„አታሞ በሰው እጅ ያምራል፣ ሲይዙት ያደናግራል „
የሰው ልጅ ልባችን በብዙ ክፋት የተሞላ ነው፡፡ ሁሉም ፖለቲከኞችን የግሉ ዘበኛ ማድረግ የፈልጋል፡፡ ደግሞም መበልጸጊያ፡፡
አንዳንድ ግዜ በጅምላ የሚደረጉ የፖለቲከኞች ጥላቻ፤ ልናገናዝበው የሚገባእና እኔስ ለዛ ምን አስተዋጽኦ አድርጊአለሁ ብሎ ሰው መገመት
አለበት፡፡ ጉዞአችን ሁሉ ተቃዋሚ ወይም ገዢው ፓርቲ ደስ እንዲለው ሳይሆን መሆን ያለበት፤ የምንወደው ፓርቲ በህዝብ ውስጥ ተፈቅሮ
ሲታይ መሆን አለበት፡፡ የምናስደስተው ፓርቲን ሳይሆን ታዲያ ህዝብን ነው፡፡ ኢሕአዲግንም የሚደግፍ ተቃዋሚን በመሳደብ፤ ተቃዋሚንም
የሚደግፍ ኢሕአዴግን በመሳደብ የትም አይደርስም፡፡ ይህ የሚረዳን እነሱን ጥላ አድርጎ መሸጋገሪያ ድልድይ ማድረግ ብቻ ነው፡፡ ይህ
እግዚአብሄር አይወደውም፡፡ ደግሞም ዘመናዊነትም የለውም፡፡ ዲሞክራሲንም ሊያመጣ አይችልም፡፡ አንድ ፓርቲ ብዙ አመት በመከላከያ
ሀይል ተገድፎ ከቆዬ የሚፈልገው ክፍል እንዳለ ማየት የሚገባን እውነት አለ፡፡ ካልሆነ ተቃዋሚዎችን ሁልግዜ ከማሰደድ ውጪ የምናደርግላቸው
ነገር አይኖርም፡፡ ገዢው ፓርቲ ብዙ ተቃውሞ እንደበዛበት ካወቀ ለዚህ አስተዋጽኦ ያደረጉት በስሙ ተዝናንተው የሚኖሩ መሆኑን ማወቅ
አለበት፡፡ ሁለግዜ ለገዢው ፓርቲ ታማኝ ሆነው ቀርበው ህዝብን በማንገላታት የሚኖሩ ሰዎች ለአገራችን የፖለቲካ ውድቀት ትልቅ አስተዋጽኦ
የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ምክናያቱም ለሕዝቡም ሆነ ደገፍነው ለሚሉት ፓርቲ የሚያደርጉት ማጭበርበር ሀላፊነት የጎደለው ነውእና፡፡ ለዚህም
ነው አንድ ግዜ አንድ ለጊዜው የዘነጋሁዋቸው በእስር የነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኛ „እባካችሁ አንድ የቀበሌ ሰራተኛ ጋር ስትጣሉ
ፖለቲካውን አትኮንኑ“ አይነት ነገር ያሉት፡፡ ግን ለነገሩ ትክክልም ቢሆኑ በኢትዮጴያ ውስጥ፤ ልብ በሉ፤ ይህ ፓርቲም ቢቀየር የባህሪ
ለውጥ እስከለለ ድረስ ተቃዋሚ ፓርቲም ስራው ውጤታማ አይሆንም፡፡ ካልሆነ ሁልግዜ በተወሰኑ ሰዎች ላይ የምናደርገው የጣት መቀሰር
ተለምዶ ያጠፋ ሳይቀጣ ያልፋል፡፡ አጥፊው ዘወትር አንድ ሁለት ሆነው ይቀራሉ፡፡ ይህ ትምህርት አይሆንም፡፡ ፖለቲካንም እንዲበላሽ
መሪዎችን ተናዳጅ ቁጡ የሚያደርግ ነገሮችም ደገፍናቸው ከሚሉ ደጋፊዎች ይመነጫል እና፡፡ ምንጩም እነሱ ህዝብ ያንገላታሉ፤ መሪዎችንም
ያስወቅሳሉ፡፡ ምክናያቱም ሰዎች አሁንም የዚህ አይነት ባህሪ ያለቀቃቸው
ስራውን እንደሚይዙት፤ እንደሚያገኙት ጥርጥር የለውም፡፡ ስለዚህ ያለው ገዢ ፓርቲ አንድ ለአምስትም አደረገው በሉኝ አንድ ለአስር
ትክክለኛ ኢንፎርሜሽን የሚሰጥ የሚለዋወጥ ቡድን መመስረት ውነት በኢትዮጲያ ይቻላል ወይ? ነው የእኔ ጥያቄ፡፡ ውነት ለጥሩ ውጤት
ታስቦ ከሆነ፡፡ እያንዳንዱ ቤት ውስጥ 60% ህዝብ የሚተዳደረው በአንድ
ሰው ጉልበት እና ገቢ እንደሆነ እናውቀዋለን፡፡ ብዙው ስራ በማጣት የሚኖር ስለሆነ፤ ይህ አንድ ሰው ያንን ሁሉ ቤተሰብ ለማስተዳደር
የመንግስት ቢሮ ውስጥ ሲሰራ ምንአልባት ለሙስና ሊጋለጥ ይችል ይሆን? ስለዚህ እውነትም ስልጣኑን የያዘው የገዢ ፓርቲ የተወሰኑ
ባለስልጣኖች እንዴት ብቻቸውን ሊወቀሱበት ይችላሉ?ብዙውን ግዜ የማየው በዚህ በፌስቡክ እንኩዋን አንዱን ብቻ ኮንኔ ወይም ሌላውን
አመስግኚ እንድጽፍ የሚፈልጉ አሉ፡፡ ግን ይህን ማድረግ ቀላሌ ቢሆንም፤ ለእኔ መሸንገል ወይም ማታለል ሊሆንብኝ ይችላል፡፡ ትልቁ
ፖለቲካ እንዳለ ሆኖ ለትልቆቹ ልተወው እና፤ ከላይ ተቃዋሚው እንዳሉት የአንድ ቀበሌ የተሳሳተ ስራ ቢሰራ ሰራተኛ ምንያህል ፓርቲውን
እንደሚንደው መገንዘብ እንዲያስተውሉልኝ መጠቆም እፈልጋለሁ፡፡ በችኮላ የትም አልተደረሰእና፡፡ ከታች የሚንድ ተቀምጦ ወደላይ እቆልላሁ
ማለት አይቻልም፡፡ ስለዚህ የኢህአዴግ ፖለቲካን በተወሰኑ ሰዎች ብቻ ተበላሸ ለማለት እኔ በበኩሌ ለመድፈር ፍላጎቱ የለኝም፡፡ ይህ
ደግሞ ከሆነ፤ በደርግ የጠፋውን ጥፋት ኮለኔር መንግስቱ ላይ ብቻ ብትጭኑት፤ አልቀበለውም፡፡ እኛስ ፖለቲከኞችን ምን ያህል ደግፈናቸዋል
ብለን እንጠይቅ፡፡ ነገም የዛሬው ሊደገም ይችላል እና፡፡ „አታሞ በሰው እጅ ያምራል፣ ሲይዙት ያደናግራል „ እንዳይሆን፡፡ በሌላ
መልኩ ግን ኢሕአዴግ ሀያ ሶስት አመት ሙሉ በስልጣን መቆየቱ ለዘመኑ ወጣት የሚዋጥለት ሳይሆን ግን ዝም ብሎ በትዝብት የሚቀበለው
ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ፡፡ የዛሬ ወጣት አለም የምትጉዋዝበትን የምርጫ መንገድ እያየ ስለሆነ፡፡ እኔ ግን በግል እይታዬ ፤
ኢሕአዴግ በግንቦት 7 ምርጫ ለቆ በነበር፤ ምንአልባት ዳግም የመመረጥ እድሉ ሰፊ ይሆን ነበር ብዬ እገምታለሁ፡፡ የምናገረው በትክክለኛው ፖለቲካ አካሄያድ እንጂ በሚስጥር የሚካሄድ ደባ በማንኛውም
መልኩ ካለ ከአቅሜ በላይ ነው፡፡ የአቅሜ ግን የሚለኝ እኛስ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ለምን እንደምንደግፋቸው እና እንደምንቃወማቸው እናውቃለን?ለምን
መሰላችሁ፤ የምንደግፈው ፓርቲ ስኬታማ እንዲሆን እንጂ ጥፋቱን ሸፋፍነን እንድናሳልፈው አይደለምእና ነው፡፡ ስለዚህ ለኢሕአዴግ ስኬት
አባሎቹ ምንያህል ሰርተዋል ወይስ የራሳቸውን ጎጆ ሲቀልሱ ነበር ወይ ብለንም እንጠይቅ፡፡ ለማንኛውም ነገር ቢሆን የእኔ ምኞት በሴትነቴ የሕግ
የበላይነት ከመጽሃፍ ወጥቶ በሰዎች መካከል እንዲኖር ነው፡፡ ምክናያቱም ህግ አልባ ሰዎች፤ ህግ አልባ ስራ አስፈጻሚዎችን በመጠቀም
እንዳንኖር የማድረግ ሃይል አላቸው እና፡፡ በነገራችን ላይ ከታች ያለውን በደል ንቆ የሚያይ ፖለቲከኛ እራሱን ለአደጋ ያጋለጠ ነው፡፡
እንዳውም ብዙውን ግዜ ከታች ያለው ሰራተኛ ብዙ ህዝብ ለማንገላታት እና ፓርቲው እንዲጠላ የማድረግ ሀይል ስላለው ተቃዋሚም ጉዳዩን
እንደ ኢሕአዴግ ችላ ባይለው መልካም ነው እላለሁ፡፡በቸር
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen