የትጥቅ ትግልን የወለደው
የኢሕአዴግ አምባገነንነት ነው፡፡
ይቅርታ ይደረግልኝ እና፤ ግንቦት 7 የሚባለውን ድርጅት በኤርትራ በኩል ትጥቅ ትግል ስለጀመረ፤ አቶ ኢሳያስ አፈወርቄ
ፈቅደውለታል እና ከሽብርተኛ ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቄ ጋር ተግባብተዋል እና ሽብርተኛ ነው የሚለውን እኔ አልስማማም ምክናያቱም፤ ድሮም የኢትዮጲያ መንግስት የነበረው ደርግ ከኢሳያስ አፈወርቄ
ጋር ሲዋጋ የነበረ ጊዜ ኢሕአዴግም ደርግን የጣለው እና ስልጣን ያገኘው ሻቢያ ጋር ለዛውም አቶ ኢሳያስ አፈወርቄ ጋር ተስማምተው ነው፡፡ ዛሬ እንደቻይና እቃ ተጠቅሞ መጣል ቢሆንም፤ ስለዚህ ይህ ያለ ነው፤ ኢትዮጲያ ውስጥ አልለቅም ስልጣንም አላጋራም ላለ በዛ በኩል ሁልግዜ
በር እና ቦታ ማገኘቱ የተለመደ ስለሆነ፡፡ ለምሳሌ ዛሬም ቢሆን ኢሕአዴግ የመንን ተጠቅሞ ተቃዋሚያቸውን አቶ አንዳርጋቸውን አፍኖ
ወስዶአል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው የታወቁ ባይሆኑ ኖሮ ይህም ባልታወቅ ነበር፡፡ ስለዚህ ግንቦት 7ን የጀመረውን የትጥቅ ትግል በእጅጉ
ያሳሰበኝ የነበረ ቢሆንም እና ደግፌው ባላውቅም፤ እሳት ካየው ምን ለየው እንደሚባለው፤ ኢሕአዴግ መረብ ተሻግሮ፤ ምንም ትጥቅ ወይም
አጃቢ ያልያዘውን ሰው ማርኮአል፡፡ በዚህም የተነሳ እኔ ግንቦት 7ን ሽብርተኛ ነው አልልም፡፡ ከሆነ ሁሉም ከሻቢያ ጋር የሰራ ሁሉ
ሽብርተኛ ነው፡፡ አልያም ሌላ አጥጋቢ ምክናት ካለ ብሰማ በሽብርተኛ አባባል ለመፍረድ ይመቸኛል፡፡ ምንአልባት ለእኛ ለሕዝብ የተሰወረ ሌላ ችግር ካለ ማለገቴ ነው፡፡ በሌላ መልኩ
የኢሕአዴግ ከተቃዋሚ ጋር ለመካፈል ወይም አብሮ ለመስራት ፍቃድኛ ባለመሆኑ ይህ ተመሳሳይ ነገር ማለትም የትጥቅም ትግል እንዲፈጠር
ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡ የትጥቅ ትግልን የወለደው የኢሕአዴግ አምባገነንነት ነው፡፡ በአገሩ ውስጥ ወይም በፓርላማ ውስጥ ተቃዋሚ
ቢኖር ኖሮ እውነት የእነሱም ግንቦት 7ን ወንጀለኛ ወይም ሽብርተኛ መሆን አብረው በፈረሙእና በነገሩን ነበር፡፡ ግን አንድ ሰው
ብቻ ተቃዋሚ ሆኖ በተቀመጠበት ቦታ ይህን አይነት ውሳኔ ሰውን ከማስፈራሪያነት እና ከማባረር፤ ሰው ፖለቲካን እንዲሸሽ እና ተቀናቃኝ እንዳይኖር፤ ብቸኛ ገዢ ለመሆን ከመርዳት ውጪ ሌላ የሚያመጣው
ፋይዳ የለም፡፡ ኢህአዴግ በአገሩ ተቃዋሚ አለ ካለ፤ ከእነሱ ጋር ሆኖ ተስማምቶ ማን ሽብርተኛ ማን ደህና እንደሆነ ቢያስረዳን ምልካም
ነው፡፡ ካልሆነ አንድ ፓርቲ ብቻ በአገሩ ውስጥ የሚናገረው ንግግር የሚየሳልፈው ውሳኔ ኢትዮጲያን የሚወክል ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡
ችግሩ እዚያ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ አገር ውስጥ አለን የሚሉ ተቃዋሚዎች ደግሞ ሁልግዜ ስሞታ እያወሩ የህዝቡን ሁኔታ በአጉል ተስፋ
ጉጉት ውስጥ ከሚጥሉን፤ አንድ ቁርጥ ያለ ነገር ቢነግሩን መልካም ነው፡፡ ኢህአዴግ ዲሞክራቲክ ነው ፈቅዶልናል
ካሉ ለምን እንደሚያማርሩ አይገባኝም፡፡ ማማረራቸውም የማይፈታ እንዲህ አውንደሚሉን የሚንገላታ ከሆነ፤ ለምን ፓርቲ ጸ/ቤታችውን ከነአካቴው ዲሞክራቲ የለም ብለው እንደማይዘጉ አይገባኝም፡፡
ምክናያቱም
በኢህአዴግ ላይ የምንሰማው እረፍት የሚነሳ በመሆኑ፡፡ የምንሰማው ሁል ነገር እጅ እጅ የሚል ሆኖአል፡፡ ወጣቱም በእስር እና በስደት
በፍርሃት እና በድፍረት አይሰቃይ፡፡ ተቃዋሚም ፓርቲ ከለለ አርፎ ይቀመጣል፡፡ እኔ ወያኔ ኢሕአዴግን ኢትዮጲያዊ አይደለም አልልም፡፡
ግን የምለው ዲሞክራሲን መተግበር ያቃተው ወይም የማያውቅ ነው፡፡ እና በስልጣን ከተወሰነ በላይ መቆየቱም እና ተቃዋሚን ያለመቀበሉ ጉዳይ ህዝቡን
ወደትጥቅ ትግል እየመራው የሚገኝ ማንአለብኝ ያለ ሆኖአል፡፡ ስለዚህ የትጥቅ ትግል ማንኛውንም መንግስት ነኝ የሚለውን የደፈረ ይሆናል፤
መሰቃየቱም እንደማይቀር፤ በእራሳቸው የትግል ዘመን አይተውታል፡፡ ሁሉም እጅ እጅ የሚል የሚመር እና የሚያሳፍር በመሆኑ፤ ሁሉንም
ተቃዋሚ የተባለውን ሁሉ እየወነጀሉ ከመስመር እንዲወጣ መገፋፋት ለእኛ
ለህዝብ እይታ የሚመች ወይም የተረጋጋ አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ አለም ሁሉ ኢሕአዴግን ዲሞክራቲክ ነው ብሎ አቅፎ ደግፎ ይዞታል፡፡
ስለዚህ ግንቦት 7 በመሳሪ ትግል ሲጀምር ግን ደግሞ ሰላማዊ የሚባሉት ፓርቲዎች የፖለቲካ አክቲቪስት እንጂ እንደፓርቲ ሆነው መታየት
እስከሚያቅታቸው እያየን ነው፡፡ ስለዚህ ትግላቸውን ጥርት እያደረጉ ቢሄዱ መልካም ነው፡፡ እስካሁን ይታሰራል ይፈታል፡፡ ወይም ኢሕአዴግን
ፍቀዱለት እና ብቻውን እንደፈለገ ያድርገው፡፡ እጣ የወጣለት ይብላ ያልወጣለት ያልቅስ፡፡ ለነገሩ የትጥቅ ትግል የተጀመረው በወራት
እድሜ መሰለኝ፤ ግንቦት 7ን ማለቴ ነው፡፡ ስለዚህ እነሱ አዲስ አበባ እስከሚመጡ ድረስ ሌላ ሃያ አመት ኢሕአዴግ ለመቆየት እድሉ
አለው፡፡ የታሰሩትን ይፈታል ስንል ሌላ ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ኢሕአዴግ
ጋር ጨዋታውን መቀየር ያዋጣ ይሆናል እንጂ በተያዘው መንገድ ሁሉ ወይ ፍንክች፡፡ ለነገሩ ሽብርተኛ መቼም እንግሊዝ አገር ወይም
አሜሪካ አገር አይቀመጥም፡፡ ስለ አቶ አንዳርጋቸው ማሻሻያ ክስ ይቅረብ፡፡ ይቅርታ በነጻነት ሀሳቤን እንድሰጥ እንድናገር ከተፈቀደልኝ፡፡ አቶ መለስም „እኛ በመሳሪያ ትግል ነው እዚህ የደረስነው፣ የፈለገ ይታገል
“ ብለው በር የከፈቱ እራሳቸው ናቸው፡፡ ካልተፈቀደም ይቅርታ፤ መቼም ከተናገርኩትም በሁዋላ ቢሆን፡፡ እኔንም ሽብርተኛ እንዳትሉኝ
አስመራ ገና አልሄድኩም፡፡ በቸር ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen