Dienstag, 1. April 2014

„አይመጣምን ትተሸ ይመጣል አስቢ“



„አይመጣምን ትተሸ ይመጣል አስቢ“

በኑሮ ውድነት የተነሳ ስራ በማቆም የደመወዝ ጭማሬ የሚጠይቅ  ሰላማዊ ሰልፍ እርግጥ ነው የአገሪቱን ኢኮኖሚ በእጅጉ ይፈታተናል፡፡ በዚህም የተነሳ በቶሎ መልስ ያገኝ ነበር፡፡ በአሁኑ ሰአት አለም በኢኮኖሚ ማእበል በተመታችበት ጊዜ፤ የስራ ማቆም አድማ ምን ያህል ይጉዋዝ ይሆን? የምናገረው ስለሀብታም አገሮች ነው፡፡ ዲሞክራሲ አስቸጋሪ አጣብቂኝ ውስጥ ሊገባ ይችል ይሆን? ሀብታም አገሮች እራህበተኛ በአገራቸው እንዳይኖር ማድረግ ቢችሉም፤ ከእንግዲሕ ይህ ዘላቂነት የሚኖረው የስራ አጥን ቁጥር በማጥፋት አልያም በመቀነስ ብቻ ነው፡፡ ግን አሁን በአለም ላይ ስራ የፈታ እየበዛ ከመሄዱም በላይ፤ ወደሀብታም አገሮች የሚጎርፈው የኢኮኖሚ ስደተኛም ሆነ የፖለቲካ ስደተኛ ይህ ነው አይባልም፡፡ አንድ አገር ምን ያህል ተጨማሪ እንደሚይዝ፤ ወይም መቼ ወሰኑን እንደሚዘጋ አይታወቅም፡፡ እስከዛው የተጨናነቀው ህዝብ በቦሌም ብሎ በባሌ ክተት ይዞአል፡፡ ይህ ከባድ የሆነ የዲሞክራሲ ፈተና ነው፡፡ አለም በአፋጣኝ የደሃ አገሮችን ስደተኛ ሁኔታ ነገሬ ብላ ካልያዘች እና መፍተሄ ካላገኘችለት አፍሪካ የጥቂት የደላቸው ሰዎች መኖሪያ ብቻ ሆና ልትቀር ትችላለች፡፡ መቼ ግን አይናቸውን ወደአፍሪካ አድርገው ፖለቲካሊም ሆነ የኢኮኖሚውን ሁኔታ መመልከት እንደሚችሉ አይታወቅም፡፡ ምንአልባት የእነሱ ዲሞክራሲ እያደር አደጋ ላይ ሲወድቅ ይሆን የአፍሪካን ፖለቲካ ጣልቃ የሚገቡበት ? ለማንኛውም የዩክራይን ለሁለት መሰንጠቅ እና የራሽያ ሁኔታ የምእራቡን አለም አይኑን እንዲከፍት ይህም አለ ለካ ብሎ እንዲመለከት ግድ ብሎታል፡፡  ሰው ኑሮውም እየተወደደበት ሲሄድእና አምባገነኖች እያስቸገሩት ሲሄዱ እጁን የሚዘረጋበት የፖለቲካ አለቃ አገር መፈለጉ አይቀርም፡፡ ምንአልባት ወደራሽያ ወይም ወደአሜሪካ፡፡ የቀዝቃዘው ጦርነት ሁኔታ ተረሳ ስንል እንደገና አለሁ ይለን ይሆን ?የአለም ነገር ድግግሞሽ ነውእና፡፡
ይህንን እንዳለ ልተወውእና፤ እስኪ ወደ አገሬ ላቅና፡፡

በኢትዮጲያ ስራ ያለው ትንሽ ስራ ከለለው የተሻለ ስለሚኖር፤ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ላይሞክረው ይችላል፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ በአፍሪካ የሚጠላበት ምክናያት ከተወሰኑ ሰዎች በላይ ማስተናግድ የሚችል ኢኮኖሚያዊ ብቃት ስለለለ ነው፡፡ ደመወዝ ጨምረኝ ብትል ከየት ይሰጥሀል፡፡ ካዝናው ሁልግዜ ባዶ ነው፡፡ ስራ ብትል ያለችውም ተይዛለች፡፡  ስለዚህ ፖለቲከኞች የሚመርጡት የተወሰኑ ሰዎችን  ይዞ ሌላውን ዝም በል እያሉ ጊዜ መግፋት ነው፡፡ ግን ጊዜ እስከመቼ ይገፋል? 20 አመት ቢበዛ እሱም እንደምንም ታለፈ ከዚያ ቢጨምር 20 ዓመት ነው፡፡ መጽሀፍ ቅዱስም 40 አመትን ይደጋግማታል እና እንጃ ነው፡፡ 40 አመት ተቀጡ ሲባልም እንሰማለን፡፡ ከዛስ በሁዋላ ያው የፈርኦን እጣ ፋንታ ነው፡፡ እኔ ብሆን በፖለቲካ ውስጥ መግባት ያለበት ትዳር ያለው እና ልጅ ያለው መሆን አለበት፡፡ ምንአልባት ይህ ለሚመጣው ትውልድ እንዲያገናዝቡ እና ደግሞም የሚያወርሱትን ባህሪ አደጋነት እና ጠቀሜታ ሊያስተውሉ ይችላሉ፡፡ አሁን ባለህበት ሁኔታ ሰላማዊ ሰልፍ ለምን ይጠቅማል የሚለውን፤ ማመዛዘን ጥሩ ነው፡፡  ያልጎደለበት የጎደለበትን የማያይበት ሁኔታ በኢትዮጲየችን ያሰራራበት ነው፡፤ በእምነትም ብንሄድ ከዚሕ የተሸለ አይደለም፡፡ አንዱ ከአንዱ አይሻልም፡፡ ሙስሊምም ውስጥ እስከአፍንጫው የሞላ ሀብት ያለው ሰው አለ፡፡ ደግሞም የተራበ ሙስሊም አለ፡፡ ክርስቲያንም ውስጥ እንደዛው ነው፡፡ ያውም በክርስቲያኑ ባይብስ፡፡ ወዳጆቼ ወሎን የማያውቅ ካለ እንግዲህ ይወቅ፡፡ ሙስሊም እና ክርስቲያን በአንድ ላይ ተፋቅሮ የሚኖር ነበር፡፡ ለሰርግ ጠላ እና ጠጅ ይጠምቁ ነበር ዛሬ ግን ትተዋል፡፡ „የዘፈን ዳርዳሩ እስክስታ ነው እንዲሉ“ እድራቸውንም መለየት ጀመሩ፡፡ እንግዲህ ይህ ኢሕአዴግ ሲገባ የተገኘው ድል ነው፡፡ ድሮም አንድ ላይ እንድንሆን ያስገደደንም የነበረ አይመስለኝም፡፡ ከሆነ ሙስሊም ወገኖቼ ሊነግሩኝ ሊያስረዱኝ ይችላሉ፡፡ እኔ ከወሎ ቤተሰብ ስወለድ ሙስሊም ዘመድ አዝማድ እንዳለኝ አውቃለሁ፡፡ እንዳውም ደጎች ናቸው፡፡ የዘመድ ሀቅ አለብን እያሉ ቤተዘመድን የሚጎበኙ ናቸው፡፡ የሆነ መለያየት እየጎላ ሲመጣ ደስተኛ አልነበርኩም፡፡ ከማሕበራዊ ሕይወት እምነት ይበልጥብናል ሁሉም ያለ ይመስላል፡፡ ያም ሆኖ ግን ያው እድሩንም ብሎ ክርስቲያኑ ባይሄድ የሞተ ያገሩን ሰው፤ ሙስሊም ዘመዱን ጎረቤቱን  ሊቀብር ይሄዳል፡፡ ሙስሊሙም እንዲሁ ወደ ቤተክርስቲያን ሄዶ ወዳጁን አፈር ያለብሳል፡፡ ወሎ እንዲህ ነው፡፡ እስከአሁን ድረስ፡፡ እድርም ቢለይ ሰው ግን በአንድ ሆኖ ይኖራል፡፡  ታዲያ ባይብስ ያልኩት፤ ወሎ ሙስሊሙ ዘወትር ሰደቃ እያለ ችግረኛውን በደንብ  ያበላል፡፡ በክርስቲያኑ አካባቢ ግን እንዲሕ አይነት ነገር ብዙም አይታም፡፡ እርግጥ ነው በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በራፍ እጅግ ብዙ ችግረኛ ቁጭ ብሎ የምእመናን እጅ ይጠብቃል፡፡ ሰውም ያለውን ይሰጣል፡፡ ግን የሚገርመኝ በፔንጤ  ቤተክርስቲያን እንዳውም አንድ የኔ ቢጤ አይገኝም፡፡ እንዳትደርስ የተባለ ይመስላል፡፡ አይገባኝም፡፡

እንግዲህ በዘር በለው በሀይማኖት በለው፤ በሁሉም ውስጥ የሚያለቅሱ ባል የለላቸው ሴቶች እና የቲሞች አሉ፡፡  የማይማሩ ልጆች አሉ፡፡ በትምህርት ቤት ውስጥ በድንገት እየጮሁ የሚወድቁ ወይም እራሳቸውን የሚስቱ እንዳሉ አይተናል ሰምተናል፡፡  ምግብ እጥረት የስኩዋርን መውረድ ያመጣል ሲሉ ሰምቻለሁ እና ጋኔል  ነው እንዳትሉኝ፡፡ በባዶ ሆዶ መማር የሚችል ምን ህል ነው ?   በኢትዮጲያ ጋኔል ስልጣን እንዳይኖረው እስላሙ በአላህአክበሩ፣ ኦርቶዶክሱ በቅዳሴውእና  ደግሞ ፔንጤው  በመዝሙሩ አሳዶታል፡፡ ግን አሁን አንተ ሁልህም ነሕ ሰይጣንን በሚጎትት ባልተለወጠ ባህሪ እየጎተትክ እያቀረብክ የምታስቸግረን፡፡ እረ ሀይማኖት ምን አግብቶት ፖለቲከኛን ወቃሽስ ከሳሽስ ይሆናል፡፡ ደጋፊስ ነቃፊስ ምን አገባችሁ፡፡ ዝም በሉእማ ገርማችሁኝ ነው፡፡ የመጣው የሄደው ሁሉ ሲነዳህ አሁን እምነት አለሕ አንተ፡፡ የትኛው ሀይማኖት ነው ያለፈ ታሪክን እየጎለጎለ የሚያወጣ፡፡ እኜ የማውቀው አማኝ የዛሬን ሲኖር እንጂ ፤ እንኩዋን ያለፈውን ለነገው እንድናስብ ተነግሮናል፡፡ በተለይ በማውቀው ክርስቲያን የሚለው“ እነሆ ሁሉም ነገር አልፎአል፤ በአዲስ ነገር ተተክቶአል ነው“፡፡ ልብ በሉ ጥሩም ሆነ መጥፎ አዲስ ነገር፤ አዲስ ምእራፍ ላይ ገብተናል፡፡ በሙጉት በጭቅጭቅ ሁልህም የተደረቀብህን ዘመን አስብ፡፡ ሙግት ግዜን የሚበላ ከመሆኑም በላይ መንፈሳዊ ማንነትን ያሸሻል፡፡ ጉቦ የሚከፈልበት ሄደህ ትከፍላለህ ደግሞም ትቀበላለህ፡፡ እንደገና የቀበሌ ሰራተኛ፣ የፍርድቤት ዳኛ ደግሞስ ፖሊስ ስታይ ታሸረግዳለህ ትሰግዳለሕ፡፡ ታዲያ አንተን ማን ይውቀስህ፡፡   መጀመሪያ ሁልህም መንግስት መንግስት ከምትል እስኪ እራስህን ከአምላክ ጋር ምህረትህን ጠይቅ፡፡ ንስሃ ግባ፡፡ ስንቱ ነው በሀሰት ምስክር ተከርቸም የገባ፡፡ ማንኛው የሀይማኖት መሪ ነው ይህን እንዲያደርጉ፤ ሰውን እንዲፈሩ ያስተማረ፡፡ እስኪ ሁሉም ጥሩ የሚሰራበት አንድ ሀይማኖት ንገሩኝ፡፡   ጉድ አይቻለሁ በአይኔ፡፡ አሉባልታ ቀልድ ፌዝ፤ እስኪ ንገሩኝ የትኛው እምነት ፊዝ፣ ውሸት ብሎም አድርባይነት የሚያስተምር፡፡ መስካሪው፣ ችላባዩ እና አወናብዶ የሚበላው እውን በአንዳችሁም ሀይማኖት ውስጥ  የለም? ስለዚህ በሰይጣንም አታመሀኙ፡፡ እንዳውም፤  ደሞ ምን አድርግ ነው የሚሉኝ ማለቱ አይቀሬ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ስም የሚጠራበት ቦታ ሁሉ ሰይጣን ድርስ አይልም ወዳጄ፡፡ ስንጠራው ግን ከቸች ለማለት በር ላይ ነው፡፡ እሱ የሚኖርበት አለም ላይ ነው ያለነው፡፡ ምክናያት እያስፈለገ የሚያናክሰው፡፡   አንደበትህን መርምር ወዳጀ፡፡ እንዳመጣልህ ተናግረህ ሆታ ከምታበዛ ዝም በማለት የእግዚአብሄርን ድምጽ ትሰማለህ፡፡  ለማንኛውም ሰው ኑሮውን ባዬ ቁጥር መንግስትን ማማረሩ አይቀሬ ነው፡፡ ምሬቱ ይብሳል እንጂ ጋብ እንደማይል ማወቅ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ደግሞ ተስፋ የሚቆርጥ ሰው አማኝን የሚሰራውን የሚመለከት ነውና ፤ጠንቀቅ ወዳጄ፡፡  አሁን ግን የምጠይቃችሁ፤ ኢትዮጲያ በዚህ ከቀጠለች  ሪቮሊሽን ሊመጣ ይችል ይሆን ? ኮሚኒስት እያቆጠቆጠ ነውእና ሌላው ክፍል ደግሞ አይኑን በኢትዮጲያ ላይ ከፈት ቢያደርግ መልካም ነው፡፡ እኔ ተናግሬአለሁ፡፡ በሁዋላ እነአሜሪካ እነጀርመን አልሰማንም እንዳይሉኝ፡፡ ወይ ይህን ያለውን መንግስት ደግፈው ህዝቡ የሚፈልገውን ያድርጉለት ካልሆነ ደግሞ ተቃዋሚን ደግፈው ያሰናብቱልት፡፡ ኮሚኒስቱ እንዳይቀድም ብዬ ነው፡፡ እንዳው ለምዶብኝ ነው የምጽፈው ?  ወይ ቁም ነገር፡፡ አይ ባዩሽ በይ በርቺ፡፡ሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀ. በቸር
ባዩሽ   

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen