ጀርመን ብዙ አይነትን ህመም በማከም በማዳን እና መድሃኒታቸውም ታላቅ ውጤት ያመጣ መሆኑ በአለም ይታወቃል፡፡
መድሃኒታቸው፣ ሕክምናቸው፣ መኪናቸውም እና ሞተሮቻቸው ጫማቸውም ጭምር አንቱ አስብሎአቸዋል፡፡ ሰውን መፍጠር ብቻ የቀራቸው እስኪመስል ድረስ ስምእና ዝናን አትርፈዋል፡፡
ሜድ ኢን ጀርመኒ ዛሬ የሚገኘው በነዳጅ ሚሌንዮሮች አገሮች ነው፡፡ የጀርመን ነገር ተፈላጊ እና ውድ መሆኑ ሚስጥርነት የለውም፡፡ ሰው በእሳት እና በተለያዬ አደጋ አልያም ተፈጥሮ የተበላሸውንም አስተካክለው
ቆንጆ እንደነበረ አድርገው በመሸኘት ያስደስቱታል፡፡
የህክምናን ነገር ሁሉ አለም የሚያደርገውን
ያደርጋሉ፡ እንደእውነቱ ቢበልጡ እንጂ የሚያንሱ አይደሉም፡፡ መቸም ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ ነውእና፤ ገንዘብ ካለ የማይሰሩት አፍንጫ የማያስተካክሉትም ጡት ነበር፡፡ እንደእኔ እድሜ ዘል ያደረገውን ቆዳ ሁሉ ሴቱ ከፈለገ እና ከከፈለ የውጭ አካሉን የ20 አመት ኮረዳ አድርገው ይሸኙታል፡፡
እስፖርት እንዳያዳብረው የሰነፈውንም
ሀብታም፤ ቀደው ጠግነው ጡንጫ ሰርተው፤ ተዋቂ ስፖርተኛ አድርገው ይለቁጣል፡፡
ቂጥ አልባ ተብላ የተሰደበችን ሴት፤ ያበጠ እና የሚያስጎመጅ ቂጥ ያበጅላታል፡፡ ወዳጄ ገንዘብ ካለህ ከእግዚአብሄር
ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃን ሕክምናቸው ይዞታል፡፡
የጀርመን ሀኪም የጀርመን ሳይነስ ሁሉን ለማስደሰት ሌት ተቀን ተግቶ ይሰራል፡፡ የጀርመን መንግስት ብታመም ያሳክመኛል፤
ቢርበኝ ያበላኛል እንጂ እኔን እየሸላለትኩ
ለመቀየር እና ጨምዳዳ ቆዳዬን ለመወጣጸር እና እንደያነዬው
እድሜ አከል ለመመለስ ግን አይከፍልልኝም፡፡
ይህ ቅንጦት ነው፡፡ ሰብአዊነት ደግሞ ከቅንጦት ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡
ሰብአዊ ፍጡር በተፈጥሮአዊ
ይዘቱ ግን የሚገባውን ህግ ደንግጎታል፡፡
አገርህ ሞተ ብለህ ከፈን የለበሰውን፤ እዚህ አገር አይምሮው ወይም ልቡ አልሞተም ብለው፤ በማስተንፋሻ
እንደገና ያሰናብቱታል፡፡ ይገርማል፡፡
ሳይንስ የደረሰበትን፡፡ ለካስ ልብም አይምሮም የተለያዬ ሞት አላቸው፡፡ ያም ሆነ ይህ ያሰንብቱዋትም ነፍስ ግን ጌታ ባለ ሰአት ታፈተልካቸዋለች፡፡ እጃቸው ሊያስገቡዋት ያልቻሉት ነፍስን ብቻ ይመስላል፡፡
ነፍስን ቢይዙ ኖሮ እኛም እሰየው አምላክን በእጃችን አገኘነው ብለን በጉቦም በምንም በጸባይም እጥፍጥፍ ብለን ፤ ፖለቲከኞች ባዘጋጁዋት ገነት ውስጥ በገባን ነበር፡፡
ታዲያ ጥቂት ነገር ግን ጀርመን በጀርመን አገር እንዳይፈጸም
የደነገገው ህግ አለ፡፡ ሳይንስ ተመራምሮ ለማወቅ መብቱ ገደብ የለለው ይመስላል፡፡ ይሁን እና ግን የምርምሩን ውጤት ካለሕግ ድንጋጌ መፈጸም አይችልም፡፡
ይህ ማለት ምርምሩን ወደህግ ማቅረብ እና ማጸደቅ እንጂ እርምጃ ላይ ለማድረግ ህግ ያስረዋል፡፡
ህጉም የሚደነገገው የህዝብን የልብ ትርታ በማዳመጥ ነው፡፡ የጀርመን በላጩ ህዝብ፤ የሳይንስን ልቅነትም የሚደገፍ አይደለም፡፡
ለምሳሌ ሰሞኑን አነጋጋሪ ምእራፍ የከፈተው፤ በጀርመን ሴትን በሳይንስ መልክ ልጅ መስጠት ነው፡፡ ካለወንድ ግንኙነት ብቻ ዘሩን ከፍሪጅ አውጥተው ሴትን ማስረገዝ ባይቸገሩም፤ ግን ሕጉ አይፈቅድላቸውም፡፡ የጀርመን ህዝብ የካቶሊክ እና የኢቫንጀሊስ
እምነት ተከታይ ነው፡፡ እምነታቸውም አይፈቅድም፡፡
የእግዚአብሄርን ነገር ይጻረራል ብለው ያምናሉ፡፡ የማያምኑትም ደግሞ ሳይነስ የሚሰራው ነገር ሁሉ ተፈጥሮን የሚያበላሽ በመሆኑ በማለት የማይደግፉት በሽ ናቸው፡፡ ሳይንስ እስከምን እንደሚሄድ ገደቡን ሊያሳዩት የሚፈልጉ ይመስላሉ፡፡
የጀርመን ህዝብ ቢችል ማዳበሪያ የነካውንም ምግብ መመገብ አይፈልግም፡፡ ግና ያ የሚቻልበት ምእራፉን አልፈናል፡፡
አለም ተጣባለች ሁሉንም መመገብ የሚችል ከሀጢያጥ የራቀ ሕይወት የለንም፡፡ ስለዚህ ሳይንስን መጠጋት ግድ ብሎአል፡፤ በማዳበሪያ የዳለበ ምግብ እና የሰባ ሰንጋ፤ በእንኩቤተር
የተፈለፈለ እንቁላል መመገብ፡፡ ሁሉም ለጤና ጠንክ ነው ቢባልም ካለዚህ መኖር አልተቻለም፡፡
ይሁን እና ደግሞ፤ እንደልብ ብሆን ምን አገባችሁ የሚልም ሞልቶአል፡፡ ማዳበሪያ ያልገባበትን መብላት ይፈልጋል ተፈጥሮ አትደግፈውም በማለት፤ ጤና አይደለም በማለት፡፡ ወንድ ወንድን ማግባት ሴት ሴትን ማግባት ግን እግዚአብሄር አይከለክልም
የሚሉት መደነጋገርም አለም ፈጥራለች፡፡ ለማንኛውም፤
ልጅ እንደውሃ የጠማው ማሕጸንም መፈጠሩ አልቀረም እና፤ በስለትም በምንም ሊያገኝ ያልቻለው፤ እኔ እግዚአብሄርን
ምንአደረኩት እና ነው ብሎ እልክ የሚገባም አይጠፋም፡፡
በዚህ የተነሳም ሳይንስን አምሎኮው ያደረገ፤ በሳይንስ የሚደሰትም አልጠፋም፡፡ ግና ሕግ ምንን ይፈቅዳል ምንን ደንግጎአል አለ፡፡ ታዲያ ሳይነስም በሕግ ለማሰር የጀርመን ህግ ሀይለኛ ነውእና፤ ቀጥል የሚል ትእዛዝን እስካላገኘ ድረስ ማንኛውንም ውጤቱን ለመተግበር ትውር አይልም፡፡ አሜሪካ የፈቀደችው የሞት ፍርድ፣ ወይም በአሰቃቂ ህመም ታሞ የመጨረሻው የህመም መስታገሻ መድሀኒት ያልረዳውን ፤የታመመን ሰው ግደሉኝ ብሎ የሚለውን ሀኪሞች ከስቃይ ገድለው እንዲገላግሉት
፣ እና በሳይነስ ልጅን መፍጠር ህጉ አይፈቅደውም፡፡
ይህ ሳይንስ በሕግ መገደቡ፤ እየቻሉ እንደማይችሉ
አስመስሎአቸው እስከዛሬ ቆይተዋል፡፡
ይህ እንዳለ ሆኖ ግን መሞትም የፈለገ ልጅም የጠማው የሌላ አገርን ህግ ለመጠቀም ግን የሚያስቆም የተደነገገ ህግ ያለ አይመስልም፡፡ የሰው ልጅ በምኑም በምኑም መብቴ ተነፍጎአል በማለት መብቴ ለሚለው ጥያቄ የወደሚያሙዋላለት
አገር ይሄዳል፡፡ የሌላውንም ህግ ተጠቅሞ ያሰከረውን እና ስነልቦናውን የጎዳውን ፍላጎቱን ለማሙዋላት ተገድዋል፡፡ ለምሳሌም የወንድ እና የሴት ጋብቻም በአንዳንድ አገሮች ሲፈቀድ በሌላው በመፈቀዱ መጋባት የፈለጉ ከአገር አገር ተራውጠው ሲፈጽሙ አይተናል፡፡
ብቻ ሁሉ አገር የሁሉን አይነት መብት ፈቃጅ አይደለም፡፡ አንዱ አንዱን ይፈቅዳል ሌላው ሌላውን፡፡ አለማችን የሁሉን ፍላጎት ለማሙዋላት ብዙ በር የከፈተች መሆኑዋን እያየነው ነው፡፡ ፍላጎት ሲያድግ ደግሞ በእርግጥም ምን ልስራ ያስብላል፡፡ የሰው ልጅ ባህሪያችን አንዳንደዬም ውሻ እንኩዋን ከሚያደርገው
በታች ዝቅ እያልን እንደምነሄድ እያየነው ነው፡፡ በህግም አይደንገግ እንጂ፡፡ ሽማግሌ ከትንሽ ህጻን ጋር የሴክሹዋል ሪሌሽን በመፈለግ እያበዱ ሱሳቸው ብዙ ህጻናታን እያበላሹ እየገደሉ መታየታቸው፤
ለአደባባይ አልተሰወረም፡፡ ፍላጎት ሲበዛም ልቅነትን ያመጣል እና፡፡
ታዲያ ዛሬ በጀርመን አገር የቤት ውስጥ መነጋገሪያ፤ የአደባባይ መሳቂያ የሚዲያ መተቻ፤ የፖለቲከኞች
እራስ ምታት፤ የሳይንስ በር መክፈቻ ሆኖ የሰነበተው እና አሁንም ያለው የወ/ሮ Annegret R. የምትባለው አንዲት የ65 አመት አሮጊት በሉዋት ባልቴት በጀርመን
የማይፈቀደውን ሕግ ጥሳ በዚህ እድሜዋ ወደ ሌላ አገር በመሻገር፤ ሳይንስ በፈጠረላት መንገድ ተጠቅማ አርግዛ በመመለሱዋ ነው፡፡
የ65 አመቱዋ አዛውንት፤ የልጅ እጦት ነው እንዲሕ ያሰከራት እንዳይባል፤
የ13 ልጆች እናት ናት፡፡ እንዳውም የመጨረሻዋ ልጁዋን የወለደችው በ55 አመቱዋ ነው፡፡ ሁሉም ግን በወንድ ግንኙነት በጤነኛ መንገድ
የተወለዱ ቢሆንም፤ በመምህርነት ሙያ የምትተዳደረው ወ/ሮ ግን አሁንም ልጅ አልበቃትም፡፡ ባልም ወይም ወንድ በጎኑዋ አለመኖሩም
የልጅ አምሮትዋን ሊቀንሰው አልቻለም፡፡ በዚህም የተነሳ ያበደ እና ሃላፊነት የጎደለው፤ በእራስ ወዳድነት የተመሰረተ እርምጃ ወስዳለች፡፡
እሱም እድሜዋ እንኩዋ ያማይፈቅድላትን፤ ማሳደግ እችላለሁ ወይ ጉልበት አለኝ ወይ የሚለውን ሳታመዛዝን በገንዘብ የገዛችውን የዘር
ፍሬ ተጠቃሚ በመሆን ከጀርመን ውጭ በመሄድ አርግዛ ተመልሳለች፡፡ የሚገርመው የሚደንቀው እግዚአብሄርም አምሮትዋን እና ይልቡዋን ስቃይ በማየት ይመስላል፤ አንድ ልጅ የተመኘችው
የበርሊኑዋ ወ/ሮ አንድ ሳይሆን በአንደዬ አራት መንትያ ማርገዙዋ ነው፡፡ አነበባችሁ፡፡ ተባረኩ፡፡ ባዩሽ ነኝ ከጀርመን አደባባይ፡፡
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen