Mittwoch, 2. April 2014

ስሜት ዲሞክራሲን አያመጣም




ስሜት ዲሞክራሲን አያመጣም

ቆንጭላችሁ አታውሩ፡፡ ወንጌል በእጁ የያዘ ከበደላችሁ ወይ ሲያጠፋ ካያችሁ ሰውየውን እንጂ ከወንጌል ጋር መታገል አትችልም፡፡ እንዳትስቱ ተጠንቀቁ፡፡ ባዩሽ ገንዘብ ተከፍሎአት መስሎህ አታልም፡፡ ማንም የማይገዛው ማንነት ነው ያለኝ፡፡ ማንም አልኩህ፡፡ ፎቶዬን እና ስሜን ግልጥ አድርጌ አስቀምጨላሀለሁ አዳሜ፡፡ ወንጌልን የማሾፍበት አይምሰልህ፡፡ እግዚአብሄርን አምናለሁ፡፡ ኢትዮጲያን ደግሞ ካለእሱ ትቀየራለች ብለህ አታስብ፡፡ ይልቅስ እጅህን ወደእሱ ዘርጋ፡፡ ካልሆነ ያው እንደለመድከው ከአንዱ ጀግና ወደሌላው ስታሸጋግራት ትኖራለህ፡፡ ሁልህም ወደዲሞክራሲ መምጣት ነው ያለብህ፡፡ ሙሰሊምም ሆነ ኦርቶዶክስ ወይም ፔንጤ የማያምንም ቢሆን ኢትዮጲያ ላይ መኖር መብቱ ነው፡፡ ይህን ተቀበሉት፡፡ ዘርም ማንኛውም ዘር በአገሩ መኖር መብቱ ነው፡፡ ሰው እምነቱ እንደገባው እንጂ የሚሆነው፤ አንተ እንደገባህ ሌላው መኖር የለበትም፡፡ አንተም የሌላውን መኖር የለብህም፡፡ እየጎተታችሁ ነገር እያመጣችሁ አንዱን ከአንዱ ለማጋጨት አትሞክሩ፡፡ እኔ በዲሞክራሲ አምናለሁ፡፡ መስማት የማትፈልጉትን ሁሉ በሰማችሁ ቁጥር ነገሩን ለመረዳት ከመሞከር እያጣመሙ ወደሌላ አቅጣጫ መውሰድ የተረገመ ሰው ተግባር ነው፡፡ እዚህ ሁላችንም የምንለፋው ወዳጀ ለዲሞክራሲ ነው፡፡ ለወኔ እና ለስሜት አይደለም፡፡ የእኔ እንደዚህ ነው፡፡ የእናንተ እንደዚህ ከሆነ እንግዲህ ነገር የምታጣምሙ ያለንበትን ዘመን አስቡ፡፡ እና ሁልህም ለዲሞክራሲ ተነሳ፡፡ ዲሞክራሲ አስብ፡፡ ከፈለክም ገነጣጥል እና ሞክረው፡፡ ከዛ አማራው ወደትግሬው፣ ትግሬው ወደኦሮሞው እና ኦሮሞው ወደአማራው ዕያለ ይሰደዳል፡፡ እንዳውም እዛው ቀረብ ይልልሀል ስደቱ፤ የአይሮፕላን ዋጋ መክፈል አያስፈልግህም፡፡ የኤርትራን ወጣት ተመልከት የሚያሳዝን ነው፡፡ ወደጠሉት ኢትዮጲያ ሲመጡ ተቀብለናል፡፡ ሰው ከሰው እንጂ ከአውሬ አይኖርም፡፡ ያልታደለውም ውሃ በረሃ እየበላው ነው፡፡ ልብ የለሕም፡፡ሁልህም ልብ ግዛ፡፡ እግዚአብሄርን በሰላም እና በነጻነት እያመለክን እንድንኖር ሰላምን በአገራችሁ ላይ ፍጠሩ፡፡ ተገነጣጥዬ ሰላም አገኛለሁ የሚል ካለ ጉም የዘገንክ መሆንህን ልንገርህ፡፡ የአፍሪካ ወጣት በገፍ አፍሪካኝ እየጣለ እየሸሸ ነው፡፡ የሚመጣው ዘመን ቀላል አይምሰልህ፡፡ አፍሪካ በድህነት እየታመሰ ነው፡፡ብሶበታል፡፡ ሌላ የሚያሳስበን ነገር አለ፡፡ እግዚአብሄር የሀይማኖት አምላክ አይደለም የልብ የሆነ የእምነት አምላክ ነው፡፡ የሰላም አየር ለኢትዮጲያ ጠቃሚ ነው፡፡ ጊዜያችሁን ትላቻ በመስበክ አታባክኑ፡፡ በቂ ጥላቻ አለምን ሞልቶታል፡፡ ተጨማሪ አያስፈልገውም፡፡ ኢትዮጲያ የሁሉ ኢትዮጲያዊ መኖሪያ መሆን አለባት፡፡ ማድረግ ካቃተሕ አፍን ዘግቶ መቀመጥ ይሻላል፡፡ ደልቶን አይደለም እዚሕ የምንለፈልፈው፡፡ ስለእግዚአብሄር ወደዲሞክራሲ ሁላችሁም ቅረቡ፡፡ ፍሬ ከርሲኪ አታውሩ፡፡ ሌላውንም ለመረዳት ሁላችሁም ሞክሩ፡፡ አንዱን አንዱ ካልተረዳው ታዲያ እንዴት ነው ዲሞክራ እየተባለ የሚጮሕ፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen