ፖለቲካ ማሸነፍ እና መሸነፍ ሳይሆን ስራ ነው፡፡
ጥያቄው ለእኔ ፤ ያለው ገዢ መጥፎ ነው ጥሩ ነው የሚለው አይደለም፡፡ ያሳሳበኝ ነገር ሁልግዜ ከዘመን ዘመን እየተሸጋገረ
እና እያደገ የመጣው የሰባአዊነት ነገር እየጠፋ የሰዎች ፍላጎት በእራስ ወዳድነት እየተመሰረተ መሄዱ ነው፡፡ በኢትዮጲያ ውስጥ የተደረጉ
ማንኛውም ለውጦች አስፈላጊነታቸው ትክክል የነበረእና አንገብጋቢም የሕዝብ ጥያቄ የነበረ ቢሆንም ግን የተመለከትነው ሁልግዜ በቤተመንግስት
ውስጥ የተወሰነ የሀይልእና የስልጣን ብሎም እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ የሆነ እንጂ ሕዝቡን ወደአስፈላጊ ዲሞክራሲ እና የመብት ጉዳይ
ሊያመጣው አልቻለም፡፡ ይህም አሳሳቢ የሆነው ነገር ድህነት እየተስፋፋ እህል ባለበት አገር ሰው ጾሙን እያደረ የሚሄድበትን ጉዳይ
ትክክል እንዳልሆነ እና አላግባብ የሚያካብቱም ሰዎች ትክክል እንዳልሆኑ የሚያገናዝብ የአብሮነት የስበአዊነት ስራ ግንዛቤ ካልተሰራ
ህዝብ ወደሚፈልገው ለውጥ ሊመጣ አይችልም፡፡ ግን ሁልግዜ የተወሰኑ ሰዎች ያመኑበትን የቤተመንግስት ለውጥ ሊያመጡለት ይችላሉ፡፡ይህ
የለመድነው ነው፡፡ ካፒታሊዝም የሚደግፈው ቢኖርም፤ ካፒታሊስት የሆኑ አገሮች እንደኢትዮጲያ ጾሙን የሚያድር ሰው የለበትም፡፡ ስለዚህ
ካፒታሊዝም በኢትዮጲያ የህልም እሩጫ ነው፡፡ በካፒታሊስት የሆኑ አገሮች
የሚኖረው ህዝብ፤ ሰውን ጾም አሳድረው ግለሰቦች የነሱን ከፍታ የሚገነቡበት ጭካኔውም የላቸውም፡፡ ለዚህ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ
ንቃተ ሕሊና ገንብተዋል፡፡ እኛ ጋር ግን የሚቀድመው ከፖለቲካው ስራ በፊት የበላይነት፣ ስልጣን፣ ከሕዝብ መሃል አባል ሰብስቦ ያንን
ክፍል ማክበር ማሰዳግ እና እንደልቡ እንዲሆን ማድረግ የራሱን ገነት መገንባት ነው፡፡ ይህ የሞኝ ጉዞ ነው፡፡ ዘላቂነት የለውም፡፡
ሕዝብ ዝም አለ ማለት አላወቀም ማለት አይደለም፡፡ ጦምአዳሪው፣ ስራ
አጡ እየበዛ በሚሄድበት አገር ኢትዮጲያ፣ በልቶ የሚያድረው ክፍል
ያኛውን ክፍል ልክ እንደዳቢሎስ በማየት ወይም እንዳልተሳካለት በመቁጠር“ ጆሮ ዳባ ልበስ“ ብሎ ይባስም ብሎ የተቸገረ እንደለለ
በማስመሰል ሁኔታውን መርሳት እጅግ የሚያሳስብ ሁኔታ ነው፡፡ ሴቶች ከመቸውም በላይ በድካም በሚገኙበት ወቅት የጥቂት ሴት ሚኒስተሮች
ቦታ መያዝ ወይም በስልጣን መቀመጥ ሴቶች እተሸለ ደረጃ ላይ ደርሰዋል ማለት ያሳዝናል፡፡ እንዳውም ከመቸውም በላይ ማጣት ያሰማራቸው
የስራ ዘርፍ ወይም መንገድ ሁሉ ለከፍተኛ ትቃት ዳርጎአቸዋል፡፡ በላጩ
ሕዝብ እየተቸገረ በድህነት እየተቆራመደ ጦሙን እያደረ የሚሄድበት አገር ላይ የሚደረጉ መረን የለቀቁ የማተርያል ውድድሮች ፤ካፒታሊዝም
የሚለውን ሲስተም ወይም አመለካካት እየጠላ እንዲሄድ እና ህዝብንም ወደኮሚኒስት ሪቮሊሽን እንዲሄድ እንደሚያደርገው ምእራቡ አለም
መጠርጠርም ያስፈልጋቸዋል፡፡ ኮሚኒዚም እያቆጠቆጠ በመሄድ ላይ ይገኛል እና፡፡ ሰው ወደእዛ የሚሄደው ይጠቅመኛል ብሎ ሳይሆን ያለበት
ሁኔታ መክፋት ይሆናል፡፡
ይህን የኢትዮጲያን በድግግሞሽ የምናልፍባቸው የማንአለብኝነት ሁኔታ ሰባአዊነትን በእጅጉ እያጠፋው እየሄደ ነው፡፡ ኢንቬስትሜንት
የሚያስፈልግበትን ትምህርት የሚሰጥ አካል ከመፈጠሩ በፊት ወይም ተገቢውን መተካካያ ሳይስተካከል ስፍራ ማስለቀቅ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡
እሱም ፖለቲከኞችን እንዳይታመኑ እና ደግሞም ኢንቬስተሮችን እንዲጠሉ የሚያደርግ ሀይል አለው፡፡ ይህ በእጅጉ ቀውስ ፈጣሪ ነው፡፡
የአካባቢን ደግሞ ሁኔታ አንድ ኢንቬስተር ሳያጠና አይገባም፡፡ ከበሳል አገሮች የሚገቡ ኢንቬስተሮች የሚመለከቱት የሚጠብቃቸውን ጥበቃ
ብዛት ሳይሆን ከማን እንደሚጠበቅ የሚያደርገውን ምንጭ ነው፡፡ ወደአፍሪካ የሚገቡ ኢንቬስተሮች ተቃዋሚ በሕዝብ መካከል የሚጫወተውን ሀይለኛ ሚና ስለሚያቁት በቀላሉ ሰፍ ብለው ነዋያቸውን
ሊያፈሱ አይገቡም፡፡ ሕዝብ ካልተመቸው ጉሬላም በለው ሰላማዊ ወደትግል መግባቱ አይቀርምእና፡፡ ስለዚህ በኢትዮጲያ ያየሁት ችግር
ለሕዝብ የሚገባውን መረጋጋት የሚሰጥ የፖለቲካ አመራሮች ሊፈጠሩ አለመቻላቸው ነው፡፤ አልያም ባላወቅነው ምክናያት ቤተመንግስቱን
ከጨበጡ በሁዋላ ጥበቃቸውም ስጦታቸውም ስራቸውም ቤተመንግስት አካባቢ ለሚገኙት ለመረጡዋቸው ሰዎች ብቻ ነው፡፡ ቤተመንግስት ስል
በሁሉም ክልል የምናየው የፖለቲከኞቻችን ቤተመንግስት አላቸው፡፡ በፓርቲ ስም የታቀፈው ክፍል እንደልቡ ሆኖ ሰዎችን በማሰላቸት አገሪቱን
ልክ እነሱ ብቻ እንዲዝናኑበት፣ እንዲናገሩበት እንዲመሩበት የተሰጣቸው እስከሚመስል ድረስ ሌላው ተሸማቆ የሚኖርበት ሲስተም የተገነባበት
ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ተበዳዩ ሕዝብ ለመኖር ሲል የሀሰት መስካሪ ከሳሽ እና ተበዳይም እርስ በእርሱ በማድረግ የበላይነትን እንዱ
ተቀናጅቶ አስታራቂ በመምሰል ሰነልቦናን በመግደል ይገኛል፡፡ ተቃዋሚም በአንድነት ሊሰሩበት ያልቻሉት የንቃተ ህሊና አለመዳበር ጉዳይ
ነው እላለሁ፡፡
ይህ ትልቅ ቀውስ ያመጣብን ነገር ብዬ የምገምተው፤ ፖለቲከኞች ቤተመንግስቱን ሲጨብጡ ልክ የእግዚአብሄርን ወንበር እንደተረከቡ
ሆኖ ስለሚሰማቸው የሚሞላቸው ትምክህት ወይም የአሸናፊነት ስሜት ፖለቲካ ስራ እንዳለው ይዘነጉታል፡፡ ፖለቲካን እንደስራ ሳይሆን
እንደድል መቀናጀት ስለሚያዩት አንደዬ የጨበጡትን ስልጣን የሚያጡት አይመስላቸውም፡፡ ይህ ሁሉንም ፖለቲከኞች ባያካትትም፤ የበለጠው
ግን በግልስግብግብነት እና በመሰረታዊ ድህነት የተነሳ ስሕተት ይፈ›ጸማል፡፡ ግን ድንገት ያንን ማጣቱ ሲሰማቸው ትኩረታቸውም አሁንም
ለመስራት ሳይሆን በመከላከል ስልጣንን መቀጠል ነው፡፡ የግል ጥቅም የአገሪቱን ጉዳይ ያዘናጋል እና፡፡ ኢሕአዴግ ዛሬ ላርመው ቢልም
በብዙው መረን ለቆት የነበረውን ነገር ዛሬ ሊያስተካክለው አይችልም፡፡ ችግርም የተፈጠረው እዚህ ላይ ነው፡፡ ባህሪ ይለመዳል እና፤
ያስለመደው ባሕሪ በእራሱ አባል እንዲናቅ እንዳይከበር የማድረግ ጫና ፈጥሮአል፡፡ ህዝብን የሚያንገላቱ ሰዎች መፈጠር የበላዮቹን
እንዲናቁ ያደርጋል እና፡፡ ይህ ልቅነት የፈጠረው ጉዳይ አገሪቱን ወደሙስና እንድትገባ አድርጎአታል፡፡ ይህም ብዙው ያመጣው ችግር
ፖለቲካ ከስልጣን በላይ የሆነ ስራ እንዳለው በመዘንጋቱ ነው፡፡ ዛሬ
የኢትዮጲያ ሕዝብ ከኢሕአዴግ ላይ እሰከአካቴው አይኑን ያነሳበት እና በዝምታ እንዲያየው የሆነበት ሁኔታ የተፈጠረበት ደረጃ ላይ
ደርሶአል፡፡ ኢሕአዴግም ሆነ ደርግ ወይም ሀይለስላሴ የተሰጣቸውን የአደራ እረጅም ጊዜ እና አመኔታ ሳይጠቀሙበት አልፈውታል፡፡ እጅግ
የሚሳዝነው ሁሉም በገዛ አገሩ ለመናገር አቤቱታ ለማቅረብ ለመክሰስ መፍራቱ ነው፡፡ ስትፈራ መናቅ እንደሚከተል መገንዘብ ነበረብን፡፡
ፖለቲካ ስራው ቀሎ የሚታይበት አገር እንደኢትዮጲያ ያለ የለም፡፡
ስልጣን ለማያዝ ብዙ መስዋእትነት ከፍለው፤ በወራት እድሜ ውስጥ ግን ስራ መስራት ሳይሆን የሚያሳዩን ማንአለብኝነት ነው፡፡
ሁሉም ሊገለሰስ የማይችለውን መገልሰስ እንደትልቅ ዝና ይቆጥሩታል እና፡፡ አሁንም የምፈራው ይህ የኢሕአዴግ መንግሰት በቀላሉ የሚነሳ
ባለመሆኑ እሱን የሚገለስሰው ደግሞ ፖለቲካ መጣል ብቻ ሳይሆን ሕዝብንስ የማንሳት ስራ እንዳለው ያውቁ ይሆን? በቸር ልበላችሁ
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen