ለግንዛቤ
አሁን ከእብደቱ ድኜ ተሻለኝ፡፡
በየተጠራው ስብሰባ ተገኝቼ ልቤ ያሰበውን ጥያቄ ጠይቄአለሁ፡፡ ስጠይቅ ጭብጨባው
ይቀልጥ ነበር፡፡ ግን ከስብሰባው ስወጣ የሚያነጋግረኝ የለም፡፡ ሁሉም ያገለኛል፡፡ አኔም ጠይቁ እየተባለ ለምንድነው እናንተስ የማትጠይቁት
ብዬ ብዙዎችን አበረታታ ነበር፡፡ በአገሪቱ መሻሻል እንዲመጣ፤ ጠቁሙ ተናገሩ እል ነበር፡፡ የፖለቲካው ባህል እንደኢይሮፕ መስሎኝ፡፡
የኢትዮጲያው የተቀየረ መስሎኝ፡፡ እውነት ይሁን ውሸት፤ ኢሕአዴጎችም ጠይቁ ስለሚሉ፡፡ እኔም መብቴን ተጠቅሜ እጠይቃለሁ፡፡ በሕዝብ
ልብ ያለውን ስለምጠይቅ፤ በጠየኩ ቁጥር ጭብጨባው ይደምቃል፡፡ ግን ስንበተን ሁሉ የራሱን መንገድ ይዞ ይሄዳል፡፡ በቃ እኔ ጋር
መታየት የሚፈልግ የለም፡፡ አንድ ቀን አንድ ፖሊስ ተቃዋሚ ጋር እንዳለሽበት
ተደርሶበታል አለኝ፡፡ እኔ ግን አንድም አላውቅም ነበር፡፡ አንድም እስከዛሬ፤ መሆንም አያስፈልገኝም፡፡ እኔ የምጠይቀው ጥያቄ ሰብአዊነትን እና መረን የለቀቀውን
የመሬት ሙስናም የመሳሰለ እና የባለጉዳይ በየቢሮው መጉላላት ነበር ጥያቄዬ፡፡ ስለ አድሎ ነበር ጥያቄዬ፡፡ የጎጥ መተሻሻት ነበር
ያደነጋገረን፡፡ ሁሉም በየገጠሩ የእከሌ ዘር የእከሌ ወገን ይባላል፡፡ ጉዳይ ሲኖረን ያገሩን ሰው በመፈለግ አማላጅ መላክ ነበር
የሰለችን፤ ጥያቄዬ ይህ ነበር፡፡ ይህን እራሳቸውም ያውቁታል፡፡
ፖሊሱ ያለኝ
ቢገርመኝም የበለጠ ያስደነገጠኝ ህዝቡ ጥያቄ እንኩዋን ለመጠይቅ ለማነጋገር
ፈሪ መሆኑ ነው፡፡ ለዛውም ጥያቄ ጠይቁ እየተባለ፡፡ የሚገርመው ብዙው ጀርባየንም እየጎሰመ ይህንን ጠይቂ ያንን ጠይቂ የታባታቸው
የሚለኝ ይበዛል፡፡ ለእነሱ ጥያቄ እኔ ለመቆም ግን የተሰጠኝ ውክልና እንደለለ አያውቁም፡፡ ግን አንቺ ብቻሽን ሙችልን ነው ነገሩ፡፡
ገረሞኝ ስኖር፤ እውነትም ከለት እለት በየቢሮው ጉዳይ ሄጄ ሳቀርብ ፤ ውሳኔ ሰጭዎች ችላ በማለት ያሰቃዩኝ ጀመር፡፡ ተላመድኩት፤
በእውነት በኢሕአዴግ ግዜ የደም እምባ አልቅሻለሁ፡፡ በቃ ክፉው ለእኔ ካላቸሁ ለእኔ እዛው የአካባቢዬ ሁኔታ ነው፡፡ አባባሌን ተረዱልኝ፤ ሳሞራም ሆነ በረከት ወይ ስብሃት የሚባል ስም አካባቢየ የለም፡፡ ያገለሉኝ የእራሴ ዘሬ ወገኔ ነው፡፡ እህት ወንድም እንኩዋን አልቀረም፡፡ ዛሬ ይቺ አርቲስት አገለሉኝ ስትል ያገለላት እኮ የሚያውቃት ሰው ነው፡፡
የቅርብ ሰው ሲያገልህ ነው ተሰምቶሕ አገለሉኝ የምትለው፡፡ የስራ ባልደረባ፤ ዘመድ፤ ያገር ሰው፡፡ እኔም እንዲህ ነው የሆንኩት፡፡
አንድ ገጠመኘሸን
ልንገራችሁ፡፡ አንድ ቀን ሶስት ሰዎች በአንድ የመገባባያ ቦታ አጋጣሚው አገናኘን፡፡ በእኔ መፌዝም ተጀመረ ፡፡ አንዱ
„ጀግና ናት“ አለ ፡፡ እኔው ጀግና? ልቤ ቀልቶ አይኔ በእንባ ሙዋምቶ
እንዳለ ያውቃል፡፡ „ልክ ልካቸውን ንገሪያቸው አለኝ“ ጀግና ያለኝ፡፡ እንዲህም እንዲህም በያቸው በማለት፡፡
እሱ ጠበንጃ እኔን ጥይት አድርጎ፡፡ ያኛው ሰው ግን
„አዎ ጠይቂ ቀውስ ናት ስላሉ አንቺን ምንም አያደርጉሽ „ አለኝ፡፡ ገረመኝ አፍ ሲያራ፡፡ ሶስተኛው ሰው ከት ብሎ በመሳቅ፤ „አዎ
ውነትም ቀውስ ነሽ፤ እንደ ኢሕአዴግ ጥሩ መንግሰት የት አለ እና ነው በማለት ፎከረብኝ“ እንዳውም ከት ብሎ ሳቀብኝ፡፡ እኔም በጣም ተሰማኝ፡፡ አይ ኢትዮጲያ በማለት፡፡ ነጋዴ ነው የሳቀብኝ፡፡
እኔም ዘወትር እንደማደርገው ለሞራሌ ስለምጥር፤ ይህ ግንዛቤ ያጠረው
ሰው ጥጋብ የነገውን ያላሳየው ጋር እሰጥ አገባ መግባቱን ትቼ መንገዴን ቀጠልኩ፡፡ አንድ ቀን ግን በመንገድ ስሄድ፤ ይህ የሰደበኝ
ሰው በመጮሕ ስሜን በመጥራት ሊቀርበኝ ፈለገ፡፡ እኔም በእርጋት ጠበኩት፡፡ ሲቃ ይዞታል፡፡ ላቡ ስምጥ ስምጥ ያደርገዋል፡፡ ደሙ
ወደላይ እንደወጣ ተሰማኝ፡፡ እፊቴ እንዳይሞት ጌታን ተማጠንኩ፡፡ የማንንም ስቃይ በአይኔ አታሳየኝ ብያለሁ፡፡ “ አንቺ እነዚህ ሰዎች እኮ አብደዋል አለኝ“ በሲቃ እና በተቆራረጠ አነጋገር፡፡ ወይ ጉዋደኞችህ ? አልኩት፡፡ “ እረ አነዚህ ወያኔዎች አለኝ፡፡“ እንዴ ወያኖዎችን የት አገኘሃቸው? ትግራይ ሄደህ ነበር እንዴ? በማለት ያንን ቀውስ ያለኝን በማስታወስ መለስኩለት፡፡ አይ እረ እዚህ እኛ ጋር ያሉት የአማራው ተወካይ ተብየዎች አለኝ፡፡ “
ምን አደረጉህ አልኩት፤ „እንዴ የጣሉብኝ ግብር ውሃ አያሰኝም፡፡ በናትሽ ስብሰባ ስለተጠራን እንድትመጪ ልክ ልካቸውን
ንገሪያቸው ፤ መቼም ጥሩ ሰው ነሽ፤ እግዚአብሄር አንቺን ጥሎልናል„ አለኝ፡፡ እኔን አፈር ይብላኝ፡፡ „ሊበሉዋት ያሰቡትን አሞራ
ጀግና ይሉዋታል“ ተባለ? እኔም የደስታ ትንፋሽ ተነፈስኩ፡፡ ለምን
መሰላችሁ፤ ያለው ነው ግብሩም አይጎዳው፡፡ እንኩዋንም እሱ የጉልት ሴት ትቀረጣለች፡፡ ብዙ አመት ሰርቶአል፡፡ ኢህአዴግንም ወዶ
የነበረው፤ የደንቡን ሳይከፍል በመኑሩ ነበር፡፡ ቁጥጥር ስለለለበት ይሆናል፡፡ እድሜ ለሙስና፡፡ ልሳቅ እንጂ፡፡ ጨካኝ አትበሉኝ፤
ሊረሽኑት ሊያስሩት አይደለም ቤቱን ያንኩዋኩበት፡፡ የእስከዛሬውን አጠራቅመው ነው ብቅ ያሉበት፡፡ ለሰው እየከፈለ እራሱን ሲደብቅ
አሁን እንዴት የከፈለውን ያጠጣውን ያፈነውን ያቁመው፡፡
ኢሕአዴግ ሰራዊቱን
ፖሊሱን ያበዛ ነው፡፡ ጤና ጣቢያ የሰራ ነው፡፡ መንገድ የሚሰራ ነው፡፡ አባይን ሊገድብ የጀመረ ነው፤ ብር እንዳነሰው አላወቀም፡፡
ሊያስገብር የመጣ መሆኑን አላወቀም፡፡ ብር ወዳጄ፤ ለፖሊሱ ለአስተማሪው ለሀኪሙ ያስፈልገዋል፡፡ ኢህአዲግ እኮ ተረጋግቶአል፡፡ አንዱ
አረጋጊም አለም ጤና ብሎ ጥያቄ አቅራቢውን ቀውስ እያለ ሞራል ሲነካ የነበረ አሁን ወያኔ አበደ ትናንት አንቺ እብድ ነሽያለኝ ነው፡፡
ደግሞም ፤ ሊረሸን አልቀረበም የገንዘብ ጉዳይ ነው፡፡ ትናንት ወርቅ ናቸው ሲላቸው የነበረው ፓርቲዎች፤ በአንደዬ እብድ አላቸው፡፡ በጤናው ቢመጣ አልተነፍስም ነበር፡፡ አዝንለት
ነበር፡፡ ገንዘብ ግን እኔም እንዲህ ተሳድጄ ተገድጄ ሳይሆን በፍቃደኝነት የገቢዬን አንድሶስተኛ ከፍዬ ነበር የምኖረው፡፡ ግብር
በዛብኝ ብዬ ሳይሆን የጮሁኩት፤ ሙስና ይቁም አታዳሉ ብዬ ነበር፡፡ አሁንም ጸጥ ካልኩበት „እባክሽ ነይእና ተናሪልን አለኝ፡፡ አየህ አሁን ከእብደቱ ደኜ ተሻለኝ፡፡ አሁን አንተ በተራህ ስላበድክ፤ ሂድና ንገራቸው
ብየው ተለያየን፡፡ እኔ ሴቱዋ ስብርብሬ ወጥቶ፤ ከውጭ አገር ይዠ የገባሁዋቸሰው ልጆች እንባዬን እያዩ፤ ለመብት ጥያቄዬ እብድ ተባልኩ፡፡ ልጅ እያስለቀስኩ ስጮሕ ፤ እውነትም ማበድ ነበር እንዴ፤ ግርም ይለኛል፡፡
ኢትዮጲያችን ይቺ ናት፡፡ እሱ ሽጉጥ ሌላው ጥይት እንዲሆንለት የሚፈልግ ፡፡ ተናገር ሲባል የሚፈራ፡፡ ሲናገሩለት የሚሳደብ፡፡ ካልተነካ
የሌላው መነካት ጆክ የሚመስለው፡፡በሉ ይበቃል አቦ አንጀቴ አሮ ነበር፡፡ አሁን ግን……… ባዩሽ ነኝ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen