ለምሳሌ ድሮ በእኛ ግዜ፤ የክርክር መድረክ፤ የድራማ ግሩፕ፡፡ የሙዚቃ ክበብ፤
የበጎ አድራጎትት ድርጅት፡፡ በቃ ወጣቱ በሆቢ የተጠመደ ነበር፡፡ በውነት ይህ ሁሉ ነገር የተፈቀደ ነበር፡፡ ወጣቱ ዘወትር በስራ
የተጠመደ፤ ነበር፡፡ የስፖርት ክበብ ነበር፡፡ የባልትና ነበር፤ ለሴቱ፡፡ ሲንጀር ይማራል፤ ጥልፍ ዳንቴል መስራት፡፡ በቃ፡፡ ገንዘብ
እኮ አናገኝበትም፡፡ ግን ዘወትር አይምሮአችን በስራ የተጠመደ ነበር፡፡ ሕዝባዊ ኑሮእድገት የሚባል ዘርፍ ብዙ አክቲቪቲዎች ነበሩ፡፡
ይታያችሁ ከደርግ በፌት ነው፤ የነበረውን ነው የምነግራችሁ፡፡ ዛሬ ግን ችግሩ ሆቢ ጠፋ፡፡ ያጠፋውም የደርግ ለውጥ ጀምሮ ይመስለኛል፡፡
በደርግ ግዜ ይህ መሰል ሆቢ አልነበረም እኮ፡፡ ይታያችሁ 7ኛ ክፍል ሆነን በእንግሊዘኛ ክርክር መከራከር እንታዘዝ ነበር፡፡ ደርግ
አዎ የኪነጥበብ ሁኔታ እራሱ እየመረጠ ለፖለቲካው መነቃቃት የሚጠቀምበት ነበረው ይመስለኛል፡፡እኔ ደርግ ከገባ በሁዋላ ከኢትዮጲያ
ወጣሁ፡፡ ብዙም ለመናገር አልችልም፡፤ ግን ስመለስ የነበረው ሁሉ ጠፍቶ ነው ያገኘሁት፡፡ አዲስ ነገርም ምንም አልነበረም፡፤ የገነነው
ቢኖር ዘፈን ነበር፡፡ በዛው ቀጠለ እና ደግሞ እየባሰ እየባሰ እየቀለጠ
እየተረሳ ሄደ፡፡ ዛሬ ሆቢ አይፈለግም ለምን ገንዘብ አያመጣም አሃ፡፡ ሌላው አሁን የክርክር መድረክ በጣም ይጠቅም ነበር ቢኖር
ኖሮ፡፡ ምክናያቱም ከትንሽነትህ ጀምሮ ለሁለት የተከፈለው አስተሳሰብ ይሙዋገትበት ነበር፡፡ ሳይሰዳደብ ሳይዘላለፍ፡፡ ታዲያ እከሌ
አሸነፈ ይባላል፡፡ መቀናናትም መጣላትም አልነበረም፡፡ እንዳውም በሚቀጥለው የሚሰጠንን ሰፍ ብለን በወራፋ በጉጉት ካለመጠበቅ በቀር፡፡
ይህ ክበብ የምወደው ነበር፡፡ ክርክር እኮ እንድትተማመን የሚያደርግህ
ነው፡፡ ምነው ዛሬ ያ አፈር በላ፡፡ ወጣቱ ታዲያ ዛሬ ማን ያስለመደውን የት የለመደውን ታዲያ ዛሬ ያምጣው፡፡ እንዳውም አፈር ድሜ
ብላ፤ አንተ ባላገር ያልሰለጠንክ ብሎ ድብን አድርጎ ስድብ ክርችም፡፡ ገና መቶ አመት ይገዛሃል ብሎ ዛቻ ፍርድ፡፡ ለምን ግን መቶ
አመት መግዛት እንዳለበት አያስረዳህም አያሳምንህም፡፡ አልያም በመሃይም መገዛት ሰልችቶኛል ይላል እንጂ ጥፋቱን ለማሳየት ግን ደፋ
ቀና አይልም፡፡ ፍጥቻ ብቻ፡፡ ጥላቻ ብቻ፡፡ እኛ ገና በለጋ እድሜ ስንከራከር ተማሪው ግጥም ብሎ እያጨበጨበ በሚስቀው እየሳቀ ነበር
የሚመለከተው፡፡ ዛሬ ድግሞ ማነው ህዝብን የሚያስተምረው፡፡ እንኩዋን ሊያስተምር የተማርነውንም አስጠፋችሁን እኮ፡፡
አይገርማችሁም ያነዬ የቤተክርስቲያንም ማህበር ሴት የምትሳተፍበት
እኮ ተጀመረ፡፡ በክፈልሀገር ነው የምነግራችሁ፡፡ እንደመአት ያየውም
አልጠፋም እኮ፡፡ አዎ የባህል ሪቮሊሽን ማለት ይህ ነው፡፡ ጦርነት የለለው ሪቮሊሽን በሀይለስላሴ ግዜ ነበር፡፡ ወታደር ያላሳለፈ፤
ያላስገደደ፡፡ እንደጉድ እግዚዮ የሚያስብል ባህል ሰንጥቀናል፡፡ ጀምረነዋል፡፡ እኔ አንዱዋ ነበርኩ፡፡ ምንአልባትም አይን ያፈጠጥኩ፡፡
እግዚአብሄርን እወደው ነበር፡፡ ለምን አልዘምርም ለምን ከበሮ አልጨብጥም ብዬ ልቤ በቅናት የተቃጠለብኝ፡፡ የታገልኩ ያፈጠጥኩ ጥያቄ
ያቀረብኩ ነበርኩ፡፡ ዛሬ አይደለም ይህ አይመቸኝም ይህን እፈልጋለሁ ይህ ለምን አይሆንም የምለው፡፡ ገና ያነዬ ነው ልጅ እያለሁ፡፡
ዛሬ በወያኔ ግዜ አይደለም እኮ የጀመርኩት መብት የሚለውን ነገር፡፡ ፓርቲ አልነበርኩም፡፡ ፓርቲ ምን እንደሁ አላውቅም፡፡ ፖለቲካ
ምን እንደሁ አላውቅም፡፡ ያው ተከራክሮ ተሙዋግቶ ተነጋግሮ አስረድቶ ማሸነፍ መማር ነበር ስራችን፡፡ ገና በለጋ እድሜ እንደጡጦ
አጉርሰውናል ክርክርን መነጋገርን፡፡ አስተምረውናል፣ አስረድተውናል፡፡
ከሴት እኮ የመጀመሪያዋ የቤተክርስቲያን ማህበርተኛ አንዱዋ እኔ ነበርኩ፡፡
ዛሬ እኮራለሁ፡፡ የእራስህ ጉዳይ አንተ ይህን ባታስተውለው፡፡ እኔ ግን የተሸጋገርኩበትን እኮራበታለሁ፡፡ የፈለኩትን በትግል አድርጌአለሁ፡፡
ታግዬ ወጥቻለሁ፡፡ ዶክተር ባዩሽ አለመባሌን አትመልከት፡፡ አይምሮዬን ግን እንዲያስብ እንዲያመዛዝን የሚያደርጉትን ነገሮች፤ በአስተሳሰብ
እድገቴ ላይ ሰርቻለሁ፡፡
አይደለም ወዳጄ፤ ለፊቴ ሜካፕ አይደለም ለሰውነቴ ልብስ፤
ለጸጉሬ ቀለም አልነበረም የማስበው፡፡ ልመለስ የማልፈልግበት ትብትብ ነገር ጥዬ መውጣት ነበር የምፈልገው፡፡ በቃ አድርጌዋለሁ፡፡
ከዛ አልፌ እኮ ነው ከደሴ በወሎ ፈረስ አውቶብስ ተጭኜ አዲስ አበባ ገብቼ ቴሌቪዝን ደሴ ሳይገባ፤ አዲስ አበባ በሩቅ እያየሁት
ምንነቱን ሳላውቅ፤ በጋምበር ጀት ተጭኘ ፈረንጅ አገር የገባሁት፡፡
ፈደንጅ አገር መግባት ፤ይህ እድገት ነው አልልህ አየደለም፤ ወዳጄ፡፡ ግን አንዲት በወገቡዋ ገንቦ እየተሸከመች እንቸት እየለቀመች
ያደገች ልጅ ማን ያስበው ነበር፡፡ አስተሳሰቤ መለወጡ ግን እረድቶኛል፡፡
ታግሎ መውጣት ነው ወዳጄ፡፡ አዎ እንጀራ በቅጠል ከመጋገር ወጥቻለሁ፡፡ ውሃ በወጌበ ከመሸከም ወጥቻለሁ፡፡ አመሰግናለሁ ያንን ዘመን፤
ያስተማሩኝ ማልቀስ አልነበረም፡፤ ተሙዋግቶ ተከራክሮ ማሸነፍ ነበር፡፡ ድልን ነበር ያስተማሩኝ፡፡ መዝሙር ክበብ ውስጥ“ ሀይለማርያም
ማሞ የጦሩ ገበሬ“ ፈረሱን እንደሰው አስታጠቀው ሱሪ“ እያልን እንድንዘምር መምህራኖች ያስተምሩን ነበር፡፡ ቲያትር ሰርተን አቅርበናል እኮ ቤተክርስቲያን ውስጥ፡፡ ንግስት እና ንጉስ
ሆነን፡፡ ወቅሰን ነው ለዚያውም፡፡ ከንጉሱ የሚፈለገውን ለባላባቱ አሳይተናል፡፡ ግን ንጉሱ በህይወት ነበሩ እኮ ያነዬ ፡፡ በማእረግ ነበሩእኮ፡፡ እኛ ተዋናይ
ነን፡፡ ተዋናይ የተሰጠውን ሆኖ ማሳየት ነው፡፡ መስተዋት ነው፡፡ ባላባቱን እንዲያስቡ አድርገናል፡፡ አይተውናል አጨብጭበዋል፡፡
ደስ እያላቸው አይተዋል፡፡ የባህል ለውጡ አልከፋቸውም፡፡ ያነዬ እኮ
ቴሌቪዝን የለም ደሴ፡፡ በምን አየንእና ነው ስልጣኔን፡፡ ማን አስተላለፈልን፡፡ ፈረንጅ የሚያደርገውን በኢንተርኔት አናይም ነበር፡፡
ግን እንፈጥር ነበር፡፡ ቴያትር በስማቸው ሰርተን ፤ አልተቆጡንም፡፡ አልተገረፍንም አላሰሩንም፡፡ ለምን መሰላችሁ እራሳቸው እንዲህ
ሁነን እንድንወጣ አስተምረውናል እኮ፡፡ ልጆች ነን ሁሉን ጨብጠናል፡፡ ገና ያላደግን፤ ህልም ያለን የነበረን፡፡ እንዲያ
ነበር አስተሳሰባችን ያደገው፡፡
እነ አቶ መለስ እኮ የያነዬ ተማሪዎች ናቸው፡፡ የዛሬ አይደሉም፡፡ ለውጡ ጥሩም ሆነ መጥፎ እንለውጣለን ብለው የተነሱ
ያነዬ በክርክር መድረክ ዘመን የነበሩ ትንንሽ ተማሪዎች አድገው ነው፡፡ ኢህአፓ በለው ኢሳፓ ወያኔ እና ደርግ አልያም ሚኤሶን የያነዬ ለጋ ሰዎች ሁሉም በዚህ ትምህርት ዘርፍ፤ በትንሽነት
በተለያየው የወጣቶች ክበብ አሳልፎአል፡፡እረ የስካውትስ ክበብ እንዴት
ይረሳል፡፡ በናታችሁ፡፡ የእነ አቶ መለስ በለው የእነ ኮለኔር መንግስቱ፤ አልያም የሳይንቲስቶቻችን የዶክተሮቹ የጀግና ወታደሮች
አልያም ለለውጥ የሚታገሉ የታገሉ እኮ ዝምብለው አልመጡም፡፡ እድሉ የነበራቸው ናቸው ለዛ ለወጣቶች ክበብ ክርክር፡፡ ባይሳተፉም
የሚሳተፉትንም አይተዋል፡፡ ከሀይለስላሴ ግዜ በሁዋላ ያሉ ግን የተማሩትን እንኩዋን ሌላው እንዲማር አልፈቀዱም እንኩዋን አዲስ የለውጥ
ባህል ሊያስተምሩን፡፡ ቢወራ ልማት ልማት፤ ፎቅ ፎቅ፡፡ የት አለ ያ በሚጠቅመው እና በማይጠቅመው ላይ የሚያከራክር፤ የሚያወያይ
የሚያነጋገር፡፡ እረ የት ገባ፡፡ ግርም ብሎኝ እኮ ነው፡፡ ታድያ ወዳጄ እኔ ባዩሽ ሰንትን ነገር እየሰነጠኩ የመጣሁ ዛሬ ለምንድን
ነው በኢህአዴግ ግዜ የማቆመው፡፡ ለምንድን ነው፡፡ ተቃዋሚ ናት ደጋፊ ናት እየተባልኩ የምጠረጠረው፡፡ አስተሳሰብ እኮ ምንግዜም
ማደግን አብሮ መጉዋዝን ይጠይቃል፡፡ እንዳው ተቀበል ብቻ ሳይሆን ለምን እንደምቀበል ምክናያቱንም ጨምር አቅርብ፡፡ አይምሮ የጦርነት
ቦታ ነው አንጎልህ ተዋጊ ወታደር፡፡ ይሰራል ያነቃቃል ይቀጥላል፡፡ ለስጋ አይደለም አይምሮ የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ነው፡፡
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen