እውን ኢሕአዴግ ከእግዚአብሄር ይበልጣል እን?
ወንድና ሴት ሊነጣጠሉ የማይታዩ በአንድነት ለአለም አስፈላጊ የሆኑ እና
ለእግዚአብሄርም ስራ ሰውን በነሱ በኩል እንዲፈጥር የሚረዱ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ መጣመር እለዋለሁ እኔ፡፡ እንደ አፈር እና ውሃ፡፡
እግዚአብሄር አፈርእና ውሃ ፈጠረ እና እጽዋቶች እንዲበቅሉ አድርጎአል፡፡ ማዳበሪያ የመጣው ሰው ለበደለው ላበላሸው እንደማገገሚያ
ለማድረግ ይመስለኛል፡፡ አለምን ባናበላሸው ኖሮ እና መሬቱን እንኩዋን ሰላሙን ብንሰጠው ኖሮ ማዳበሪያ ባላስፈለገን ነበር፡፡ በሌላ
መልኩ ግን ፤ እንደጊዜው ወንድ ወንድን ሴት ሴትን አግብቶ ለእግዚአብሄር
ስራ ማሳያ፤ ዘርን እንዲፈጥሩ የሚያደርግ ሁኔታ የለም፡፡ ቢጣመሩም ማለቴ ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ሁሉም የሰው ልጅ አስፈላጊ እንደሆነ
እራሱ መገንዘብ እና እኔ ለዚህ አለም አስፈላጊ ሆኜ ተፈጥሬአለሁ ብሎ እራሱን መቀበል አለበት፡፡ እዚህ አለም ላይ የሚንቀሳቀሱ
ነገሮች ሁሉ የአንተንም ፍቃድ ወይም ተቃውሞ ማለትም አይስማማኝም ብለሕ አስተያየትህን ለመስጠት ወደሁዋላ የሚያስብልህ ነገር በጭራሽ
አይኖርም፡፡ በዚህ መልኩ በዚህ አለም ላይ አንተም ለመኖር ውዴታህ ብቻ ሳይሆን ግዴታህ ነው፡፡ ምክናያቱም ማንም በምርጫ አልተፈጠረም፣
አልተረገዘም ደግሞም አልተወለደም፡፡ በግዴታ እያለቀስክ ወደዚህ አለም ተልከሃል፡፡ ድርሻም አለሕ፡፡ መኖርም መካፈልም አለብህ መብትህ
ነው፡፡ በእግዚአብሄር ካየነው፡፡ ግን እስኪ ይችን ነገር ተካፈሉኝ፡፡
ስለአምባገነን አሰላሰልኩ እና፤ አምባገነን ማለት እኔ ብቻ ልኑር ልዘዝ
ልብላ ልጠጣ የሚል፤ እግዚአብሄር ከፈጠረው ህዝብ መካካል እሱ ጥቂቶችን መርጦ መሳሪያ አድርጎአቸው የሚኖር ሀጢያተኛ ማለት ነው፡፡
አምባገነን እራሱን የሾመ የምድር አምላክ ማለት ነው፡፡ ቢችልም እግዚአብሄርን
ቦታውን ለመሻማት የተነሳ ጨካኝ፣ ስግብግብ፣ የነገን ሁኔታ የማያስብ፣ አስተሳሰብን መካፈል የማይችል እና እራሱ ጠይቆ እራሱ የሚመልስ
ደግሞም የሚወስን ነው፡፡ አምባገነንን ሁሉም አለም አንድ ግዜ አስተናግዶአል፡፡
በአፍሪካ ግን ድግግሞሽ ይታይበታል፡፡ የሚገርመኝ ግን አምባገነንነት ከወንዶች የተፈጠረ መሆኑእና ደግሞም የሚስተናገድ መሆኑ ነው፡፡
ከወንዶች አለም ብቻ ሳይሆን ከጎኑ የተፈጠረችውም ሴት እንድትንቀጠቀጥለት ይፈልጋል፡፡ ብዙ ግዜ ወንዶች፤ በጉልበታቸው እና በሀይላቸው
ተጠቅሞ የመኖር ተፈጥሮአዊ ስጦታ ያላቸው ሳይሆን አይቀሩም ብዬ አስባለሁ፡፡ ሁሉም በስልጣን አለም የአምባገነንነት ድርሻ ባይደርሳቸውም፤
ግን አባወራ፤ የጎበዝ አለቃ፣ ምስለኔ፣ ጭቃሹም እያለ የሚቀጥለው ነገር ሁሉ በብዛት የተስተናገደው በወንዶች ነው፡፡ ሴትም ወንድም
የመልካም መሪነት ተሰጥትኦ ቢኖራቸውም፤ አምባገነን ግን የሚፈጠረው
ከወንዶች ውስጥ ነው፡፡ ወንዶች ደፋሮች ናቸው፡፡ ይህ ድፍረት ከተፈጥሮዊ ነገራቸው ጋር የተጣመረ እንደሆነ ያጠናው ካላ ቢያሳውቀን
መልካም ነው፡፡ ለማንኛውም ስለአምባገነን ሳወራ ወንዶች ላይ ጣት መቀሰሬ አልቀረም፡፡ ብዙ ሚሊዬን ህዝብ የሚያልቀው በአንድ አምባገነን
ትእዛዝ ነው፡፡ ተኩዋሹም ተከታዩም ሁሉንም ጾታ ቢነካም፡፡ ልብ በሉልኝ ሴቶች አይገሉም አይተባበሩም አይደለም የምለው፡፡ ግን አምባገነን
ሆኖ የሚያዘው አንድ ነው፤ እሱም ወንድ ነው፡፡ ማስገደድ ይችላል ማስፈጸም ይችላል፡፡ የሚገርመው የአምባገነን ሁኔታ፤ መጥፎም መሆኑን
እያወቀ ተግባሩን የሚፈጽምለት ሰው አያጣም፡፡ ጀብዱኛነት ብዙውን
ባህሪ የተላበሰው በወንዶች ላይ ነው፡፡ ይህ ባህሪያቸው ብዙውን ግዜ ችኩል ያደርግእና ያሰቡትን ያለሙትን በቶሎ ይፈጽሙታል፡፡ መግደል
ማሰር የደመነፍስ ስራ ጀብደኛነትን ያሳል፡፡ የገዛ ባህሪያቸውም ብዙ
ጊዜ ሲጥላቸው ሲያዋርዳቸው እናያለን፡፡ ሁሉም አንድአይነት ባይሆንም
ውንብድና ግን ታላቁን ቁጥር ዬዘው በወንዶች ነው፡፡ የሴት ውንብድና ካለወንድ አይዞሽ ባይነት አይፈጸምም፡፡
ወንዶች ጦርነትን መፍጠርእና መምራትም ተሰጥትኦ አላቸው፡፡ ወንዶች ሰውን በአሰቃቂ ሁኔታ ይመረምራሉ ያሰቃያሉ፡፡ በአምባገነንነት ደግሞ
ሰቆቃ ማድረግ የሚወዱእና መንገዱንም እንደግዴታ አድርገው የሚያዩ ናቸው፡፡ አስገድዶ መደፈርም በወንዶች ይካሄዳል፡፡ ወንዶች እርስበእርሳቸውም
እንደአውሬ ሲደባደቡ እናያላን፡፡ የወንዶች ተፈጥሮአዊ ስጦጣ አልምን በጦርነት ያምሳል ደግሞም ይጋብዛል፡፡ በቃ የተነቀፈ የመሰለው
ወንድ እማ ሽንፈቱ አይድርስ ነው፡፡
ግን ዛሬ በኢይሮፕ ብዙ የወንዶች ባህሪ ተቀይሮአል ሰላማዊ አስተሳሰብን
ይዞአል፡፡ አንባገነንም ደዝባው እየጠፋ የሄደበት ማንአለብኝ አመራራ የቀረበት ህዝቡ በዲሞክራሲእና በሰላም ለመኖር የወሰነበት በታሪካቸው
ውስጥ እንደዛሬው ዘመን ተፈጥሮ አያውቅም፡፡ ሕዝብ ነጻ ሆኖ እየተደሰተዘ
ለአጭሩዋን ዘመኑን ለመኖር ወስኖአል፡፡ ሰው ከፈለገ፤ ፖለቲከኞችን ይቆጣል፣ ይተቻል፣ ይገስጻል፣ ይመርጣል፣ ይሾማል ባጠቃላይም
የመሻር ችሎታ እና መብት ተላብሶአል፡፡ ጀግና ህዝብ ካልክ ይህን መብት ታግሎ የደረሰ ነው፡፡ ፈረንጅ ህዝብ ለዚህ ደረጃ በቅቶአል፡፡
ጀግና ነው፡፡ ቀልድ የለም እሱን ማታለል ማንም አይችልም፡፡ በየቀኑ ፖለቲካውን ያል ይመረምራል፡፡ እንደኛ አይከለከልም፤ ሊከለክለው
የሚችል የለም፡፡ ምክናቱም መሪውም እንደህዝቡ የተቀየረ ነው፡፡ የሰለጠነ ነው፡፡ ከእራስ ወዳድነት ወጥቶአል፡፡ አገሩን እንጂ ኪሱን
አያይም፡፤ አምባገነን የሰላም ጦስ መሆኑን አውቆአል፡፡ የዘር የባልይነት የሚባል ነገር ብታነሳ መሳቂ ነህ ማሃይም ነህ፡፡ ሞኝ
ነው እንዴ ብቻዬን ይመቸኝ የሚል ይልሃል፡፡ ዘረኝነት፤ የበላይነትን የሚመኝ ክፍል ያዘጋጀው እና በጥላቻ እና በእልቂት የተሞላ
መሆኑን ሁሉም ልምዱን አካብቶበታል፡፡ ዘረኝነት የድንቁርና ምንጭ
መሆኑ ታውቆአል፡፡ አይምሮ ነው ወሳኙ ላካ፡፡ ጉልበትን መጠቀም አዲዮ ያለበት ዘመን ላይ ኢይሮፕ ገብታለች፡፡ በህዝብ ትግል ሁሉም
ተቀይሮአል፡፡ እኔ< እበልጣለሁ የሚያመጣው ትርፍ ትእቢት፣ ሀይልእና ጉልበት ነው፡፡ እራስህን መቆጣጠር እና እራስን መግዛት
ሚዛናዊ ያደርግሃል፡፡ ከዛ ነው ዲሞክራቲክ ልትሆን የምትችለው፡፡ ከልብህ ትእቢት ጥርግ ብሎ ሲወጣ፡፡ አስተዳደጋችንም ለአገራችን
ወሳኝነት አለው፡፡ ጀብዱኛ መሆን እውስጥህ ነቀርሳ መትከል ነው፡፡ የመሪዎቻችን ችግር ይህ ነው፡፡ መሸነፍን አለመቀበል ከጀብዱኝነት
የተያያዘ ነው፡፡ አንድሰው አምባገነን የሚሆነው ህዝብ ሲፈቅድለት ነው፡፡ መከላካያው ሲፈቅድለት ነው፡፡ ዳኛው ሲፈቅድለት ነው፡፡
ሁሉም መዋቅር ከአምባገነን ነጻ ካልወጣ የተጻፈ ህግ ከወረቀቱ ተነስቶ አይራመድም፡፡ ዳኛ፣ መከላከያ ከህዝብ ጎን መቆም ግድ ሊለው
ይገባል፡፡ በደሃ ላይ ፤ባልመረጠው ህዝብ ላይ፣ በደካማ ላይ እና በተቃዋሚው ላይ ክንዱን የሚነሳ ወንድ አስተዳደጉን ይጠይቅ፡፡
ጀብዱኛ አድርገው ገለው አሳድገውት ይሆናል፡፡ አንዱ ሌላውን እንዲጫን የሚል ሳይንሳዊም ሆነ መንፈሳዊ ሕግ የለም፡፡ ፈሪ ስለሆንክ
ነው የተወሰነብህ፡፡ አንዱ አንዱን ቀምቶ የሚበላበት የሚከብርበት እራስን ወዳድነት ከምድሪቱ መጥፋት አለበት፡፡ ይህ ምንም አይነት
ሙግት አያስፈልገውም፡፡ ደሃእና ሀብታሙ ልዩነቱ ሆድእና ጀርባ ነው፡፡ አንድ ፓርቲ አይምሮ ብቻ ወይ አስተሳሰብ ብቻ ለኢትዮጲያ
በቂ አይደለም፡፡ አንድ ፓርቲ ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ ሊኖር ይችላል፡፡ ግን መከላካውንም ፍርድቤቱንም ካዝናውንም ለመግዛት ምንአይነት
ፍጡር ቢሆን ነው፡፡ ይህ እጅ እጅ የሚል ነገር ህዘብ ሊገባው ይገባል፡፡ ተመችቶሃል ወይ የአድሎእና የጥቂት ሰዎች መናሀሪያ የሆነችው
ኢትዮጲያ፤ ካልተመቸህ ወኪል የሚሆንህን ሰው መጠበቅ መከላከል መብትህ ነው፡፡ ነገ ወኪል እንዳታጣ ለዲሞክራሲእና ለሰላም ድምጽህን
ማሰማት መድፈር አለብህ፡፡ ፍርሀታችን ለማንም አይጠቅምም፡፡ አድርባይ የበዛበት ኢትዮጲያ ባህሪውን ይቀይር፡፡ በፍርሀት እና ደግሞም
በግል ጥቅም ወገንህን አገትጎዳ፤ ነገ የዛሬው ያልፋል፡፡ እምነትም ያለሕ ለእግዚአብሄር ተንቀጥቀጥ እንጂ ለሰው ከንቱ ምግባር እራስህን
አትሽጥ፡፡ እኔ ባዩሽ አበበ በእግዚአብሄር አምናለሁ፡፡ „ሽ ጦር ቢሰለፍ አምላክ ከእኔ ጋር ነውእና ማን ይቃወመኛል“፡፡ ሰው በውሸትም
ለማደር ሲል ያቃጥራል፡፡ ግን አንድ ነገር አለ፤ እግዚአብሄር ግን የሚመሰክርልኝ ዘመን ይመጣል፡፡ ሰው እምነቱን ይተግብር እንጂ
አይደብቀው፡፡ ኢይሮፕን ኢይሮፕ ያደረገው የህዝብ ፍላጎት እንጂ የፖለቲከኞች አይደለም፡፡ አንተ ፈልግ የኢትዮጲያ ህዝብ፡፡ እንኩዋን
ሰው፤ እግዚአብሄርም ክፉና በጎውን አሳይቶ፤ ወደመረጥከው ሂድ ብሎአል፡፡ እውን ኢሕአዴግ ከእግዚአብሄር ይበልጣል እን? ሰላማችን ተቃዋሚም በሰላም ሲሳተፍ ብቻ ነው፡፡ በአንድ ፓርቲ የትም አለም
ሰላም ሆኖ አያውቅም፡፡ በቸር ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen