ውድ
ሴት እህቶች፤ ፌስ ቡክን ፈረንጆች የሚጠቀሙበት ለቁም ነገር ነው፡፡
ስለዚህ ለፖለቲካ እና ለሶሻል ችግሮች መወያያ በብርቱ አድርጉት፡፡ ሞራላችሁንም ለመጣል ብዙ የሚሳደቡ ሰዎች በሰልፍ ይመጡባችሁዋል፡፡
ስለዚህ እኒህ የሚሳደቡ ሰዎችን ወያኔ ነው ወይ ተቃዋሚ ነው እያላችሁ ስህተት ውስጥ አትውደቁ፡፡ ቢቻላችሁ ስማቸውን የውሸትም ቢሆን
ፊት ለፊት በማውጣት ማዋረድ ነው፡፡ እነሱ ጋር እሰጥ አገባ አያስፈልግም፡፡ ድሮም አይምሮ ቢኖራቸው ስድብ አይጽፉም እና፤ ባዶነታቸውን
እያሳዩ ስለሆነ እና ስለማይገባቸው ስድብ አትመላለሱ፡፡ ምንም መሰረት የለላቸው ስለሆነ የማንም መጠቀሚም ሆነውም ሊሆን ይችላል
አልያም ለእራሳቸው ለዘቀጠ ባህሪ፡፡ የፖለቲካ ሰው ቢሆን እንዳውም የእሱን ፓርቲ እንድትወድለት ነበር ጥረት ማድረግ እና ማስተማር
ማግባባት ያለበት፡፡ ውነት እነዚህን ሰዎች የሚልክ ካለ ግዜውን በከንቱ እንደሚያባክን ቢረዳ ጥሩ ነው፡፡ ሴቶች ሁሉንም መከራ አቁዋርጣችሁ
ለመሻገር ጥረት አድርጉ፡፡ ከፌስቡክም ብትሰርዙት ወይም ብትሰርዙዋት ስምቀይረው ስለሚመጡ ተውአቸው አትሰርዙዋቸው፡፡ እናንተ ናችሁ፤
ስድብ አያግደኝም፤ አሮጊት መባል አያበሳጨኝም እድሜ መጨመርም ያለ ነው፣ ባል ፈልገሽ ነው ፌስ ቡክ ላይ የገባሽው ብትባሉም፤ እንኩዋን
የማይፈልግም ቢፈለግም ጤነኛ አስተሳሰብ ነው፤ ደሃም ብትባሉ ያለ ነው፡፡ ምንም ስድብ የሚባል ነገር በዚህ አለም ላይ የለም፡፡
ስድብ የምታደርገው እራስህ ሰሚው ነው፡፡ ልክ ፈረንጆች እሰለጠኑበት የአስተሳሰብ ደረጃ ላይ ድረሱ፡፡ ስድብ አይገደኝም፡፡ አጥንቴን
አይሰብረውም ማለት አለባችሁ፡፡ ስድብ ደግሞ መንፈሳችሁን እንዲያጠነክረው ስድብ የሚወጣው ከቆሸሸ፣ ከወረደ፣ እና እራሱን ካጣ የሰይጣን
መሳሪያ ከሆነ ሰው መሆኑን ተገንዘቡ፡፡ ስለዚህ ፌስ ቡክን ለቀና መነቃቃት የሚጠቀም ኢትዮጲያዊ ሁሉ እራሱን እንደወታደር ነቃ ያድርግ፤
ይበርታ፡፡ ከቶም እናንተ ስድብን በስድብ አትመልሱ፡፡ ምንም መልስ አትስጡ፡፡ በኢትዮጲያ ባህል ሴቶችን ሲያስበረግጉ ሲያሳፍሩ የነበሩ
ነገሮች ሁሉ ወደሁዋላ ጎትተውን አልፈዋል፡፡ ዛሬ አንገት ማቀርቀር ቀርቶአል፡፡ ስድብን ሽንፈት የያዛቸው ሰዎች ይጠቀሙበታል እና
ወደፊት እግራችሁን አስኪዱ እንጂ ወደሁዋላ አትራመዱ፡፡ ስለመብታችሁ ካልደፈራችሁ ምንግዜም ነጻ አትወጡም፡፡ ነጻነት ማለት ደግሞ
ዋናው እና መጀመሪያው ሴቶችን ከሚሳንስ ባህል ለመውጣት መታገል ነው፡፡ ይህ የመጀመሪውን ደረጃ ልተወጣ ሴት ወደሁለተኛው መሸጋገር
አይችልም፡፡ መጀመሪያ አይንአፋር አድርጎ ነገሮችን እንዳትጋፈጡ ከሚያደርጋችሁ አሉባልታን አለመሸሽ ነው፡፡ ሰዎች ምንግዜም እናንተን
ለመጣል የሚሉት አያጡም፡፡ ስም ማጥፋትም ይከተላል፡፡ ሴቶችን ለማሸማቀቅ ለመቅበር አንዱ ባህል መሳደብ መሆኑን እወቁ፡፡ እና በስዶች
በበለጣችሁዋቸው ሰዎች አነጋገር እንዳትሸነፉ፤ ፌስቡክን ለቁም ነገር፤ ለአይምሮ እድገት፤ መሰል ወንድሞቻችሁ
ጋር ሶሻል እና ፖለቲካል ጉዳዮችን ለመነጋገር ተጠቀሙበት ፡፡የሞተው የወደቀው ሴትን የሚያስበረግግ ወይም አይን አፋር አድርጎ ከፊስቡክ
የሚያባርር ነገር ዛሬ የሞተ ባህል ነው፡፡ የሞተው ነገር ሕይወት እንዳትዘሩበት አይምሮአችሁን ክፈቱ፡፡ እኔ ማንም በእኔ ላይ የሚለው
አይገደኝም፡፡ እዛው ሰምቶ የሚከተለውን አይምሮ ያጨናንቀው እንጂ፡፡ መቼም ወሬ የሚበዛው አዳማጭ ቦዘኔ ሲያገኝ ነው፡፡
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen