ዘመነ ኢሕአዴግ „ አለም
„ ተከፍታ ለኢትዮጲያውያን ተለቀቀችለት
አንድ ነገር አለ፤ ኢትዮጲያ በአለም ዙሪያ የምትታወቀው በኢኮኖሚዋ ደሃ ተብላ ነው፡፡
ብዙ ግዜ የሚነገረውም ከሕዝቡ ቁጥር ግማሽ ያህሉ ጭራሽም ጠግቦ የማያድር፤ እናት ለልጁዋ ይቅርብኝ ብላ ሳትበላ እንደምታደር ይነገራል፡፡
እንኩዋን በያይነቱ ልብስ ሊቀያይር ቀርቶ የእለት ጉርሱን ለመሙላት ደፋ ቀን የሚል ነው፡፤ ማንም እስካልተጎራ ድረስ በቤታችን ውስጥ
ብዙ ጎዶሎ እንዳለ አንክደውም፡፡ እንዳውም በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ብዙ ግዜ አንድ ወይም ሁለት ብቻ ሰራተኝ ነው ገቢ ያለው ፡፡
በቤተሰባቸው ውስጥ የሁሉም ሃለፊ ሆነው ጫና እንደሚበዛባቸው ነው፡፡ ሌላው ስራም የለውም የእሱን እጅ ብቻ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ነው፡፡
ይህ ለእይታ ተጠጋግቶ መኖር ፍቅር ያስመስለዋል፡፡ አይደለም አንዱ የሌላው ጥገኛ ስለሆነ ነው፡፡ አንዱ ካለአንዱ መኖር ስለማይቸድል
ነው፡፡ በፈረንጅ አገር ልጆች ወላጆቻቸውን አይጠይቁም ይባላል፡፡ እርግጥ ነው ብዙውን ግዜ ይህ ይታያል፡፡ ግና እውነቱን በቅርብ
ሆኜ እንደተረዳሁት፤ ችግር ስለለለ አንዱ የአንዱ ጥገኛ ስላልሆነ ብቻ እንጂ የጥላቻ ባህል ኖርዋቸው አይደለም፡፡ የፈረንጅ ልጅ
18 አመት ሲሞላው ከቤተሰብ መገንጠል ያለ ነው፡፡ የእራሱን ህይወት መመስረት ያለ ነው፡፡ በእኛ አገር ግን ይህ እንዳይሆን ድህነቱ
ጥገኛ አድርጎታል፡፡ ብዙ ሰው እንዳውም ለትዳር እንኩዋን ሳይታደል በእናት አባቱ ቤት ጎልማሳነቱን የሚያቃጥለው ብዙ ነው፡፡ከነበረበት
ቤት እንዳይለቅ አልያም እንዳይወጣ፤ ጎጆ የመቀየስ ችሎታ የለውም፡፡ ገቢ ይላልእና፡፡ ስራ የለውም ወይ ቤት መስራት አልያም መከራየት አይችልም፡፡ እንግዲሕ የውጮቹ
ብዙውን ግዜ ስለኢትዮጲያ ድህነት ሲናገሩ፤ የጠላት ወሬ የሚሉ የአገራችን
ሰዎች ሞልተዋል፡፡ አይደለም እውነቱ ግን ይህ ነው፡፡ ብዙ ሰው በባዶ ሆዱ ያድራል፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ ስላለበት፤ የቀን ኑሮውን
እንዲሁ እየተጠጋጋ መኖር ያለ ነበር፡፡ መቼም የጉድ ነው እንዴት
እንደሚኖር፡፡ የውጮቹ ጻፉት እኛ ግን በየቀኑ እያየነው ነው፡፡ አዎ ጠግቦ የማያድር ደሃ ነው፡፡
ይህ ለብዙ ግዜ የቆዬ ቢሆንም፤ በሀብታም እና በድሃ መካከል ያለው ልዩነት እጅግም
እንደዛሬው ጎልቶ የታዬ አልነበረም፡፡ ብዙ ማተሪያል ባልታየበት ወቅት ብል ይሻላል መሰል፡፡ በኢሕአዴግ ግዜ ብዬ ተቃዋሚውን የማስደሰት ንግግር እንዳይሆን፡፡ ያነዬ ፤
እከሌ ደሃ ነው እከሌ ሀብታም ነው የሚባል የተጋነነ ወሬ አልነበረም፡፡ ሙስናውም በገንዘብ የተወሰነ ሳይሆን ምንአልባት አንገትን
በመድፋት እና ትህትናን በማሳየት ነበር ብዬ እገምታለሁ፡፡ ዛሬ ግን ይህ ድህነት እስከነአካቴው ጦም አዳሪእና በረንዳ የወደቀ አፈራ፡፡
ለምን ቢሉ አግበስባሹ በእጅጉ እያሻቀበ በመውጣቱ ነው፡፡ ሙስናው ደራ፡፡ „ ለብሳ የማታቀውን የሰው ጃኖ ለብሳ፤ ነይ ተመለሽ ቢሉዋት
ወዴት ተመልሳ“ ሆነ ነገሩ፡፡ ያ አንዱ የአንዱ ጥገኛ ሆኖ ሲኖር
የነበረውም ብልተጥ አመጣ፡፡ ለምን ብዬ ወንድሜን እህቴን ሌላውን በላለሁ ተባለ፡፡ ሰበካውም ይህ እንዲጠፋ እና እርስ በእርሱ የጎሪጥ
እየተያዬ ዘመኑን እንዲያማርር መሰለ ነገሩ፡፡ ሰነፍ እና ጎበዝ በማለት ለዩት፡፡ ስራ ያልተሳካለት ሰነፍ ተብሎ ተፈረደበት፡፡ ስራ
እንደምንም በተለያየው ሙስና ስራ የተወሸቀው ጎበዝ የተነቃቃ እየተባለ ይሞገስ ጀመር፡፡ ደሃ በሆነች አገር የስነልቦና ናዳ ሆነ
ዳቦው፡፡
ከመሬቱም መፈናቀል መጣ፡፡
በጠገኝነቱ መረዳዳቱ ቀርቶበት፤ አውራውም ልቀቅ ሆነ፡፡ መሬቱም ማምረቻ
ሳይሆን ልማቱ በሚሊዬን እየሸጡ የእራስን ኬስ ማዳለብ ሆነ፡፡ አንዳንዱ መሬት አምስት ስድስት ግዜ በትርፋማ ገንዘብ መቸብቸብ ሆነ፡፡
መሬት የኢትዮጲያ አልማዝ፤ መሬት የኢትዮጲያ ቤንዚን ሆነ፡፡ እከሌ ከበረ ተባለ እንጂ የሀብት ቁጥጥር ኢህአዴግ አያውቃትም፡፡ ገንዘብ ገንዘብ ብቻ፡፡ ምን ገዶ፡፡ እምነትም ይህን የማይቃወመው በንዋይ ማደግ
ትክክለኛ መሆኑን መሰበክ ያዘ፡፡ ገንዘብ ገንዘብ ንዋይ ንዋይ፡፡ ለኢትዮጲያዊ በዘመነ ኢሕአዴግ
አለም ተከፍታ ተለቀቀችለት ፡፡ ሁሉም በተከፈተው በር ገባ፡፡ አለማዊም
ሆነ፡፡ ከተማ ወደላይ ማደግ ሲገባው፤ አዲስ አበባን እንደላስቲክ
ለጠጡዋት፡፡ ቢሚሊዬን ያጠራቀሙ ዛሬ አዲስ አበባን ወደላይ እንገንባት
ያን አፍርሱ ይህን አፍርሱ ሆነ፡፡ ከምንየው አዲስ አበባ በየሜዳው እንደልቡዋ ሄዳ፤ አዲስ አበባን ትልቁን ከተማ ሳይሆን ትልቁ
መንደር ሆነች፡፡ ሁሉም አዲስ አበባ በሆነበት ኢትዮጲያ፤ የቻለ ሙልጭ
እያለ ገባባት፡፡ ፊንፊኔ ተጨናነቀች፡፡ የቻላ የሚያገኝባት የሚከብርባት ትንሽዋ ሳውዝ አፍሪካ ልትሆን፤ ወንበዴም የሚፈጠርባት ሆነች፡፡
እንአቶ መለስም ሙስና ዋጠን ማለት ያዙ፡፡ አፍ እንዲከፍት የሰለጠነው አውሬ ዋጠን ቢሉት ምንዋጋ ነበረው፡፡ የቁራ ጩሀት ሆነ፡፡
ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ
ይፈታል እንዲሉ፡፡ ብርን መከመር በኢትዮጲያችን ፤ ስንቱ ጦም ባደረባት ተፈጠረ፤ ገደብ የለለው ልዩነት ተወለደ፡፡ እኔ ብቻ ልኑር፤ የእኔ ብቻ ዘመድ
ዘር ይኑር መጣ፡፡ የገንዘብ ሰው ሲፈጠር የሚርበው እየበዛ እንደሚሄድ ጥርጥር የለውም፡፡ ዛሬ የኢትዮጲያ ሕዝብ ድህነት በእጅጉ
አሻቅቦአል፡፡ ዛሬ የአማኝም ሀብታም ተፈጥሮአል፡፡ የሚያካብት፤ አንቱ የሚባሉ፡፡ ድሮ መስቀሉን ይዞ ግብረገብ ያስተምር ነበር ቄስ፡፡
አዎ ግብረ ገብ እና ስብእናን፡፡ ሙስሊሙም የሰው ሀቅ አይነካም ሲባል እኔ እንኩዋን ደርሸበታለሁ፡፡ ዛሬ ያ ሁሉ መከባበር አፈር
ድሜ ገባ፡፡ አንዱ አንዱን እየሰደበ እየከሰሰ ኪሱን መሙላት ሆነ፡፡ እርግጥ ነው፡፡ የአንዱ ሀብታም መሆን የሌላው ድህነት ነው፡፡
ልብ ብሎ ላስተዋለው፡፡
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen