ቅድስእና የጎደላት ቤተክርስቲያን
በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደልብ እንድንሆን የተሰጠን ህግ የለም፡፡ በአለባበስም
ሆነ በአነጋር በመዘመርም ፈር የለቀቀ የእግዚአብሄር ያልሆነ ነገር ከማድረግ ብንቆጠብ ጥሩ ነው፡፡ እየሱስ“ ላጠብቅ ነው እንጂ ላፈርስ አልመጣሁም“ ብሎአልእና ሴት እህቶች የጠራራ ወረርሽኝ መስለው እጆሮአቸው ላይ አንዳች የሚያክል ጉትቻ አድርገው ከቁዋንጃ በላይ የሆነ አጭር ቀሚስ ወይም የሰውነትን ቅርጽ የሚሳይ ሱሪ ልብስ ለብሰው በምእመናን ፊት ለመዘመር ባይነሱ መልካም ነው፡፡ እንዳውም የኢትዮጲያ ሴቶች ጸጉር ቆንጆ ሆኖ እያለ ይህ ሁሉ የመቀጠል እሽቅድምድም
ምን እናደመጣው ሊገባኝ አይችልም፡፡ ቆንጆ ጸጉር እንኩዋን የለኝም የምትል ሴት ካለች፤ እግዚአብሄር ለምን እንደእሱ አድርጎ እንደፈጠራት በመደሰት እራሱዋን ተቀብላ ሌላውም እንዲቀበላት
የእራስ መተማመን መፍጠር አለባት፡፡ ሌላው ደግሞ መንፈሳዊነት
የሚጀምረውም ከዚህ ነው፡፡ ሰው ጊዜውን ማጥፋት ያለበት ስብእናን በሚያስተምረን
በሚያኖረን በመንፈሳዊ ሕይወት ላይ እንጂ በስጋ መሆን አይገባውም፡፡ እራሳችንን ከሚገባው ወይም የእኛን የስጋ መልክ እንኩዋን እንዳያሳይ የምንቀያይረው
ነገር ሁሉ ምልከትነቱ የመቅናት ሊሆን ይችላል፡፡ ያቺን ሌላዋን ለመምሰል የምናደርገው ህይወት ምንም አይነት የቅድስና ህይወት የለውም፡፡ ይህ በስጋችን ላይ የምናደርገው ኢንቬስትሜነት
በጣም የሚገርመው የቅድስእና ህይወትን ከማሳጣቱም በላይ በኢኮኖሚውም
የሚጎዳን ነው፡፡ እስኪ ያለውን ውድድር ተመልከቱ፤ የሰው ጠጉር መግዛት ከፈለጋችሁ በኢትዮጲያ እስከአስር ሽህ ብር የሚያስወጣ ነው፡፡ ይህ ሀብታም ሴቶች መግዛት አቅም ቢኖራቸውም አነስተኛ ገቢ ያላቸውም ሁለተኛ ሶስተኛ እያለ እስከእንሰሳ
ጠጉር ከዚያም አልፎ ከኬሚካል የተሰራ ተገዝቶ እላይት ላይ ተሰፍቶ ይኬዳል፡፡ እንግዲህ ወገኖቼ በመንፈሳዊ ህይወት ውስጥ ነን የሚለው እራሱን ቢመረምር መልካም ነው፡፡ እንደክርስቲያኑ ቁጥር ብዛት ፍሬ ማፍራት በምድሪቱ ላይ አልተቻለም፡፡ ይህ ግዴታ ወደእግዚአብሄር የምንመለስበት
ወቅት ሊሆን ይችላል፡፡ ወንዱሞችም ቢሆን፤ ስህተቱ ያቺን በቤተክርስቲን ከሚገባ በላይ አሸብርቃ እና ሕግ የለለው አለባበስ ቅድስናን የማያመጣ ነገር እያዬ ትኩረቱ ወደዚች ሴት ስለሚሳብ ሌሎች ወጣት እህቶችን ስርአት እንዳይኖራቸው መጥፎ አርአያነት ይፈጥራል፡፡
ለነገሩ ሊያሳስበን የሚገባ የአንድ ሴት ህይወት ሳይሆን ቤተክርስቲያን አቅጣጫዋን እየሳተች በሄደች ቁጥር የእግዚአብሄር ነገር እየተረሳ ስለሚሄድ ነው፡፡ እሱም ካስተዋልን ሰው እንደተፈጠረ መልኩን ካልተቀበለ እግዚአብሄርን
እየረገመ ነው ማለት ነው የሚኖረው፡፡
ጎራዳ አፍንጫ ቆርጫጫ ጸጉር እያልን በውስጣችን በማንነታችን
ከታገልን መንፈሳዊ ህይወትም የለም፡፡ እንዳውም እንደእውነቱ ከሆነ ጆረአችንን እንኩዋን ለጉትቻ መበሳት አይገባንም ነበር፡፡ ምክናያቱም እግዚአብሄር
ቢያስፈልገን ኖሮ ጆሮአችንን እያዘጋጀ እየበሳ ይልከን ነበር፡፡ እኔም ጆሮዬን የተበሳሁ ሴት ነኝ እና ሁላችንም የተጉዋዝነው እስከገባን ድረስ ወይም እንደወረስነው ነው፡፡ እኛ ግን መውረስ ያለብን እግዚአብሄርን ነው፡፡ ሁሉም በልክ እንጂ ከጣራ በላይ ሁኑ አላለንም፡፡ ስለዚህ እንደእኔ ሁላችንም ቅድስና እንዴት እንደሆነእና ለምንስ አሁን እየተረሳ እንደመጣ ለምድራችን በረከት ሲባል ማስተዋል ጥሩ ነው፡፡ አገራችን ከመቸውም በላይ ችግር ላይ እንደወደቀች እና እግዚአብሄርም ከሰው አስተሳሰብ ውስጥ እየተረሳ የመጣ እየሆነ ሄድዋል፡፡ ማንም ክርስቲያን ደግሞ እንኩዋንስ አርአያ ሊሆን ቀርቶ ጭራሽ ገደል ከታች እየሆነ እየሄደ በመሆኑ እጅግ በጣም ያሳፍራል፡፡
በነገራችን ላይ ተሸፋፍነው የመጣም የተለዬ ልብ ይኖራዋል ማለት ሳይሆን ግን ማንም ሰው ወደቤተክርስቲን
የሚሄደው ለውድድር ወይም ያለውን ማተርያል ለማሳየት ሳይሆን እግዚአብሄርን በመፈለግ ነው፡፡ ይህ የተዘፈቃችሁበት የማተርያል አለም ከምንመኘው እና ከምንጠብቀው
ሰማያዊ አለም ጋር በጭራሽ አይገናኝም፡፡
እግዚአብሄርንም እያሰደብን እንዳንሄድ የቤተክርስቲያን መሪዎች አጢነው ቢመለከቱት መልካም ነው፡፡ በኢትዮጲያ ቤተክርስቲያን
ውስጥ በፈረንጆች ቤተክርስቲያን
እንኩዋን ከምናየው ስርአት ያለው አለባበስ በጣም የተለዬ ሆኖአል፡፡ ወንዶቹም ሚስቶቻቸውን በመምከር ያስተካክሉ፡፡ እንዳው ያማረኝን የጉጉት ልብስ ለመልበስ ስል ህግንም ማጣመም ጥሩ አይደለም፡፡ ብዙ ሰውም ውስጡ በመጨናነቅ እና የሚሄድበት አጥቶ ግራ ተጋብቶ ቁጭ ብሎ እየታዘበ እንዳለ እያየን ነው፡፡ እኔ ቤተክርስቲያን
ስሄድ መመልከት የምፈልገው ስርአት ያላት ሴት እንጂ እንደተራራ ያልተፈጠረባትን
ጠጉር እና አጭር ቀሚስ ለብሳ እፊቴ ቆማ ስትዘምር ደስ አይለኝም፡፡ እንዳውም አንዳንድ ቤተክርስቲያኖች
እንደሚያደርጉት ልብስ ለብሰው፤ ጸጉራቸውን ሸፍነው ሁሉም ቢዘምሩ መልካም ነው፡፡ ደግሞም ለእግዚአብሄር
ሲል እንዳው ድምጽ ስላለው ብቻ አይደለም አንድ ሰው መዘመር ያለበት፤ ዘፋኞችም እኮ ድምጽ ተሰጥተዋል፡፡
እንግዲህ ዘፋኑም ዘማሪውም መለየት ያለባቸው በስርአት ነው፡፡ ሁሉም ካጎፈሩ ምን ይባላል፡፡ ደግሞም ወንጌልን ስለተማረእና ስለጨረሰ መሆን የለበትም ማስተማር ያለበት፡፡ የቅድስና ህይወታቸው የሚጀምረውም ከዚሁ ከአለባበስ ነው፡፡ የለለውን የሚለብስ የእግዚአብሄር ያልሆነን እየፈጸመ ይገኛል እና፡፡ አንተ ያፈርክበትን አንቺ ያፈርሽበትን እየሱስ ሌላው እንዲቀበለው
አትመኙ፡፡ እንዳውም ታስታላችሁ እንጂ፡፡ሌላው መንፈሳዊ ቤተክርስቲንም ውስጥ ሆነ ውጭ ባህሪውም አለባበሱም አንድ መሆን አለበት፡፡ በሰላም ሲዘምር እና ሲያስተምር ያየሁት እውጭ ሲጃጃል ባየው፤ ያሰማኝን ሁሉ ይንድብኛል፡፡
ዘመኑ እግዚአብሄር የሚሰራበት ስለተቃረበ ልብ ያለው ከልቡ ይሁን፡፡ የሰዎች እንባ በዝቶአል ዙፋንም ይነቃነቃል እግዚአብሄርም ይወርዳልእና፡፡ ሕዝብ ሲጨነቅ የሚደርሰው አቅም ያለው ነው፡፡ ከብት ሲበተን እረኛው ሊሰበስብ ይነሳል እንጂ እንዴትስ ዝም ይላል፡፡
የማንም ቤተክርስቲያን አትፈርስምእና ሁሉም በእራሱ ባሕሪ ላይ የዝመት እንጂ በሌላውስ ለመናገር ይችላልእን? ኦርቶዶክስም ሁን ፔንጤ
የቅድስናውን ሕይወት አትርሳ፡፡ እራስህን ከተደበላለቀው ነገር ለይ፡፡ ክርስቶስ የመሰረታትን ቤተክርስቲያን ሊገዳደራት እንጂ ሊያፈርሳት
የሚችል ማንም የለም እና አትጨነቅ፡፡ ጎርፍ ያልፋል እነጂ መች ባህር ይሰራል፡፡ አንተ ግን እንደቃሉ ሁን፡፡
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen