ይድረስ ለተቃዋሚ፣ ለገዢው ፓርቲም እና ለኢትዮጲያ ህዝብ
ነጻ ፕሬስን አምንበታለሁ፡፡ በወቅቱ ጥቂት የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ሊያገለግሉኝ ያዳመጡኝ
ነበሩእና፡፡ ነጻ ፕሬስ በአለም ላይ አለ፤በኢትዮጲያ የማይኖርበት ምክናያት ሞኝነት ነው፡፡ ይህ እከክልኝ ልከክልህ በሆነ ስራ አስፈጻሚ
በሚፈራበት አገር፤ የነጻ ፕሬስ መኖር የሚጠቅመው ለገዢው ፓርቲ ነበር፡፡ ግን ያለማወቅ ጉዳይ ገዢው ፓርቲ ነጻ ፕሬስን አይፈልገውም፡፡
ለምሳሌ እከክልኝ ልከክልህ ያሉ ስራ አስፈጻሚዎች የመንግስትን ሚዲያ የተበደለው ህዝብ ክፍል እንዳይጠቀምበት አፍነው ይይዙታል፡፡
በዚህም የተነሳ ገዢው ፓርቲ ያልሰራውን ስራ ለማየት ሊቸገር ይችላል፡፡ ስለዚህ ነጻ ፕሬስ ግን ሲጽፈው፤ ያንን አንብቦ መንግስት
ስራ አስፈጻሚውን ለምን ይህ ሆነ ተደረገ ብሎ መጠየቅ እና ለማስተካከል ይችልነበር፡፡ አሁን ግን በአንድ አገር ላይ ሁለት ዜጋ
መፍጠር ማለት አንዱን እንደልብህ ሁን ሌላውን ተበደል ማለት ይሆናል፡፡ የእኔን ሕይወት የሰቆቃ አድርገውት የነበረው፤ እና ታላቅ የሆነ ስቃይ አስከትለውብኝ
የነበሩትን ለመክሰስ አልቻልኩም፡፡ እነዚህ ሰዎች ያደረጉብኝን ስቃይ ለኢትዮጲያ መንግስት ፍርድ ቤት ከስሼ ለማስቀጣት ቀርቶ ለማስታገስ
እንኩዋን የምችልበት መንገድ በሙሉ የተዘጋ ነበር፡፡ ይህ የሆነበት
ምክናያት ብዙዎቹ ስራ አስፈጻሚዎች ሰንሰለታቸው ከጥቅም አንጻር የተሳሰረ ስለነበር ነው፡፡ በተለይ ክፍለሀገር እኔ በነበርኩበት
ወሎ ውስጥ ይህ መሰል ከባድ ፈተና የተጋረጠ ነው፡፡ ያለችኝን ገንዘብ አራግፌ ለመቁዋቁዋም ያደረኩት ጥረት ያተረፈልኝ ድህነትን፤
ኪሳራ እና የአይምሮ ቶርች ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ቤተሰቤን ለመበተን ተገድጃለሁ፡፡ በውነቱ አውሬዎች ናቸው ጨካኞች ናቸው ክፉዎች
ናቸው፡፡ የሴት ቤት ተበትኖ በእኔ ጫንካ እነዚህ ስራ አስፈጻሚዎችን መሸከም ማለት ዛሬ ሊያፍሩ ይገባቸዋል፡፡ ሰው ትንሽም ሰብአዊነት
እንዴት እንደሚያጣ እጅግ በጣም ይገርመኛል፡፡ሴቶች ጉዳይ የምትባለውንም አንዲት ሴት ቀርቤ በደሴ ውስጥ ማለቴ ነው ባነጋግራት፤የእኔ
ድርጅቴ ወርቅ ነው፡፡ አንቺ የድርጅቴ ተቃዋሚ ነሽ እያለች ልታዳምጠኝ አልቻለችም፡፡እኔም በማላውቀው ነገር እንደሚዳክሩ እና የሴቲቱንም
ንብረት እያዘረፉ፤ ዘራፊያቸውን ለመተባበር ሲሉ ካለው ኢህአዴግ ጋር ጠላት አድርገው ሊያቀርቡኝ ወይም እንዳላተሙኝ ተረዳሁ፡፡ ሰው ተቃዋሚ ከተባለ እንደላቀለት እና፤ ተስቦ እንደያዘው ሁሉ ሰው
እንደሚሸሸው አውቃለሁ፡፡ ይፈራዋል፡፡ በዚህ ከእውነት ውጪ በሆነ
ነገር ብዙ ተሰቃየሁ፡፡ ድፍን ዘጠኝ አመት የምሰራብትን እና ሰርቼም ግብር የማስገባበትን ቤት በራፉን ለጋራጅ አሳልፈው ሰጡት፡፡ ባለጋራጁ እናቱ በወቅቱ የደሴ የሆነ ነገር
ተመራጭ ስለነበረች የእኔን ክስ ሁሉ ከንቱ አደረገው፡፡ ይህንን ሁሉ ብዙው የደሴ ህዝብ ያውቀዋል፡፡ እንደእኔ እንባ እንደ ጎርፍ
የወረደው ያለ አይመስለኝም፡፡ እንባ ጎርፍ ቢሆን ኖሮ የእኔ ብዙ ሰውን በወሰደ ነበር፡፡ ግን ገና አልሞላም መሰል መሰል፡፡ እንባዬ
አንድ አካባቢ ላይ ባህር እንደሰራ አልጠራጠርም፡፡ የባለጋራጁም ግሩፖች፤ በራፌ ላይ በመቆም፤ ቀውስ እያሉ ይሰድቡኝ ነበር፡፡ በገዛ
ቤት መግቢያ ያሳጡኝ ወጣቶች፤ እናታቸው እሆናለሁ፡፡ የአንተን እናት ለማትረፍ የሌላውን እናት ማጥፋት በአንዳንድ ጎረምሶች ተባዝቶ
ይገኛል፡፡ ጥሩ ሲስተም ያፈራው ይሆን ጥሩ ወላጅ፤አዎ እዚህ ላይ ተምታቶብኛል፡፡ ሲስተም ሴትን በማስለቀስ ? ምን ይጠቀም ይሆን? ስለዚህ ስራዬን አቁዋርጬ ልጆቼን ወደጀርመን መለስኩኝ፡፡ ድህነት ባሪያ የማድረግ፤
ለማኝ የማድረግ ተጽእኖ ፈጣሪ ነውእና፡፡ የማበላቸው የመሰረትኩት ስራዬ በወንዜ ልጆች ተናግቶአል፡፡ ወንዝ በለኝ እንዲህ ነው፡፡
ሁሉንም አናጉት፡፡ የእነሱን ግን አቆሙት ወንድ ናቸውእና፡፡ ሴቶቻቸውም ባለወንድ ናቸውእና፡፡ በእኔ መውደቅ ሳቁ ተሳለቁ፡፡ አዎ
ለጊዜው ሳቅ በሳቅ ሆነ፡፡ እነሱ አያፍሩም እኔ ግን አፈርኩላቸው፡፡ ጠበቃም ብፈልግ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ባለጋራጁንም ሆነ፤በፈራፌን የሰጠውንም የቀበሌ ሊቀመንበር ፤እናቱ የምታገለግልበትን ቀበሌ ለመክሰስ አልቻልኩም፡፡
እንደእውነቱ ከሆነ ስቃዬ ሁሉ የጀመረው እነስዬ አብርሃ፤ እነታምራት ላይኔ ሁሉ በነበሩበት ግዜ ጀምሮ ነው፡፡ የእኔ እንጀራ ተዘግቶ
ቤተሰቤ ተበትኖ ግን ያ ባለጋራጅ ወጣት ከብሮ አዲስአበባም ሆነ ደሴ እስከቤተሰቡ ድረስ ከብረው መኖር ጀምሩ፡፡ አዎ ምን ነበር
ቢተወኝ፤ የተዋጣለት ባለሙያ ነበር፡፡ ሁሉ እጁን ይወደዋል፡፡ የትም ቢሆን ሰርቶ ማግኘት ይችል ነበር፡፡ አባት የለላቸውን ልጆች
ሰርቼ ባሳድግ ምን ነበር፡፡ የኢትዮፒ አስከፊውን ገጽታ ማንም ሊያነሳው እና ሊጋፈጠው አይደፍርም፡፡ ግን እንዲሕ ነው ኢትዮጲያችን፡፡
እከሌ ጥሩ ሙስሊም ነው፤ እከሌ ጥሩ ክርስቲያን ነው ይባላል፡፡ በሁሉም ውስጥ ግን ኩነኔም እንዳለ ለማወቅ አንደፍርም፡፡ እውነት
ከፈጣሪ ነው፡፡ እኔ ግን ሴት በመሆኔ ጉልበቴ ተሙዋጦ እንባ ብቻ የዠ ከስሬ፤ የነበረኝን ነገር እየሸጥኩ መብላት ጀመርኩ፡፡ እዚህ
ላይ ባለጋራጁ ሙስሊም ልጅ ፈሪሃ እግዚአብሄር ቢኖረው ኖሮ፤ እረ ባዩሽን ይህችን ብቸኛ ሴት እኮ እየገፋሁዋት ነው ማለት በቻለ
ነበር፡፡ እውነትን ለመረዳት ሀቅን ለመወጣት ሁሉም እምነት ያዛል እና፡፡ ይህቺ ሴት ካለባል ልጅ ይዛ እንዴትስ ሀቁዋን እነከላሁ
ብሎ ባለመገመቱ ጭራሽ ግሩፕ እየላኩ ሕይወቴን የሰቆቃ ማድረጋቸው እስከአሁን ይገርመኛል፡፡ አዎ ያገሬ ሰዎች ድንቅ የሚለኝን ክፈሳቶች
አይቻለሁ፤ ኖሬውማለሁ፡፡ ምንም እንኩዋን ለዚህ አይነት ህገወጥነት የጋበዘው የኢትዮጲያ መንግስት ስራ አስፈጻሚዎች ቢሆኑም የሰው
ልጅ ፈጣሪ አለኝ እምነት አለኝ ስለሚል እምነቱ የሚለውን ቢዳስስ መልካም ነበር፡፡ ዛሬ እኔ እጅግ በጣም ተንገላትቼ እንደገና በጀርመን
አገር እገኛለሁ፡፡ ኢሕአዴግ ጋር መፍተሄ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት ሁሉ ከንቱ ሆነ፡፡ ሰውን የሚያንገላቱበት ስርአት በእራሱ መረጃ
እንኩዋን ይዘህ የማታቀርብበትን መልክ እየቀየሩ መጡ፡፡ ሳስታውሰው ሰውነቴን ይወረኛል፡፡ ውስጤን ቅዝቃዜ ይጨምርበታል፡፡ ዛሬ ግን እኔም የምጠብቀው ፍርድ ነው፡፡ ፍርድ፤ ለኢትዮጲያ ህዝብ ጆሮ የሚደርስ
ፍርድ፡፡ ብዙ የስነልቦና ተጽእኖ በማድረግ፤ ንብረቴ ሁሉ እንዲባክን ያደረጉትን ሰዎች ክስ ብመሰርትባቸው ደስ ይለኛል፡፡ ግን ይህ አሁን ባለው መንግስት አይቻለም፡፡ ለምን አይቻልም? የእነሱ አባል ያለማጣት ፍላጎት ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ግን በዚህ አጋጣሚ ለሁሉም
ልገልጥ የምችለው አንድ ነገር አለ፡፡ ኢትዮጲያ ወንበዴ አጥታ አታውቅም፡፡ የሴት ህይወት ግን እጅግ አዘቅት ውስጥ የወደቀ ነው፡፡
ይህ ህሊናውን የማይወቅሰው አድራስን ወዳድ በበዛበት አካባቢ የሚከሰጥ ነው፡፡ አንድን ሰው መንግስት እስኪወቅሰው መጠበቅ ባልነበረብን፡፡
ግና ቁስሌ ቁስሉ፤ ጭንቀቴ ጭንቁ፤ ችግሬ ችግሩ የሆነ ልቡ የራራ ሰው ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ከቶም ተቃዋሚ በመባሌ ብቻ ሰው ከእኔ
ጋር መሆን ፈራ ነበር፡፡ እኔ ለነገሩ አልነበርኩም፡፡ ግን ብሆን ኖሮ እራሱን ሰው ከእኔ በማሸሽ አዳነ ማለት ነው፡፡ አንድ ነገር ግን አውቃለሁ፤ እኔን ያስለቀሱኝ፣ የገፉኝ፣
እና ቤተሰብ እንድበትን ያስገደዱኝ ሁሉ ያካበቱትን አይበሉትም፡፡ ዘራቸውም እርጉም እንደሚሆን አውቃለሁ፡፡ እግዚአብሄር ይፈርዳል፡፡
እነዚህ ሰዎች ለእግዚአብሄርም ስራ እንቅፋት ናቸውእና ይፈርድባቸዋል፡፡ ግን ይህን ጥሁፍ የሚያነብ እና የሚያስተላልፍም ሁሉ መረዳት
ያለበት ግን ፤ተቆጣጣሪ የለኝም እና መንግስትም እንደፈለገ ለቆኛል የሚል ትንሽ ህሊናውን ቢያመዛዝን መልካም ነው፡፡
ያነዬ ተቃዋሚ ናት ነፍጠኛ ናት እያላችሁ የምታስቸግሩኝ ሰዎች፤ እኔ ነፍጠኛ ከተባልኩ
እናንተም ናችሁ፤ ምክናያቱም እናንተም ያሳደዳችሁኝ ትግሬ አልያም ኦሮሞ አይደላችሁም እና፡፡ ተቃዋሚ የምትሉኝ ግን ለመብላት ለመበዝበዝ
እንዲመቻችሁ እንጂ እኔ እስከዛሬው ቀን ድረስ የማንም የፖለቲካ አባል ሆኘ አላውቅም፡፡ ብቃወምም ሰይጣናዊ የሆነን ተግባር፤ ሙስናን
እና ማንአለብኝነትን ደግሞም እራስ ወዳድነትን ነው፡፡ የፓርቲ አባል ለመሆንም አልፈልግም፡፡ ውነት የፓርቲ አባል ካልሆንኩ አንድ ፓፈርቲ ሊረዳኝ ካልፈለገ፤ ለእኔ ይህ
ፓርቲ ሳይሆን አምባገነን ነው፡፡ እዛ በአባልነት ብቻ የሚረዳ ፓርቲ ጋር ምንም ግንኙነት ሊኖረኝ አይችልም፡፡ ለዚህ አይምሮዬ በቂ
የሆነ እድገትን ይዞአል፡፡ይህ ማለት ግን ነጻነቴን ያስገኝልኛል ማለት
አይደለም፡፡ ፓርቲዎች ግን እዚሕ የሚገባው እድገት ላይ መድረስ ግድ ሊላቸው ይገባል፡፡ አባሉን ብቻ የሚንከባከብ ፓርቲ እድገቱ የተገደበ ይሆናል፡፡ በኢትዮጲያ አንዱ
ፓርቲ ድምጥማጡ ካልጠፋ ሌላው መሪ መሆን የሚችል አይመስለውም፡፡ ይህ ሁሉ መታየት ያለበት ነገር ነው፡፡
አያችሁ ለመብቴ ለመቆም የግድ የፖለቲካ አባል መሆን የለብኝም፡፡ እንደእናንተ አይነት
ምንግዜም ከኢትዮጲያ ይጠፋል ብዬ አልገምትም፡፡ ደፋ ቀና የምለው የግድ በኢኮኖሚ እራሴን ለመቻል ነበር፡፡ ግን ባል የለላት ሴት
እንዳትቁዋቁዋም እንዳትሰራ የተከለከለበት አገር መሆኑን ሳላውቅ ኪሳራ ላይ ጥላችሁኛል፡፡ ይህ በእራሱ ያልሰለጠነ እስከአሁን ድረስ
ደግሞ ከመካከለኛው ዘመን ሊወጣ ያልቻለ አመለካከት ሆኖብኛል፡፡ ይህ
ሴትን የሚጫን ሁዋላ ቀር አስተሳሰብ እንዲቀር ባለኝ አቅም ግን እታገላለሁ፡፡ መቼም ሰውን መግደል አልያም ማሰር እንጂ መልስ የሚሰጥ
ወይም ከወደቀበት ሰውን የሚያነሳ በአገሬ አንድ ሀይል መፍጠር እንዳልቻልን ሁሉም ልቦናው ያውቀዋል፡፡ ሰውም ታፈራለች ብዬ በበኩሌ መገመት አቅቶኛል፡፡ ምንአልባት ስቃዬ እይታዬን ሸፍኖት ሊሆን
ይችላል፡፡ ሰው ሆዱን ከተመለከተ አገሩ ወገኑ ትዝ አይለውም እና፡፡ በድጋሜ የምለው እስከአሁን የተቃዋሚ ፓርቲ አባል አይደለሁም፡፡
ያዘረፋችሁኝ ያስለቀሳችሁኝ ደግሞም ያሳደዳችሁኝ ለእራሳችሁ ኪስ ስትሉ እንጂ እኔ ለመሰደድ ምክናያት ለመበደል ምክናያት ኖሮብኝ
አልነበረም፡፡ እኔ ኢሕአዴግ አባል አይደለሁም ማለት ተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ አለሁ ማለት አይደለም፡፡ ደግሞም ሁሉም የግድ የፓርቲ
አባል መሆን የለበትም፡፡ እኔ ግን አንዲት ሴት ነኝ፡፡ ያስለቀሳችሁት የበተናችሁት የአንዲት ሰላማዊ ሴት ሕይወት ነው፡፡ ይህ እግዚአብሄር
ይፋረዳችሁ፡፡ ይህ ሁሉ ሊያሳፍራችሁ እና ሊያጸጽታችሁ ይገባል፡፡ ለኢትዮጲያ አልያም ለፓርቲው ተቆርቁራችሁ እንዳልሆነ ለማወቅ የተሳነኝ
ደንቆሮ አይደለሁም፡፡ እናንተም ይህንን ስሙን ማስፈራሪያ አድርጋችሁ የምትጠቀሙበትን ኢሕአዴግን ገደል አፋፍ ላይ እንዳቆማችሁት
ሊገባችሁ የሚችል ምንም ግንዛቤ የላችሁም፡፡ ኢሕአዴግ ከሰማሕ እና ከገባህ፤ ደሴ ላይ እስር ውስጥ ተወርውሬ ነበር እና ለምን እንደታሰርኩ
እና ማን እንዳሰረኝ ለማጣራት ትችላለህ፡፡ ስህተቶች እንዴት እየተፈጸሙ እንዳሉ አስተውል፡፡ ሰውም ለምን ወደተቃውሞ መሄድ እንደሚገደድ
ተረዳ፡፡ ሰው የእራሱን ህይወት በሰላም ለመኖር ግድ ጥያቄ ማቅረቡ አይቀርም እና፡፡ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ እና ደሴ ወረዳ ፍርድ
ቤት ያለውን እና ደሴ ቀበሌ 10 ቡዋንቡዋ ውሃ ያለውን ሁኔታ ማጣረት እናመገመት ይቻላል፡፡ በደሴ ኢምግሬሽንም ተገኝቼ እርዳታ
እንዲያደርጉልኝ እና በእኔ ላይ የሚደረገው ዘመቻ እንዲቀንስልኝ ብዙ ጥረት አድርጌአለሁ፡፡ ግን ምክናያቱን ባልተረዳሁት መሰረት
የሰቆቃ እንባ አልቅሼ ወጥቻለሁ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ብዙ ጉዳዮች
አሉ፡፡? አልፈልግም፡፡ እኔም እንደማንኛውም ሰው የመኖር መብት እንዲከበርልኝ እና ጉዳዮቼ የህግ ምላሽ እንዲያገኙ እንጂ፡ በዚህም
የተነሳ ትግሌን በዚህ መልኩ እቀጥላለሁ፡፡ እኔ ሴት ነኝ፤ ኢትዮጲያም ለመኖር የግድ የወንድ መከታ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ መከታ
የሚስፈልገኝ መሆን የለበትም፡፡ የሚያስፈልገኝ የህግ የበላይነት እንጂ፡፡ ኢሕአዴግ አሁን ያለሕ በአገሪቱ ውስጥ አንተ ብቻ ነሕ፡፡
በአንተም ጊዜ ብዙ የተደጋጋመ ግፍ ደርሶብኛል፡፡ በፍርሃት እና በሰቆቃ የሚገባኝ ህግ መጠቀም ባለመቻሌ ቁሳዊም ሆነ አካላዊ ጉዳት ደርሶብኝ ከአገር ወጥቼለሁ፡፡ ወጥቻለሁ
ማለት ግን አልመለስም ማለት አይደለም፡፡ ማንኛውንም የፖለቲካ ፓርቲን ፈልጌ እንዲህ ሆንኩ ብዬ አልለውም፡፡ ሁሉም የጠጠመደበት
ሪዮተ አለም አለውእና፡፡ ግን ችግሮቼን ባገኘሁት ሚዲያ ፌሴ ቡክ ላይ በተደጋጋሚ አቅርቤአለሁ፡፡ ለሰብአዊነት አለሁ የሚል አካል
ወይም ተደማጭነት ያለው ሚዲያ ወይም ጋዜጠኛ ሁሉ ሊገናኘኝ ይችላል፡፡
ለጥያቄዎቼ መልስ ለችግሮቼ መፍተሄ እሻለሁ እና፡፡ ለነገሩ በኢትዮጲውያኖች እጅ ያለ ሚዲያ ሁሉ ግልጋሎቱ የሚውለው ለዲሞክራቲክ ለሆነ ነገር ሳይሆን ላመኑበት ጉዳይ ብቻ ልምድ
የካበተ ባህል ውስጥ ያለ እንዳሆን ፍርሃቱ አለኝ፡፡ ይህ በብዛት የርኢዮተ አለም ማራመጃ የሆነ ሚዲያ ሰብአዊነትን ይመለከታል ብዬ
ለማመን እቸገራለሁ፡፡ በዚህም የተነሳ የነጻ አገልግሎት የሚሰጡ ሚዲያዊች በተለይ ለሴት አምድ የሚሰጠው ሎሚ መጽሄት በመሰደዱ አዝናለሁ፡፡
የሎሚ መጽሄት አዘጋጅ አቶ ግዛቸውን በዚህ አጋጣሚ ላመሰግነው እወዳለሁ፡፡ አጥንት፣ዘር፣ ደግሞም ሀይማኖት እና ጾታ ወይም የፖለቲካ
አቁዋም ሳይጠይቅ ሚዲያውን እንድንጠቀም እድል ሲሰጥ ተመልክቻለሁ
እና፡፡ በሳውዲ አረቢያ ያሚንገላቱትን ሴት እህቶችም ችግር እና ሰቆቃ ብዙ ይጽፍ ነበር፡፡ በቸር ባዪሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen