ዳንኪራ
ታድልህ ይሆን ወይስ ለመከራ
ባላደረከው ነገር ስምህ ሲጠራ
„የለም የለም እኔ አይደለሁም፣
አላደረኩም
አልዋሸሁም አልቀጠፍኩም
ብለህ ብትናገር ብትለፈልፍ
ጠበቃ አብዝተህ ብታሰልፍ“
ዕድል ይሆን መከራ
ስምህ የሆነው መራራ
ዳኛው ሲገለምጥህ ሲያንገላታህ
„መብት አለኝ፤ አለኝ ልናገር
ዳኛ ፍቀድልኝ ለእውነት ቆሜ ልከራከር
አንተም ፖሊስ ተወኝ አትጎትትኝ
ለግርብረት አታቻኩለኝ
ከእኔ ጋር እውነት አለች
በቀኑዋ ትፈርዳለች“
ብለህ ብትናገር ብትጮሕ
ላንቃህ ደርቆ ማን ሰማህ ?
እውነት እውነት እያልክ ትጣራለህ
ወላጅ አባቱዋን እረስተህ
እስኪ አንጋጥ ወደሰማይ
አታገኛትም ከምድር ላይ
መስፈሪያ ስፍራ አጥታ
በአለም ክፋት ተሰላችታ
መደበቅም ሰልችቶዋት
ወስድአታል እና የላካት
አንጋጥ ወደእሱ ወደሰማይ
ፍርድን በቶሎ እንድታይ
በዚህም በዛም ለቅሶ
የስንቱ እንባ ፈሶ
ወዮላት ያቺ ሀሰት
ማን ይናገራት ይሰራት
ዳንኪራ መታች በደስታ
የሰውን ውድቀት አብዝታ
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen