለል ብለው ሰላም አሉኝ፡፡ አዎ
የመሰከሩበት አፍ እንደዛ እንደፖሊስ ጣቢያው ትክክል ቦታውን አልያዘም ነበር፡፡ ዛሬ ዛሬ ግርም የሚለኝ አገሬ ላይ ለመኖር
የደፋሁት አንገቴ ነው፡፡ ከዛም በሁዋላ ብዙ ሰዎች እናን ማጥቃት ማቆም ጀመሩ፡፡ ሌሎችንም ታአምራት እና ልምድ እንዳካፍላችሁ፤
ብዙ ሰው እንዲያነበው አድርጉ፡፡ በሰው እንዳትተማመን የስም ማጥፋት ወንጀል፤ ሰው እንዲሸሽህ የሚያደርግ ሀይል አንድ የሚቀናብህ
ደግሞም የፖለቲካ አለማ ይኖረዋል ብሎ በሚፈራህ ግለሰብ ወይም ቡድን
ይነዛል፡፡ የሚቀበሉት ግን ሞኞች እና ሀጢያተኞች ናቸው፡፡
ውድ ወገኖች እማካፍላችሁ ሁሉ ከእውነት ያልራቀ ነው፡፡ ብዙ ጉዳቶች አሉ፡፡ ሰው ግን መሰረተ ቢስ ሆኖም የሰውን ህይወት
እንዴት እንደሚያቃውስ ሳውቀው ዘወትር እገረማለሁ፡፡ የሚገርመኝ ከኦርቶዶክስ ቤት ወደፔንጤ የወሰደኝ ፍርሃቴ አይሎ ስለነበር ነው፡፡
እዛም ግን ለእኔ ሰው አልተገኘም፡፡ ግን የሚገርመው ኦርቶዶክስም እያለሁ ብቻዬን እንዳልሆንኩ እግዚአብሄር የመሰከረልኝ እና የረዳኝ
ነገሮችን ሁሉ አይኔ እንዳያይ ተሸፍነው ነበር፡፡ ከብዙዎቹ ጥቂቶችም፤ የእግዚአብሄር ታአምር በቅርብ አይተው የተረዱ እኔን ከመከታተል
ሲቆጠቡ አየሁ፡፡ መኪናም ይዠ መውጣት ጀመርኩ፡፡ እኔ ግን እንደድሮዬ
አገሬ ብዬ መዝናት አቆምኩ፡፡ ሰው ከሰው እንጂ ከመሬቱ ጋር አይኖርም እና፡፡ አንድ ወጣትም ከተወሰነ አመታታ በሁዋላ፤ „ እትዬ
በመኪናሽ እንድትገጪኝ ብዙ ጥረት አድርጌ ነበር ግን፤ አሪፍ ነጂ መሆንሽ ዛሬ ዛሬ ገባኝ እና ይቅርታ አድርጊልኝ አለኝ፡፡ እኔ
ግን የምለው ነጂው እግዚአብሄር ነው፡፡ ሁለተኛ ግን ከእኔ ጥፋ ላይህ አልፈልገም አልኩት፡፡ መለወጥም አላየሁበትእና፡፡ የሚወራኝ
ጫት ጨብጦ ነበር እና፤ ሱስ ከተገዢነት አያወጣህም እና፡፡ ዳግም መላኩም አይቀርም፡፡ ሁላችሁንም እወዳችሁዋለሁ፡፡ ሰው ከዘመዱም
ከወገኑም አደይደለም የሚኖረው፤ የሚኖረው እግዚአብሄር ከሚልክልኝ ሰው ጋር ነውእና፡፡ ሰው ከለለ እግዚአብሄር የለም ማለት ሳይሆን ሰው አላከልህም
ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር አሰሱን ገሰሱን ለአንተ አይሰጥም እና፡፡ በሚያስፈልግህ ሳይሆን በሚጠቅምህ እግዚአብሄር ይሰራል፡፡ ዛሬ
ወደእዛ ብቸኝነትን እያጽናና ያኖረኝ፤ በረሃ ሳያስበላኝ ለዛሬ ደረሰኝ ኦርቶዶክስ ተመልሻለሁ፡፡ እዛ ደሴ ሚካኣልም አንድ ቀን እቆም
እና ያቺን እርግብ አይ ይሆናል፡፡ ሁላችሁም ከጸለያችሁልኝ፡፡
እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር ይሁን
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen