እኔን ያስገለለው አባቴን የገደለው የወያኔው ጥይት
ጀርምን አገር ልቤ ጭንቅ ጭንቅ አለ፡ ደርግም አልወርድ አለ፡፡ እኔም አገሬ ናፈቀኝ፤ እህት ወንድም እናት አባት፡፡ በተለይ አባቴ „እማኘነሽ“ እያለ የሚጠራኝ፡፡ እኔ ብሎ እማኝ እቴ፡፡ በቃ ስወለድ ጀምሬ እስከእለት ግንቦት 10
ወያኔ ግቢያችንን እስከተቆጣጠረበት
ድረስ እና አባቴን በዚሁ ግንቦት 10
እስከገደሉበት ድረስ „እማኘነሽ“ ነበር እያለ የሚጠራኝ፡፡ እኔ ብሎ እማኝ እቴ፡፡ ጉድ እኮ ነው፡፡ የስደቱን አለም ናቅኩት፡፡ ከዛሬ ነገ ደርግ ይወርዳል ብዬ ስጠባበቅ የነበርኩት ባለመቻሌ ጨርሸ እንዳልቀውስ እና አይምሮ የሳተ ሰው እንዳልሆን ናፍቆቴን ልወጣ ኢትዮጲያ ዘው ብዬ ገባሁ፡፡ አካሄዴ ግን አንድ ወር ቆይቼ ለመመለስ ነበር፡፡ ይዞኝ የገባውን ፈረንጅ አዋክበው ወዲያው እንዲመለስ ሲያደርጉት እኔን ግን የደርግ መንግስት የኢትዮጲያ ፓስፖርቴን ቀምቶ እዛው አስቀረኝ፡፡ መውጣት አልቻልኩም፡፡ ሶስት ወር ከደህንነት ቢሮ ጀኔራል ተስፋዬን ደጅ ጠንቼ ለአንዲት ቀን ለ10 ደቂቃ አገኘሁት፡፡
እሱም ከኢትዮጲያ መውጣት ከእንግዲሕ አይፈቀድልሽም
አለኝ፡፡ ግን ለካስ ሁሉም በእግዚአብሄር
እጅ ሆኖ ከአንዱ ሁለት አመት በሁዋላ ደርግም ወረደ ወያኔም ገባ፡፡ ተፋጠነ፡፡ በዚሕም የተነሳ ደሴ ግንቦት 10
አባቴ ባጠገብ ቁጭ ብዬ የወያኔን ገባሁ ምለክት እንደፈንድሻ የሚንጣጣውን
ጥይት ከሩቅ እየሰማን፤ ድንገት የከባድ መሳሪያ ጩሐት የሰማን መሰለኝ፡፡ ወዲያውም ቤተሰቦቼ ተሰባስበው ወደቤት ሲገቡ እኔ ግን ከግቢ ወጥቸ ሄድኩ፡፡ ብቻ የጥይቱ ጫጫታ የሰው መተረማመስ ግራ ገባኝ፡፡ እንዲሕ በቶሎ ሁሉም የሚፋጠን መሆኑን ማን ያውቃል፡፡ ትንሽ ጋብ ሲል መለስ ብል እግቢያችን ዋይታ ጠበቀኝ፡፡ አባቴ ከቤተሰቤ ሁሉ ለየት ባለ መልኩ የሚያጽናናኝ፡፡ በወቅቱ እንደተስፋ አይቸው የነበረው፤ በጥይት ተመቶ ሞቶአል ላካ፡፡
እንግዲሕ ተባራሪም ጥይት አልመታው፡፡
መላው ቤተሰቡ አንድ ከተባራሪው ጥይት ይከላከልልናል አሉት የምድር ቤት ተብሎ በሚጠራው ክፍል ውስጥ ተሰባስበዋል፡፡ አባቴ የጸሎት መጽሃፍ ይዞአል አሉ፡፡ ቁጭ ብሎ ያንን እያነበበ እያለ የጥይት ውርጅብኝ አሉበት ክፍል በር ላይ አወረዱበት እያሉ ሲወራ ሰማሁ፡፡ በጣምም የእንጨቱ በር እንደወንፊት ተበሳስቶአል፡፡
ምን ኢንፎርሜሽን እንደተባሉ የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ የጦር ካምፕ ይመስል ከበውት ነበር አሉ፡፡ እንግዲሕ ሁሉም በመሬት ላይ ተደፍተዋል፡፡
ከጥይቱ ለመዳን፡፡ ከዛ ሁሉ ጥይት ግን አንዲት ጥይት አባቴን አግኝታ ገደለችው፡፡
እናቴም ደንግጣእና እራሱዋን ስታ ወደተኩሱ ወጣች፡፡ „አንድ ሽማግሌ ገላችሁዋል እና ተኩሱን አቁሙ እኛም እሬሳችንን እናንሳ“፡፡ እያለች በዋይታ ግቢውን አቀለጠችው፡፡ እነሱም ገብተው ሬሳውን አዩ፡፡ ሙሉ ትጥቅ የታጠቀ እና አዛዥ የመሰለውም ወታደርም በትግረኛ ሌላውን „ዋ አንተ ገብረእግዚአብሄር“ በማለት የሚለውን ብሎ ስሙን ጠርቶ ተኩሱን አስቆመ“ ሰውየውም በድርጊቱ እና በተደረገው ስህተት ማዘናቸውን ገልጠው ወደሚቀጥለው
አገር ማየዝ አመሩ፡፡ ቤተሰብም የእኔን ወደኢትዮጲያ መመለስ እንደመጥፎ እድል ቆጠሩብኝ፡፡ ጥርጣሬም በውስጣቸው ሰፈረ፡፡ግልጥ
ከልጅነት ጀምሮ የምትናገረውን ባዩሽን ፍለጋ የመጡም መሰላቸው፡፡
ደግሞም እየቆዩም ለሞቱም ምክናያት እኔን በማድረግ በአይምሮአቸው
ገነቡ፡፡ በመካከሉ በመገለል እና በስቃይ አሳለፍኩ፡፡ የናፈኩትን አባቴ ወቅት እና ግዜ ደግሞም አጋጣሚዎች ነጠቁኝ፡፡ ፍቅሬን ላሳይ ናፍቆቴን ልወጣ ቀርቶ በዘፈቀደ በተተኮሰች ጥይት የተነሳ እኔም ተገለልኩ፡፡
አንድ ቤት ላይ ተነጣጥሮ የተደረገው ተኩስ ግን ምንነቱን ሳይገባኝ እንቆቅልሽ ሆኖ ቀርቶአል፡፡
በደርግ ባመጣው ለውጥ እና የክልሉ የአየር መዛባት ያመጣው መከራ ወሎ እጅግ የተዳከመ የኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ ነበር፡፡ የ84 አመትን ሽማግሌ ግን ደርግ ወርዶ ወያኔ ይገለዋል የሚል ግምትም አልነበረም፡፡
ግን አንድ ነገር አለ፡፡ አባቴ ጥሩ ሰው እና በሰፈርም የተወደደ አደበተ እርቱኡ ነበር፡፡ በዛን ወቅት ቤተሰቡን በሱ ጸሎት ሸፍኖ አስጥሎአል፡፡ እሱን ግን አሳልፎ ሰጥቶአል፡፡ ይህ ባይሆን እንዳወረዱባቸው
የጥይት ጋጋታ ሁሉም ባለቁ ነበር፡፡ ወይም አንድ ከልጅ ልጆቹ ውስጥ እናም ከልጆቹ ውስጥ በገደለ ነበር፡፡ ይህ አልሆነም፡፡
እግዚአብሄርም ባለእድሜ ይቅደም የተባለ ይመስል አዛውንቱን ቀድሞ ወሰደ፡፡እርግጠኛ ነኝ፤ ያቺ አባቴን የገደለች እኔን ያስገለለች መናጢ ጥይት ሌላ ከመካከላቸው ገላ በነበርእና አባቴ በሕይወት ቢኖር ኖሮ እጅግ በጣም ልቡ ይሰበር እና አዝኖ ይሞት ነበር፡፡ ግን ከልጆቹ መሃል እና ከልጅ ልጆቹ መሃል እነሱን በጸሎቱ እየተከላከለላቸው እለተ ግንቦት 10 ወያኔ የወሎን ድል በተቀዳጀበት ቀን ይህችን አለም ተለይቶአል፡፡ ቤተሰቦቼንም
ያንን ጥይት የበሳሳውን በር እንዲያስቀምጡት
እንደፈረንጆቹ ባህል ጥረት አድርጌ ነበር፡፡ ግን የነበረብኝ መገለል እጅግ በጣም ከባድ ስለነበር የሚያዳምጠኝ
አንድም ሰው አልነበረም፡፡
ለዚህም ድርጊት ከአስተዳደሩ
የተሰጠ ይቅርታም አልነበረም፡፡
እንደነገሩስ ካሳም በከፈሉ ነበር፡፡ ተባራሪ ጥይት አልመታውም እና፡፡ መቼም ኢሕአዴግ ሲገባ የሰፈር አውደልዳይ ሁሉ አጅቦ አመልካች ጣቱን ይቀስር ነበር፡፡ ሆድ ጦሙን አያድርምእና፡፡ ግን ምን ብለው ዋሽተዋቸው ይሆን????????
እውነት የእኔ ከኢሮፕ ተመልሶ እዛ ሰፈር መገኘት እትልቆቹ ጉራ አሰልፈውኝ ይሆን? ያም ሆነ ይህ አዎ ግንቦት 10 በትግረኛ ተናጋሪ ወታደር እጅ አባቴ ተገሎአል፡፡ አንዳንዶች ዲሞክራቲክ የሆነ ሀሳቤን ስሰነዝር እርቅና ሰላምን ስናገር „ወያኔ ነሽ ወይስ ባንዳ ይሉኛል፡፡“
ተቃራኒው ደግሞ „ስልጣናችሁን
ልታስመልሱ ነው እናንተ አማሮች አታገኙዋትም“
ይሉኛል፡፡ ግን ሁለቱም ቅም አይለኝም፡፡ እራሱ አባቴን የገደለው ገብረእግዚአብሄር ቢመጣ ጥያቄዬ ንስሀ ገባህ ወይ ብዬ ነው እንጂ የምጠይቀው ይሙት ብዬ አላስፈርድበትም፡፡ ከሳሹም ሌላ ፈራጁም ሌላ ነውእና፡፡ ሰውስ ልክሰስ ቢል ምን አቅም አለውእና፡፡
በሰው እጅ የተደበቀንም
ነገር የሚያውቀው እሱው ፈጣሪ ነው፡፡ ተበቃይ እንዳልሆን ከአባቴ ብዙ ትምህርት ወስጃለሑ፡፡
እሬሳውን ሊያረጋግጡ ሲገቡም፤ በእጁ ያገኙት የጸሎት መጽሀፍ እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡ ወገኖች ሁላችንም እናልፋለን፡፡
ይቅር ይምንለው ለእምነታችን
እንጂ ጠላትን ስለወደድነው
እና ስለተመቸን አይደለም፡፡
በደረሰብኝ መገለል እንድታዘብ ያደረገኝ በይምሰል የሚፈረድ ፍርድ ሰውን ከመግደል ያለፈ ከባድ ወንጀል ነው፡፡ „አትፍረድ“ ወዶ አልደነገጋትም እና፡፡ እንግዲሕ የእማኘ ነሽ አባት ከእማኘነሽ የተለየው በዚሕ መንገድ ነው፡፡ አዎ ጠብቀህ ጠብቀህ ይቅርታም የሚልሕ አታገኝም፡፡ አንተም ለእግዚአብሄር ትተወዋለሕ፡፡
ካለሰው በተፈረደብኝ ፍርድ ሁሉ እንድኖር ያደረገኝ አዎ እየሱስ ጌታ ነው፡፡ ለእሱ እውነቱእና ሀሰቱ ግልጽ ነውእና፡፡
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen