አንዱ አገር ዛሬ የሌላውን ዜጋ አስሮ ለሌላው ቢያስተላለፍ አይድነቅህ፡፡
ዘመን በዘመን ይተካል፡፡ ሁሉም ነገር የማናውቀው አዲስ ነገር እያመጣ
ያስደንቀናል፤ ያስደነግጠናል፡፡ ግን ደግሞ የሰው ልጅ ዘምን አልፎ ዘመን ሲተካ የሚያመጣውን አዲስ ነገር መቀበል ያቅተዋል፤ ምድር ቃጤ ትሆንበታለች፡፡ ይህ
የምንኖርበትን አለም ካለግንዛቤ እንደምንኖርባት ያስረዳል፡፡ አዎ ዘመን አልፎ ዘመን ሲታካ ያላዘነው ያዝናል፡፤ ያዘነው ይስቃል፡፡
ይህም የሚሆነው ደግሞ ዘምን አልፎ ዘምን ሲተካ እንጂ ምንም አይነት ነገር ዘላለማዊነት የለውም፡፡ ግማሹ በትዕግስት ግማሹ በመናደድ
የሚጠባበቃት የህይወት ለውጥ ብዙ መስዋእትነትን ታስወስዳለች፡፡ እንግዲህ ሁሉም እናዳለ ይሆንእና፤ ተዋጋህም ወይም በትእግስት አሳልፈውም
ዘመኑ ለአንተ ክፉ ከሆነብህ ስነልቦናህ አይወርዱ አወራረድ ይወርዳል፡፤ ይህም የሚሆነው ስለከፋህ
ብቻ ሳይሆን የደላውንም እያዩ መኖር ነው፡፡ የደላው ዘመኑ መሆኑን ግን ካወክ በረድ ቀዝቀዝ ብለህ ዘመንህን ትጠባበቅ ነበር፡፡
ወዳጄ ሆይ ዘመኔ አይመጣም አትበል፡፡ ዘመን ወደልጅህም ይሄዳል እና፡፡ ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ያም ሆነ ይህ ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ፤
አለም ባላገናዘብነው መንገድ አንድ አይነት የስርአት መንገድ ይዘን እንደምንጉዋዝ አለማወቃችን ነው፡፡ እስኪ እንግዲህ በዚህ መልኩ
አብረን እንመልከተው፡፡ ጥንት የባላባቱ ስርአት ባሪያ እየገዛ አልፎ ነበር፡፡ ከዛም ኮሚኒዝ እና ሶሻልሊዝም ብቅ አለና የአለምን
ህዝብ ለሁለት ሰነጠቀው፡፡ የባሪያ ስርአትም ቀስ እያለ ነጻነትን ለመጎናጸፍ ቻለ፡፡ ቼ በለው የተባለው ቸኩቬራ ማኦ፤ ደግሞም ሌነን
የመሳሰሉ እውን ሊሆን ያልቻለ ፍልስፍና አምጥተው የአለምን ስርአት ለሁለት ሰንጥቀውት አልፈዋል፡፡ ይህ ሁለት ስርአት በአለማችን
ላይ ምእራብ እና ምስራቅ ወይም ግራ እና ቀኝ ዘመም ብሎ ከፍሎ እስከአሁን
ድረስ የአይምሮ እረፍት የለሽ ኑሮ እንድንኖር ተገደናል፡፡ አለም እንግዲህ በዘመን የምታመጣው ደንቀራ ቢጤ ባታጣም፤ ግን ግፍ የቸገረው
ሰው የሚፈለስፈው ፍልስፍና ሁሉ ሌላን ግፍ እየወለደ በመምጣቱ ዛሬ ደግሞ አዲስ ምእራፍ ገብተናል፡፡ ስለዚህ አለም ምንግዜም ስርአትዋ
ግሎባል የሆነ መንገድ እየያዘ ነው፡፡ ሁሉም ኮፒ አድርጎ የመጉዋዝ መንገድ ዘውር ብለን ብናየው ያለ ነው፡፡ ስርአትም እንደወረርሽኝ
አየር የሚያስተላልፈው ወይም እንደኢንፍሎዚያ ይሆናል፡፡ ስለዚህ አለም አንድ አይደለችም ብትሉኝ ለእኔ ምንብዬ እንደምመልስላችሁ
አላውቅም፡፡ እርግጥ ነው፡፤ ስርአቱ በአለም ላይ ሁሉ አንድአይነት ነው፤ ልዩነቱ ስርአቱን ግን በወጉ ተጠቅመውበት የሚያልፉት ብልጦቹ
ናቸው፡፡ ዛሬስ ኢንተርናሽናል የሆነው የአለም መሪዎች ጎን በጎን መስራት መተባበር አይሆንም እን፡፡ በቱኒዚያ የፈነዳው የህዝብ
አመጽ በአረቡ አገር የተቀጣጠለው የመተላለፍ አባዜ ነበረውእና፤ እዛም
እዛም ጭሮ መሪዎችን በልቶ ሲያልፍ አየነው፡፡ መሪዎችን እና መሰል ደጋፊዎቻቸውን ያሳልፍ እንጂ ግን ለህዝብ ለውጥ እናዳላመጣለት
እዛም እዛም ሲተቹ ሲወቅሱ ሲያማርሩ እያየን ነው፡፡ ከአንዱ ትግል ወደአንዱ ሲሸጋገሩ እግርአውጪኝ ሲሰደዱ፡፡ አምባገነንንም ገደልን
ብለው ድልን ተቀናጀን ያሉትም ወይም አሁንም በአምባገነን የሚመሩ ወደምእራቡ አለም እግር አውጪኝ ሲሽሹ እያየን ነው፡፡ በጀርባው ምንም ይኑር አይኑር፤ ብቻ የአንድ ሰሞን ግርግር አንድ ሌላ የዘመን ምእራፍ ከፍቶአል፡፡ ስደት በባህር፤
ስደት በእግር፤ ስደት በተገኘው መንገድ፡፡
አንድ ነገር ግን ስመለከት፤ ኢይሮፕ የኢንተርናሽናል ህዝብ መናሀሪያ እንደአሜሪካ
እየሆነች ነው፡፡ ከፋውም አልከፋውም ተመቸውም አልተመቸውም፤ አረቡ፣ ነጩ፣ ጥቁሩ እና የኤሽያ ስደተኛ ሁሉ ወደአንድ ኮንትኔንት
ክተት መያዙን ነው፡፡ ይህ ግሎባልን ካልፈጠረ ምን ይፈጥራል፡፡ ስለዚህ ግሎባልን እቃወማለሁ የሚል ካለ፤ ወዳጄ ሆይ፤ የማረዳህ
ወደድንም ጠላንም አለም መንገዱን ሀ ብላ መጀመሩዋን ነው፡፡ ግሎባል ገና ነው የሚል ካለ ተሳስቶአል ብል ግንዛቤየየን ዜሮ ያደርገው ይሆን? አንተ አጥበህ ዳንኪራ ስትመታ፤
ኦሮሞው ትግሬው ኤርትራዊው ሌላውም የቻለ ሁሉ የክተቱ ተጋሪ እንደሆነ ልንገርህ፡፡ እንግዲሕ የወደፊቱ ሁኔታህን አገናዝብ፤ ድካምህ
ሁሉ ከንቱ እንዳይሆንብህ አለም ዘርን ከዘር እያቀላቀለች ማኖር ጀምራለች እና አትደንግጥ፡፡ ግን አስተውል፡፡ አንዳንዶቻችንም እንኩዋን
ደህና መጣህ የምንለው መንገድ እንዲሆን ያሳለፍነው ክፉ መንገድ ሁሉ ግድ ይላል፡፡ አገርህ ላይ የአገርህ ሰው ካሳደደህ ወይ ከበደለህ
ነጩስ ወይም ሌላው ምን ከዚህ የከፋ ያደርግ ብለህ መቀላቀልን ትመርጠዋለህ፡፡ ሰውን ባህሪ እንጂ ከእንግዲህ የሚያገናኘው ዘር አለመሆኑን
እንድትረዳ የሚያደርግህ፤ የከበበህን ኢንተርናሽናል ሰው ስታየው ነው፡፡ ሁሉም ዘሬን እያለ ቢፍጨረጨርም ግን ዘር ወደማጥፋት መንገድ
እንዳይገባ የሚያደርገው የእንተዋወቅ መንገድ የአለም ችግር በር የከፈተለት ይመስላል፡፡ አብሮ መኖር አብሮ መካፈል እንግዲህ በዚህ
መልኩ እንዲቻል ምንአልባትም ግሎባል የሆነው፣ ከዛም ከዛም የተውጣጣው እና የአይምሮው እድገቱ ከፍ ያለው ህብረተሰብ ክፍል በጋራ
መፍተሄ ለመፍጠር ይመቸው ይሆናል፡፡ አትደንግጥ፤ በአፍሪካም ጥቁር ሚሌኒየር እንደነጭ ተፈጥሮአልእና፡፡ በነጩም አለም ድህነት የሚቆዝመው
አለመጥፋቱን እየኮበለለ የሚመጣውን ስናይ ነው፡፡ እንግዲህ ዘመኑ የዘር ልዩነት የሚያሳስበው ሳይሆን በሀብታም እና በደሃ መካከል
ያለው እጅግ በጣም እየተራራቀ የሚሄደው ልዩነት ይሆናል፡፡ ስለዚህ አንዱ አገር ዛሬ የሌላውን ዜጋ አስሮ ለሌላው ቢያስተላለፍ ምን
ይደንቃል? ምክናያቱም ግሎባል መሪዎችንም ያቀራርባል እና፡፡ መሪዎችንም ብቻ ሳይሆን ሌላውም እንዲሁ የሚቀራረብበት አብሮ የሚሰራበት
መንገዱ ግሎባል ገሃድ ያደርገዋል፡፡ እንግዲህ ዘመኑ ተመቸም አልተመቸም፤ ዛሬ የአንዱ ነው፤ ነገ ደግሞ የሌላው፡፡ በነገራችን ላይ
ለብዙ ኢትዮጲያውያኖች የማሳስበው፤ በዚህ በግሎባል ሁኔታ ጀርመን ሆንክም አሜሪካ ከፖለቲካ እስር ቤት ለማምለጥ ምንም አይነት ዋስትና
የለህም፡፡ አለማችን ተቀራርበው እየሰሩ ነውእና እንዳትታለል፡፡ ማመን ያለብህ ወይ አላማህን እንጂ አገርን መሆን የለበትም፡፡ ከአገሩ
ለቀህ ከወጣህ የሚገጥምህ ችግር እንዲህ ቀላል መስሎ አይታይህ፡፡ እንኩዋን ለአንተ ለነጩም እስር እንዳልቀረለት በቂ ትምህርት የወሰድክ
መሰለኝ፡፡ እኔ ለእራሴ ጀርመን ስለሆንኩ ቅጣት ይቀልልኛል ብዬ አልገምትም፡፡ አጥፊ ሆኘ ከተገኘሁ የኢትዮጲያ መንግስት እንደማይለቀኝ
አውቃለሁ፡፡በመካካላችን ችግር ቢኖር ማለቴ ነው፡፡ በቸር ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen