Dienstag, 8. Juli 2014

ኢሕአዴግ „የማን አባት ገደል ገባ“„የማን አባት ገደል ገባ“



ኢሕአዴግ „የማን አባት ገደል ገባ“„የማን አባት ገደል ገባ“

ጥላቻ ጥላቻን ይወልዳል፡፡ዛሬ የአገርህን ሰው ያንገላታ ነገ ወደአንተ መምጣቱ አይቅረም፡፡ በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ ኤስተርን፤ ሞርዶኪየስ፤ እርዳታ ጠየቃት፡፡“ የእስራኤል ሕዝብ ሊጠፋ ነውእና ባለቤትሽን ንጉሱን ተማጸኝልን አላት፡፡ እሱዋም ከብዙ ሚስቶች መካካል አንዱዋ በመሆኑዋ፤ እንደማይቻል ተስፋ በመቁረጥ ተናገረች፡፡ ግን ሞርዶኪዮስ በዚህ አላለፋትም፡፡ ከቶም ማንነቱዋን እስራኤልነቱዋን አስታወሳት፡፡“ ወገንሽ ሲያልቅ አንቺ በንጉስ ቤት ስለሆንሽ ይቀርልሽ መሰለሽን“ አላት፡፡ ከቶም „አንቺ ንጉሱን ያገባሽው ለዚህ ቀን እንዲጠቅም እንደሆነስ ምንታውቂያልሽ“ ብሎ ዝም እንዳትል ወደማንነቱዋ እንድትመለስ አደረጋት፡፡
ውድ ወገኖች፤ እሁንም እንጉሶች ቤት የሚሳደዱት እና ለኢትዮጲያ ሲሉ ለሚንከራተቱት  ለሚጥሩት  ቤተሰብ እና ዘር የሆናችሁ መንግስታቱ ውስጥ እንዳላችሁ እሙን ነው፡፡ ታዲያ እናንተ ሁሉ እያላችሁ ለምንስ በምድራችን በአገራችን ውስጥ ብዙ መደነጋጋሮች ይኖራሉ? ውነት የኢትዮጲያ የወንድማማቾች/ የአንድ አገር ሰዎች በቁዋንቁዋ እና በባህል የተሳሰሩ የተዋለዱ እና የተጋቡ እንደዚህ ሲሆኑ ማየት፤ ውነት ሰርከስ ነውእን? ቲያትር ነውእን? እግርኩዋስ መሰላችሁእን? ወይስ የእስፔን የበሬ ውጊያ፡፡ ያሳዝናል፡፡  አንድ ፖለቲካ ፓርቲ በስልጣን ሲሆን በመረጋጋት የሚመራበትን መንገድ ይፈልጋል እንጂ፤ እንዳውም ጭራሽ ሲታማ እና ሲነገርለት የነበረውን ታሪክ እውን ለማድረግ ወደእርምጃ ባልገባ ነበር፡፡ ትናንት ኮለኔር መንግስቱ የነገሩን እውነት ነበር ማለት የጀመረው ዛሬ ደግሞ ተቃዋሚ የሚለን ላካ ትክክል ነው የሚል ጨምሮባታል፡፡
ሌላው ውድ ወገኖች፤ ያ ትውልድ ችግር የገጠመውእና እስከዛሬ ድረስ በመሰደድ፤ በመጠርጠር የሚኖር መሆኑን እናውቀዋለን፡፡ ምንም ባልተፈጠረ ነገር ተቃዋሚ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ግለሰቦች ላይ ለአለፈው 20 አመት ሲደረግ የነበረው ክትትል፤ በአገሩ ባይተዋር ማድረግ፤ ዘመድ ወገን ጉዋደኛ እንዲሸሸው ማድረግ ለምን እንዳስፈለገ ዛሬ ኢሕአዴግን እና አባሉን ብጠይቅ መልካም ነው፡፡ „ የጅብ ቸኩል ቀንድ ይነክሳል እንደተባለው ሁሉ፤ ኢህአዴግን ህዝብ ወደተመኘው ዲሞክራሲ እንዲመጣ ባወቅነው እና በቻልነው ለመርዳት ወደሁዋላ አላልንም ነበር፡፡ እውነት ዲሞክራሲን የሚፈልግ መስሎን፡፡ አንዳንዶቻችን ማለቴ ነው፡፡ ግን የምናደርገው ድርጊት ሁሉ፤ ከኢሕአፓ ወይም ከሌላ ጋር በማጠጋጋት እውነትን እና ስህተቱን ለመለየት አዳገተው፡፡ በዛ ላይ ሙስናውን፣ አሉባልታውን እና ማንአለብኞችን  ከማየት እና ከመታዘብ ውጪ ምንም ልናደርግ አልቻልንም፡፡ ብዙ ቤተሰብ ተናግቶብን የምንኖር እንዳሉ ማንም ሊገባው አልቻለም፡፡ ከባድ የስነልቦና ጦርነት የተካሄደብን ቁጥሩ እንዲህ ቀሎ አይታይም፡፡ በጣም በትልቁ የታዘብኩት ነገር፡፡ „የማን አባት ገደል ገባ“ በማለት የሚኖረው  ኢሕአዴግ የሚለው የነበረው፤ ዲሞክራሲን እራሳችሁ እውን አድርጉ እያለ፤ እሱ በሾማቸው ሹማምንት እና በሰላማዊው ሕዝብ መካከል የፈጠረብን ፍጥጫ ነበር፡፡ የኢሕአዴግ ትግል መቁዋጫ የለለው ነው፡፡ ትግል ከሰላም ወደ አስከፊ ተቃውሞ ህዝቡ እንዲገባ የሚገፋፋ፡፡ ተቃውሞ የደም መፋሰስ የጠማው አይነት እይታ፡፡ አንድም ቀን 20 አመት ሙሉ የዲሞክራሲን ፍንጭ ከሕብረተሰቡ መካካል ሳይፈጥር፤ እንዲሁ በማስፈራራት፤ ደግሞም እ በህግ መኖር ሳይሆን እራሳችንን  ዘዴ ፈጥረን ቀን እስኪያልፍ ለመኖር  የተገደድንበት ሲስተም ውስጥ አስገብቶን በዝምታ መቆየታችን የማይካድ ሀቅ ነው፡፡
ግን ዛሬ በትልቁ መናገር የምፈልገው፤ ወደሰላም ለመምጣት ያልፈለገው ኢሕአዴግ፤ ስልጣን ከኦሮሞው፣ ስልጣን ከአማራው፣ ስልጣን ከትግሬው ፣ ስልጣን ከኤርትራው፣ ስልጣን ከደቡብ ህዝብ እና ከሌሎችም ጎሳዎች በልጦበት በዘፈቀደ እና በማንአለብኝነት  አሮጌውን ትውልድ አጠፋለሁ ብሎ የሚያደርገው ማሳደድ፤ አዲስ ታጋይ ትውልድ እራሱ ፈጠረ ብል የተሳሳተ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክናያቱም ሶሻሊስት ሳይሆን ሶሻሊስት፣ ኢምፐርያሊስት ሳይሆን ኢምፐርያሊስት፣ ተቃዋሚ ሳይሆን ተቃዋሚ  ነህ፤ ብለህ አንድን ሰው ብትጨቀጭቀው ሶሻሊስት፣ ኢምፐርያሊስትም  ምንድን ነው ብሎ ለማወቅ ይጥራል፡፡ ብታሳድደው ደግሞ ወገን ባገኝ ብሎ ወደእዛ አንተ ወደጠላሀው ይሄዳል፡፡  20 አመት ታዲያ በዚህ መልኩ ኢሕአዴግ፤ እራሱን አስተካክሎ ተቃዋሚ ጋር ተባብሮ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ መጣር ሲገባው፤ ስልጣን አንቆ ብቻ፤ እራሱን እንዲቃወሙት እንጂ እንዲረዱት የማያደርግ የተቃዋሚ ፋብሪካ እራሱ ከፍቶ ሲፈበርክ የቆዬ በመሆኑ እውን ኢትዮጲያን ማስተዳደር ኢሕአዴግ ይፈልጋል ወይ? ብዬ ዛሬ ዛሬ ተጠራጥሬአለሁ፡፡ ትንቢት ከእግዚአብሄር ከሆነ ሺህ ጦር ቢሰለፍ መፈጸሙ አይቀርም፡፡ ትንቢት ግን ከሰው አንደበት በአድርባይነት ከወጣ አይፈጸምም፤ እንዳውም ከሰው አንደበት የተፈጠረ ትንቢት  በቁጣ ይፈርሳል፡፡ በእግዚአብሄር ስም ውሸት ተዋሽቶአል እና፡፡  እራሱ ፖለቲከኞችን አንገታቸውን እንዲያቀረቅሩ፤ የእራሱንም ሰዎች ለእውነት እንዳይሰሩ የሚያደርገው የኢሕአዴግ ሁኔታ እስከመቼ እንደሚዘልቅ አላውቅም፡፡ ግን በዚህ ከቀጠለ እና ለተቃዋሚ በር ካልከፈተ ኢሕአዴግ „የፈርኦን ልብ ደነደነ ተብሎ መጻፉን እንደበጎ አድርጎ ቆጥሮአል ማለት ነው፡፡ የፈርኦን እባቦችን እንድ የሙሴ ብትር ውጣቸዋለች እና፡፡
„ ቅዠት ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም“ ነውእና፤ ኢሕአዴግ በእራሱ አባል እንኩዋን ሊመረጥ ያልቻለ ግን የተፈራ መሆኑን አብረን አይተነዋል፡፡ ተቃዋሚ እየበዛ የሚሄደው፤ የተቃዋሚ መጠንከር ሳይሆን የገዢው ፓርቲ የተሳሳተ መስመር መሆኑን ሊያውቀው ኢሕአዴግ አልገባውም፡፡ ሰው ሲሰላች እና እንዳው ዝም ብሎ ካለምክናያት ሲገፋ ንቀትም እንደሚያድርበት ማወቅ ልባምእነት ነው፡፡  እኛ ተቃዋሚ ናቸው ተብለን ስንገላታ፣ ድምጻችንም ሳይሰማ / ያልነበርነውም ማለቴ ነው/ ብዙ ሰው ከእኛ በመፍራት ሸሽቶአል፡፡ እንደእኔ አይነቱም ጥግ ይዞ አልቅሶአል፡፡ እርግጥ ነው ፈሪ ነኝ እላላሁ፡፡ ፍርሀቴ ግን ሰላምን በመፈለግ እንጂ፤ ይህ የሰፈር አውደልዳይ ወይም ደግሞ ለሆዱ ሲል የሰውን የተረጨብኝን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ተከትሎ ፈርቶ ያጎበደደውን አይደለም፡፡ የለም እኔ በዘመኔ ፈሪ ሆኘ አላውቅም፡፡ ግን በትእግስት የተጀመረውን ዲሞክራሲ ተብዬ ልየው ብዬ እንጂ፡፡ ፈሪ ብሆን እቀላቀላቸው ነበር፡፡ ፈሪ ብሆን ጉቦ እከፍል ነበር፤ ፈሪ ብሆን አንዱን አድርባይ አገባ ነበር፡፡ አዎ የሴት ህይወት የማትረፍ መንገዶች እነዚህ ናቸውእና፡፡ አይደለሁም እንዳትሳሳቱ፡፡ ግን ኢትዮጲያውያኑን በሙሉ፤ ማለቴ ኦሮሞውን ትግሬውን አማራውን ሌላውንም ከአንጀቴ ስለምወዳችሁ በማየው ነገር ሁሉ  አዝኛለሁ፡፡ ችግራችን ዘር አልነበረም እና፤ የትግል አቅጣጫው ሁሉ እንዳይስት አስቀድሜ በፍርሃት አልቅሻለሁ፡፡ ዛሬ ግን አላለቅስም፡፡ ምክናያቱም ጥያቄዬ ተመልሶልኝ ሳይሆን  ብዙ ሰው እውነት እና ውሸቱን የሚለይበት ደረጃ ላይ መድረሱእና፤ እንደእኔ አይነቱ እብድ ተብሎ ስላልቀረ፡፡ ዛሬ ሁሉም እኩል እብድ የሚባልበት ንቃተህሊና ላይ ስለደረሰ፡፡ እውነት ግን፣ እንደእብድ ደፋር ናት እና ለነብዩስ ይህ ስም መች ቀረለት እና ታፍራለሕ? እውነት እውነት እላችሁዋለሁ፡፡ በጌታዬእና በእየሱስ ክርስቶስ ስም፤ እስላምም ሁን ክርስቲያን፤ ዘርህም ሆነ ጎሳሕን ሳለይ ሁላችሁንም እንድወዳችሁ እምነቴ ያስገድደኛል እና፡፡ በቸር ባዩሽ  

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen