በራስ መተማመን የሚያሳጣህን ነገር በሙሉ፤ ከሕይወትህ ውስጥ ውልቅ አድርገህ
ላታወጣው ትችላለህ፡፡ ግን ከአይምሮህ ውስጥ ማውጣት እና ሀ ብለህ መኖር መጀመር ትችላለህ፡፡ አንተ አዲስ የምትሆነው፤ የጎዳህን
የጠቀመህን መለየት ስትችል ነው፡፡ አንዳንድ ግዜ በህይወት ልምዴ ያገኘሁት በኑሮም ሆነ በአስተሳሰብ ደረጃ ከአንተ እንኩዋን ሊቀራረቡ
የማይችሉ ሰዎች፤ በአንተ ላይ ተጽእኖ ያሳድሩብሃል፡፡ የሉም እኮ ግን ያሉ ይመስልሃል፡፡ ደግሞም ልብ ብትል ካለስነልቦና ተጽእና
እና ካለጉዳት በስተቀር የጠቀሙህ ነገር የለም፡፡ ግን የጠቀሙህ እየመሰለህ እነሱን ተከትለህ እሸኮለሌ ስትል ትኖራለሕ፡፡ እራሱ
ሰው የሚያገልህ አንዱ መስፈርት የእሱ ባህሪ አገልጋይ ሊያደርግህ ስለሚፈልግ ነው፡፡ እግዚአብሄር ያለው፤ „ሰውን እንደራስህ አድርገህ
ውደድ እንጂ፤ ከአንተ አብልጠህ ውደድ“ የሚል ነገር በማንኛውም ቦታ
አልተጻፈም፡፡ የሚገርመው እና በሕይወት ልምድ የተለማመድኩት ነገር፡፡ ከእራስህ አብልጠህ ሰውን የምትወደው፤ በራስ መተማመንህ ሲጠፋ
ብቻ ነው፡፡ ካለእነዚህ ሰዎች መኖር የማትችል እየመሰለህ እነሱን ለማቅረብ ትጥራለህ ትሞክራለሕ፡፡ እነሱ ግን አይመጡም፡፡ ወደአንተ
የሚመጡት እጅህን አልያም እንደባሪያ አገልግሎትህን ስለፈለጉ ሊሆን ይችላል እና፤ በአካባቢህ ያለውን ወዳጄ የምትላቸውን እና የአንተን
ቀረቤታ መመርመር ጥሩ ነው፡፡ ከአንተ በላይ የወደድከው ሰው ምንም ሊወድህ አልያም መውደዱ ቀርቶ ሊያከብርህ አይችልም፡፡
ለምሳሌ ብዙ ወንዶች በእራስ መተማመናቸውን የሚያጡት፤ በሱስ ሲጠመዱ ነው፡፡ ሱስ ኪስህን የሚያራቁት እና የሌላውን እጅ የሚያሳይ በመሆኑ፤ ጥገኛ እና ተለማማጭ የማድረግ ሀይል አለው፡፡ በዚህም የተነሳ ከሚጫወቱብህ ሰዎች ለመላቀቅ መጀመሪያ ከሱስ የጸዳ ህይወት መጀመር አለብህ፡፡ „እንደእውነቱ ኩራት እራት ነው“ እንዲሉ፤ ብዙ ግዜ የሚረዳህ ለእለት ዳቦ ብቻ ላይ የምታደርገው የአይምሮ መሰባሰብ ሊሆን ይችላል፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ ብዙ ጥበብ የተሞላበት የህይወት ምክር የያዘ መሆኑን የተረዳሁት ካነበብኩት በሁዋላ እንጂ ቄሱ ስለነገረኝ አይደለም፡፡ እኔ አንድ ግዜ መጽሀፍ ቅዱስን ያነበብኩት እንደታሪካዊ መጽሃፍ አድርጌ እንጂ እንደእመነት አልነበረም፡፡ እራሱ እምነትን ለማወቅ፤ ታሪኩን እና አመጣጡንም መረዳት መልካም ነውእና፡፡ እዚህ ላይ የምናገረው ስላነበብኩት እንጂ፤ ማንኛውም የእምነት መጽሃፍ ለሕይወት አስተማሪነት እንዳለው፤ ለአንድ ሰው እራሱን እንዴት እንደምትገለገልበት የሚረዳሕ የህየወት ማንዋል ነው ብዬ እገምታለሁ፡፡ ብዙ ግዜ የሀይማኖት መሪዎች ከደረሰባቸውም ወይም ከሌላ ስውር አላማ ጋር በማያያዝ በኢሞሽን ሊሰብኩት ይችሉ እና አንተን ሊያስቱህ ወይም ደግሞ ይህስ ይቅርብኝ ብለህ እንድትሸሽ ሊያደርጉሕ ይችላሉ፡፡ ይሁን እና ግን እኔ ሁሉንም የምለው፤ የእምነት መጽሃፍ በእራሱ ምን እንደሚል በእራስህ ካለማንም መሪነት ማንበቡ እና መረዳቱ ከዛም መከተሉ ጥሩ ነው፡፡ ይህ ከሆነ አንተ ያገኘሀውን እውቀት ማንም ሊቀማሕ አልያም ሊያበላሽብህ አይችልም፡፡
እኔ እንደተረዳሁት እምነት የሌላውን እምነት እንዲያጠፋ የተዘጋጀ አልመሰለኝም፡፡
ይህ ለመሆኑ ምንም አይነት መረጃ የለኝም፡፡ ግና በጀርባው ኮተት ካለው ያ አደጋ ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ እምነት ማንም
የማይወስድብህ፤ የአካባቢን ሰላም ሳይሆን የአንተን ሰላማዊ እንድትሆን ምሪት ነው፡፡ በቃ ታዲያ እምነት ሁሉም እኩል ካላነበበው
እና ካልተረዳው የአንተ ብቻውን በቂ ሆኖ የአካባቢን ሰላም አልያም ፍቅር ያመጣል ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ እምነት ፤ የእምነት
መጽሃፉን ምእራፉን በመጥቀስ ማንበልበል ብቻ ሳይሆን፤ እንዴት እንደምትኖር የሚረዳህ ነው፡፡ ካልሆነ ሸምድደሃል እንጂ ተረድተሃል
ማለት አይደለም፡፡ እምነት ከትእቢት ከጉራ እና ከማንአለብኝነት የሚያወጣ
ነው፡፡ እምነት የአካባቢን ሰላም ለመጠበቅ ዋስትና የለውም፡፡ እምነት አለኝ ብሎ እምነት የለሽ ተግባር ሲፈጽም በምታዩት፤ መደንገጥ አይገባችሁም፡፡
ምክናያቱም ብዙዎች እምነትን እንደባህሪ ሽፋን ይጠቀሙበታል እና፡፡ እንዳልኩት ለእምነቱ አንተ እራስህን ጋራንቲ ካላደረክ ከሌላው
መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ እውነተም ሁሉም ባህሪውን ለውጦ ብታየው ሕይወት በቀለለህ ነበር፤ ግን ይህ ሊሆን አልቻለም፡፡ ስለዚህ አንተ
እራስህ በእራስህ መተማመን አለብህ፡፡ የሚጠቅምህም ነገር እራስህን ከውዥንበር አውጥተህ ካለመጉዋጉዋት እንድትኖር ሰለሆነ፡፡
እምነት አንተን ከሰላም ፈላጊዎች ውስጥ አንዱ እና ያልተስገበገበ ዜጋ
ውስጥ አንዱ ያደርግሃል፡፡ ዋናው እምነት ለአንድ ሰው የሚረዳው ሕይወትን ሳትስገበገብ እና በዚህ አለም ማተርያል እንዳትበገር የሚረዳ
ነው፡፡ ለምሳሌ በማታገኘው ነገር በጉጉት እራስህን እንዳታዞር እና አደጋ ላይ እንዳትወድቅ ያደርጋሀል፡፡ ስለዚህ ወንዶች የእራስ
መተማመናቸውን እንዲያገኙ፤ ሱስ ከሚያሲይዝ ነገር እራሳቸውን መታደግ ብቻ ነው፡፡ ሱስ የያዘው ሰው ምንም በእራስ መተማመን የለለው
ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ድራግ/ጫትም በድራግ ተመዝግቦአል/ ፣አልኮሆል ፣
ሴክስ እና ሙስናን መውደድ፤ ተራ እና ወራዳ እሆነ ነገር ላይ ይጥሉሃል፡፡ እነዚህን የምታደርጋቸው መጥፎነታቸውን እያወክ
በመሆኑ ከእራስህ ጋር ተሙዋጋች ከማድረግም አልፎ፤ እራስህን ከሳሽ ያደርጉሃል፡፡ እነዚህ ነገሮች ሱስ የሚያሲዙ እና ደረጃቸውን
እየቀየሩ የሚመጡ በመሆናችው፤ የበለጠ የሚያስፈልጉህ እንጂ በቃኝ የምትላቸው አይደሉም፡፡ ከህግ ጋርም የሚያጋጩህ፤ ወደወንጀል የማስገባት
ባህሪ ያላቸው እና ጥገኛ የሚያደርገሁ ናቸው፡፡ ጥገኛም የሚያደርጉህ እራሳቸውን ከሱስ የጸዳ ያደረጉእና፤ የሰውን ልጅ እንዴት አድርገው
እንደሚጠቀሙ የሰይታን ጥበብ የተሞላቸው ክፉ እና ጨካኞች ናቸው፡፡ ብዙውን ግዜ ለሱስ የሚጋለጡ የዋሆች እና፤ ደጎች፤ የዚህ አለም
መከራን በጭራሽ መቻል ያቃታቸው ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፡፡ ይህ ማለት ግን ሁሉም ሱስ የለለው እንደእነሱ ጨካን ነው ማለት አይደለም፡፡
እነዚህን ሰዎች መለየት እንድትችል ጠበብን ፈልገሕ ማግኘት ከእራስህ ነው፡፡ ለሱሱህ ስትል ዋጋው ያማይከፈለው ባሪያ ትሆናለህ፡፡
ባርነት ዋጋ ካወጣ፤ ባሪያ ሳይሆን እራስህ የማንክበት ሰራተኛ ያስብልሃል፡፡ ስለዚህ የወንዶች እራስ መተማመን ማጣት ብዙ ግዜ በሱስ
ውስጥ የተደበቀ ይሆናል፡፡ ለእራሳቸውም አይታወቃቸውም፡፡ ወንዶች ሽንፈትን ስለማይቀበሉ፤ በአፋቸው በሚናገሩት ቃላት ብቻ መተማመናቸውን
ለማሳየት ይጥራሉ፡፡ ግን ይህ ድብቅ አይሆንም፡፡ ለሌላው ማለቴ ነው፡፡
በእራስ መተማመን የለላት ሴት ብዙውን ግዜ ግዜዋን የምታሳልፈው፤
በመዞር እና ወሬ በመሰብሰብ ይሆናል፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክናያት፤ ሰው በመፈልግ እዛም እዛም በመሄድ ጉልበቱዋን አልያም ሰዎች
የሚፈልጉትን አገልግሎት በመስጠት እንደምትወዳቸው ለማሳየት ትጥራለች፡፡ ተቀባይነትን ሰፍ ብላ በመጠበቅ፡፡ እነሱም እሱዋን እየተጠቀሙ
እለሉበት ያሉላት በማስመሰል ወሬ አቀባባይ እና አዳማጭ በመሆን ይገለገሉባታል፡፡ እንግዲህ በእራስ መተማመን የለላት ሴት ጊዜዋን
ገንዘቡዋን እና ጉልበቱዋን የምታባክን ናት፡፡ በየቤቱ የሚዞር ሴት አጠገብ ወሬ አታውራ፡፡ ምክናያቱም ነገም ሌላ ሰው ፍለጋ ሌላው ቤት ስለምትሄድ እዛም ለመጠጋጋት የምታወራው
ይሆናል እና፡፡ ለማንኛውም ሴት ጉዋደኛ በፈለገች ቁጥር እና በጣረች ቁጥር ወሬኛ የማድረጉ አዝማሚያ ስለሚኖር ሴቶች ሊጠነቀቁ ይገባል፡፡
ይህንም በእራስ መተማመን የሚያሳጡት ሌሎች ሴቶች መሆናቸውን ሴቶች ሊገነዘቡ ይችላሉ፡፡ እሱም ብዙውን ግዜ አንዳንድ ሴቶች ሁልግዜ
ከእነሱ የሚያሳንሱት ሴት ይፈልጋሉ፡፡ በአስተሳሰብም፤ በፋይናንሻልም በትምህርትም ሳይበልጡ በልጠው ለመታየት የመብለጥ አባዜ የወረሳቸው
አሉ፡፡ እነሱም ይህንን የሚለማመዱት፤ ያልሆኑትን ነኝ በማለት በአፋቸው የሚዘሩት ዘር ነው፡፡ የዋህም ይህንን እውነት አድርጎ በመቀበል፤
የምትበልጣት ይመስላት እና፤ በእራሱዋ ላይ ሌላዋን መሾም ትጀምራለች፡፡ አለቃዋ ታደርጋታለች፡፡ ግን ባዶ መሆኑዋን አታቅም፡፡ ምንም
የለላት መሆኑዋን አይገባትም፡፡ እሱዋም የእሱዋን ታላቅነት እያወራቻት በሄደች ቁጥር ይህቺኛዋ እያነሰቸ ትሄዳለች፡፡ በዚህ የተነሳ
ወሬ አምራች እና ምንይዠ ልቅረብ ማለት ትጀምራለች፡፡ ወሬ ካጣችም መፈልሰፍ ይመጣል፡፡ በቃ ከዛም ያቺ የማነስ ዘር በላይቱዋ ላይ
የዘራች ሴት ውድቀቱዋ እያደገ እያደገ ይሄድና በመጨረሻም ተወዳጅ ሆና በየቤቱ ዘዋሪ ትሆናለች፡፡ ብዙው እራሱን የሚገነባው የሌላውን
ማነስ ሲሰማ ነውእና፡፡ እሱዋም በዚህ መልኩ የእራስ መተማመኑዋን በማጣት ኢንፎርሜሽን ሴንተር ሆና ትቀራለች፡፡ ስለዚህ ምክሬ እራሳቸውን
በአለባበሳቸውም ሆነ በአነጋገራቸው የበላይ አድርገው ከሚያቀርቡ ሴቶች፤ ሴቶች ቢርቁ መልካም ነው፡፡ አንድ ሰው ስለእራሱ ትልቅነት
ካወራ ጀብዱኝነት ካወራ አንተን እንቺን እያሳነሰችሽ ነውእና፡፡ በእራስ መተማመን ማጣት መንገዱ ሀ ብሎ የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡
ስለዚህ ለአንዳንዱ ጉረኛ ሴት ጆሮን ሸበብ ያዋጣል፡፡ ካልሆነ ነገ ደግሞ ምጥታ አቶ ስብሃትን አልያም ጠቅላይ ሚኒስተር ሀይለማርያም
ዘመዴ ናቸው ብላ፤ ከዛሬ ነገ አማላጅ ትሆነኛለች ብለሽ አገልጋይ
ሆነሽ ትቀሪያለሽ፤ አልያም የሚያሻሹት ድመት፡፡ ያልሆነ እያወሩ ያሳንሱሻል እና ልጄ ሆይ ጠንቀቅ፡፡ ሰላማት ባዩሽ ነኝ፡፡
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen