አንዳንዶች ፌስቡክን እንደሚያጠፋቸው በመቁጠር
ሊያጠፉት ይጥራሉ፡፡ ወጣቶችን ይከለክላሉ፡፡ ፌስ ቡክ እንዲሕ መጥፎ ቢሆን ኖሮ በኢዮሮፕ የፈረንጁ ወጣት፤ ለይኑቨርሲቲም በቅቶ ለአገሩ
ትርፋማ ባልሆነ፡፡ ሌላውም የዲሞክራሲን እድገት ተቀብሎ በአገራቸው ልማት ባልተሰለፈ፡፡ ወጣቱ በሙሉ ማለት ይቻላል የፌስቡክ ተጠቃሚ ነው፡፡ ጊዜውንም
በከንቱ ነገር አያባክነውም፡፡ እንዳውም ብዙውን ግዜ የሴክስ መሰል ነገር የሚጠቀሙት ወጣቶች ሳይሆኑ፤ ሌላ ችግር ያለባቸው፤ ሴት
ማግኘት የማይችሉ እና የሆነ የጤና ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ ዛሬ የአለምን ህዝብ ባህል እና ማንነት እያስተዋወቀ እንዲቀራረብ እና
ዘረኝነት ከሰዎች አይምሮ ቦታ እንዲያጣ እያደረገው የሄደው፤ የፌስ ቡክ ግንኙነቶች ያመጣው እድገት ነው፡፡ ፌስ ቡክ ከፈለክ ጠቃሚ
የሆነ ነገር በመመልከት በመምረጥ እና እርስ በእርስም በመነጋገር አይምሮን ለሚያሳድግ ነገር መጠቀም ይቻላል፡፡ ፌስ ቡክ የፈረንጆችን
ወጣቶቻቸውን የሚገል ቢሆን ኖሮ ደዝባውን ባጠፉት ነበር፡፡ ዛሬ የአለም
ህዝብ በማንኛውም አገር ከሚኖሩ መሰል ባህሪ ካላቸው ሰዎች ጋር አስተሳሰብን ይጋሩበታል፤ ይካፈሉበታል፡፡ የአለም ሳይንቲስቶች መገናኛም
መተዋወቂያም ሆኖአል፡፡ እንዳውም ባህሪ ለባህሪ ለመተዋወቅ ሰፊግዜ የሚሰጥ የፌስቡክ ግንኙነቶች መሆናቸው በሰፊው እየተነገረ ነው፡፡
ስለዚህ መልእክቴ ለእኛ አገር ሰዎች፤ ፌስቡክን የማይጠፋውን ለማጥፋት ከመታገል፤ ወጣቱን ፊስቡክን ለምን እንደሚጠቀሙበት
አይምሮን አስፍቶ መሪ መሆን ያስፈልጋል፡፡ያደነቆርከው ወጣት ለእራስህም ጥቅም የለውም እና አባትነትህንም ይክደዋል፡፡ ያጠመድከው
ወፍ አንድ ቀን በር ቢያገኝ በራሪ መሆኑን አትዘንጋ፡፡ ሌላው ፌስ ቡክ ላይ የምትገናኙትን ሰው ቀድማችሁ አትመኑ፡፡ ምክናያቱም
ብዙም አይምሮአቸው በርካሽ ነገር የወደቁ ሰዎች ይጠቀሙበታል እና፡፡ ዛሬ የሰለጠነው አለም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ፌስቡክንም ሚስቶቻቸውን
እና ባሎቻቸውን ለመምረጥ ይጠቀሙበታል፡፡ እንዳውም ፊት ለፊት በቶሎ የምታገኘው ሰው ጋር መገናኘት፤ በሳል የሆነ መተዋወቅ ሳታደርግ
፤ ዘሎ ወደጋብቻ አልያም ወደግብረስጋ ግንኙነት በመገስገስ፤ ያልተፈለገ
ልጅ ወይም ያልጠበከው ትዳር ውስጥ አዝፍቆ ሲያጨቃጭቅህ ይኖራል፡፡ ለማንኛውም ወሳኝ አብሮነት፤ በትዳርም ሆነ በፖለቲካ አስተሳሰብ
ወሳንነት አለውእና፡፡ በፊስ ቡክ ግን የምትተዋወቀውን ሰው፤ በቶሎ
ስለማታገኘው የሰፋ የመተዋወቅ ጊዜ በምታደርጋቸው የረጅም እርቀት ንግግር አትራፊነትም አለው፡፡ በፋስ ቡክ ሁሉም ስለእራሱ የሚፈልገው
የፖለቲካ ፓርቲ በሰፊው መነጋገር መጨቃጨቅ እና መረዳዳት ይችላል፡፡ የሰውን አስተሳሰቡን ለመረዳት ወይም የተለየውን አስተሳሰብ
ለማቀራረብ፤ እረጅም ውይይት ወሳኝነት አለው፡፡ ዛሬ በፌስ ቡክ መገናኘት የሚመሰረተው ትዳር በኢይሮፕ ትልቁን ቁጥር የያዘ ሆኖአል፡፡ ይህም የዘንድሮን ጋብቻ ሰፋ ያለውን ስፍራ
እንዲሸፍን አድርጎታል፡፡ በፌስቡክ የሚመጣውንም የአገር ገቢ ኢንቬስትሜንት ትርፋማ አድርጎታል፡፡ ዛሬ አንዱ አሁግር ከሌላው ጋር
የሚያደርገው የፌስቡክ ትውውቅ መንገድ፤ ሰውን ከዘረኝነት መንፈስ እያወጣ ግሎባል የሆነ ማይንድ የማስያዝ አቅሙ ከፍተኛ ሆኖአል፡፡
ስለዚህ ፌስ ቡክን ለሚገባ ነገር በመጠቀም ለተለያዩ የአስተሳሰብ እድገት እና አብሮ የሚያስኖረውን የዘረኝነት ጠላት የሆነውን አለምን
በመቅረብ ተማማሩ፡፡ ለማንኛውም ፖለቲካም አስተሳሰብ ሆነ ማህበራዊ ህይወት ለመጠናከር ወጣቱ ትዳርም እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን
እና የጠንካራ ቤተሰብ መመስረቻ ነውእና ንቃችሁ ማየት የለለባችሁ አንዱ የህይወታችሁ ክፍል መሆኑን አትዘንጉ፡፡ ትዳር አላማን የማያጠናከር
ይህ ነው የማይበል አስተዋጽኦ ያለው ነው፡፡ መነጋገር እና መተዋወቅ እና በአስተሳሰብ መቀራረብ
እንጂ ሀብት የጥሩ ቤተሰብ መመስረቻ መሰረት ሊሆን አይችልም፡፡ ካለጠንካራ ቤተሰብ ለአገርእና ለእኩልነትም መታገል ውድቀት ያመጣል፡፡
እኔ የምናገረው ምንአልባት እኔ ካጠፋሁት እና ከተሳሳትኩት ነገሮች በመነሳት ይሆናል፡፡ ሕይወት በእራሱ የማይቁዋጭ/ መጨረሻ የለለው/
ዩንቨረሲቲ/ ነው፡፡ ጠባብእነት አካባቢን ከመበከል አልፎ የእራስንም ሕይወት የማበላሸት ሃይል አለው፡፡ ስለዚህ ልብ የምትሉትን
ልብ በሉእና ግዜአችሁን በከንቱ አታሳልፉት፡፡ የፖለቲካ ጉዋዶቻችሁ እና መሰሎቻችሁንም ለመፈለግ ፌስቡክ ትልቅ አስተዋጽኦ
አለው፡፡ እናንተ በፌስ ቡክ ላይ መናገር ያለባችሁ የምታምኑበትን እንጂ የማታምኑበትን አታውሩ፡፡ ይህ በእራሱ ወላዋይነትን ያመጣል
እና፡፡ ለማንኛውም እርምጃ ድፍረትን ይጠይቃል፡፡ አይምሮን ከሚገል የባህል ትብታብ መውጣት ለእራስ እድገት ትልቅ ወሳኝነት አለው፡፡
የእራስህ የአስተሳሰብህ ውሳኔ ከለለህ ፈረሱ ለሚጎትተው ጋሪ ተሸከርካሪው ጎማ ትሆናለሕ፡፡ ጎማ ካለፈረስ ጉልበት ዋጋ የለውምእና፡፡
ሁልግዜ የሚያንቀሳቅስህ ሃይል ፈላጊ አትሁን፡፡ በቸር የምላችሁ ባዩሽ ነኝ፡፡
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen