Sonntag, 15. Februar 2015

ሞራል ያልተጻፈውን ሕግ ስለመጠቀም




ለወጣቶች፤  
ሞራል ያልተጻፈውን ሕግ ስለመጠቀም

ባለ ድረገጾች ድረገጻችሁን ትንሽ ጎብኘት አድርጋችሁ ለኢትየጲያውያን ብሎም ጤነኛ የሆነው የአለም ክፍል ህዝብ ማየት የማይፈልገውን ሞራል የለሽ ፖስተሮችን አስወግዱ፡፡ ወዲያው ለማጥፋት ሞክሩ፤ ይህ አይደለም አለም የሚያስፈልጋት፡፡ ሞራል እና ስብእና ነው፡፡ ይህን የሚልኩ ሰዎች በጣም በከፍተኛ ደረጃ በፍራስትሬሽን የወደቁ በመሆናቸው ጤነኛ የሆነ ሰው ማየት አይፈልግም፡፡ ማንኛውም እምነት፤ ደግሞም ማንኛውም ሕብረተሰብ በዚህ በኩል አንድ አይነት ባህሪ አለው፡፡ ስድነትን አይፈልገውም፡፡

ባለድረገጾች ጤነኛ ያልሆኑ ነገሮችን ከድረገጻችሁ ውስጥ አውጡ፡፡ ይህ ፈረንጅም ሆነ ማንም ጤነኛው ህብረተሰብ አይፈልገውም፡፡ የብዙ ፍራስትሬሽን የሆኑ ሰዎች አዘቅጥ ውስጥ የገቡ ፖሰት ካርዶችን ወዲያው ለማጥፋት ሞክሩ፡፡ ካልሆነ ይህንን የማያደርጉ ከሆነ ጤነኛ የሆነው ኢትዮጲያዊ ወይም ኤርትራዊ ከድረገፁ ይለይ፡፡ ኢትዮጲያም ሆነ ኤርትራ ወይም የአለማችን ሕብረተሰብ በዚህ ችግር የለውም፡፡  የሴክሹዋል ችግር ያለበት ህብረተሰብ አይደላችሁም፡፡ እንደሚመስለኝ፡፡ በስመእግዚአብሄር የምጠይቃችሁ  እራሳችሁን ከዚህ መቅሰፍት ለዩ፡፡ ከዚህ አይምሮን እየሰረቀ ሰውን ወደእሳት የሚልክ የሰይጣን ባለአደራዎች እራቁ፡፡ ለተሻለ ነገር አይምሮአችሁን አይናችሁን አውሉት፡፡ ማንም ጤነኛ አይምሮ ይህንን ያውቃል፡፡ ተስፋ የቆረጠ ሰው ሊያደናግሩዋችሁ  ከሚራወጡ የሰይጣን ፈረሶች እራቁ፡፡ እነሱ ምንአልባት እንደተለከፉ ላይታወቃቸው ይችላል፡፡ ይህ በሁለት ሰዎች የሚፈጸም እንጂ ለሌላ የሚተላለፍ አይደለም፡፡

እናንተ ግን ጤነኛ ናችሁ፡፡ ግዜያችሁን ሊገልባችሁ ሰይጣን ይነሳል እና እወቁት፡፡ እሱንም ገስጹት፡፡ በፈረንጅ አገር እንዲሕ አይነት ነገር በሶሻል ሚዲያ አይለቀቅም፡፡ ለእንደዚህ አይነት ሰዎች ለእራሳቸው ተከልሎላቸው የተገሉሉ የተናቁ ሆነዋል፡፡ ፈርንጅ ይህንን ሲያይ የሚውል አይምሰለህ፡፡ የተሳሳተ ፕሮፖጋንዳ እየተከተላችሁ እነዚህ ሞራል የለላቸው ነገሮች ስልጣኔ አይምሰላችሁ፡፡ የለም ይህ የፈረንጅ ስልጣኔ አይደለም፡፡ ስልጣኔያቸው፤ ዳቦዋቸውን እኩል ማካፈል መስራት እና ዲሞክራሲያቸው ላይ ማተኮር ነው፡፡ ሰባኣዊነትን ነው ወጣቱ የሚያውቀው፡፡ ነውር ነገሮች የሚተላለፉት የእራሳቸው ሚዲያ አለ፡፡ እዛም ከ18 ዓመት እድሜ በታች ትውር አይልም፡፡ እዚህ የእናንተ ሶሻል ሚዲያ ግን እንደልቡ እያደረጋችሁት ነው፡፡ በልጅ እና በአዋቂ መካከል ያለውን እድሜ ክልል አክብሩ፡፡

ሰላሳ አምስት አመት ፈረንጅ አገር ስኖር፤ ስድ የለቀቀ ነገር በእኔ አካባቢ የለም፡፡ እነዚህ ጥቂት ስድ የሆኑ ሰዎች የሚኖሩት በተከለለላቸው አካባቢ ብቻ ነው፡፡ እሱም ቢሆን የፈለገ፤ ወደዛ መሄድ ይችላል እንጂ የማይፈልገውን መበከል አይፈቀድላቸውም፡፡ ለምሳሌ አንድ ነገር አለ በኢትዮጲያውያኖች አካባቢ የሚነገር፤ ፈረንጅ በየሜዳው ፈሱን ይፈሳል የሚባል፤ ስህተት ነው፤ እኔ ይህንን በጀርመን አይቼ አላውቅም፡፡ የማንንም ፈስ ተጋሪ ሆኖ የሚያሸትም ህብረተሰብ የለም፡፡ አምልጦት እንኩዋን አንዱ ቢለቀው፤ የእሱ ባለማስመሰል ይሆናል እንጂ፤ ጣት እስከምንቀስር ድረስ አያደርገውም፡፡ እንኩዋን እግሩን አንስቶ ሊፈሳ ይቅር እና፡፡ ነውር የሆኑ ባህሎች የሚታወቅበት አገር ነው፡፡ ማግሳትም ትልቅ ነውር ነው፡፡ አፍንጫን ሳያፍኑ ማንጠስ እንኩዋን ብዙ ትችት እና ትዝብት ይሆናል፡፡

ሰሞኑን በሚዲያ የሰማሁት ምክር አለ፡፡ እሱም ሚኒስከርት ለብሳችሁ በአውቶብሱ ወይም በባቡር ውስጥ መቀመጥ እንዴት አስቀያሚ እንሰደሆነ እና ሰዎች ይህንን በመዘንጋት ስለሚያደርጉት እንዲጠነቀቁ ይናገር ነበር፡፡ ሴት ብቻ አይደለም ወንዶችም ቢሆን ተንፈራጦመቀመትን የማይበረታታ ይሉታል፡፡ በአጠቃላይ በህዝብ ትራንስፖርት አቀማመጥን እንኩዋን በተመለከተ ሲያስታውሱ እና ቲፕ ሲሰጡ ነበር፡፡ የተበላሸ ኖሮ ብቼ ሳይሆን፤ እንዳይበላሽ፤ ከጊዜ ብዛት ነውር የሆነውን እንዳይረሳ፤ ሪፖርተሮች ያሳስቡ ነበር፡፡ ልብ ብለንም ስናይ ይህንን የሚያደርግ እጅግም ብዙ የለም፡፡ ሁሉም በፖርሳው የነውርን አካባቢዎች ሸፈን በማድረግ ይቀመጣሉ፡፡ ፊት ለፊታቸው ሌላ ሰው ስለሚቀመጥ መረበሽ እና አቅጣጫን ማሳት ነው ይላሉ፡፡ ለሁሉም ነገር የሞራል ገደብ ባልተጻፈ ህግ የተደነገገ መሆኑን ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ ይህንንም ሰው ይጠቀምበታል፡፡ ያውቃል፡፡ ካልሆነም በተመልካች አካባቢ ግልምጫ እና መሳቂያ ወዲያው በማድረግ፤ ሰው እርስ በእርሱ በመተያየት የማይዋጥ ነገር እንዳደረገ ያሳዩታል፡፡ ስለዚህ ወጣቶች ፤ያልተጻፈ ሕግ እንዲሁ በተፈጥሮ ውስጣችንን ያነቃቃን የእግዚአብሄር ነገር አለ እና ይህንን እንፈጽመው፡፡ እንዳው ፌስ ቡክ ስሜን መልኬን ስለቀየርኩ ማንም አያውቀኝም በማለት እንዳገኛችሁ አትሁኑ፡፡ እውነቱ አንድ ነገር ነው፤ እሱም እግዚአብሄር በስምህ ሳይሆን በማንነትህ የሚሰራ አምላክ ነውእና አሳችነትህ ለእሱ ድብቅ አይደለም፡፡ በአለም ላይ ያለው ያልተጻፈ ሕግ፤ ሁላችንንም በአንድ የባህሪ ባህል ያገኛኘናል፡፡ እሱም ሰው የተባለ ፍጡር ክፉና ደጉን ያውቀዋል፤ ተደብቆም የሚያደርገው ለዚህ ነው፡፡ ሰላም ይብዛላችሁ ባዩሽ ነኝ፡፡    

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen