ሰው ለሰው የፈጠረው ድሕነት
ሁሉም
ልቡ እውነቱን ያውቀዋል፡፡ ግና ሊጋፈጠው አይፈልግም፡፡ ጀግንነት በጦርነት ብቻ ሲገለጽ የኖረበትን ባህል መላቀቅ አቅቶናል፡፡ ጀግንነት
ለእኔ እውነትን ማየት ነው፡፡ እውነቱ ደግሞ ሁሉ በልቶ የሚያድርበት አገር አለመሆኑን አውቃለሁ፡፡ በባዶ ሆዱ የሚተኛ፤ እናት ልጄ
ይበልጥብኛል ብላ አንጀቱዋን በመቀነት አስራ ሳትበላ ጾም የምታድርበት አገር ናት ይህቺ የምንወዳት የምንገበገብላት ኢትዮጲያ፡፡
ሁሉም ትኩረቱ በቤተምንግስት ዙሪያ ብቻ ነው፡፡ ይቅርታ እና ገዢው ፓርቲም ብቻዬን ብሎ አላስደርስ አላካፍል ብሎ ስልጣንን የሙጥኝ
ብሎ ቤተመንግስት ይጠብቃል፡፤ ተቃዋሚም ማነው ወንዱ የሚጭበረበርእና ተወርዳታላህ እያለ ተቃዋሚም ሰላሙን ነስቶታል፡፡ እንደእውነቱ
ገዢው ፓርቲ መግዛት አይበለው፡፡
ሌትም ቀንም እራሱን ወታደር አድርጎ በጫካ ባለው ልምድ አሁንም ቀጥሎበታል፡፡ ሲጠብቅ
ያድራል ይውላል፡፡ አንዱ አንዱን መድረሻ እንደሚያሳጣው ደግሞ የለመድነው ባህል ነውና ማየት ነው፡፡ „የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል“ እንዲሉ ሕዝባችንም በስደት ከአለም እየተበተነ፣
በአገር ውስጥም ያልተለመደ ከቆሻሻ እየተመገበ እና ሴቶችም ወንዶችም በጋጥ ወጦች፣ በልቆች፣ ከመጠን በላይ በጠገቡ እየተደፈሩ፤ ህዝብ ጠባቂ እና ወኪል ያጣ
ሆኖአል፡፡ የተቃዋሚ በአገር ውስጥ አለመሳተፍ፤ በውጭ አገር የሚገኙ የኢትዮጲያ ኢንባሲንም ጉልበት እንዲያጣ እንዳደረገው ድብቅ
አይደለም፡፡ ምክናያቱም ገዢው ፓርቲ ሁሉንም በስደት ያለውንም ሆነ በሌላ ምክናያት በውጭ አገር ያለውን የኢትዮጲያ ዜጋ ተቃዋሚ
ነው በማለት፡ ባለው ጥርጥር ለጅብ የሰጠው ይመስላል፡፡
በውጭ አገር ገዢው ፓርቲም በመሳሪያ ኑ ብሎ ጦርነት ይጋብዛል፡፡ ተቃዋሚም አጅሬ በምርጫ
እምቢ ብሎአል ደግሞም በሰላማዊ ትግል አይወርድም እና በትጥቅ ትግል እናውርደው ብሎ ይጋብዛል፡፡ ገዢው ፓርቲ ጀግና ነኝ እስካለ ድረስ ሌላ የሚወዳደረ መነሳቱ የማይቀር ነው፡፡
መቼ ይሆን ከዚህ ከእንቢተኝነት እና ከጀግና ባህል የምንወጣው? ሁሉንም ልባችን ያውቀዋል፡፡ ነገሩ ግን ጀግናውም ፈሪውም፣ ተበይውም በይውም እና በዳዩም
ተበዳዩም በደም የተሳሰረ በባህል የተሳሰረ መሆኑ ነው፡፡ „አወኩሽ
ናኩሽ „ ሆነእና ነገሩ፡፡ ብዙ ህዝብ ተረሳ፡፡ ሰውም የእራሱን መንገድ በፍርሃት መጉዋዝ ያዘ፡፡ ብዙ አዲስ ባህሎችንም ፍርሃት
እንደሚወልድ ያላወቀው፤ የመጠጥ የጫት እና የሴክስ ሱስ ወጣቱ ሲጠመድ
እና ከእግዚአብሄር መንገድ ሲወጣ ልቅነትን ሲላመድ፤ ፈረንጆች ያመጡብን ባህል ትላለህ፡፡ ለምን አንደምንታለል አናውቅም፡፡ ፈረንጅስ
እንዳው እንደምትለው ስድ ቢሆን ከእራሳቸው አልፈው ለስደተኛም የሚተርፍ ስርአት ባልገነቡ ነበር፡፡
ውድ ወገኖች
እሕል ገባያ ላይ ያለበት አገር የራበው እና የተቸገረ ካለ፤ ይህ ነው ድህነት poverty የሚባለው እንጂ በአየር መዛባት በድርቅ
ጊዜያዊ መፈናቀል የሚመጣበት አይደለም፡፡ ድህነት ማለት አንድ ያልተስተካከለ በሙስና የተጣበበ ስርአት ሲኖር ነው፡፡ ስለድህነት
ሲነሳ፤ በእርጥባን ማጠቃለል የሚፈልግ አለ፡፡ ይህ ሁሉንም አያዳርስም፡፡ እንዳውም ሌላ ሙስና ከፋች ነው፡፡ሁሉም የመረጠውን መርዳት
ይፈልጋል እና፡፡ ሲስተሙም መርጦ የምትረዳውን ሊያቀርብልህ ይፈልጋል፡፡ ለመሆኑ
ለምንድን
ነው ሰው እግዚአብሄር ለሚፈቅድለት ምግብ ተረጣቢ የሚሆነው? ስንት ልጅ ነው ትምህርት ቤት የማይሄደው? ደግሞም፤ ትምህርት ቤት
በባዶ ሆዱ ሄዶ እየጮሀ የሚወድቀው? እያዞረው የሚደፋው የሚያንቀላፋው፡፡
ለምንድን ነው ሌላው ቢቀር እንኩዋን ሆዱ ሞልቶ የማይሄድ ዜጋ በሚኖርበት አገር አንዱ ረጣቢ ሌላው ተረጣቢ የሚሆነውእና ይህንን
ሞራል የሚጥል የሚያደቅ ስነልቦናን የሚንድ ነገር የምትፈርዱበት ? ምድሪቱ ለሁሉም እንጂ ለዘራፊእና ለሌባ፤ ቀምቶ ለሚበላ ለሚያካብት
እና በሙስና ለተዘፈቀ ብቻ ደግሞም እራሱን ለሚወድ ብቻ አይደለም፡፡ ረጣቢ እና ተረጣቢ ዜጋ በአንድ አገር ላይ መኖር የለበትም፡፡
ማንም ሰው ሌላው ቢቀር ከእራሃብ መውጣት አለበት፡፡ ሁሉም የማግበስበስ ባህል ያመጣው ስልጣኔ የምትሉት የዳረገው ይህንን ነው፡፡
አሁንም ልናፍር ይገባናል፡፡ አስተሳሰቤን አላነሳውም፡፡
መጠለያ እና ምግብ የሰው
ልጅ መብቱ ነው፡፡ የእኔእና የአንተ ልጅ ተምሮ ሌላው የማይማርበት፣ የእኔ እና የአንተ ልጅ ጠግቦ ሌላው የሚርበው፣ የእኛ የትኛው
ጉብዝና ነው፡፡ የትኛው እድላችን ነው፡፡ ይህ እምነት የለሽ ሕይወት ይብቃን፡፡ አንተ አማራ ነሕ አንተ ትግሬ ኦሮሞ እየተባበልን
ደሃውን እኩል የሚያበላውን ሲስተም እንደመገንባት ጥላቻን እንገነባለን፡፡ የለም ወዳጄ አስተሳሰቤን አላነሳውም፡፡ ለመሆኑ ትግራይ
አገሩን የሚያሰፋው አማራው በአማራነቱ እንዲራብ ነው? ለመሆኑ ኦሮሞ መሬቱን የሚያሰፋው ደቡቡን ለማራብ ነውእን? ለመሆኑ አማራው
መሬቱን የሚያሰፋው ሌላውን ለማስራብ ነውእን፡፡ አዎ ይህን ያሰበ ሁሉ ማፈሪያ ነው፡፡ አይምሮህን አስፋ እና ይልቅስ ሁልህም በሪዮተ
አለምም ሆነ በጭካኔ የምትፈጥረውን አሰቃቂ ድህነት ተቃወመው፡፡ በጋራ ተነስተሕ የራበው እንዳይኖር አድርግ፡፡ ካልሆነ እምነት የለህ
ፖለቲካ የለህ፡፡ እንዳው መዳከር ብቻ፡፡ ተመልከት እያንዳንድህ ስትሸራኮት ድህነት/ Povrty ከቀን ወደቀን እየጨመረ ሄደ፡፡
ይህን ማየት ያስጠላል እንደአማኝ ደግሞም እንደፖለቲከኛ፤ አልያም እንደሰብአዊነት እና እንደህዝብ እንደዘር፡፡ ባዩሽ ነኝ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen