Dienstag, 28. April 2015

በእረስ መተማመኑን ያጣ የማይከፈለው ባሪያ ነው




           በራስ መተማመን የሚያሳጣህን ነገር በሙሉ፤ ከሕይወትህ ውስጥ ውልቅ አድርገህ ላታወጣው ትችላለህ፡፡ ግን ከአይምሮህ ውስጥ ማውጣት እና ሀ ብለህ መኖር መጀመር ትችላለህ፡፡ አንተ አዲስ የምትሆነው፤ የጎዳህን የጠቀመህን መለየት ስትችል ነው፡፡ አንዳንድ ግዜ በህይወት ልምዴ ያገኘሁት በኑሮም ሆነ በአስተሳሰብ ደረጃ ከአንተ እንኩዋን ሊቀራረቡ የማይችሉ ሰዎች፤ በአንተ ላይ ተጽእኖ ያሳድሩብሃል፡፡ የሉም እኮ ግን ያሉ ይመስልሃል፡፡ ደግሞም ልብ ብትል ካለስነልቦና ተጽእና እና ካለጉዳት በስተቀር የጠቀሙህ ነገር የለም፡፡ ግን የጠቀሙህ እየመሰለህ እነሱን ተከትለህ እሸኮለሌ ስትል ትኖራለሕ፡፡ እራሱ ሰው የሚያገልህ አንዱ መስፈርት የእሱ ባህሪ አገልጋይ ሊያደርግህ ስለሚፈልግ ነው፡፡ እግዚአብሄር ያለው፤ „ሰውን እንደራስህ አድርገህ ውደድ እንጂ፤ ከአንተ አብልጠህ ውደድ“  የሚል ነገር በማንኛውም ቦታ አልተጻፈም፡፡ የሚገርመው እና በሕይወት ልምድ የተለማመድኩት ነገር፡፡ ከእራስህ አብልጠህ ሰውን የምትወደው፤ በራስ መተማመንህ ሲጠፋ ብቻ ነው፡፡ ካለእነዚህ ሰዎች መኖር የማትችል እየመሰለህ እነሱን ለማቅረብ ትጥራለህ ትሞክራለሕ፡፡ እነሱ ግን አይመጡም፡፡ ወደአንተ የሚመጡት እጅህን አልያም እንደባሪያ አገልግሎትህን ስለፈለጉ ሊሆን ይችላል እና፤ በአካባቢህ ያለውን ወዳጄ የምትላቸውን እና የአንተን ቀረቤታ መመርመር ጥሩ ነው፡፡ ከአንተ በላይ የወደድከው ሰው ምንም ሊወድህ አልያም መውደዱ ቀርቶ ሊያከብርህ አይችልም፡፡


            ለምሳሌ ብዙ ወንዶች በእራስ መተማመናቸውን የሚያጡት፤ በሱስ ሲጠመዱ ነው፡፡ ሱስ ኪስህን የሚያራቁት እና የሌላውን እጅ የሚያሳይ በመሆኑ፤ ጥገኛ እና ተለማማጭ የማድረግ ሀይል አለው፡፡ በዚህም የተነሳ ከሚጫወቱብህ ሰዎች ለመላቀቅ መጀመሪያ ከሱስ የጸዳ ህይወት መጀመር አለብህ፡፡ „እንደእውነቱ ኩራት እራት ነው“ እንዲሉ፤ ብዙ ግዜ የሚረዳህ ለእለት ዳቦ ብቻ ላይ የምታደርገው የአይምሮ መሰባሰብ ሊሆን ይችላል፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ ብዙ ጥበብ የተሞላበት የህይወት ምክር የያዘ መሆኑን የተረዳሁት ካነበብኩት በሁዋላ እንጂ ቄሱ ስለነገረኝ አይደለም፡፡ እኔ አንድ ግዜ መጽሀፍ ቅዱስን ያነበብኩት እንደታሪካዊ መጽሃፍ አድርጌ እንጂ እንደእመነት አልነበረም፡፡ እራሱ እምነትን ለማወቅ፤ ታሪኩን እና አመጣጡንም መረዳት መልካም ነውእና፡፡ እዚህ ላይ የምናገረው ስላነበብኩት እንጂ፤ ማንኛውም የእምነት መጽሃፍ ለሕይወት አስተማሪነት እንዳለው፤ ለአንድ ሰው እራሱን እንዴት እንደምትገለገልበት የሚረዳሕ የህየወት ማንዋል ነው ብዬ እገምታለሁ፡፡ ብዙ ግዜ የሀይማኖት መሪዎች ከደረሰባቸውም ወይም ከሌላ ስውር አላማ ጋር በማያያዝ በኢሞሽን ሊሰብኩት ይችሉ እና አንተን ሊያስቱህ ወይም ደግሞ ይህስ ይቅርብኝ ብለህ እንድትሸሽ ሊያደርጉሕ ይችላሉ፡፡ ይሁን እና ግን እኔ ሁሉንም የምለው፤ የእምነት መጽሃፍ በእራሱ ምን እንደሚል በእራስህ ካለማንም መሪነት ማንበቡ እና መረዳቱ ከዛም መከተሉ ጥሩ ነው፡፡ ይህ ከሆነ አንተ ያገኘሀውን እውቀት ማንም ሊቀማሕ አልያም ሊያበላሽብህ አይችልም፡፡
እኔ እንደተረዳሁት እምነት የሌላውን እምነት እንዲያጠፋ የተዘጋጀ አልመሰለኝም፡፡ ይህ ለመሆኑ ምንም አይነት መረጃ የለኝም፡፡ ግና በጀርባው ኮተት ካለው ያ አደጋ ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ እምነት ማንም የማይወስድብህ፤ የአካባቢን ሰላም ሳይሆን የአንተን ሰላማዊ እንድትሆን ምሪት ነው፡፡ በቃ ታዲያ እምነት ሁሉም እኩል ካላነበበው እና ካልተረዳው የአንተ ብቻውን በቂ ሆኖ የአካባቢን ሰላም አልያም ፍቅር ያመጣል ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ እምነት ፤ የእምነት መጽሃፉን ምእራፉን በመጥቀስ ማንበልበል ብቻ ሳይሆን፤ እንዴት እንደምትኖር የሚረዳህ ነው፡፡ ካልሆነ ሸምድደሃል እንጂ ተረድተሃል ማለት አይደለም፡፡  እምነት ከትእቢት ከጉራ እና ከማንአለብኝነት የሚያወጣ ነው፡፡  እምነት የአካባቢን ሰላም ለመጠበቅ ዋስትና የለውም፡፡  እምነት አለኝ ብሎ እምነት የለሽ ተግባር ሲፈጽም በምታዩት፤ መደንገጥ አይገባችሁም፡፡ ምክናያቱም ብዙዎች እምነትን እንደባህሪ ሽፋን ይጠቀሙበታል እና፡፡ እንዳልኩት ለእምነቱ አንተ እራስህን ጋራንቲ ካላደረክ ከሌላው መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ እውነተም ሁሉም ባህሪውን ለውጦ ብታየው ሕይወት በቀለለህ ነበር፤ ግን ይህ ሊሆን አልቻለም፡፡ ስለዚህ አንተ እራስህ በእራስህ መተማመን አለብህ፡፡ የሚጠቅምህም ነገር እራስህን ከውዥንበር አውጥተህ ካለመጉዋጉዋት እንድትኖር ሰለሆነ፡፡

          እምነት አንተን ከሰላም ፈላጊዎች ውስጥ አንዱ እና ያልተስገበገበ ዜጋ ውስጥ አንዱ ያደርግሃል፡፡ ዋናው እምነት ለአንድ ሰው የሚረዳው ሕይወትን ሳትስገበገብ እና በዚህ አለም ማተርያል እንዳትበገር የሚረዳ ነው፡፡ ለምሳሌ በማታገኘው ነገር በጉጉት እራስህን እንዳታዞር እና አደጋ ላይ እንዳትወድቅ ያደርጋሀል፡፡ ስለዚህ ወንዶች የእራስ መተማመናቸውን እንዲያገኙ፤ ሱስ ከሚያሲይዝ ነገር እራሳቸውን መታደግ ብቻ ነው፡፡ ሱስ የያዘው ሰው ምንም በእራስ መተማመን የለለው ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ድራግ/ጫትም በድራግ ተመዝግቦአል/ ፣አልኮሆል ፣  ሴክስ እና ሙስናን መውደድ፤ ተራ እና ወራዳ እሆነ ነገር ላይ ይጥሉሃል፡፡ እነዚህን የምታደርጋቸው መጥፎነታቸውን እያወክ በመሆኑ ከእራስህ ጋር ተሙዋጋች ከማድረግም አልፎ፤ እራስህን ከሳሽ ያደርጉሃል፡፡ እነዚህ ነገሮች ሱስ የሚያሲዙ እና ደረጃቸውን እየቀየሩ የሚመጡ በመሆናችው፤ የበለጠ የሚያስፈልጉህ እንጂ በቃኝ የምትላቸው አይደሉም፡፡ ከህግ ጋርም የሚያጋጩህ፤ ወደወንጀል የማስገባት ባህሪ ያላቸው እና ጥገኛ የሚያደርገሁ ናቸው፡፡ ጥገኛም የሚያደርጉህ እራሳቸውን ከሱስ የጸዳ ያደረጉእና፤ የሰውን ልጅ እንዴት አድርገው እንደሚጠቀሙ የሰይታን ጥበብ የተሞላቸው ክፉ እና ጨካኞች ናቸው፡፡ ብዙውን ግዜ ለሱስ የሚጋለጡ የዋሆች እና፤ ደጎች፤ የዚህ አለም መከራን በጭራሽ መቻል ያቃታቸው ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፡፡ ይህ ማለት ግን ሁሉም ሱስ የለለው እንደእነሱ ጨካን ነው ማለት አይደለም፡፡ እነዚህን ሰዎች መለየት እንድትችል ጠበብን ፈልገሕ ማግኘት ከእራስህ ነው፡፡ ለሱሱህ ስትል ዋጋው ያማይከፈለው ባሪያ ትሆናለህ፡፡ ባርነት ዋጋ ካወጣ፤ ባሪያ ሳይሆን እራስህ የማንክበት ሰራተኛ ያስብልሃል፡፡ ስለዚህ የወንዶች እራስ መተማመን ማጣት ብዙ ግዜ በሱስ ውስጥ የተደበቀ ይሆናል፡፡ ለእራሳቸውም አይታወቃቸውም፡፡ ወንዶች ሽንፈትን ስለማይቀበሉ፤ በአፋቸው በሚናገሩት ቃላት ብቻ መተማመናቸውን ለማሳየት ይጥራሉ፡፡ ግን ይህ ድብቅ አይሆንም፡፡ ለሌላው ማለቴ ነው፡፡

           በእራስ መተማመን የለላት ሴት ብዙውን ግዜ ግዜዋን የምታሳልፈው፤ በመዞር እና ወሬ በመሰብሰብ ይሆናል፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክናያት፤ ሰው በመፈልግ እዛም እዛም በመሄድ ጉልበቱዋን አልያም ሰዎች የሚፈልጉትን አገልግሎት በመስጠት እንደምትወዳቸው ለማሳየት ትጥራለች፡፡ ተቀባይነትን ሰፍ ብላ በመጠበቅ፡፡ እነሱም እሱዋን እየተጠቀሙ እለሉበት ያሉላት በማስመሰል ወሬ አቀባባይ እና አዳማጭ በመሆን ይገለገሉባታል፡፡ እንግዲህ በእራስ መተማመን የለላት ሴት ጊዜዋን ገንዘቡዋን እና ጉልበቱዋን የምታባክን ናት፡፡ በየቤቱ የሚዞር ሴት አጠገብ ወሬ አታውራ፡፡  ምክናያቱም ነገም ሌላ ሰው ፍለጋ ሌላው ቤት ስለምትሄድ እዛም ለመጠጋጋት የምታወራው ይሆናል እና፡፡ ለማንኛውም ሴት ጉዋደኛ በፈለገች ቁጥር እና በጣረች ቁጥር ወሬኛ የማድረጉ አዝማሚያ ስለሚኖር ሴቶች ሊጠነቀቁ ይገባል፡፡ ይህንም በእራስ መተማመን የሚያሳጡት ሌሎች ሴቶች መሆናቸውን ሴቶች ሊገነዘቡ ይችላሉ፡፡ እሱም ብዙውን ግዜ አንዳንድ ሴቶች ሁልግዜ ከእነሱ የሚያሳንሱት ሴት ይፈልጋሉ፡፡ በአስተሳሰብም፤ በፋይናንሻልም በትምህርትም ሳይበልጡ በልጠው ለመታየት የመብለጥ አባዜ የወረሳቸው አሉ፡፡ እነሱም ይህንን የሚለማመዱት፤ ያልሆኑትን ነኝ በማለት በአፋቸው የሚዘሩት ዘር ነው፡፡ የዋህም ይህንን እውነት አድርጎ በመቀበል፤ የምትበልጣት ይመስላት እና፤ በእራሱዋ ላይ ሌላዋን መሾም ትጀምራለች፡፡ አለቃዋ ታደርጋታለች፡፡ ግን ባዶ መሆኑዋን አታቅም፡፡ ምንም የለላት መሆኑዋን አይገባትም፡፡ እሱዋም የእሱዋን ታላቅነት እያወራቻት በሄደች ቁጥር ይህቺኛዋ እያነሰቸ ትሄዳለች፡፡ በዚህ የተነሳ ወሬ አምራች እና ምንይዠ ልቅረብ ማለት ትጀምራለች፡፡ ወሬ ካጣችም መፈልሰፍ ይመጣል፡፡ በቃ ከዛም ያቺ የማነስ ዘር በላይቱዋ ላይ የዘራች ሴት ውድቀቱዋ እያደገ እያደገ ይሄድና በመጨረሻም ተወዳጅ ሆና በየቤቱ ዘዋሪ ትሆናለች፡፡ ብዙው እራሱን የሚገነባው የሌላውን ማነስ ሲሰማ ነውእና፡፡ እሱዋም በዚህ መልኩ የእራስ መተማመኑዋን በማጣት ኢንፎርሜሽን ሴንተር ሆና ትቀራለች፡፡ ስለዚህ ምክሬ እራሳቸውን በአለባበሳቸውም ሆነ በአነጋገራቸው የበላይ አድርገው ከሚያቀርቡ ሴቶች፤ ሴቶች ቢርቁ መልካም ነው፡፡ አንድ ሰው ስለእራሱ ትልቅነት ካወራ ጀብዱኝነት ካወራ አንተን እንቺን እያሳነሰችሽ ነውእና፡፡ በእራስ መተማመን ማጣት መንገዱ ሀ ብሎ የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡ ስለዚህ ለአንዳንዱ ጉረኛ ሴት ጆሮን ሸበብ ያዋጣል፡፡ ካልሆነ ነገ ደግሞ ምጥታ አቶ ስብሃትን አልያም ጠቅላይ ሚኒስተር ሀይለማርያም ዘመዴ ናቸው ብላ፤  ከዛሬ ነገ አማላጅ ትሆነኛለች ብለሽ አገልጋይ ሆነሽ ትቀሪያለሽ፤ አልያም የሚያሻሹት ድመት፡፡ ያልሆነ እያወሩ ያሳንሱሻል እና ልጄ ሆይ ጠንቀቅ፡፡ ሰላማት  ባዩሽ ነኝ፡፡

Samstag, 18. April 2015

ዲሞክራሲ በአይምሮው ያለ ከእጁ ግን ያፈተለከበት፤ ወያኔ ኢሕአዴግ



            እኔ አሁንም ብሆን መኖር የምፈልገው ኢትዮጲያ ነው፡፡ እዚህ ያለሁት ኢትዮጲያ ለመኖር የኢኮኖሚ ችግር ኖሮብኝ አልነበረም፡፡ ሀብታም አይደለሁም፡፡ ግን የራበኝ አይደለሁም ነበር፡፡ እጀ ዶማ እስከሚመስል እሰራለሁ እና ደግሞም አካባቢዬም እንዴት እንደምሰራ ያውቀኛል፡፡  እራሴን ደብቄ እጄን በቀዳዳ ብቅ አድርጌ ባሳያችሁ፤ በእጁ የሚሰራ የወንድ ገቤሬ እጅ ነው የምትሉት፡፡ ስራ አያሳፍርም፡፡ እኮራበታለሁ፡፡ እግዚአብሄር ጥረህ ግረህ ብላ ነው እንጂ ያለው፤ ሰርቀህ አቃጥረህ አወናብደህ ብላ አላለም፡፡ ስለዚህ ለእለት ጉርሴ ካለመልፋት አማራጭ የለኝም፡፡ ታግሎም የሚያወጣኝ ካለእግዚአብሄር ማንም የለኝም፡፡ እኔ መነደር ለመንደር የኢህአዲግ ሰባኪ ሆኘ ገንዘብ ለማግኘት አልራወጥም፡፡ ወሬ ስሰበስብ ወይም ፈጥሬ መንግስት እና ህዝብን በማጋጨት አልተዳደርም፡፡  ይህን አስመስክሬአለሁ፡፡ አገሬ በመግባቴ ወያኔ ነሽ ያለኝም እንደነበር አውቃለሁ፡፡ ኢትዮጲያ ባለመግባት ወያኔ አለመሆንን ማስመስከሪያ መሆኑ መስፈርቱ በምን እና እንዴት እንዳስቀመጡት አላውቅም ነበር፡፡ አልገባኝምም ነበር፡፡ አገሩ ግን ወያኔም ለሆነውም ላልሆነውም መሆኑን ሁሉ ማመን እና መቀበል አለበት፡፡ ትግሉ የመብት ጉዳይ እንጂ የዜግነት ጉዳይ አይደለም፡፡ ስለዚህ ማንነቴን በቀላሉ ወያኔ ገዛ ብዬ የምጥለው አይደለም፡፡ ትግል ሰብአዊ መብትን የተመረኮዘ ነው፡፡ ያልገባው ኢትዮጲያ በመኖሬ አግሎኝ ሊሆን ይችላል፡፡ እሱም አላስደነግጠኝም፡፡ ለፍቸ በአገሬ ለመኖር ግን ቆርጨ የተነሳሁ ሴት ነበርኩ፡፡ ወያኔ ለእኔ አምስት ሳንቲም የሚሰጠኝ ድርጅት አይደለም፡፡ እንዳውም በእኔ እና በመሰሎች ህዝብ የሚተዳደር እንጂ፡፡ ወያኔ ይገዛል ተብሎ አገርን መጥላት እና መሸሽ ፖለቲካ አይደለም ለእኔ፡፡ ይህን ለማለት ሌላ አገር አላገኘሁም፡፡ ጥግ አግኝቼ ሊሆን ይችላል፡፡ ያ ማለት ግን አገር አገኘሁ ማለት አይደለም፡፡ ለእኔ አገር ማለት አንድ ናት እሱዋም ኢትዮጲያ ናት፡፡ እሱዋም ብቻ ስለሆነች ነው እኮ ያስጠጉን አገሮች ብልጭ ሲልባቸው ከአገራችን ውጡ ብለው፤ በእሳት የሚጫወቱት፡፡
            እንዳውም አገሩን ለተወሰኑ ሰዎች እንዲተው በተቃዋሚ ውስጥ ሆኖ አገሩን ባዶ ለማድረግ የሚጥር ቡድን ያለ የመሰለኝ ነበር ሰው ስደትን ሲደግፍ ሳይ፡፡ ብዙ የተሳሳተ የፖለቲካ አካሂያድ ሁሉ ሲፈጸም አይቻለሁ፡፡ ሁሉም እኮ ደፋር ቢሆን እኔ ለምን ፈሪ እሆናለሁ ታዲያ፡፡ ተቃዋሚም ገዢው ፓርቲም ሁሉም የተሳሳተ ህዝብን ያደናገረ ፖለቲካ አካሄያድ ሄደዋል፡፡ ግብር ከፋይ ነው የሚያስተዳድረው የወያኔ መንግስትን፡፡ በዚህ ከሆነ አገር እንዳንገባ የተፈለገው፤ ይህም ሞኝነት ነው፡፡ ሁሉም የሚገነባውን የትም ይዞት አይሄድም፡፡ ተስገብግቦ ሙስናም ውስጥ የገባው እንደማይበላው እናውቃለን፡፡ እግዚአብሄር ብዙ ጥበብ ያለው አምላክ ነው፡፡ አንዳንዱ በመድሃኒት መግዣ ብሩን ያወጠዋል፡፡ አንዳንዱ ወዲያ ወዲህ ሲደብቅ ሲያንከራትት እንቅልፍ አልባ ይሆናል፡፡ በግፍ የተገኘ ገንዘብ እርባና የለውም፡፡ ልጅ አያወጣም፡፡ ይህንን ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ እኔ የእራሴን ሀቅ እንጂ ስለሰው ግብዝነት ብዙም አልጨነቅም፡፡ የእራሴንም በአቅሜ ተወጥቻለሁ፡፡ መወቀስ የሚኖርብኝ ተስገብግቤ የኢትዮጲያን የግብር ገንዘብ አባካኝ ብሆን ነበር፡፡ ይህን ለማድረግ ብፈልግ እንኩዋን እድሉን ለማግኘት የሚያበቃ የፖለቲካ ተሳትፎ የለኝም፡፡ ሰው አይናገርም ማለት ደንቆሮ ነው ማለት አይደለም፡፡ አለመናገርም እንዳውም ብዙ እንድትረዳ የሚያደርግህ ጥበብ ነው፡፡ ብዙ ግዜ፡፡ ታዲያ መጨረሻ ላይ ስትናገር ለምን እና እንዴት እንደምትናገር ታውቀዋለህ ፡፡ዛሬ የምናገረውን አውቃለሁ፡፡ የምመሰክረውንም አውቃለሁ፡፡
           መጨረሻ ላይ በኢትዮጲያ ተስፋ መቁረጥ ላይ ያደረሰኝ፤ ሰዎች ህግ መቼም አይሰራም ብለው፤ በማንአለብኝነት እርህራሄ የለለው ነገር ሲወጡብኝ ስላየሁ ነው፡፡ የቀበሌው ፍርድ ሸንጎ፤ የወረዳው ፍርድ ቤት  ወንብድናን የሚያበረታቱ እንጂ የሚያስተምሩ ሆነው አላገኘሁዋቸውም፡፡ ይቅርታ ፤ በሰው ደረጃ ሁሉም አንድ አይነት ሊሆን አይችልም፡፡  ግና ሕግ ካልሰራች ለእኔ ተቁዋሙ የሚሰራውን ስህተት ሳይሆን የማየው፤ ህግ አፍራሽ አካል እራሱ ወያኔ ኢህአዴግ ያመነው እና የማይቆጣጠረው መሆኑን ነው፡፡ እንደእውነቱ ጠበቃ ማግኘት እንኩዋን ትቸገራለህ፡፡ ምክናያቱም ሚስጥሩን የሚያውቁት እራሳቸው ናቸው፡፡ የከክልኝ ልከክልህ ሁኔታ ከባድ ነው፡፡ ታድያ የሕ ኢህአዴግ ዲሞክራሲን ለማስተማር ችሎአልእን? ወይስ እንዳው የአልበርት አነስታይን አስተማሪ ነው፡፡  የኢትዮጲያን መንግስትን የያዘው አካል በአሁኑ ሰአት ወያኔ ኢሕአዴግ ስለሆነ በመንግስት ስም የሚደረጉ ስህተቶች ሁሉ ኢህአዴግ የጠነሰሳቸው እንጂ የተቃዋሚ ሊሆኑ አይችሉም፡፡   እሱን እንደሚነካው መገንዘብ አለበት፡፡ አንድ ፓርቲ ይህንን ብቻውን ለማስተካከል አይችልም፡፡ እውነትም ለኢትዮጲያ ከታሰበ ተቃዋሚም መሳተፍ አለበት፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲ የለለው አገር፤ አልያም የተከለከለበት አገር እንደእውነቱ ከሆነ በህዝብ ውስጥ መደነጋገር ይፈጠራል፡፡ ይህንን መደነጋገር ደግሞ ማንም ሊያጸዳው አይችልም፡፡ በተቃዋሚ አለመኖር የሚጎዳው እራሱ ገዢ ፓርቲው ነው፡፡ ሰላማዊውንም ምኑንም መለየት አቅቶት ከሁሉ ጋር የተጋጨ እና የሚከበር ሳይሆን የሚፈራበት ደረጃ ላይ ደርሶአል፡፡ ቀና ለውጥ የሚፈልገውን ከሌላውም መለየት ያልቻለበት ሁኔታ አይቻለሁ፡፡ ይህም ከዲሞክራሲ መንገድ አውጥቶታል፡፡ ለኢህአዴግ ዲሞክራሲ በአይምሮው ያለ ግን በተግባሩ ከእጁ የወጣበት ሆኖአል፡፡ ለምሳሌ እራሴ አንድ ምሳሌ ነበርኩ፤ አንዲት የእለት ጉርሱዋን የምታራውጥ ሴት፤ አማራ ስለሆነች ባለፈው ዘመን መተቸት፤ ከውጭ ስለመጣች የዲያስፖራ ሚስጥረኛ መባል፤ ደግሞ እድሜዬ በኢህአፓ ክልል ስለሆነ እንደኢሃፓ በማየት እንዳው በእግር በፈረስ ሲከታተሉት መኖር መቀወስ ነው፡፡ ሌላ አልለውም፡፡ ለእኔ ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም እንጂ፤ ከምንም የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ግንኙነት የነበረኝ እና አባልም የነበርኩ ሴት አልነበርኩም፡፡ ይሁን እና ግን እበላ ያለው እና ምን ወሬ ይዠለት ለቀን አባል ከፋዬ ላቅረብ ያለ፤ እኔ የህግ እርዳታ እንዳላገኝ አድርጎኝ አልፎአል፡፡ ለወንበዴ እና ለሌላ አሳልፎ ሰጥቶኛል፡፡ እንኩዋን ያልሆንኩትን ተቃዋሚ ሆኘ ብገኝ እንኩዋን፤ ይህን ያህል ማግለል እና በደል በአንዴት ሴት ላይ ማሳለፍ፤ በውኑ ጨካኝ እና ግብዝነት ሞኝነት እና ሀላፊነት የጎደለው እውቀት የጎደለው ነበር፡፡
          ታዲያ ዛሬ ዳግም ወደስደት የተጉዋዝኩት፤ መብቴን የረገጡት ሰዎች ወደእራሃብ ጎዞ ሊወስዱኝ ፈታኝ የሆነ ተግባር ስላካሄዱብኝ ብቻ ነው፡፡ ዋንኛው የሴት ትግል በኢኮኖሚ እራስን መቻል ሆኖ ሳለ፤ የኢሀአዴግ አቀንቃኞች ግን የሚፈትኑኝ የኢኮኖሚ ምሶሶዬን በመምታት ነበር፡፡ ይህንን ጉዳይ ይዠ በደህንነቱ ቢሮ ተገኝቻለሁ ደግሞም በተለያየው ፖሊስ ጣቢያ፡፡ ግን ነገሩ ሁሉ የተናቀ ሆኖ ታይቶአል አልፎአል፡፡ እኔም ደም አልቅሸ ወጥቻለሁ፡፡ ነገሩ የሚገርመው ፈሬ ሆኘ አልነበረም ያለቀስኩት፡፡ ብዙ ሰው አንባዬን አይቶታል፡፡ ለወያኔዎችም ድብቅ አልነበረም፡፡ ትናንት ዘሬ እንኩዋን እንደተባለው አስለቃሽ ሆኖ ከሆነ ዛሬ እኔን ማስለቀስ ምን ትርፍ እንዳለው አላውቅም፡፡ እንደእውነቱ በዛሬው የተማመነ የትናንትናውን ማንሳት ባላስፈለገ፡፡  ያለቀስኩት ህጋዊ በመሆኔ እና ህግ አልባ አገር በመኖሬ ነው፡፡ ዲሞክራሲን አስተምራለሁ የሚለው ኢህአዴግ ግን የሚደግፈው ኢዲሞክራቲክ የሆኑትን ነው፡፡ ታዲያ ብዙዎቻችንን እያስገለለ እንደአውሬ ብቻችንን እንድንጣል ማድረጉ ምን ይጠቅመዋል፡፡ ብዙ ያልገቡኝ ነገሮች አሉ፡፡ ሰው  በአገሩ መብላት ካልቻለ የስደተኛው ማእበል ለምን ሊባል እንደማይቻል አሁን አየሁት፡፡ አውቃለሁ መስራት እንደምችል አስመስክሬአለሁ፡፡ መስረቅ እንደምችል አይደለም ያሳየሁት፡፡ እኔ ባዩሽ አበበ ከ0 ተነስቼ መስራት እንደምችል  እና የእራሴን ጉልበት መጠቀም አውቃለሁ፡፡ በሰው ጉልበት ሀብት ማካበት ቀርቶ ፤ የሰው ላብ አልበላም፡፡ በዚህ ላይ እንደእኔ የሆኑ ትግሬም ኦሮሞም ሌሎችም ሴቶች አይቻለሁ፡፡ ለዚህ የአቶ መለስ እህት ምስክር ናቸው፡፡ ከገባችሁ፡፡  ካለምንም የመንግስት ከለላ እየተንገላቱ ሊቁዋቁዋሙ የሚጥሩ ህሊናቸውን ያልሸጡ ብዙ ሴቶችም አሉ፡፡ ደግሞም በመንደር አውደልዳይነት ሰውን በዘሩ፤ በመልኩ እና በጥቃቅኑ ስነልቦናውን እያደቀቁ ወሬ እያመላላሱ የሚበሉ፡፡ ጉሮሮአችን ደርቆአል፤ ደክሞናል፡፡ ድራግ ያደነዘዘው ፖሊስ እኮ እርዳንም ቢሉት ጆሮው አይሰማም፡፡ እሱ የሚሰማው በገንዘብ ነው፡፡ እንደሰለጠነው ልል አልችልም፤ አደሰልጣኙ አይደለሁም እና፡፡ ኢሕአዴገፍ ዲሞክራሲ ካለ፤ ለምን እራሱን አልመረመረም፡፡ ዲሞክራሲስ ካለ እንዳው ይህ ሁሉ ፖሊስ ምን አስፈለገ፡፡ ምን ያስበረግጋል፡፡ ኢሕአዴግ ከገባ ጀምሮ ህዝብን የሚያረጋጋ ነገር ምን ሰራ፡፡ ምን የፖለቲካ ለውጥ አመጣ ያው ነው ያው ነው፡፡ ጭራሽ አቶ መለስ ከሞቱ በሁዋላ ብዙ ገሀድ የወጣ ነገር ተፈጠረ፤ ላቡዋ በቂጡዋ እየተንጠፈጠፈ የምትሰራንም ሴት ገረድ ማለት፡፡
       በህግ የበላይነት የማያምኑ እና በኢህአዴግ አባጋሮች ሀግ የማይባሉ  ብዙዎች ናቸው፡፡ ተቃዋሚም ቢመጣ ብዙ ኢሕአዴግ ገደል የከተተው የሰው ባህሪ ተፈጥሮአል፡፡ የሚያዩትም የሚሰሙትም በገንዘብ ነው፡፡ ወዳጄ ገንዘቤን እኮ ግብር ከፍዬ ከመንግስት ጋር የምካፍለው እንዲጠብቀኝ እንጂ የገንዘብ እና የጫት ሱስ ላደነዘዘው በጎን እየደጎምኩ በአገሪቱ ለመኖር ፍቃድ መውሰድ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ የሚከፍላቸው ደመወዝ ሊያንስ ይችላል፡፡ እኔ ግን ተደራቢ ከፋይ መሆን አልፈልግም፡፡ ሙስናን እቃወማለሁ፡፡ በአገር አላስኖር ማለት እራሱ የሙስናው ማደግ ውጤት ነው፡፡
በቸር ባዩሽ








       















Freitag, 17. April 2015

አለማችን፤ የሳይነስ እድገት ፤ ሴቱን ወደእብደት




ጀርመን ብዙ አይነትን ህመም በማከም በማዳን እና መድሃኒታቸውም  ታላቅ ውጤት ያመጣ መሆኑ በአለም ይታወቃል፡፡ መድሃኒታቸው፣ ሕክምናቸው፣  መኪናቸውም  እና ሞተሮቻቸው ጫማቸውም ጭምር  አንቱ አስብሎአቸዋል፡፡ ሰውን መፍጠር ብቻ  የቀራቸው እስኪመስል ድረስ ስምእና ዝናን አትርፈዋል፡፡ ሜድ ኢን ጀርመኒ ዛሬ የሚገኘው በነዳጅ ሚሌንዮሮች አገሮች ነው፡፡ የጀርመን ነገር ተፈላጊ እና ውድ መሆኑ ሚስጥርነት የለውም፡፡ ሰው በእሳት እና በተለያዬ አደጋ አልያም ተፈጥሮ  የተበላሸውንም አስተካክለው ቆንጆ እንደነበረ አድርገው በመሸኘት ያስደስቱታል፡፡ የህክምናን ነገር ሁሉ አለም የሚያደርገውን ያደርጋሉ፡ እንደእውነቱ ቢበልጡ እንጂ የሚያንሱ አይደሉም፡፡ መቸም ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ ነውእና፤ ገንዘብ ካለ የማይሰሩት አፍንጫ የማያስተካክሉትም ጡት ነበር፡፡ እንደእኔ እድሜ ዘል ያደረገውን ቆዳ ሁሉ ሴቱ ከፈለገ እና ከከፈለ የውጭ አካሉን 20 አመት ኮረዳ አድርገው ይሸኙታል፡፡ እስፖርት እንዳያዳብረው የሰነፈውንም ሀብታም፤ ቀደው ጠግነው ጡንጫ ሰርተው፤ ተዋቂ ስፖርተኛ አድርገው ይለቁጣል፡፡ ቂጥ አልባ ተብላ የተሰደበችን ሴት፤ ያበጠ እና የሚያስጎመጅ ቂጥ ያበጅላታል፡፡  ወዳጄ ገንዘብ ካለህ ከእግዚአብሄር ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃን ሕክምናቸው ይዞታል፡፡

የጀርመን ሀኪም የጀርመን ሳይነስ ሁሉን ለማስደሰት ሌት ተቀን ተግቶ ይሰራል፡፡ የጀርመን መንግስት ብታመም ያሳክመኛል፤ ቢርበኝ ያበላኛል እንጂ እኔን እየሸላለትኩ ለመቀየር እና ጨምዳዳ ቆዳዬን ለመወጣጸር እና እንደያነዬው እድሜ አከል ለመመለስ ግን አይከፍልልኝም፡፡ ይህ ቅንጦት ነው፡፡ ሰብአዊነት ደግሞ ከቅንጦት ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡ ሰብአዊ ፍጡር በተፈጥሮአዊ ይዘቱ ግን የሚገባውን ህግ ደንግጎታል፡፡

አገርህ ሞተ ብለህ ከፈን የለበሰውን፤ እዚህ አገር  አይምሮው ወይም ልቡ አልሞተም ብለው፤ በማስተንፋሻ እንደገና ያሰናብቱታል፡፡ ይገርማል፡፡ ሳይንስ የደረሰበትን፡፡ ለካስ ልብም አይምሮም የተለያዬ ሞት አላቸው፡፡ ያም ሆነ ይህ ያሰንብቱዋትም  ነፍስ ግን  ጌታ ባለ ሰአት ታፈተልካቸዋለች፡፡ እጃቸው ሊያስገቡዋት ያልቻሉት ነፍስን  ብቻ ይመስላል፡፡ ነፍስን ቢይዙ ኖሮ እኛም እሰየው አምላክን በእጃችን አገኘነው ብለን  በጉቦም በምንም በጸባይም እጥፍጥፍ ብለን ፖለቲከኞች  ባዘጋጁዋት ገነት ውስጥ በገባን ነበር፡፡

ታዲያ ጥቂት  ነገር ግን ጀርመን በጀርመን አገር እንዳይፈጸም የደነገገው ህግ አለ፡፡   ሳይንስ ተመራምሮ ለማወቅ መብቱ ገደብ የለለው ይመስላል፡፡ ይሁን እና ግን የምርምሩን ውጤት ካለሕግ ድንጋጌ መፈጸም አይችልም፡፡  ይህ ማለት ምርምሩን  ወደህግ ማቅረብ እና ማጸደቅ እንጂ እርምጃ ላይ ለማድረግ ህግ ያስረዋል፡፡ ህጉም የሚደነገገው የህዝብን የልብ ትርታ በማዳመጥ ነው፡፡ የጀርመን በላጩ ህዝብ፤  የሳይንስን ልቅነትም የሚደገፍ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ሰሞኑን አነጋጋሪ ምእራፍ የከፈተው፤ በጀርመን ሴትን በሳይንስ መልክ ልጅ መስጠት ነው፡፡  ካለወንድ ግንኙነት ብቻ ዘሩን ከፍሪጅ አውጥተው ሴትን ማስረገዝ ባይቸገሩም፤ ግን ሕጉ አይፈቅድላቸውም፡፡ የጀርመን ህዝብ የካቶሊክ እና የኢቫንጀሊስ እምነት ተከታይ ነው፡፡ እምነታቸውም አይፈቅድም፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር ይጻረራል ብለው ያምናሉ፡፡ የማያምኑትም ደግሞ ሳይነስ የሚሰራው ነገር ሁሉ ተፈጥሮን የሚያበላሽ በመሆኑ በማለት የማይደግፉት በሽ ናቸው፡፡ ሳይንስ እስከምን እንደሚሄድ ገደቡን ሊያሳዩት የሚፈልጉ ይመስላሉ፡፡ የጀርመን ህዝብ ቢችል ማዳበሪያ የነካውንም ምግብ መመገብ አይፈልግም፡፡ ግና የሚቻልበት ምእራፉን አልፈናል፡፡ አለም ተጣባለች ሁሉንም መመገብ የሚችል ከሀጢያጥ የራቀ ሕይወት የለንም፡፡ ስለዚህ ሳይንስን መጠጋት ግድ ብሎአል፡፤ በማዳበሪያ የዳለበ ምግብ እና የሰባ ሰንጋ፤ በእንኩቤተር የተፈለፈለ እንቁላል መመገብ፡፡ ሁሉም ለጤና ጠንክ ነው ቢባልም ካለዚህ መኖር አልተቻለም፡፡

 ይሁን እና ደግሞ፤ እንደልብ ብሆን ምን አገባችሁ የሚልም ሞልቶአል፡፡ ማዳበሪያ ያልገባበትን መብላት ይፈልጋል ተፈጥሮ አትደግፈውም በማለት፤ ጤና አይደለም በማለት፡፡ ወንድ ወንድን ማግባት ሴት ሴትን ማግባት ግን እግዚአብሄር አይከለክልም የሚሉት መደነጋገርም አለም ፈጥራለች፡፡ ለማንኛውም፤ ልጅ እንደውሃ የጠማው ማሕጸንም መፈጠሩ አልቀረም እና፤ በስለትም በምንም ሊያገኝ ያልቻለው፤ እኔ እግዚአብሄርን ምንአደረኩት እና ነው ብሎ እልክ የሚገባም አይጠፋም፡፡ በዚህ የተነሳም ሳይንስን አምሎኮው ያደረገ፤ በሳይንስ የሚደሰትም አልጠፋም፡፡ ግና ሕግ ምንን ይፈቅዳል ምንን ደንግጎአል አለ፡፡ ታዲያ ሳይነስም በሕግ ለማሰር የጀርመን ህግ ሀይለኛ ነውእና፤ ቀጥል የሚል ትእዛዝን እስካላገኘ ድረስ ማንኛውንም ውጤቱን ለመተግበር ትውር አይልም፡፡ አሜሪካ የፈቀደችው የሞት ፍርድ፣ ወይም በአሰቃቂ ህመም ታሞ የመጨረሻው የህመም መስታገሻ መድሀኒት ያልረዳውን ፤የታመመን ሰው ግደሉኝ  ብሎ የሚለውን  ሀኪሞች ከስቃይ ገድለው እንዲገላግሉት እና በሳይነስ ልጅን መፍጠር ህጉ አይፈቅደውም፡፡

ይህ ሳይንስ በሕግ መገደቡ፤ እየቻሉ እንደማይችሉ አስመስሎአቸው እስከዛሬ ቆይተዋል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ግን መሞትም የፈለገ ልጅም የጠማው የሌላ አገርን ህግ ለመጠቀም ግን የሚያስቆም የተደነገገ ህግ ያለ አይመስልም፡፡ የሰው ልጅ በምኑም በምኑም መብቴ ተነፍጎአል በማለት መብቴ ለሚለው ጥያቄ የወደሚያሙዋላለት አገር ይሄዳል፡፡ የሌላውንም ህግ ተጠቅሞ ያሰከረውን እና ስነልቦናውን የጎዳውን ፍላጎቱን ለማሙዋላት ተገድዋል፡፡ ለምሳሌም የወንድ እና የሴት ጋብቻም በአንዳንድ አገሮች ሲፈቀድ በሌላው በመፈቀዱ መጋባት የፈለጉ ከአገር አገር ተራውጠው ሲፈጽሙ አይተናል፡፡ ብቻ ሁሉ አገር የሁሉን አይነት መብት ፈቃጅ አይደለም፡፡ አንዱ አንዱን ይፈቅዳል ሌላው ሌላውን፡፡  አለማችን የሁሉን ፍላጎት ለማሙዋላት ብዙ በር የከፈተች መሆኑዋን እያየነው ነው፡፡ ፍላጎት ሲያድግ ደግሞ በእርግጥም ምን ልስራ ያስብላል፡፡ የሰው ልጅ ባህሪያችን አንዳንደዬም ውሻ እንኩዋን ከሚያደርገው በታች ዝቅ እያልን እንደምነሄድ እያየነው ነው፡፡ በህግም አይደንገግ እንጂ፡፡ ሽማግሌ ከትንሽ ህጻን ጋር የሴክሹዋል ሪሌሽን በመፈለግ እያበዱ ሱሳቸው ብዙ ህጻናታን እያበላሹ እየገደሉ መታየታቸው፤ ለአደባባይ አልተሰወረም፡፡ ፍላጎት ሲበዛም ልቅነትን ያመጣል እና፡፡


ታዲያ ዛሬ በጀርመን አገር የቤት ውስጥ መነጋገሪያ፤ የአደባባይ መሳቂያ የሚዲያ መተቻ፤ የፖለቲከኞች እራስ ምታት፤ የሳይንስ በር መክፈቻ ሆኖ የሰነበተው እና አሁንም ያለው የወ/ሮ Annegret R. የምትባለው አንዲት የ65 አመት አሮጊት በሉዋት ባልቴት በጀርመን የማይፈቀደውን ሕግ ጥሳ በዚህ እድሜዋ ወደ ሌላ አገር በመሻገር፤ ሳይንስ በፈጠረላት መንገድ ተጠቅማ አርግዛ በመመለሱዋ ነው፡፡ የ65 አመቱዋ አዛውንት፤  የልጅ እጦት ነው እንዲሕ ያሰከራት እንዳይባል፤ የ13 ልጆች እናት ናት፡፡ እንዳውም የመጨረሻዋ ልጁዋን የወለደችው በ55 አመቱዋ ነው፡፡ ሁሉም ግን በወንድ ግንኙነት በጤነኛ መንገድ የተወለዱ ቢሆንም፤ በመምህርነት ሙያ የምትተዳደረው ወ/ሮ ግን አሁንም ልጅ አልበቃትም፡፡ ባልም ወይም ወንድ በጎኑዋ አለመኖሩም የልጅ አምሮትዋን ሊቀንሰው አልቻለም፡፡ በዚህም የተነሳ ያበደ እና ሃላፊነት የጎደለው፤ በእራስ ወዳድነት የተመሰረተ እርምጃ ወስዳለች፡፡ እሱም እድሜዋ እንኩዋ ያማይፈቅድላትን፤ ማሳደግ እችላለሁ ወይ ጉልበት አለኝ ወይ የሚለውን ሳታመዛዝን በገንዘብ የገዛችውን የዘር ፍሬ ተጠቃሚ በመሆን ከጀርመን ውጭ በመሄድ አርግዛ ተመልሳለች፡፡ የሚገርመው የሚደንቀው እግዚአብሄርም  አምሮትዋን እና ይልቡዋን ስቃይ በማየት ይመስላል፤ አንድ ልጅ የተመኘችው የበርሊኑዋ ወ/ሮ አንድ ሳይሆን በአንደዬ አራት መንትያ ማርገዙዋ ነው፡፡  አነበባችሁ፡፡ ተባረኩ፡፡ ባዩሽ ነኝ ከጀርመን አደባባይ፡፡