ለኢትዮጲያውያኖች ፤
የአንድ ለአምስት መሰረቱ
ሰው ያሰበውን እና የተለማመደውን በመጻፍ ወይም በመናገር ማካፈል እጅግ በጣም የሚከብድበት አገር ኢትዮጲያ ተወልጄ አድጌአለሁ፡፡ አገሬ ኢትዮጲያ ላይ በተለያየው አጋጣሚዎቼእና በደረሱብኝ ኢሰብአዊ ነገሮችም ሆነ በእራሴው ደግሞ እጅ ያለመስጠት ሁኔታ ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ በምእራቡ አለም ላይ በስደት እገኛለሁ፡፡ ይሁንና ግን በተለያየ ግዜ ኢትዮጲያ ለመኖር ወደኢትዮጲያ እየሄድኩ ሞክሬአለሁ፡፡ በማንኛውም ምእራብ አለም አሜሪካ፣ ጀርመን፣ አውስትራሊያ እና ካናዳ በተጉዋዝኩባቸው ሁሉ መልካም የሆኑ ፈረንጆች አጋጥመውኛል፡፡ ግን የአገሬ ናፍቆት አይሎ ስለነበርእና በአገሬም ደርሰውብኝ የነበሩ እጅግ አሳዛኝ ተግባሮች በሕይወቴ ላይ ሚዛኔን ጠብቄ እንዳልሄድ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሁኔታ ጥለውብኝ ስለነበር ፈረንጆች ያቀረቡልኝን እድል ሳልጠቀምበት አልፎአል፡፡ ይሁንና ግን ዛሬም በተለያየው ውጣ ውረድ ሕይወቴ የጀርመን ጉዋደኞቼ ጣልቃ እየገቡ የሚያደርጉልኝ የስነልቦና ድጋፍ ልረሳው የማልችለው ፍጹም የሆነ ሰብአዊነትን በእነሱ ውስጥ እንድማረውም እረድቶኛል፡፡ ይገርማል አገሬ ወገኔ ያልኩት ሰባብሮ ጥሎኝ፤ ሌላው እንደጠላት ሳየው የነበረው ፈረንጅ ሲገነባኝ፡፡ የሕይወቴ ገጠመኞሽ አዳጋች ተራራ ያስተማረኝ ዘረኝነት ዝምብሎ በጭፍን የምናስበው አስተሳሰብ እንጂ፤ ማንኛውም ዘር ለሰው አስፈላጊ እንደሆነ ነው፡፡ ወደ ቁም ነገሩ ልመለስ እና፤
የተወደዳችሁ ኢትዮጲያውያኖች፤
እኔ ችግር ደርሶብኝ የነበረው በአገሬ በወንዜ እና በዘሬ ሰዎች ነው፡፡ እኔ የማውቀው በእኔ ዙሪያ የተሸከረከሩትን
ጉዋደኛ ብዬ ዘመድ ብዬ እና በስራዬም አካባቢ ያሉትን ስለሆነ የኢትዮጲያን ሕዝብ እንዲሕ ነው ባዬ ለመወንጀል
ይከብደኛል፡፡ ምንም እንኩዋን በጣም ከባድ እና ሊረሱ የማይችሉ ግን
ተለማምጄ መኖር እንዳለብኝ የተረዳሁት ችግር ቢኖርም በጣም ክፉ፣ በጣም በዳይ፣ አስለቃሽ እና አሳዛኝ ነገር የሚፈጸመው ሰው በቀረበው
ወዳጁ በሚለው እንደሆነ እንድትረዱት እፈልጋለሁ፡፡ ይህ ሁኔታ ስመለከተው ግን „ጠላት ከእሩቅ አይመጣም“ የሚባለውን እውነት መሆኑን
አረጋግጫለሑ፡፡ ይረዳኝል ትረዳኛለች ብለህ የተጠጋህው ሰው ጭራሽ የአንተን ችግር የእሱ ሞራል ማጠናከሪያ አድርጎት አንተን በማሳነስ
ሲኮፈስ ታየዋለሕ፡፡ ተላላኪ ሊያደርግህም ይፈልጋል፡፡ የአንዳንዶችን ከንቱነትም የተረዳሁት ቤተክርስቲያን ይሂዱ እንጂ፤ ዘመድ አስቀየመኝ
ብለሕ ለአንዱዋ ብትነግራት፤ የእሱዋን ዘመድ ወርቃማነት ነግራ ልታስቀና ትፈልጋለች፡፡ ያጋጠሙኝን ነው የምነግራችሁ፡፡ ቀሚስ የለኝም
ብትል የእሱዋን ቀሚስ አውጥታ ውድነቱን ልትናገር ትፈልጋለች፡፡ አንድ ባለስልጣን እኮ በደለኝ ብትል እሱዋ አፈጉባኤውን ወይም የውጭ
ጉዳይ ሚኒስተሩን እንደምታውቀው ትነግርሀለች፡፡ እጅግ ያሳዝናል፡፡ የደሃ ዘር ነኝ ብትል እሱዋ የሞተውን የደጃዝማች ዘርነቱዋን
ትነግርሃለች፡፡ እከሌ እኮ እንዲህ በደለኝ ብለህ ለመንፈሳዊ አባት ብታማክር ፤ እንዴ እሱ እኮ ለቤተክርስቲያን ይህን እያደረገ
ነው ወይም ይህን እያደረገች ነው እና የማይታመን ነገር ነው ብለው ከእነገብሬል አብልጠዋቸው በቄሱ እንኩዋን እንደወሬኛ እና እንደማረባ
ሆነህ ትገለላለህ፡፡ ደግሞም ማሀበራዊ ህይወቱ ወርቅ ነው እየተባለ ዲያቆናቱም ሲመሰክርለት እየሰማህ፤ ተበዳይ ወሬኛ ሀሰተኛ ሆኖ
ምንም አይነት መረዳት ባለማግኘት እንዲቆዘም ይደረጋል፡፡ እንዳውም ይረዳኛል ብለሕ ያጫወትከው ሰው በትልቁ ደግሞ የአንተው ስም
አጥፊ ሆኖ ይቀራል፡፡ ወዳጆቼ „ የወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል“ ለኢትዮጲያ ባህል ትልቅ አባባል ነው፡፡ እንግዲህ እንደኔ ከሆነ
አይምሮ ባልተለወጠበት አካባቢ በውነት ችግርን መናገር ማለት ወረቀትን ፎቶ ኮፒ ማሽን ላይ ማድረግ ነው፡፡ ይበዛል ይበዛል ይበዛል፡፡
ፎቶ ኮፒ ቀለሙ ሲያበቃ ወይ መብራት ሲጠፋ ነው የሚቆመው፡፡ ሰውም እስካልሞተ ድረስ በስቃይ አለንጋ አንዱ ገራፊ ሌላው ተገራፊ
ሆኖ ይኖራል፡፡
ይህ ሊመራችሁ ይገባል፡፡ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ግን እየባሰበት የሚሄድ እንጂ እየተሸለ የሚሄድ አይደለም፡፡
አገራችንም ይህን ተረድታ አይምሮን የሚቀይር ነገር መስራት አልቻለችም፡፡ እንዳውም የተበላሸውን ባህሪ የፖለቲካ ፍጆታ ቀለብ እየሆነ
የሚደሰትበትም አይጠፋም፡፡ በፖለቲካም የተጠላው
ሰው እንዲሁ አንድ ፖለቲከኛን እስከሚሰባበር እስከሚወድቅ እስከሚሸማቀቅ ጤናውም እስከሚታወክ ነግ በእኔ ሳይሉ የስነልቦኛ ጦርነት
ያካሂዱበታል፡፡ ወድእነሱ ወደአሰቡት አላማ ለማምጣት በጭራሽ የለም፡፡ ይሙት በቃ ፍራጃ፡፡ የተሳሳተ የሚማር አይመስላቸውም፡፡ ፖለቲካ እንደእምነት
መጽሀፍ የሚታይበት አገር ኢትዮጲያ፡፡ ኢትዮጲያን የምንወዳት አንዳንዶቻችን ጥሩ ልምድ ወይም የተሻለች አገር ሆና ሳይሆን ግን እኛም
አገራችን ስለሆነች እና የተሰጠችን ምድር ስለሆነች ነው፡፡ ሰው ግን ደግሞ በአይምሮው የተቀረጸው እና የተገነባበት ሆኖ እንጂ ምድር
ሁሉ ለሰው የተሰጠች ነበር፡፡ ግን ሰው በተሞላው ይኖራል እና አገሬ የሚል አባዜ ተተናውጦናል፡፡ አገሬ እላለሁ ዘሬ ለማለት ግን
እኔም ሰው ነኝ እና ዘሬም ያልሆኑ ችግሬን ተጋርተዋል እና በሁሉም የሰው ዘር አምናለሁ፡፡ መልካምነት የሚፈልቀው ከዘር ሳይሆን
ሰብአዊነትን ከመረዳት ነው፡፡ እንዲህም ስላችሁ ከጀርመን አገር ክፉ ነጭ የለም ማለቴ አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ ደግሞ አንዲት
ከኤርትራዊ እና ከትግራይ ጋብቻ የተወለደች ሴት በሕይወቴ ላይ ትልቅ የሆነ ስራ ሰርታለች፡፡ ማንም ባልደረሰብኝ አጋጣሚ በውድቅት
ለሊት ተገኝታ ነፍሴን ታድጋኛላች፡፡ ወደ 17 የሚሆኑ ወንዶች ከበውኝ ነበር፡፡ ግን ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በመገኘት እነዛን ወንዶች
አንድ ቃል ተናገረች፡፡ „ ለአንዴት ሴት 17 ወንድ ለማስደንገጥም ለመግደልም ከተገኜ በውነት ይህቺ ሴት ጀግና ናት ማለት ነው፡፡
ባትሆንስ ምነው አንድ ወንድ ብቻ በበቃት“ ፡፡ የሚገርመው በእኔ ዘር ግንድ ያልሆኑ፣ የዘር ጥላቻ ፖለቲካ የነዳቸው የዋሆች፣ አርቀው
ማስተዋል የተሳናቸው፣ የረዳሁዋቸው ሁለት ሰዎች አስራ አምስት አጋር ጨምረው ነበር ሊያጠቁኝ የመጡት፡፡ አዲስአበባ ላይ ይህ ብልሹ
ነገር የተፈጠረው የዘር ፖለቲካን የሚያራምዱ የሚነዙት ዝሪት ነው፡፡ እርግጥ ነው ፌድራል ፖሊስ በፍጥነት ባይደርሱልኝ ኖሮ ዛሬ
በህይወት ባልተገኘሁም ነበር፡፡ የከተማው ፖሊስ እማ ፌደራል እጅ ከፍንጅ ይዞ የሰጠውን ወደፍርድቤት ሳያቀርባቸው ቀርቶአል፡፡ እግዚአባሄር
ግን አፋጣኝ ፍረድ የሰጠበትን ሁኔታ ለመመልከት ችያለሁ፡፡ ይሁንና ኢትዮጲያ እንዲሕ እንደፓራዲስ የምታየው ገነት አይደለም ወዳጀ፡፡
ግን ሊለወጥ የሚገባው ነገር እንዳለ መረዳቱ እና ማተኮሩ የሚገባ ነው፡፡ ወገኖቼ ካለትዳር ላለች ሴት ኢትዮጲያ ሲኦልም ይሆናል፡፡
ተቀበሉት፡፡ እንዲህ ሰው የሚናገረው ካየው እና ከተለማመደው ነው፡፡ በዚህ ባልተለወጠ ነገር ላይ የህግ የበላይነት ጠቃሚ ቢሆንም
ግን ምንያህሉ ወደዛ መስመር ሄድዋል የሚለው አስቸጋሪ ነው፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ግን የግሩፕ ወገንተኝነት ከጥንት ጀምሮ ባንሰራራበት
አገር የተወሰነ ሰው ላይ እያተኮሩ መሰባበር ያለ እና የተለመደ ነው፡፡ አንድ ግዜ ኢሕአዴግ አንድ ለአምስት እያደራጀ ነው የሚል
ነገር ፌስቡክ ላይ አይቼ ነበር፡፡ እና ተንሽ አሳቀኝ፡፡ ሰው በግሩፕ ከኢህአዴግም በፊት የሚኖር መሆኑን እናውቃለን፡፡ ስለዚህ
አንድ ለ20 ቢያደርገው ከባሃሉ ውጭ ሊሆንበት ይችላል፡፡ ብዬ አሳቀኝ፡፡ ቁም ነገሩ ሰው ግሩፕ መስራቱ ሳይሆን ግሩፕን ብዙው የሚጠቀምበት
ሌላውን ለመሰባበር መሆኑ ነው፡፡ እንግዲሕ ኢትዮጲያ ለእኔ ፓራዲስ ባትሆንም ግን አገሬ ናት፡፡ እንጂ የለለውን ነገር አለ ብል
የማበራክተው ውሸትን ነው፡፡ ዛሬ እኔ የምታገለው አገሬ ኢትዮጲያ ህዝቦችዋ የአስተሳሰብ ለውጥ አምጥተን ሰብአዊነትን እንድንገነባ
ነው፡፡ ይህ ከሆነ የሚያለቅሰውን ቁጥር ልንቀንሰው እንችላላን፡፡
ጉራ እና ትእቢትህን ለተቸገረው ብታሳየው አይረዳውም፤ መረዳት ያለብህ ግን ባትሰጠውም እቅፍ አድርገህ ልክ ሌላው አለም እንደሚያደርገው
ጀርባውን መታ መታ አድርገህ አይዞሕ ወዳጀ ያልፋል ብለሕ አጽናኝ ቃል ስትነግረው ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ውስጥ መግባት ማለት ክርስቲያን
ሆነ ማለት አመኑዋል ማለት አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ አጽናኝ እንጂ መረበሽን የሚፈጥር አይደለም፡፡ ወገን ማለት ደግሞ የደሙ መቀራረብ
ሳይሆን የምትረዳዳው ነው፡፡ እዚህ ግን የሰው ባህሪው በቤተክርስቲያ ስጦታ በመስጠቱ የሚወሰንለት ከሆነ እና ደግሞም ባፈራው አጃቢ
ከሆነ እንግዲህ ያልሰጠው ካለመስካሪ የሚኖርበት አለም ማለት ነው ኢትዮጲያ፡፡ ስለዚህ የማግኘት ወሳኝነት የሰውን ባሕሪ የሚወስነው
ከሆነ ሰው ከፍቅር ይልቅ ለገንዘብ ላይ ቢሮጥ ስህተት አይደለም ማለት
ነው፡፡ ሕመምተኛ የማይፈለግ ከሆነ ደግሞ ሰው ጠንቁዋይ ፍለጋ ቢሮጥ ስህተት አይደለም ማለት ነው፡፡ ሰው ዘመድ እና ወገን ከለለው
የማይፈለግ ከሆነ እግዚአብሄርን ትቶ ለሹማምንቱ ቢያጎበድድ ምንም ሐጢያት የለውም ማለት ነው፡፡ ሴት አጠገቡዋ ወንድ ከለለ የምትደፈርእና
የምትዘረፍ ከሆነ ብዙ ባል ቢኖራት ሀጢያትነት የለውም ማለት ነው፡፡ ሴት ፖሊስ የማይደርስላት ከሆነ ጡንቻው የፈረጠመ ሀይለኛ ወንድ
እንድትፈልግ ትገደዳለች ማለት ነው፡፡ ይህ እንደባህል ስር የጠመጠመ ነገር የባህሪ ለውጥ ካላመጣ አበበ መጣ አሰፋ መርገም መብላት
ነው፡፡ በቸር ልበላችሁ መሰል፡፡,
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen