Samstag, 28. Februar 2015

እፈረሰ አገር ምን ፓርቲ ያስፈልጋል፤ ወንበዴ እንጂ

እፈረሰ አገር ምን ፓርቲ ያስፈልጋል፤ ወንበዴ እንጂ

የኢትዮጲያ ህዝብ ለመንግስቴ/ለገዢ ፓርቲ/ ሲል፤ እንጂ ለአገሬ የሚል የለም፡፡ ይህን ባህሪ መገንባት  አልቻልንም፡፡ ሚኒሊክን ፣ ሐይለስላሴን  ደግሞም ደርግን፤ ኢሰፓ ኢሰፓ ሲል፤ አሁን ደግሞ አፍቃሪ ኢህአዴግ ወያኔ ወያኔ ይላል፡፡  ደግሞም ነገ   ግንቦት 7 ይምጣ አልያም ሌላ ሲል ለእሱ ሲያጫፍር ይገኛል፡፡ አበላሉን የሚያውቅ ዘዴኛ ህብረተሰብ ፖለቲከኞቻችንን ማፍራታቸውን አላወቁም፡፡  እስኪ በፈጠራችሁ አገሬ የሚል  እንጂ ፓርቲ ነጥሎ የማያፈቅር መሪ ፍጠርልን ብላችሁ ጸልዩ፡፡ ሽ ዘመን ይኖር ይመሰል፤ ሌባውን ሁሉ በጉያህ ሸጉጠህ፤ ሴት አስለቃሹን ደሃ አሳዳጁን በብብትህ ይዘህ የእኔ ልጅ ወርቅ ነው የምትል ሁሉ እስኪ አሰብ አድርግ፡፡ የጋራ ነገር የሚፈጥር ሕዝብ ከየት እንፍጠር፡፡ ይህን ፓርቲ አፍቃሪ ህዝብ ይለወጥ ብላችሁ ጸልዩ፡፡ ይህ ካልሆነ፤ ሁሉም የእራሴ የሚለውን የተነከረበትን ባህር ዋኝቶ መውጣት አይችልም፡፡


እስኪ ስንቱ ነው አገሬ ወገኔ የሚል፡፡ ሁልግዜ ፓርቲ አፍቃሪ፤ መሪ አፍቃሪ፤ ሚኒሊክ ፣መለስ ስትል መዳከር ብቻ፡፡ አገሬ በል የኢትዮጲያ ሕዝብ፣ ሰላሜ በል የኢትዮጲያ ህዝብ ፣ወገኔ በል የኢትዮጲያ ህዝብ  ፣ነጻነቴ በል የኢትዮጲያ ህዝብ፣ ድህነቴ ጥማቴ በል የኢትዮጲያ ህዝብ፡፡ መብቴ በል የኢትዮጲያ ህዝብ፤ ፓርቲዬ እያላችሁ ከአጽም ጋር አትታገሉ፡፡ ሚኒሊክም መለስም አልፈዋል፡፡ እኛ መኖር ነው የምንፈልገው፡፡ እያለቀሱ መብት ተጉዋድሎበት ፍርድ ተዛንፎበት መኖር ይብቃን በሉ፡፡ ያም ያም እየተነሳ አይገልምጠኝ በሉ፡፡ አንተ ሌባውን በጉያህ የደበክ፤ መጀመሪያ ከቤትህ ያለውን አስወጣ፡፡ አንተ ፍርድ የምታጉዋድል፤ መጀመሪያ እራስህን ለውጥ፡፡ በቃ ፓርቲ አፍቃሪ ሳይሆን አገር አፍቃሪ በእግዚአብሄር ስም ሁኑ፡፡

 ምንም ቢሆን አንድ ዘር ከአንዱ ዘር በልጦ ለመኖር ይቸገራል እና፤ አንተ እበልጣለሁ የምትል ውል ስራ፡፡ እንዴት እንደምትበልጥ የምታሳውቀው፤ እራስህን ነጥለህ በማዳን ሳይሆን ሌላውንም ፤ሰው ነው ወገኔ ነው ስትል ነው፡፡ ካልሆነ መብለጥ እንዲህ፤ ከማን ጋር ተወዳደርክ እና፡፡ ዘር ከዘር አይወዳደርም፡፡ የዘራው አንድ እግዚአብሄር ነውእና፤ መርገምትህን አትከናነብ፡፡ ይገርመኛል ይደንቀኛል፡፡ ሌባ ጋር እየበላ እያቦካ እየደገሰ ጣትን ቤተመንግስት ላይ መቀሰር፡፡ ስንቶቻችን ነን ያንን የምናደርግ? ለዘመናት የሚጫወትብንን አድርባይነት እንዴት እንላቀቀው?አንተ ፓርቲ አፍቃሪ የሆነክ፤ ሌላውም የእራሱ የሚያፈቅረው ፓርቲ እንዳለ ለምን ዘነጋህ፡፡ ጆሮ ያለው ካለ ይስማ፡፡ ኢትዮጲያ የደከማት አገር ሆናለች እና መደገፍ እንጂ መገፍተር አያስፈልጋትም፡፡ በቁዋፍ ያለችውን አገርህን ለመታደግ፤ ወያኔም ሁን ሌላ ፓርቲ አፍቃሪ መሆንህን ወደጎን ተወት አድርግ እና አገር አፍቃሪ ሁን፡፡ ፓርቲህ የሚኖረው አገር ሲኖር ነው፡፡ እፈረሰ አገር ምን ፓርቲ ያስፈልጋል፤ ወንበዴ እንጂ፡፡
ባዩሽ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen