በውነቱ የሴቶችን ችግር ተቃዋሚም ሆነ ገዢው ፓርቲ መፍተሄ ሊሰጠው አይችልም፡፡ ምክናያቱም ህግን ማስፈጸም የሚችለው
አካል ሁሉ በቂ የሆነ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን መጥፎ እንደሆኑ እና እንዴት መረዳት እንዳለባቸው፤ ጉዳቱስ ምን እንደሚመስል
ምንም አይነት ትምህርትም ሆነ ንቃተህሊና የሰጣቸው ዮፖለቲካ አካል ስለሌለለ ነው፡፡ በአጠቃላየይ የሴቶች ጉዳይ በኢትዮጲያ ግንዛቤን
የሚያስጨብጥ ስራ አልተሰራም፡፡ ያሰበውም የለም፡፡ አዎ የሴቶች እኩልነት ተብሎ በሁልም ይነገራል፡፡ ግን „ መጣፈጥሽ ቀርቶ ግምሽ
በለለቀኝ“ ሆነእና ነገሩ፤ ከአፍ ወሬ ያላለፈ እና ዝም ብሎ የውጩችን
ዲሞክራቲክ ነን ከሚለው ፕሮፖጋንዳ የተለዬ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡ የሚገርመው ሕግ አውጪዎችም ሆነ ሕጉን አስከባሪዎቹ የሴት ችግር
ምንነቱንም የሚያውቁት አይደለም፡፡ የሴት የመጀመሪየያው ቀዳሚው ነጻነቱዋ ባሉዋን መፍታት እና ማግባት ላይ የተወሰነ እኩይ ምግባር አይደለም፡፡ የሴቶች
ትግል ትዳርን የሚከለክል አይደለም፡፡ ይህ ውሸት የሆነ እይታ፤ ያልነቃ ህሊና የሚያስበው ነው፡፡ በውንድ ግንኙነት ብቻ የተመሰረተ ችግር አይደለም፡፡ ብዙ የታዘብኩት ፤ የሴቶች
ትግል ማለት ባልእና ሚስትን በማፋታት የሚያበቃ አልያም የተወሰነ ደግሞም ሴቱዋን ሳታገባ የሚያስቀር አይነት እኩልነት አይደለም፡፡
ይህ ከሆነ እኩልነት ሳይሆን ጎዶሎነት ነው፡፡ የሴቶች ትግል ማለት፤ የመጀመሪያው ሴትንም በእኩልነት ከኢኮኖሚ ጥገኝነት የሚያወጣት
ዋንኛውን ትግል መስፈረት የሚመለከት ትግል ነው፡፡ በኢኮኖሚ እራሱዋን ያልቻለችን ሴት ከወንድ ለመለየት መጣር ይህ እራሱ ሴቱዋን
ከቤት ወደልመና የሚከት አልያም ወደሴት አዳሪነት የሚገፋፋ ነው፡፡
በዚህም የተነሳ ሴት ለምታደርገው ማንኛውም የኢኮኖሚ
ተጽእኖ ማንም የሚረዳት የሚተባበራት አካል የለም፡፡ እንዳውም ሴት እንድትሰራ ድሮም አልተከለከለችም፡፡ግን እንድትቀጥልበት እና እንድታድግ የሚያደርጋትን
ቀውስ ሊነሳላት ቀርቶ ጭራሽ የበለጠ በየአቅጣጫው እንድትበዘበዝ እና ሞራልዋ እንዲነካ የሆነበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡ ለምሳሌ
አቶ መለስ በስልጣን በነበሩበት ግዜ እንኩዋን የታየው ሁኔታ አሁን ጭራሽ ደዝባው እንዲጠፋ ተደርጎአል፡፡ ይህ የጸጥታ አስከባሪ
እና ደግሞም የመንግስት ህግ አስፈጻሚዎች እራሳቸው ለሴት እኩልነት ያላቸው ክብር ዝቅ ያለ በመሆኑ እና በነጻነቱዋም ስለማያምኑበት፤
ለሚደርስባት ተጽእኖ ሁሉም ምንም አጋዥነት የላቸውም፡፡ ሴቶች ነጻ ወጥተዋል ብለው የሚያምኑት፤በእራሳቸው አካባቢ ያሰለፉዋቸውን
ደመወዝተኞች ከቁጥር በማብዛት ነው፡፡ እነዚህ ሴቶች ደግሞ ከ80% በላይ ያለውን በኢኮኖሚ እራሱን ለማስቻል ያልቻለውን ሴቶች በጭራሽ
አይወክልም፡፡
በአለም ዙሪያ የቢሮ ሴቶችም ቢሆን ያለባቸው ጫና በእውቀት
ሳይሆን ውድድሩ በዘመድ አልያም ሴቱዋ በምታሳየው እራስን አሸብርቆ በማቅረብ መሆኑ ይነገራል፡፡ ይህ ደግሞ የወንድ ወንዶች አለም፤
እንኩዋን ሴትዋን ወንዱንም ያርበተበተ ያስጨነቀ በመሆኑ፤ ይህንን ስራአት ለመቁዋቁዋም አንዳንድ ሴቶች ከመጠን ያለፈ እራሳቸውን በሜክአፕ በውድ
ልብስ እና ጌጣጌጥ በማሸብረቅ፤ ከሌላዋ ሴት በልጠው አለቆቻቸውን ለመማረክ ይጥራሉ፡፡ ትንሹዋን የተፈቀደችውን ቦታ ለማሸነፍ ማለት
ነው፡፡ ይህ ዘወትር እውቀት ያላቸው እና በእውቀታቸው ማደግ ያልቻሉ
ሴቶች የሚያሰሙት ምሬት ነው፡፡ ስራቸውን ከማሳየት ይልቅ መልካቸውን እና አለባበሳቸውን የሚያዩ
ብዙም ወንድ አለቆች እንዳሉ ይነገራል፡፡ እድገት በብልህነት እና በማወቅ ሳይሆን በመልክ መሆኑ ብዙ ግዜ የሴቶችን እድገት እንደሚገደብ
ይነገራል፡፡ ለውድድሩም የገባችው ሴት፤ ደመወዝዋ የሚውለው ለዚሁ ጌጣ ጌጥ በመሆኑ፤ ትዳር ስትይዝ ለትዳሩዋ እና ለቤተሰብዋ አጋዥ
የማትሆንበት ብዙ የኢኮኖሚ ቀውስ ይፈጠራል፡፡ እንዳውም አንዳንድ ባሎች የእሱዋ ደመወዝ ተጨማሪ ወጪ ነው ያመጣብኝ፤ እቤት ብትውል
ይሻል ነበር የሚሉም እና ምሬት የሚያሳዩም አልጠፉም፡፡ ሴቶችን ወንዶች ወደአድባባይ ወደትምህርት ቤት እና ወደማወቅ የሚያደርጉትን
ግፊት እና የአደባባይ አመኔታ ይቀንሳል፡፡ ምክናያቱም በዚህ የአንድ ሱሪ ጫማ ወይም የአንድ ቀሚስ ዋጋ ከአንድ ኩንታል ጤፍ በሚበልጥበት
የኩዋሊቲ ውድድር፤ ሁኔታው የባልንም ባጀት አይነካም ማለት ዘበት ነው፡፡ ለውድድሩ የሚፍጨረጨሩትን ሴቶች ሁኔታ ለመጥቀስ ነው፡፡
አይ እውቀቴ ብቻ ነው የሚበቃኝ ያለች ሴት ስራ ቢኖራትም ምንአልባትም በእውቀት ከእሱዋ በታች ለሆኑ ሴቶች ታዛዥ መሆኑዋ የማይቀር
ሀቅ ነው፡፡ እሱዋ በምትሰራው ሌላው የሚያድግበት ሁኔታም ይኖራል፡፡ ታዲያ የጥቂት ሴቶች እድገት ብዙሃኑን የሚወክል ከቶም ሊሆን
አልቻለም፡፡ፖለቲካው የሚያፈራው ዘወትር በእራሳቸው የተጠመዱ ወንዶች እና ሴቶችን መሆኑ ይታያል፡፤ ለሌላውም አይምሮ እድገት አይተርፍም፡፡
ዘወትር ሴቶች በጌጣ ጌጥ አለም እንዲያምኑ ማድረግ፤ የተማሩትንም ሴቶች ቢሆን ለስደት የሚጋብዝ ነው፡፡ እውጭ አገር ብትመጣ በተማረችው
ስራም ባታገኝም ለቁሳቁሱ መግዣ የእጥፍ እጥፍም ታተርፋለች፡፡ በዚህም የተነሳ ስደቱ እንዳው ስራ ያጣውን ብቻ ሳይሆን፤ በየመስሪያ
ቤቱ የሚደረገው የንዋይ ውድድር እድገቱዋን እንደሚቀንሰው ስለምታውቅ፤ ስደትን ማሰቡዋ የማየቀር ነው፡፡
የሴቶች ችግር መፍተሄ የሚያገኘው፤ በሚንስተር ጽ/ቤት
የተቀመጡ ፖለቲከኞች ፍላጎት ወይም እነሱ ባዘዙት የሚፈጸም ሳይሆን፤ በዚህ ነገር ላይ በመንግስት ተቁዋም ውስጥ ያሉ ወንዶች ፤በሴቶች
ጉዳይ ላይ በቂ ግንዛቤ ሲያካብቱ እና ሲማሩ ብቻ ነው፡፡ ስራ አስፈጻሚዎች
አልያም ሲቪል ሰርቫንቱ፤ ህብረተሱቡ ውስጥ ሰርጾ የሚገባ የለውጥ
ድማም ማሳየት ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ የፈለገው የሴቶች ህግ ቢደነገግ፤ ባልነቃ ህብረተሰብ መካከል የህልም እሩጫ ይሆናል፡፡ ይህም
ያመጣው ቀውስ እራሳቸው በሴቶች ጉዳይ ላይ በቂ ግንዛቤ የለላቸው ፖለቲከኞች በስልጣን ስለሚቀመጡ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ አነሰም
አደገም ማንኛውም ሴት በኢኮኖሚ እራሱዋን ለመርዳት የምታደርገው ጥረት ምንም አይነት እርምጃ ሊያሳይ አልቻለም፡፡ ጭራሽ አቶመለስ
ከሞቱ በሁዋላ በአቶ ሀይለማርያም ግዜ ያለው ሁኔታ፤ የፈጠረው ክስተት፤ ልክ ሴትን እንደፈለክ አድርግ ተብሎ የተላለፈ ሰርኩላር ያለ እስኪመስል ድረስ፤ በህብረተሰቡ መካከል የሚያለቅሱ ሴቶች እጅግ በዝተው
ይታዩ ነበር፡፡ ለምሳሌ አንዲት በቡና ቤት ውስጥ የምትሰራ ወጣት፤ አንዱ ከከፈላት በሁዋላ ሌላው ጉዋደኛውም አብሮ ሊጠቀምባት የተነሳው
ጋጥ ወጥነት፤ አቶ መለስ ከሞቱ በሁወላ በድምቀት ሰብሮ የወጣ አይን አውጣ የሆነ ልቅ ባህል ይዞ የወጣ ነው፡፡ ብዙ ሴቶችም እራሳቸውን
ለማቁዋቁዋም ያደረጉት ጥረት አልሳካ ያለበት እና ተስፋቸው የተሙዋጠጠበት እና ስራቸውን እንዲተው የተደረጉትም አሁን አቶ ሀይለማርያም
በስልጣን ከሆኑ በሁዋላ ነው፡፡ የከተማው ፖሊሶች የሴትን ጉዳይ በንቀት እና በማሾፍ የተመለከቱትም የበለጠውን ግዜ የያዘው ባለፉት
ሶስት አመቶች ነው፡፡ የሴት ሞራል በእጅጉ አዘቅት ውስጥ የገባው ዛሬ አቶ ሀይለማርያም ጠቅላይ ሚኒስተር ከሆኑ በሁዋላ ነው፡፡
በአረብ አገር ሴቶች በእጅጉ መንገላታት እየደመቀ የመጣውም፤ እና ይፋ የወጣውም፤ አቶ ሀይለማርያም ስልጣን ላይ ከወጡ በሁዋላ ነው፡፡
አንዲት ልጅ በ5 ወንዶች አዲስ አበባ ላይ ለአምስት ሬፕ ተደርጋ የሞተችው በአቶ ሀይለማርያም ግዜ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ልቅነት የመጣው
መንግስት ስለፈለገው ሳይሆን በሴቶች ላይ ለሚደረገው ተጽእኖ የተሰጠው ቀዳሚ ስፍራ እንደገና ደዝባው እየጠፋ እና እየተረሳ በመሄዱ ነው፡፡ ከዛም በላይ መንግስት
የሚያደርገው እርብርብ እራሱ ያመነበት ሽብር በሚለው ነገር ላይ እንጂ፤ ባላመነበት ግን ባለው የሴቶች ጉዳይ ላይ አይደለም፡፡ ይህም
እራሴን ስለሚመለከተኝ ነው፡፡ ሰው እራሱን ነጻ ሳያወጣ ሌላውን ነጻነት ማውጣት አይችልም፡፡
ብዙ አደባባይ የማያውቃቸውም ተግባሮች ተፈጽመው፤ ሚዲያ ባለማግኘት አልያም
በባህል ተጽእኖ የተነሳ ተድበስብሶ ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡ ይሁን እና ግን የሴቶች ጉዳይ ህግ በመደንገግ ብቻ የሚያበቃ
አይደለም ብዙ ፍቅር እና መረዳትን የሚጠይቅ ተግባር በመሆኑ፤ የሰው አስተሳሰቡ ካልተቀየረ የህግ የበላይነት መስመር ይይዛል የሚለው
አመለካከቴ ለጊዜው በአለት ላይ ቤት እንደመስራት ሆኖ አይቸዋለሁ፡፡ እኔ እራሴ እዚህ የምጮህ፤ መስራት እና መኖር የምችልበት ሁኔታ
በመናቁ እና በመዘንጋቱ፤ ጥቃቱም የሚያስቆመው የህግ የበላይነት ተፈጻሚ ሆኖ ለማየት ባለመቻሌ ነው፡፡ እኔ ኢህአዴግ ስራ ይሰጠኛል፤
ወይም ተቀዋሚ ሲመጣም ስራ ይሰጠኛል የሚል ህልም ሰንቄ አልተነሳሁም፡፡ ምንአልባት ግን ለዘመናት የተጨቆንኩበትን የታሰርኩበትን
ነጻነት በጸጥታው በኩል ሊተባበሩኝ ጥቃትን ሊከላከሉልኝ ይችላሉ የሚል የህግ ተፈጻሚነትን ፣ተስፋ እና እምነት ይዠ ካልሆነ በቀር፡፡
እሱም አፈርድሜ በልቶአል፡፡ ህግ አስከባሪውም እራሱ አጥቂ ሆኖ በማየቴ እጅግ አዝኛለሁ፡፡ በቃ ሴቶች ስራ ለመፍጠር የሚያበረታታ
አካልም ሆነ የህግ የበላይነት በምድሪቱዋ ኢትዮጲያ ላይ አይታይም፡፡ እንኩዋን ሕጉ ለእኔ ሊወክልኝ ሊሙዋገትልኝ ቀርቶ እራሱ ህጉ
የሚሞግተኝ ሳላጠፋ የሚቀጣኝ እንዲሆን የህግ አስከባሪዎች እና አስፈጻሚዎች አድርገውታል፡፡
ያም ያም የሚጎስማት ሴት ላይ ጭራሽ እራሳቸውም ፖለቲከኞች ህግ አስፈጻሚዎች እና ጸጥታ አስከባሪዎች ለሴት ያላቸው ግንዛቤ
ዜሮ ነው፡፤ ተቃዋሚ የተሻለ ነው ለማለትም ገና አልደረስኩም፡፡ ሁሉም የሚታፈርበት ግን ልትዘነጉት የማትችሉት ጉዳይ መሆኑን ልብ
እንድትሉ እና ንቃተህሊናችሁን እንድታዳብሩ እጠብቃለሁ፡፡ ማንም የፖለቲካ ፓርቲ ለሴት ስራ መፍጠር የሚችልበት ሁኔታ በለለበት ኢትዮጲያ፤
ሰርታ እንዳትበላ እየተደረገ ነው፡፡ ይህም የህግ እና የሚገባው የህግ ትብብር፤ በንግድ ሚኒስተር፣ በአገርውስጥ ገቢ፣ በአስተዳደር፣
እና በጸጥታ አስከባሪዎች ብሎም ማንኛውም ተቁዋም፤ ምንም አይነት የመረዳት እና የመርዳት ንቅናቄ የለውም፡፡ ለዘመናት በጥገኝነት
በድርብ ተጽእኖ ታስራ የምትኖር ሴት፤ ከጉዋዳ ወጥታ ወደአደባባይ እራሱዋን ለመርዳት የምታደርገው ጥረት ጭራሽ አስደንጋጭ፣ አሸማቃቂ፣
አሳፋሪ እና አስበርጋጊ ሆኖአል፡፡
ግን ሰርቼ ደግሞ ዳቦዬን ለመብላት ፤አስፈላጊውን ጸጥታ ለማግኘት እና በሴትነቴ
እንድደገፍ፤ ለማድረግ ደግሞ ፖለቲከኞቻችን ዘመናዊ ፓለቲካን ማራመድ ግድ ባላቸው ነበር፡፡ ግን አሁንም ቢሆን አስተዳደሩ ከወንዶች
አለም፤ ከአባጋሮች አስተሳሰብ የወጣ መስፈርት የወጣ ነገር የለውም፡፡ ኑሮ በጉልበት አድርገውታል፡፡ ስለዚህ ለፖለቲከኞችም እራሱ
በሴቶች ጉዳይ ንቃተ ህሊናቸው ዜሮ በዜሮ ነው ብል ላፍርበት አይገባኝም፤ በአይኔ የማየው በእጄ የዳሰስኩት፤ በአይምሮዬ የማይጠፋ
ጥፋቶችን በመኖር ስቃዩን አይቻለሁ እና፡፡ በዚህ በኩል ሁለቱም ተቃዋሚዎችም ገዢውም ፓርቲም እኩል እንደሚሆኑ አልጠራጠርም፡፡ ምክናያቱም
የሴቶች ትግል ፍቅርን እና መረዳት ይላል እና፡፡ እነዚህ ተረዳድተው ተራርቀው የማይሰሩ ፖለቲከኞች ለሴቶች ለውጥ ያመጣሉ ብዬ መገመት
አልችልም፡፡ ምክናያቱም የሴቶችን ጥቃት የሚያመጣው የሁለቱ ፍጥጫ ወደሃይል የተለወጠ በመሆኑ፤ በህብረተሰቡ መካከልም ለሴት ሀይለኛ
ህግ አላባ ይፈጥራል እና፡፡
ሴቶች በብዛት የሚጠቁት ፖለቲከኞች በጋራ የማይሰሩበት፤ የሚፈራሩበት አገር
ላይ ነው፡፡ ሁከት ለሴቶች እና ለህጻናቶች ጥቃት ከፍተኛ የሆነ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ነው፡፡የሁለቱ መጠባበቅ በህብረተሰብ ውስጥ
ደካማ ሆነው የሚገኙትን የሚያበረታታ ነገር አይፈጥርም፡፡ እነሱንስ
ማን ይጠብቃቸው? እኔ የምታገለው የእራሴም መብት ስለተነካ ነው፡፡ የተነካች እና እኔም እነካለሁ ያለች ሴት ለእራሱዋ ስትል ለመብቱዋ
ትነሳ፡፤ ትንሳ ስል ዘነዘና አንሺ ማለቴ አይደለም፡፡ ግን እራሱ እንዴትም እንደተጨቆንሽ ለማገናዘብ አይንሽን እና አይምሮሽን ክፈቼ፤፤
ሴት ሆይ ሰው እንጂ እንሰሳ አይደለሽም፡፡ እናት፣ እህት፣ ሚስት፣ እና ልጅ ነሽ፡፡ አንቺ የአገር ምሶሶ ነሽ አንቺ ፈረሽ ማለት
አገር የለም ማለት ነው፡፡ቤተሰብም የለም ማለት ነው፡፡ ይህን ወንዶች አያውቁትም፡፡ ምክናያቱም ወንዶችን እንደማትወዳደሪ አድርገውታል
እና፡፡ ሴትን ያልባረከ አይባረክም፡፡ እናት ሆነሽ አምጠሻል ወልደሻል እና፡፡ ትውልድ ሁሉም ሊያመሰግንሽ ይገባል፡፡
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen