„ኢትዮጲያ“ የአለም ሸቀጥ ማራገፊያ የሆነችበት ዘመን
ኢንዱስትሪ አየርን የሚበክልበት ነገሮች ቢኖርም፤ ቁጥሩ እየበዛ ስራ አጡ በሽ ላለባት ኢትዮጲያ ኢንዱስትሩ ወሳኝነት ነበረው፡፡ ይሁንእና ግን አመርቂ የሆነ ኢንቬስተር ሊገኝ አልቻለም፡፡ አልያም ሊፈቀድለት አልቻለም፡፡ ወይም ደግሞ ኢንቬስተር ሞኝ አይደለም የፖለቲካ ተቃዋሚ በለለበት አገር ንዋዩን እና እውቀቱን የሚያፈስ፡፡ በአምባገነን አገዛዝ እጅ የወደቀች አገር ነገ የሚገጥማትን ያውቃል እና፡፡ ኢንቬስተር ሳያጠና ሳያስጠና ምን ጥልቅ አድርጎት፡፡ ኢትዮጲያ የሚያስፈልጋት በእጃቸው የተጨበጠ ነገር ያላቸውን እንጂ ባንክን እየተበደሩ ኢንቬስት የሚያደርጉ ደሃዎችን ቢቀርባት በተሸለ ነበር፡፡ እነዚህ ለሚፈናቀሉት ሰዎች ወሮታ ወይም ካሳ ለመክፈል አይችሉም እና፡፡ መሬት ሊያገኙ የሚሮጡ ኢንቬስተሮች ሳይሆን አትርፈው ትርፋማ ነገር ለአገሪቱ ህዝብ የሚተው መሆን አለባቸው፡፡
ዛሬ በቢሊዬን አካብተው ምን እንሰራ የሚሉ ኢንቬስተሮች የተትረፈረፈበት ዓለም እንደሆነ ዘወትር ይነገራል፡፡ አለም የገንዘብ እጦት ሳይሆን የመረጋጋት ችግር ይታይባታል እና፡፡ እኒህን ባለሀብቶች
ለመሳብ የሚያስፈልገው፤ ኢትዮጲያን አመርቂ በሆነ በዲሞክራሲ ሜካፕ በማስዋብ እንጂ፤ ተፈጥሮሽ ብቻ ይበቃል በማለት አይደለም፡፡ በተፈጥሮዋ አለም መኖሩዋ ከቀረ ውሎ አድርዋል፡፡ ዛሬ ጥያቄው ሌላ ሌላ ቸኮል ቸኮል ያለ ነገር ሆኖአል፡፡
የኢሕአዴግ
ጠባዩ ግን መንግስትን እንቅ አድርጎ ይዞ ማን እዛች አገር ድርስ ይበል፡፡ ባለሀብቱም እኔው ኢንቬስተሩም እኔው በማለት ሲፍጨረጨር ይታያል፡፡ ይህ እንኩዋን ለደሃ አገር ለሀብታም አገሮችም አልጠቀመም፡፡ በዘር የተደራጀ
ፖለቲካ ያለበት አገር ፤ ባለነዋዩም ነገ እሱን እንደማይነካው ምን ዋስትና አለው፡፡ ኢትዮጲያ ድንግል መሬት ተብላ በእግዚአብሄር እጅ አደራ የተሰጠች ይመስል፤ እራሱዋን የጠበቀች ልጅአገረድ ዋጋ እንዳታወጣ መደረጉ ምን አይነት አባት ቢኖራት ነው ለማለት ያስደፍራል፡፡ እሙ ኢትዮጲያ የሸቀጥ ማራገፊያ ሆነሽ መቅረትሽ ነው የሚያሳዝነው፡፡ ለዛውም አየር በካይ በሆነ በፕላስቲክ ነገር፡፡ ትርፍሽ ተፈጥሮሽን በቆሻሻ ማበላሸት አየርሽን መበከል እንዳየሆን ፍሪልኝ፡፡ በእራሳችን በተጠቀምንበት ኢንዱስትሪ ሳይሆን ሌሎች ባተረፉበት እኛ አገራችንን እየበከልናት እንገኛለን፡፡
ኢትዮጲያን የተወሰኑ ሰዎች የሚያሽከረክሩዋት፤ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች አክብረው ይነሳሉ፡፡ የማንክደው የምናየው ሀቅ እየሆነ ሄድዋል፡፡ አምባገነን ታዲያ ሌላ ትርፍ ምን አለ፡፡ የሚደግፈውን የቁሳቁስ ከበርቴ ብቻ አማሎ እና ህዝብን ጉም አስጨብጦ አሰቅቆ አስፈርቶ እንደጅረት ውሃ ገዢ ፓርቲ ምንግዜም ያልፋል፡፡ እንኩዋን ሳትወደድ ብትወደድም፡፡ ሁሉም አላፊ ነው፡፡ የእግዚአብሄርም ጣት ትገለጣለች እና፡፡ መኪናው መንገድ
ተሰራ፤ ለታደሉት ባለእንዱስትሪ አገሮች እቃቸውን እንደልብ በአገራችን በረጅሙ ትሬንታ ኩዋትሮ/ባልሽንጣሙ ተሳቢ/ ቶቶሎ ብሎ እንዲያስገባ፡፡ እንዲያከፋፍል፡፡ አዎ ኢሕአዴግ ነፍሴም፤ ይህ ነውእንጂ መንግስት የሚባል ተባለ፡፡ ሸቀጥ አቅርቦ እህዝቡ አይን ላይ እነደኮኮብ እያበራ፡፡ የትኛው ኢንቬስተር ኢትዮጲያ ውስጥ የፈበረከውን እቃ ለኢትዮጲያ ህዝብ እያዞረ ሊሸጥበት ነው ታዲያ፡፡ ሁሉ ሕዝብ ፍሪጅ እና ቴሌቪዠን መሰል ነገር፤ ይፈልጋል፡፡ አዎ ሰልጥኖአል፡፡ ስልጣኔ ይህን ካልነው፡፡ ሰማይም ገብቶ ምድር ሊገዛ ሰፍ ብሎ እየገዛ ነው ያለው፡፡ ዛሬ ከሚበላ ቁስቁስ ከማን አንሶ ሆኖአል እና፡፡ ሰው ማየት አለበት፡፡ ገመናን ደብቆ ሰው መምሰል ነው ይባላል፡፡ ግን ሁሉም ከእኛ ፋብሪካ አይገዛም፤ ከባህር ማዶ ከመጣለት ኢንቬስትሜንት ካነሳቸው አገሮች ከነቻይና ወይም ከሌላ ነው፡፡ ኢትዮጲያ ትልቁዋ ሱፐር ማርኬት፡፡ „የለለ ነገር እኮ የለም፤ ዛሬ የት ደርሰናል“ ይባላል ታዲያ፡፡ ያለፈውን መንግስት ይወቀሳል፡፡ እኛ የሰራነውን ተመልከቱ ይላል፡፡ ትምክህተኛው ታዲያ ማነው፡፡ የሚገርመው በሚኒሊክ ግዜ እንዴት ሙባይል አልገባም አይነት ነገር ሆነ እንካ ስላንቴው፡፡ የዛሬው ስህተት እንዳይታይ ወደሁዋላ ወስዶ ሊያስጎበኘን ሊያስቆጨን ፈለገ፡፡ ተመርቀው ይሆን ቸይናዎች፡፡ አስፋልት ሰሪዎቹም እነሱ፤ የሚመላለሱትም ቁሳቁሶች የእነሱ፡፡ የእራሳቸው ህዝብ የኢንዱስትሪያቸውን ውጤት በመግዛት ያነሳቸው ቸይናዎች፤ ለእኛም ገባያ ተረፉ፡፡
ታዲያ ከእንግዲህ ኢንዱስትሪ የምንሰራው ለማነው፡፡ እኛ እኮ እቃዎችን ገዝተን ልንጨርስ ነው፡፡ ወደፊት የሚታለመው ኢንዱስትሪ ለማን ልንሸጥ ነው፡፡ ምንአልባት ለጀርመን ወይስ ለአሜሪካ፡፡ በአፋችን እየበለጥን ከነሱ መጥተናል እና፡፡ በፕሮፖጋንዳ ማን ደርሶብን፡፡ ሰፍ ብሎ ነጋዴው ቻይና ሄዶ በኮንቴነር አፍሶ ያመጠዋል፡፡ በተወናበደ ቀረጥ የገባል፡፡ ምንአልባትም ምንዛሬው ጥቁር፡፡ ጥቁር በጥቁር፡፡ በቃ የአገራችን ኢንቬስተር ዛሬ ሸቀጥ አስገቢው ነው፡፡ ያስቃል ነገሩ፡፡ ሄዶ አፍሶ ማምጣት ምን አይነት ኢንቬስትሜንት፡፡ አድካሚ ነውን? ወይስ አይምሮ የሚጠይቅ? ስንት ሰራተኛ ቀጠረ፡፡ ስንት ወጣት እረዳ፡፡በቃ ባለኢንዱስትሪ አገሮችን
በማክበር እንዲኖር የተደረገው ወጣቱ ትውልድ ታዲያ ቁም ነገር እንደማውራት በስድብ ሲሰዳደብ ሲያሾፍ፤ ወርቅ መንግስት ሲል ይውላል፡፡ አይደለም ለእኔ፤ ሸቀጥን ማራገፊያ አደረገን እንጂ፤ የትኛው እንዱስትሪ እኒህን ሲሳደቡ የሚውሉ ወጣቶች አስቀጥሮአቸው ነው፡፡ በቃ ሌላው አለም የለፋበትን የስራ ውጤት በየሱቁ ተደርድሮ ማየታቸው ገዢው ፓርቲን ሰማይ ሰቅለውት አረፉ፡፡ እቤታቸው እንኩዋን ሳይገባ፤ በመስራት ሳይሆን በመግዛት የሚኖረው መካከለኛው መደበ ኢትዮጲያ፤ የማይጨበጥ ውድድር ውስጥ የገባው እግረ መንገዴን ሰላም ናችሁ? በማለት ከጀርመን ጎበስ ብዬ እጅ እነሳለሁ፡፡
አዎ ለቻይና እቃ እና ምርት አልያም ለሌላ ለታደሉ አገሮች የሸቀጣቸው ማመላለሻ አስፋልትን አለምተናል፡፡ ባለሀመሮችም፤ቆንጆዋን መርጠው ሻጥ አድርገው የሚንሸራሸሩበት፡፡ ልማት አልሚው መንግሰታችን ኢሕአዴግ የረሳው ወይ ያልሰማው ነገር ቢኖር፤ ቻይናን መጀመሪያ ያነሳት ጥንት እንጀርመን እነአሜሪካ፤ ምእራቡ አለም ሰርቶ ለሕዝቡ ያቀረበውን እሱዋም ኮፒ አድርጋ ሰርታ በማቅረቡዋ ነው፡፡ ለኢኮኖሚዋ መነሻዋ የእራሱዋ ሕዝብ የእራሱዋ የፋብሪካ ውጤት አየገዛ ተጠቃሚ በመሆኑ ነው፡፡ የኢትዮጲያ ስራ
አጥ ታሳቢ ምንግዜም ሆኖ አያውቅም፡፡ ብቻ በወሬ እንዲታመስ የድንቁርና መርዙን፤ አማራ፤ ኦሮሞ ትግሬ
እያለ የዘረኝነት መርዙን
እንዲረጭ የተዘጋጀ ይመስላል፡፡
ለዚህ ነው የተማረውም የእራስ ወዳድ ሲስተም አብሮ ገንቢ የሆነው፡፡ ምነው እንኩዋን ከራሳችን ፋብሪካ ልጆቻችንም ሰርተው ዋጋ ካወጡበት ኢንዱስትሪ ፈጥረን ብንገዛ፡፡ ኢሕአዴግእዋ፤ እንቅልፍ ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም እንዲሉ እውነቱን እንጋፈጥ ካልክ ኢትዮጲያን የሸቀጥ ማራገፊያ አድርገሃታል፡፡ ትልቁዋ የገባያ ቦታ፡፡ የዋሑ ኢሕአዴግ፤ እውን ኢትዮጲያን ይወዳል ወይ ብዬ ሳስበው፤ ቢወድስ የሚጠላው ሰው ባልኖረ ነበር፤ አልያም ከተቃዋሚ ጋር ስልጣን ሲጠብቅ ከሚውል፤ አይኑን ለሰላም በር ከፍቶ፤ ዙፋኑ ላይ በሀይል እንደወጣ ቀስ ብሎ እንኩዋን በወረደ፡፡ ለማንኛውም ሸቀጥ መጠቀማችን ዘመናዊነት ነው፡፡ ግን ገዢ ብቻ ሆነን መቅረታችን፤ ቤታችን በቆሳቁስ አይምሮአችንን በጉራ፤ በወሬ በእብሪተኝነት እና በማይጨበጥ ነገር ሞላው፡፡
በቸር ኑ
የምላችሁ ቁልጭ እኔው እራሴ ባዩሽ ነኝ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen