Samstag, 11. April 2015

ጦርነት ጋባዡ የወያኔ የዲሞክራሲ ፖለቲካ




              ደርግ ገዢ በነበረበት ሰአት፤ የነበረው ወያኔ የበተነው መከላከያ ሰራዊት ግን የደርግ ያልነበረ፤ በሀይለስላሴም የነበረ ከመላው ኢትዮጲያ ብሄር ሳይለይ እና እምነት ሳይለይ የተዋቀረ ነው፡፡ ውጊያውም ከአንድነት ፍቅር የተነሳ ለአንድነት ነበር እንጂ ለንዋይም እንዳልሆነ ሁሉም ልቡ ያውቀዋል፡፡ መንግስቱም ብዙ ሕዝብ ቢጨርስም፤ እሱም የሚያወራው ስለብሄር ሳይሆን ስለአንድነት ነበር፤ አንድ የሆነ ኢትዮጲያ የሚል ስም ነበረ በሰው አይምሮ፡፡“ ኢትዮጲያ ትቅደም“ ነበር፡፡ በቃ የብሄር ስም ጠቅሶ አንዱን በአንዱ አልኮነነም፡፡ ስለዚህ አንድ ነገር የኢትዮጲያን ህዝብ የሚያገናኘው ነበር፡፡ እሱም ኢትዮጲያ አንድ ህዝብ፤ አንድ አገር፤ ዳር ድንበርህን አትቁረስ ጠብቅ ነበር፡፡ እንግዲህ ደርግ በአንድ ቴማ ላይ አሳልፎአል፡፡ እሱም ወደድንም ጠላንም አንድነት ነበር፡፡ ኤርትራንም  ህዝቡዋንም በጉልበት ኢትዮጲያዊ ለማድረግ ጥሮአል፡፡ ደርግ ግን ኤርትራ ወግቶናል አልያም ልገንጠል ብሎአል እና፤ እናንተን ሻቢያ ናችሁ ብሎ ጠርጥሮ የኤርትራን ህዝብ ከማሃል አገር አላፈናቀለም፤ አላንገላታም፤ ከህዝቡ ማሃበራዊ ሕይወት ነጥሎ እንዲገለል አላደረገም፡፡
        የእሱ የአንድነት አላማው ግን በወያኔ እና በሻቢያ ተሸንፎአል፡፡ በመነጋገር ሳይሆን፤ በመስማማት ሳይሆን እና በምርጫ ውሳኔ ሳይሆን በጦርነት ተሸንፎአል፡፡ ሁለቱም የሚያውቁት ጦርነትን ነው፡፡  የህዝቡን ፍላጎት የጠየቀ እና ያካተተ፤  ወያኔም ሆነ የደርግ መመሪያ የላቸውም፡፡ ሁለቱም አምባገነኖች ናቸው፡፡ ክህዝቡ ጋር የሚያገናኛቸው ጦረኛ የሆነውን መምረጥ እና ማዋጋት ነበር፡፡ ሁለቱም የኢትዮጲያን ህዝብ አዋግተዋል፡፡ ለሞት እና ለእልቂት ዳርገዋል፡፡ አንዱ ሻቢያን ለመምታት ሌላው ሻቢያን በመደገፍ፡፡ ሻቢያን ለማጠፋት ደርግ ተንቀሳቅሶአል፡፡ ሻቢያን ወግኖ ወያኔ ተንቀሳቅሶአል፡፡ ሁለቱም ግን የተጠቀሙት የኢትዮጲያን ህዝብ ነው፡፡ በቃ ይህ ያየነው የኖርነው ሀቅ ነው፡፡ ሁለቱም ደግሞ የፖለቲካ ተቃዋሚያቸውን እየመቱ ያጠፉ ፤ ማንንም የማይሰሙ፤ የጦር ጀግና ብቻ ነበሩ፡፡ ደርግም በዚህ የተነሳ አንድነትን እንኩዋን የሚፈልገውን አካል ለተካሄደው ጦርነት አጋዥ አልነበረም፡፡ እንዳውም በማንም ይሁን በማንም እንዲሸነፍ እና ከኢትዮጲያ እንዲጠፋ ይፈልጉ ነበር፡፡ ምክናያቱም ተቃዋሚን በአደባባይ ይረሽናቸው፤ በአዋጅ የሞት ፍርድ በግልጽ ያስበይንባቸው ነበር እና፤ እንደሰው በላ ይታይ ስለነበር ነው፡፡ ደርግ አላማው ሁሉ ኤርትራን ማዳን ነበር፡፡ ኤርትራን እስከቀይ ባህር ኢትዮጲያ ማድረግ፡፡ ልብ በሉ፡፡ ስለዚህ ደርግን የወጋ ሁሉ ሻቢያን የወገነ ተብሎ የሚበየንበት የኤርትራ ጉዳይ የአንድ አገር ጉዳይ አጣብቂኝ ውስጥ አስገብቶት ስለነበር ፤ እንደአስገንጣይ በማየት ብዙ ምሁሮችን እና ኢትዮያን በእውቀታቸው ሊታደጉ የሚችሉ ጨርሶአል፡፡ ደርግ የፈራውም አልቀረ፤ ኤርትራ በወያኔ ብርታት በሻቢያ በተጠቀመው የቶር ስልት የተጠቀመውን ተጠቅሞ፤  ለአንደዬ እና ለመጨረሻ ግዜ መገንጠሉዋ እውን ሆነ፡፡
         ሻቢያ አላማው ኤርትራን ከኢትዮጲያ መገንጠል ነበር፤ በፈለገው መንገድ አላማውን ያሳካ ጀግና ፓርቲ ነው፡፡ ኢትዮጲያውያኑን ሴቱንም ሆነ ወነዱን ፤ ፖለቲካ ፓርቲዎችንም በዛን ሰአት ተጠቅሞም  ቢሆን፤ ገዝቶአቸውም ሆነ በፍቃደኝነት ያዘውም፤ አላማውን እግብ ያደረሰ ለኤርትራ ህዝብ ጀግና የሆነ ፓርቲ መሆኑ፤ በህዝቡ እልልታ እና ደስታ በወቅቱ ያየነው ነው፡፡ ከኢትዮጲያ መገንጠል ያመጣላቸውን ትርፍ እንግዲህ እራሳቸው ነው የሚያውቁት፡፡ እኔ ተጠቅመዋል ወይም ተጎድተዋል ብዬ ለመደምደም አልችልም፡፡ ሰው ለእራሱ እራሱ ይወቅ፡፡ በቂ ተመክሮ እና ልምድ አካብተዋል፡፡ ኢሳያስ አፈወርቄ ግን ህዝቡ በወቅቱ የጉዋጉዋበትን ነጻነት የሚለውን ነገር ፈጽመውለታል፡፡  እንዳውም ብዙዎች ሻቢያ የሚለውን ስም የጀግና መግለጫ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር፡፡  ሻቢያ በኤርትራ ህዝብ የሚወደድ የሚወደስ የተዘመረለት የተዘፈነለት ነበር፡፡  የዛሬውን አያድርገው እና ለማለት አልችልም፡፡ ግን ዛሬም የኤርትራ ህዝብ አድግር አውጭኝ ከአገሩ በየክፈላተ ሀገሩ እየተሰደደ ነው፡፡ ወያኔም ከዘመናት ጭቆና አላቀኩህ ያለው የኢትዮጲያ ህዝብም እየተሰደደ በየክፍለ አለማቱ እየተሰደደ ነው፡፡ ለማንኛውም  ወያኔ በሻቢያ ተደግፎ አዲስ አበባ ይግባ፤ ወይም ሻቢያ ወያኔን ተጠቅሞ ኤርትራን የማስገንጠል ድል ይቀዳጅ የማውቀው ነገር የለኝም፡፡
ግን ሁለቱም መረዳዳታቸው አለምም ሆነ እኛም የማንክደው የቅርብ ግዜ ታሪክ ነው፡፡ ወያኔም በኢትዮጲያ ላይ ስልጣናቸውን ካደላደሉ በሁዋላ፤  አንድ ሰው ኤርትራን እንዳይነካ እንዳያስብ፤ ህዝቡዋንም መብታቸው ነው ኢትዮጲያ መኖር ብሎ ነገረን አስረዳን አስገደደን፡፡ ይባስ ብሎ ህገመንግስቱም ላይ የመገንጠልን መብት ደነገገ፤ አበረታታ፡፡ ሌላውም ብዙ ተስፋ ጥሎበት ወያኔ ለሉአላዊነት የሚያስብ ነው ብሎ ሆ አለለት፤ መገንጠልን የሚያልምም ሌላ ቡድን አይጠፋም እና፡፡ መፍተሄ ግን መገንጠል እንደሆነ የሚያጤን የለም፡፡ ብዙ ግዜ የመገንጠል አላማ የሚገነጥለውን ህዝብ ለማሳደግ ሳይሆን፤ አሰቃይቶሃል ተብሎ ጥላቻ ሰባኪዎች ያስቀመጡለትን ለመበቀል ይመስላል፡፡
በዛን ግዜም ኤርትራውያን ኤርትራም ተገንጥላ እንደልብ ዘና ብለው በኢትዮጲያ ህዝብ ወዲያ እና ወዲህ እያሉ መኖር ጀመሩ፡፡ ግና ደግሞ ወያኔ የኢትዮጲያን ህዝብ የመገዛት አቅሙን ቀላል መሆኑን፣  ጸጥ ብሎ መገዛት  የሚችል  መሆኑን እና ቤተመንገስት ያሉ ገዢዎችን እንደሚፈራ እንደሚንቀጠቀጥ ከተረዱ በሁዋላ፤  ሻቢያ አታስፈልገኝም ከእንግዲህ በማለት፤ ኤርትራዊ የሚባል አይኑን እንዳላይ በማለት በድንገተኛ የኤርትራውያኖች የጅምላ ዲፖርቴሽን መካሄድ ጀመረ፡፡ ደግሞ የኢትዮጲያን ህዝብ አንድ ሰው ከኤርትራውያን ጋር ግንኙነት እንዳይኖረው በማለት ጣቱን ቀሰረ፡፡ ኤርትራውያኖችን ሰላም የሚል ሁሉ እንደሻቢያ መፈረጅ መጣ፡፡ እነሱን ያገዘ የደበቀ ወዮለት ተባለ፡፡ ቤቱ ሁሉ ታመሰ አገር ታመሰ፡፡ የተዋለደው ባልና ሚስት እናት እና ልጅ ተለያዬ፡፡ ይህ ግን የአብሮ መኖር ፈተና በደርግ ግዜ የተደረገ አልነበረም፡፡ ደርግ ውጊያው ያነጣጠረው ከሻቢያ ወታደር ጋር እንጂ ከህዝቡ ጋር አልነበረም፡፡ ኤርትራውያኖችም በሰላም ከሚኖሩባት ኢትዮጲያ፤ ከሚፈቃቀሩት ጎረቤት እንደእርግማን፤ በድንገተኛ መልኩ የተዋለደው ሁሉ ፤ ንብረታቸውን ሜዳ ላይ በማፍሰስ፤ ያሰማሩትን ሳይሰበስቡ፤ ያበደሩትን ሳይረከቡ፤ የተበደሩትን ሳይከፍሉ፤ የጋገሩትን ሳይበሉ፤ ያቦኩትን ሳይጋግሩ ከመቅጸበት እየታፈሱ ወደ ኤርትራ ተጉዋዙ፡፡ ከጤፉ አገር ጎጃም፤ ከጥራጥሬው አገር ወሎ፤ ከቡናው አገር ኦሮሚያ ክልል፤ ከሙዙ አገር ደቡብ ፤ ከሰሊጡ አገር ጎንደር፤ ከገብሱ አገር መንዝ ፤ ከሰንጋው አገር አሩሲ ለአንደየእና ለመጨረሻው ተለዩ፡፡ የማስታውሰው የኢትዮጲያ ህዝብ ግን አማራው ደቡቡ ምስራቁ ምእራቡ፤ ከእነሱ ጋር አብሮ የበላው ነጠላውን እያንጠለጠለ  ኤርትራውያኖችን ያሉበትን ፍለጋ ቀጠለ፡፡ አብሮ የመብላት ባህል አስተሳስሮት ነበር እና፡፡ ወግ ነው ስርአት ነው እምነት ነው የሁለታችንም አንድ ባህል ነበረእና፡፡ በክፉ ግዜ የሚሸሽ እንደዛሬው አልነበረም፡፡ ዛሬ ብዙው ከፍቅር ባህል የታጠበ ይመስላል፡፡ ወያኔ ዘመናዊ የሰለጠነ አደረገው፤ በእሱ አስተሳሰብ፡፡ የኤርትራ ዘር ያለበትን መደበቅ የደፈረውም ደበቃቸው፡፡
            የኢትዮጲያም ህዝብ ስላላገዘው ነው ነገሩ ደርግ የተሸነፈው፡፡  ሰውም ገብቶት ይሁን ሳይገባውም እንበል፤ ጠልቶት ነበርእና፡፡ እንዳውም ፤ „ቂጡን በሳንጃ ካልወጉት አይነሳም“ እያሉ ኮለኔር መንግስቱ  እራሳቸው ሕዝቡ ወጣቱ ወያኔን እንዲወጋ ብዙ የቅስቀሳ ጥረት አድርገው ነበር፡፡ የሰማ ግን አልነበረም፡፡ „የእያንዳንድህ ቤት ይንኩዋኩዋል “ ደግሞ  የመጨረሻው ለኢትዮጲያ ህዝብ የተውት የፖለቲካ ትንቢት ነበር፡፡  የኢትዮጲያ ወጣት ወዶ ዘማች አልነበረም፡፡ ስለዚህ ዋናው መከላከያ ሰራዊትም ይህንን ውጊያ ሊቁዋቁዋመው አልቻለም፡፡ ደርግ ከምእራቡ አለም መገለልም ጋርም ፈታኝ ወቅት ነበረው፡፡ምእራቡ አለምን ቢወግን ኖሮ ለመላው አፍሪካ የሚበቃ አንድ ለማድረግ የሚችል የጦር መላ እና ስትራቴጄ የሚያውቅ  ጀግና ብልህ ሰራዊት አቅፎ ነበር፡፡ የአንድነቱም የሚለው የፍቅር ዘር በአይምሮው ያንዣበበ የፍቅር እና የነቃ ትውልድ ግዜው አፍርቶ ነበር እና፡፡ በወጣቱ አይምሮ ሪቮሊሽን የሚል የጋራ አንድ ቃል ነበርእና፡፡
       እማንክደው  ሀቅ ኢትዮጲያ ያልቻለችው ጥሩ ዲሞክራሲን አምኖ ተቃዋሚውን ነጻነት ሰጥቶ ለምርጫ የሚያበቃ የፖለቲካ መሪ ማግኘት እንጂ፤ የጦር መሪ የምታጣ አገር አይደለችም፡፡ ህዝቡ በሙሉ ጥሩ የተሳካለት ጀግና ወታደር የሚወጣው ነው፡፡ ይህ በአለም አልተካደም፡፡ የትም አገር ዘምቶ አሸንፎ እና ጎበዝ ተብሎ ይሚወጣ ሰራዊት እናፈራለን፡፡  ነጥዬ እኔ ትግሬ ፣ አማራ፣ ኦሮሞ ወይም ሌላ እያልኩ እያወዳደርኩ ማነው ጀግናው አልልም፡፡ ከሁሉም ውስጥ ጀግና ጦረኛ የወጣው እና በብዙ መልኩ ያስመሰከረ ነው፡፡ ሞሶሎኒን  ካለጫማ አሸንፎአል፤ ኮሪያን ዘምቶ የአሸናፊነት ሊሻን ተሸልሞአል፡፡  ደግሞም አሁንም ህብረብሄሩ ያለውን እየፈጸመ እያሸነፈ ነው፡፡  ደርግ አልያም ወያኔ ሳይሆን ሕዝቡ ጀግና ወታደር የመሆን አቅም እና ተሰጥኦ አለው፡፡ ለጦርነት ፈሪ አይደለም፡፡ ስለዚህ የሚቀጣጡቡት አይደለም፡፡ ወያኔ ኢትዮጲያን ኢትዮጲያ ለማድረግ ጦርነት ኑ ግጠሙኝ የሚለው እኮ፤ እሱ የያዘውም ጦር ኢትዮጲያዊ መሆኑን አልተረዳም፡፡ እርግጥ ነው፤ ሌላውም የሚነሳው ኢትዮጲያዊውን  ነው እሱም ጀግና ለቅሞ ይዞ እንደሚነሳ ይታወቃል፡፡ በቃ በጦርነትም ከተባለ፤ ኢህአዴግ የሚጋብዘው እኮ አሁንም ጀግናን ነው፡፡ ጀግና ለጀግና አንድ ህዝብ ኑ ተዋጉ ይገርማል ግብዣው ለነገሩ፡፡ በቸር ባዩሽ  

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen