Samstag, 18. April 2015

ዲሞክራሲ በአይምሮው ያለ ከእጁ ግን ያፈተለከበት፤ ወያኔ ኢሕአዴግ



            እኔ አሁንም ብሆን መኖር የምፈልገው ኢትዮጲያ ነው፡፡ እዚህ ያለሁት ኢትዮጲያ ለመኖር የኢኮኖሚ ችግር ኖሮብኝ አልነበረም፡፡ ሀብታም አይደለሁም፡፡ ግን የራበኝ አይደለሁም ነበር፡፡ እጀ ዶማ እስከሚመስል እሰራለሁ እና ደግሞም አካባቢዬም እንዴት እንደምሰራ ያውቀኛል፡፡  እራሴን ደብቄ እጄን በቀዳዳ ብቅ አድርጌ ባሳያችሁ፤ በእጁ የሚሰራ የወንድ ገቤሬ እጅ ነው የምትሉት፡፡ ስራ አያሳፍርም፡፡ እኮራበታለሁ፡፡ እግዚአብሄር ጥረህ ግረህ ብላ ነው እንጂ ያለው፤ ሰርቀህ አቃጥረህ አወናብደህ ብላ አላለም፡፡ ስለዚህ ለእለት ጉርሴ ካለመልፋት አማራጭ የለኝም፡፡ ታግሎም የሚያወጣኝ ካለእግዚአብሄር ማንም የለኝም፡፡ እኔ መነደር ለመንደር የኢህአዲግ ሰባኪ ሆኘ ገንዘብ ለማግኘት አልራወጥም፡፡ ወሬ ስሰበስብ ወይም ፈጥሬ መንግስት እና ህዝብን በማጋጨት አልተዳደርም፡፡  ይህን አስመስክሬአለሁ፡፡ አገሬ በመግባቴ ወያኔ ነሽ ያለኝም እንደነበር አውቃለሁ፡፡ ኢትዮጲያ ባለመግባት ወያኔ አለመሆንን ማስመስከሪያ መሆኑ መስፈርቱ በምን እና እንዴት እንዳስቀመጡት አላውቅም ነበር፡፡ አልገባኝምም ነበር፡፡ አገሩ ግን ወያኔም ለሆነውም ላልሆነውም መሆኑን ሁሉ ማመን እና መቀበል አለበት፡፡ ትግሉ የመብት ጉዳይ እንጂ የዜግነት ጉዳይ አይደለም፡፡ ስለዚህ ማንነቴን በቀላሉ ወያኔ ገዛ ብዬ የምጥለው አይደለም፡፡ ትግል ሰብአዊ መብትን የተመረኮዘ ነው፡፡ ያልገባው ኢትዮጲያ በመኖሬ አግሎኝ ሊሆን ይችላል፡፡ እሱም አላስደነግጠኝም፡፡ ለፍቸ በአገሬ ለመኖር ግን ቆርጨ የተነሳሁ ሴት ነበርኩ፡፡ ወያኔ ለእኔ አምስት ሳንቲም የሚሰጠኝ ድርጅት አይደለም፡፡ እንዳውም በእኔ እና በመሰሎች ህዝብ የሚተዳደር እንጂ፡፡ ወያኔ ይገዛል ተብሎ አገርን መጥላት እና መሸሽ ፖለቲካ አይደለም ለእኔ፡፡ ይህን ለማለት ሌላ አገር አላገኘሁም፡፡ ጥግ አግኝቼ ሊሆን ይችላል፡፡ ያ ማለት ግን አገር አገኘሁ ማለት አይደለም፡፡ ለእኔ አገር ማለት አንድ ናት እሱዋም ኢትዮጲያ ናት፡፡ እሱዋም ብቻ ስለሆነች ነው እኮ ያስጠጉን አገሮች ብልጭ ሲልባቸው ከአገራችን ውጡ ብለው፤ በእሳት የሚጫወቱት፡፡
            እንዳውም አገሩን ለተወሰኑ ሰዎች እንዲተው በተቃዋሚ ውስጥ ሆኖ አገሩን ባዶ ለማድረግ የሚጥር ቡድን ያለ የመሰለኝ ነበር ሰው ስደትን ሲደግፍ ሳይ፡፡ ብዙ የተሳሳተ የፖለቲካ አካሂያድ ሁሉ ሲፈጸም አይቻለሁ፡፡ ሁሉም እኮ ደፋር ቢሆን እኔ ለምን ፈሪ እሆናለሁ ታዲያ፡፡ ተቃዋሚም ገዢው ፓርቲም ሁሉም የተሳሳተ ህዝብን ያደናገረ ፖለቲካ አካሄያድ ሄደዋል፡፡ ግብር ከፋይ ነው የሚያስተዳድረው የወያኔ መንግስትን፡፡ በዚህ ከሆነ አገር እንዳንገባ የተፈለገው፤ ይህም ሞኝነት ነው፡፡ ሁሉም የሚገነባውን የትም ይዞት አይሄድም፡፡ ተስገብግቦ ሙስናም ውስጥ የገባው እንደማይበላው እናውቃለን፡፡ እግዚአብሄር ብዙ ጥበብ ያለው አምላክ ነው፡፡ አንዳንዱ በመድሃኒት መግዣ ብሩን ያወጠዋል፡፡ አንዳንዱ ወዲያ ወዲህ ሲደብቅ ሲያንከራትት እንቅልፍ አልባ ይሆናል፡፡ በግፍ የተገኘ ገንዘብ እርባና የለውም፡፡ ልጅ አያወጣም፡፡ ይህንን ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ እኔ የእራሴን ሀቅ እንጂ ስለሰው ግብዝነት ብዙም አልጨነቅም፡፡ የእራሴንም በአቅሜ ተወጥቻለሁ፡፡ መወቀስ የሚኖርብኝ ተስገብግቤ የኢትዮጲያን የግብር ገንዘብ አባካኝ ብሆን ነበር፡፡ ይህን ለማድረግ ብፈልግ እንኩዋን እድሉን ለማግኘት የሚያበቃ የፖለቲካ ተሳትፎ የለኝም፡፡ ሰው አይናገርም ማለት ደንቆሮ ነው ማለት አይደለም፡፡ አለመናገርም እንዳውም ብዙ እንድትረዳ የሚያደርግህ ጥበብ ነው፡፡ ብዙ ግዜ፡፡ ታዲያ መጨረሻ ላይ ስትናገር ለምን እና እንዴት እንደምትናገር ታውቀዋለህ ፡፡ዛሬ የምናገረውን አውቃለሁ፡፡ የምመሰክረውንም አውቃለሁ፡፡
           መጨረሻ ላይ በኢትዮጲያ ተስፋ መቁረጥ ላይ ያደረሰኝ፤ ሰዎች ህግ መቼም አይሰራም ብለው፤ በማንአለብኝነት እርህራሄ የለለው ነገር ሲወጡብኝ ስላየሁ ነው፡፡ የቀበሌው ፍርድ ሸንጎ፤ የወረዳው ፍርድ ቤት  ወንብድናን የሚያበረታቱ እንጂ የሚያስተምሩ ሆነው አላገኘሁዋቸውም፡፡ ይቅርታ ፤ በሰው ደረጃ ሁሉም አንድ አይነት ሊሆን አይችልም፡፡  ግና ሕግ ካልሰራች ለእኔ ተቁዋሙ የሚሰራውን ስህተት ሳይሆን የማየው፤ ህግ አፍራሽ አካል እራሱ ወያኔ ኢህአዴግ ያመነው እና የማይቆጣጠረው መሆኑን ነው፡፡ እንደእውነቱ ጠበቃ ማግኘት እንኩዋን ትቸገራለህ፡፡ ምክናያቱም ሚስጥሩን የሚያውቁት እራሳቸው ናቸው፡፡ የከክልኝ ልከክልህ ሁኔታ ከባድ ነው፡፡ ታድያ የሕ ኢህአዴግ ዲሞክራሲን ለማስተማር ችሎአልእን? ወይስ እንዳው የአልበርት አነስታይን አስተማሪ ነው፡፡  የኢትዮጲያን መንግስትን የያዘው አካል በአሁኑ ሰአት ወያኔ ኢሕአዴግ ስለሆነ በመንግስት ስም የሚደረጉ ስህተቶች ሁሉ ኢህአዴግ የጠነሰሳቸው እንጂ የተቃዋሚ ሊሆኑ አይችሉም፡፡   እሱን እንደሚነካው መገንዘብ አለበት፡፡ አንድ ፓርቲ ይህንን ብቻውን ለማስተካከል አይችልም፡፡ እውነትም ለኢትዮጲያ ከታሰበ ተቃዋሚም መሳተፍ አለበት፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲ የለለው አገር፤ አልያም የተከለከለበት አገር እንደእውነቱ ከሆነ በህዝብ ውስጥ መደነጋገር ይፈጠራል፡፡ ይህንን መደነጋገር ደግሞ ማንም ሊያጸዳው አይችልም፡፡ በተቃዋሚ አለመኖር የሚጎዳው እራሱ ገዢ ፓርቲው ነው፡፡ ሰላማዊውንም ምኑንም መለየት አቅቶት ከሁሉ ጋር የተጋጨ እና የሚከበር ሳይሆን የሚፈራበት ደረጃ ላይ ደርሶአል፡፡ ቀና ለውጥ የሚፈልገውን ከሌላውም መለየት ያልቻለበት ሁኔታ አይቻለሁ፡፡ ይህም ከዲሞክራሲ መንገድ አውጥቶታል፡፡ ለኢህአዴግ ዲሞክራሲ በአይምሮው ያለ ግን በተግባሩ ከእጁ የወጣበት ሆኖአል፡፡ ለምሳሌ እራሴ አንድ ምሳሌ ነበርኩ፤ አንዲት የእለት ጉርሱዋን የምታራውጥ ሴት፤ አማራ ስለሆነች ባለፈው ዘመን መተቸት፤ ከውጭ ስለመጣች የዲያስፖራ ሚስጥረኛ መባል፤ ደግሞ እድሜዬ በኢህአፓ ክልል ስለሆነ እንደኢሃፓ በማየት እንዳው በእግር በፈረስ ሲከታተሉት መኖር መቀወስ ነው፡፡ ሌላ አልለውም፡፡ ለእኔ ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም እንጂ፤ ከምንም የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ግንኙነት የነበረኝ እና አባልም የነበርኩ ሴት አልነበርኩም፡፡ ይሁን እና ግን እበላ ያለው እና ምን ወሬ ይዠለት ለቀን አባል ከፋዬ ላቅረብ ያለ፤ እኔ የህግ እርዳታ እንዳላገኝ አድርጎኝ አልፎአል፡፡ ለወንበዴ እና ለሌላ አሳልፎ ሰጥቶኛል፡፡ እንኩዋን ያልሆንኩትን ተቃዋሚ ሆኘ ብገኝ እንኩዋን፤ ይህን ያህል ማግለል እና በደል በአንዴት ሴት ላይ ማሳለፍ፤ በውኑ ጨካኝ እና ግብዝነት ሞኝነት እና ሀላፊነት የጎደለው እውቀት የጎደለው ነበር፡፡
          ታዲያ ዛሬ ዳግም ወደስደት የተጉዋዝኩት፤ መብቴን የረገጡት ሰዎች ወደእራሃብ ጎዞ ሊወስዱኝ ፈታኝ የሆነ ተግባር ስላካሄዱብኝ ብቻ ነው፡፡ ዋንኛው የሴት ትግል በኢኮኖሚ እራስን መቻል ሆኖ ሳለ፤ የኢሀአዴግ አቀንቃኞች ግን የሚፈትኑኝ የኢኮኖሚ ምሶሶዬን በመምታት ነበር፡፡ ይህንን ጉዳይ ይዠ በደህንነቱ ቢሮ ተገኝቻለሁ ደግሞም በተለያየው ፖሊስ ጣቢያ፡፡ ግን ነገሩ ሁሉ የተናቀ ሆኖ ታይቶአል አልፎአል፡፡ እኔም ደም አልቅሸ ወጥቻለሁ፡፡ ነገሩ የሚገርመው ፈሬ ሆኘ አልነበረም ያለቀስኩት፡፡ ብዙ ሰው አንባዬን አይቶታል፡፡ ለወያኔዎችም ድብቅ አልነበረም፡፡ ትናንት ዘሬ እንኩዋን እንደተባለው አስለቃሽ ሆኖ ከሆነ ዛሬ እኔን ማስለቀስ ምን ትርፍ እንዳለው አላውቅም፡፡ እንደእውነቱ በዛሬው የተማመነ የትናንትናውን ማንሳት ባላስፈለገ፡፡  ያለቀስኩት ህጋዊ በመሆኔ እና ህግ አልባ አገር በመኖሬ ነው፡፡ ዲሞክራሲን አስተምራለሁ የሚለው ኢህአዴግ ግን የሚደግፈው ኢዲሞክራቲክ የሆኑትን ነው፡፡ ታዲያ ብዙዎቻችንን እያስገለለ እንደአውሬ ብቻችንን እንድንጣል ማድረጉ ምን ይጠቅመዋል፡፡ ብዙ ያልገቡኝ ነገሮች አሉ፡፡ ሰው  በአገሩ መብላት ካልቻለ የስደተኛው ማእበል ለምን ሊባል እንደማይቻል አሁን አየሁት፡፡ አውቃለሁ መስራት እንደምችል አስመስክሬአለሁ፡፡ መስረቅ እንደምችል አይደለም ያሳየሁት፡፡ እኔ ባዩሽ አበበ ከ0 ተነስቼ መስራት እንደምችል  እና የእራሴን ጉልበት መጠቀም አውቃለሁ፡፡ በሰው ጉልበት ሀብት ማካበት ቀርቶ ፤ የሰው ላብ አልበላም፡፡ በዚህ ላይ እንደእኔ የሆኑ ትግሬም ኦሮሞም ሌሎችም ሴቶች አይቻለሁ፡፡ ለዚህ የአቶ መለስ እህት ምስክር ናቸው፡፡ ከገባችሁ፡፡  ካለምንም የመንግስት ከለላ እየተንገላቱ ሊቁዋቁዋሙ የሚጥሩ ህሊናቸውን ያልሸጡ ብዙ ሴቶችም አሉ፡፡ ደግሞም በመንደር አውደልዳይነት ሰውን በዘሩ፤ በመልኩ እና በጥቃቅኑ ስነልቦናውን እያደቀቁ ወሬ እያመላላሱ የሚበሉ፡፡ ጉሮሮአችን ደርቆአል፤ ደክሞናል፡፡ ድራግ ያደነዘዘው ፖሊስ እኮ እርዳንም ቢሉት ጆሮው አይሰማም፡፡ እሱ የሚሰማው በገንዘብ ነው፡፡ እንደሰለጠነው ልል አልችልም፤ አደሰልጣኙ አይደለሁም እና፡፡ ኢሕአዴገፍ ዲሞክራሲ ካለ፤ ለምን እራሱን አልመረመረም፡፡ ዲሞክራሲስ ካለ እንዳው ይህ ሁሉ ፖሊስ ምን አስፈለገ፡፡ ምን ያስበረግጋል፡፡ ኢሕአዴግ ከገባ ጀምሮ ህዝብን የሚያረጋጋ ነገር ምን ሰራ፡፡ ምን የፖለቲካ ለውጥ አመጣ ያው ነው ያው ነው፡፡ ጭራሽ አቶ መለስ ከሞቱ በሁዋላ ብዙ ገሀድ የወጣ ነገር ተፈጠረ፤ ላቡዋ በቂጡዋ እየተንጠፈጠፈ የምትሰራንም ሴት ገረድ ማለት፡፡
       በህግ የበላይነት የማያምኑ እና በኢህአዴግ አባጋሮች ሀግ የማይባሉ  ብዙዎች ናቸው፡፡ ተቃዋሚም ቢመጣ ብዙ ኢሕአዴግ ገደል የከተተው የሰው ባህሪ ተፈጥሮአል፡፡ የሚያዩትም የሚሰሙትም በገንዘብ ነው፡፡ ወዳጄ ገንዘቤን እኮ ግብር ከፍዬ ከመንግስት ጋር የምካፍለው እንዲጠብቀኝ እንጂ የገንዘብ እና የጫት ሱስ ላደነዘዘው በጎን እየደጎምኩ በአገሪቱ ለመኖር ፍቃድ መውሰድ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ የሚከፍላቸው ደመወዝ ሊያንስ ይችላል፡፡ እኔ ግን ተደራቢ ከፋይ መሆን አልፈልግም፡፡ ሙስናን እቃወማለሁ፡፡ በአገር አላስኖር ማለት እራሱ የሙስናው ማደግ ውጤት ነው፡፡
በቸር ባዩሽ








       















Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen