የዛሬው ሕልሜ
እማያልም ካለ በእኔ ማለም ይውቀሰኝ
ሕልሙን ደፍሮ ሰው ከተናገረ፤ ሁሉም የሰው ልጅ ሕልም ያያል፡፡ አንዳንዱ ገደል ለገደል ሲዘል፤ አንዳንዱ ሲበር፤ አልያም ሲዋኝ፡፡ ሌላው ሰርግ ደግሶ ሲድር፤ አልያም ጠጅእና ጮማ ሲቆርጥ፡፡ እረ ጉድ አትበሉእና አንዳንዱ ደግሞ ቤተመንግስት ገብቶ ሲዳክር፤ እግዚአብሄርም ጋር ሲነጋገር፡፡ ምን ይህ ብቻ ደግሞ ውብ የሆነች ሴት ጋር ሲሸራሸር፤ ሴቱዋም አገኘዋለሁ ብላ ያልጠበቀችውን ጉብል ይዛ በውሃ ዳርቻ ስትዝናና ማለም፡፡ ሌላው ሲገደል አልያም ሲገድል፡፡ እረ ምኑ ቅጡ የህልም ነገር ከተነሳ፤ ወርቅ ሲቀበል ወርቅ ሲጥል፡፡ ዘመዱን ሲቀብር አልያም የሞተ ሰው ጋር ሲነጋገር፡፡ ሕልም እንደልቡ፡፡ ታዲያ እየገረመኝ እኔ ደግሞ ህልሜን ሳካፍላችሁ ከርሜአለሁ፡፡ እናንተም ከደፈራችሁ ሕልምን በበኩሌ ብትነገሩኝ አልቆጣም፡፡ መብትህ ነው ወዳጄ፡፡ ሁሉም የሚስቀው፤ የእራሱን ጉድ በጉያው ደብቆ ነው፡፡ ተደብቀህ ከምታለቅስ፤ እራስህን ነጻ አድርገህ እበድ ቢሉሕ አያምህም፡፡
ንገረኝ ህልምህን፤ አልስቅም አላለቅስም፡፡ መቼም የሳይንስ ማሽን ተተክሎብን አደለም የምናልመው፤ የእግዚአብሄር ጥበብ እንጂ፡፡ ሳይንስን ተወው፤ በይመስላል የሚፈርድ፡፡ በቃ ሳይነስ ያላረጋገጠው ሁሉ የእብድ ነግግር ትባላለህ፡፡ ግንሳ ነጻ ትሆናለህ፡፡ ሕልም ቅዠት ነው አልያም መልዕክት ነው፡፡ እራስን ነጻ ማውጣት እንድትለማመዱ ይረዳችሁዋል፡፡ ያየሁትን ሕልም ባጫውት ደግሞ ምንድን ነው ወንጀሉ፡፡ በቃ ታይቶአል አሃ፡፡ ሕልሙ እውን የፈጸማል ወይ አይደለም የሚያሙዋግተን መሆን ያለበት፡፡ ህልሙ ግን ታይቶአል ወይ ነው፡፡ አዎ ሕልም እረኛው፤ ማይገባበት ቀዳዳ የለ፤ ወይስ የማያንኩዋኩዋው በር፡፡ ታዲያ ፌስቡክ የሚያገለግለው፤ እራስን ነጻ ማድረግ ነውእና፡፡ ሕልም አላየሽም ብሎ የሚሞግተኝ ካለ፤ የእሱን ህልም አለማየት በዋስትና በተረጋገጠ የሳይንስ ወይም የእምነት ማረጋገጫ ሊከሰኝ ይችላል፡፡ አዎ ህልምን ሁሉም ያልማታል ነው የምላችሁ፡፡ ይህን ካልኩኝ ዘንዳ፤ ዛሬ ወደአሳለፍኩት ለሊት ልጋብዛችሁ፡፡
በእኔ ቤት በእኔ አልጋ ላይ በጸጥታ በተኛሁበት መሰስ ብሎ አይምሮዬን ለካ ህልም ተብዬው ወደ እራሱ አለም ውስጥ ይዞት ነጉዶአል፡፡ የማላቀው አካባቢ በመውሰድ ኢትዮጲያዊያኖች መካካል አሳደረኝ፡፡ ሲወጣ እንጂ ሲገባ የማይታወቀውን ሕልም እረኛውን እንደልቡ ብየዋለሁ፡፡ ስጋሕ የፈለገ ይሁን ብሎ እጅ ሰጥቶ፤ መርፌ እንኩዋን ቢወድቅ በሚሰማበት በድቅድቁ ጨለማ አገር አማን ብሎ ይተኛል፡፡ „እንቅልፍ የሞት ታንሽ ወንድም“ ብለው አበው ሲያሙት ሰምተናል፡፡ ውነትም ሞት፡፡ ሕልም አይምሮህን ጠልፎ በፈለገበት አቅጣጫ ይዞህ ሲነጉድ፤ ሌባ እንኩዋን ቤትህን ገብቶ ማንጎዳጎድ ይችላል፡፡ ስጋ ካለአይምሮ ካለሕሊና ውነትም በድን፡፡ አዎ አይምሮ በማናውቀው ነገር የእግዚአብሄር ሳይንስ በእንቅልፍህ ውስጥ ይጠለፈዋል፡፡ ታዲያ አዳክሮ አዳክሮ ብንን በማድረግ፤ በተመለከትከው ህልም በስምአብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብለህ አይንህን መዳጥ ትጀምራለህ፡፡
ሕልሙ መደምደሚያው ያልታዬ አልያም የተጠቃለለ ይሆናል፡፡ እኔ ግን ዛሬ ለሊት ሳልደመድመው በእንጥልጥል ብንን አልኩ፡፡ ከመበርከኬ በፊት ግን ባየሁት ለግላጋ ጠይም ሰውዬ ልቤ ትንሽ ስብር አለብኝ፡፡ አጠገቡ ያሉ ሰዎች ሲጠቁዋቆሙበት አየሁ፡፡ ምንድን ነው ብዬ ጠጋ ብል፤ ሊይዙት መሆኑን በሽኩሽኩታ ሰማሁ፡፡ አዎ ይህ ሲያዩት መልኩ እንኩዋን የሚናገር ሰላማዊ ሰው እንዲያዝ የሚባል ማዘዣ ሊያወጡ ይሩዋሩዋጣሉ፡፡ እነማን አንደሆኑ ቅርብ ወዳጆቹም ተደርሶበት ተጠንቶ አልቆዋል ሲሉ ሰማሁ፡፡ እኔም „ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ“ ነውእና፤ እኔም አቀው ይመስል ልቤ አዘነ፡፡ ይሕ ማንአለብኝ ብሎ ስጋን የናቀ ህልም ከጀርመን ከሰላሙ ቤቴ አይሆኑ ቦታ አምጥቶ ስለከተተኝ፤ አብሬ መያዝ ፈርቼም እንደሁ አላውቅም፡፡ ወይስ የእሱ ሁኔታ አሳዝኖኝ፡፡ ብቻ ጭንቅ ውርስ አደረገኝ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ሰውየው ሊይዙት የተዘጋጁትን አያያቸውም አላሰባቸውም፡፡ እኔም ሲያዝ ሳላይ ብንን አልኩ፡፡ መቼም ጌታ ለጭንቀት አትስጠኝ፤ አሰቃቂ ነገር አታሳየኝ ብዬ ለምኘዋለሁ እና፡፡ በውነት የዘወትሩ ልመናዬ የምችለው ስጠኝ ነው፡፡ ሊይዙት የዶለቱት ግን ሁሉም ሲቪል የለበሱ ነበሩ፡፡ ተቃዋሚ ይሆን ወይስ የአስተዳደሩ ሰው???? ያዥውንም ተያዡንም አትጠይቁኝ፡፡ ሕልም አቅጣጫ እንጂ መደምደሚያው በአንተ ጸሎት ብርታት ይወሰናል እና፡፡ አሁን እስኪ ምን አድርጊ ነው የምትሉኝ፡፡ እኔ አልማለሁ ብዬ እኮ አደለም የተኛሁት፡፡ የእግዚአብሄር የሰጠንን ግዴት እረፍት ለመፈጸም እንጂ፡፡ ለካስ ተኝቶም እረፍት የለም፡፡ ወይስ ሌላ? ሰው መልካምን ይመኛል፡፤ የሚያልመው ግን አቶ ሕልም የመደበለትን ነው፡፡ በቸር ልበላችሁ፡፡ ባዩሽ

Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen