ኢሕአዴግ የመከላከያውን ቁጥር እያሰፋ እያጠናከረ ይሄዳል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች በመካከላቸው ያለውን ችግር ፈተው መጀመሪያ ተፋቅረው ያሳዩን፡፡ የኢትዮጲያ ህዝብ አብሮ የመኖር ችግር
የለበትም፡፡ ግን እነሱ ካልተስማሙ በህዝቡ መካካል ችግር ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ እኔ እንደምገምተው፤ በኢትዮጲያ የሚቀጥለውን ምርጫ
ኢሕአዴግ ላያሸንፍ ይችላል፡፡ ግን ያለማሸነፉ ሁኔታ ደግሞ ስልጣኑን ላያስለቅቀው የሚችልበት ምክናያት፤ የተቃዋሚዎች መስመር ያለማያዝ
ችግር ሊሆን ይችላል፡፡ ኢትዮጲያ ጠንካራ ሰዎች ይኖራታል፡፡ ግን ጠንካራ ሰው አለ ማለት ጠንካራ ፖለቲካ ፓርቲ አለ ማለት አይደለም፡፡
ግንቦት 7 የሚባለው ፓርቲ በኢትዮጲያ ውስጥ ተገኝቶ ምርጫ እንዳይሳተፍ ከገዢው ፓርቲ ጋር ያለው ከፍተኛ ያለመግባባት ጉዳይ እንደማይገኝ
እናውቃለን፡፡ እንግዲህ ሌሎቹስ ተፈቅዶላቸው የሚንቀሳቀሱት ፓርቲዎች ምን ያህል ለዚህ ምርጫ ተዘጋጅተዋል? እንግዲህ፤ ሰላማዊ ትግልን
አምነውበት የጀመሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫ ዝግጅት ማድረጋቸው ወሳኝነት ስላለው፤ ምን ይሆን ዝግጅቱ፤ መቸም እንግዲህ ህዝቡ
የሆነ ለውጥ መፈለጉ የማይካድ ሀቅ ነው፡፡ በእርግጥ ኢሕአዴግ እረጅም ግዜ ስልጣን ላይ በመቆየት ያለፉትን የመሪዎች ታሪክ የደገመ ድርጅት ነው፡፡ አዲስ ቤት አይተናል፡፡ አዳዲስ
መኪናዎችም እስከ ሀመር ድረስ ሊመዚንም አይተናል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ሴቶቻችንም ሆነ ወንዶቻችን ባሸበረቀው ልብስ ለብሰዋል ተጫምተዋል፡፡
ምን ይህ ብቻ፤ እድሜ ለቻይና ምርቶቹዋን ፍስስ አድርጋልን እቃ በእቃ ሆነናል፡፡ ግን ግን፤ ከደርግ ወታደር በረንዳ ላይ መውደቅ፣
ልጆቹ ትምህርት ቤት ሳይገቡ በየጎዳናው መውደቅ፣ እና ደግሞም እጅግ የበዛ የጎዳና ተዳዳሪ እና ቁጥሩ የበዛ ሴት አዳሪ ተመልክተናል፡፡
ከዛም አልፎ የስደት ጋጋታ፤ አንዱ እርቦት ሌላው የተሻለ ኅይወት ፍለጋ አልያም ፖለቲካው ያልተስማማው፡፡ አዲስ በአዲስ፤ ኢህአዴግ
የመናገርም ዲሞክራሲ መስጠቱ አይካድም፡፡ ግን ከአንድ ወይ ከሁለት አልያም ከሶስት ንግግር በላይ ካለፈ ዋ ሊከተል ይችላል፡፡ እንዳውም፤
„አዝን ብዬ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች“ ያለ ይመስላል፡፡ እሰየው ያለውም አልተገኘም፡፡ ተቃዋሚ ሁሉ“ አፋኝ ነው ይሉታል፡፡ ግን
አንድ ነገር ተረዳሁ፤ ሁለት ነገር አለ.
1ኛ. ኢሕአዴግን እንደጠላት አይቶ መታገል እና
2ኛ. ኢሕአዴግን እንደፖለቲካ ፓርቲ አይቶ መቃወም፡፡
ልብ ብዬ ሳየው በዚህ በሁለቱ መካከል ተቃዋሚ የተምታታበት ይመስላል፡፡ ኢህአዴግን የማይዋጥለትን ጠላትእነት ተቀዋሚ
የአለማንሳቱ ሁኔታ፤ ኢሕአዴግም ተቃዋሚን እንደጥላት አድርጎ መቀበሉ፡፡ ይህ ትልቅ ፈተና ሁለቱም የሚያደርጉት ድርጊት ፍልሚያ መቁዋጫ
የለለው ነገር እየሆነብን መጥቶአል፡፡ ማንን እንመን እንግዲሕ የሚለው ህዝብም፤ እኔ ምን አገባኝ እንደፈለጉ ይሁኑ ያሉ ይመስላል፡፡
አንዳንዱም የድሮውን ቆሎዬን አልጣ እንጂ ሲል ሌላው ደግሞ ካለው እንዳይጎልበት ይሩዋሩዋጣል፡፡ ሁለቱንም የሚያስታርቅ ጠፍቶአል፡፡
አልተመቸኝም እኔ፤ ግን አልተመቸኝም ማለት የሚመቸኝ አገኛለሁ ማለት አይደለም፡፡
ኢህአዴግ ብዙ አዲስ ነገር ይዞ ብቅ ያለ ነው፡፡ በሙስና የታጠረው ኢሕአዴግ፤ ግብርም ከሕዝብ በእጅጉ ይሰበስባል፡፡
ይህ ጉዳይ ትክክል እና የሚበረታታ መሆን ቢገባውም ግን ሁለት አስቸጋሪ ነገር ተከስቶአል፡፡አንዱ ህብረተሰቡን ያስደነገጠ፤ ሌላው
ደግሞ ለሙስና ያጋለጠ፡፡
1ኛ ግብር በአግባቡ ወይም ጭራሽ ከፍሎ የማያውቀውን ህብረተሰብም አስኮርፎአል፡፡
2ኛ የግብር አሰባሰቡ ሁኔታ በአድሎ እና በግለሰብ ጥላቻ ደግሞም ተቃዋሚን ለመምታት የሚጠቀሙበት መሳሪያ ሆኖአል፡፡
እነዚህ ነገሮች ግብር የሚለውን ነገር እንደአባጨጉዋሪ እንዲታይ እያደረገው ነው፡፡ የምኖረው ጀርመን ነው፡፡ ጀርመን
ህዝቦችዋ ከፍተኛ ግብር ያስገባሉ፡፡ እነሱም የሚገባው ግብር ለትክክለኛ አላማ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚያውሉት ያምናሉ፡፡ በእኛ
አገርስ፤ ግብር ተከፍሎስ ምን ያህል ለውጥ አምጥቶአል? ደሃ መመገብ
ቻለ? ደሃን ማስተማር ቻለ? አይችልም፡፡ ምክናያቱም መከላከያ ሰራዊቱ ለፖለቲካ ፓርቲወች ይበልጥ አስፈላጊ ናቸው፡፡ እነሱም ደመወዝ
ይላሉ፡፡ አመጸም በበዛ ቁጥር፤ መከላከያው እንደፖሊስ ደግሞም ደህንነት
የመሳሰሉ ቁጥሩ እያደገ ይሄዳል፡፡ ይህ የግብር ከፋዩን ህዝብ ገቢ
በእጅጉ ይፈታታናል፡፡ ለመሆኑ በአገራችን ህዝብ የሚገባው ግብር ኢትዮጲያን ለማስተዳደር በቂ ይሆን ወይ? ባለፈው አንድ መረጃ አንብቤ
ነበር፡፡ በመከላከያ ሰራዊት ደመወዝ ጭማሪ ብሎ የሚጠይቅ ስራውን መልቀቅ ይችላል የሚል፡፡ አይጨመርም ነው ነገሩ፡፡ እሰየው ልበል
እንዴ? እንኩዋን ጭማሪውን ይቅር እና አሁንም ያለውን ደመወዝ መክፈል መቻላችን ጎበዝ ህዝብ ነን እላለሁ፡፡ ከሰማይ እኮ አይመጣም
ብሩ፡፡ ይህ መንግስት እንቅልፍ ያለው አይመስለኝም፡፡ የደርግ ወታደር አይቶ የማያውቀውን ደመወዝ እየከፈለ ነውእና፡፡ ደመወዙ ሁሉ
አድጎአል፤ ችግሩ የኑሮው መወደድ እና የሰው ልጅ ፍላጎት መጨመር እንጂ ደመወዙን የሚያሳንሰው፡፡ ለማንኛውም ተቃዋሚ ከኢሕአዲግ
ጋር እርቅ ካላደረገ ኢሕአዴግ የመከላከያውን ቁጥር እያሰፋ እያጠናከረ ይሄዳል፡፡ ስለዚህ ኢሕአዴግ ነፍሴ፤ ግብር ከፋዩ ህዝብ እጅግም
ብዙ ስላልሆነ እባክህ ጫና እንዳይበዛብን እና ግብር ከፋዩን ጭራሽ እያጣህ እንዳትሄድ ተቃዋሚ ላይ ላላ እረገብ በል፡፡ አንተ ጠንከር
ባልክ ቁጥር እነሱም ከረር ይላሉ እና፡፡ በመጨረሻም የማስታውሰው ከሚቀጥለው ምርጫ በሁዋላ የሚመጣው ውጤቱ ምንአልባትም ግንቦት 7 የሚባለው በለስ የቀናው ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ፡፡
በነገራችን ላይ የኢትዮጲያ ህዝብ ሆ ብሎ እንደ ኢጅብት ወይም እንደቱኒዚያ የማይነሳበት ምክናያት፤ በእነዚህ አገር ሁሉም ሀብታም
ባይሆንም ሁሉም ጦሙን አያድርም፡፡ አረብ አገር እኮ ለእኛስ ተርፈው የኛ ሰው ወደዛ ስራ ፍለጋ እየሄደ አይደል፡፡ በረሃው አገር
ለምለሚቱን ኢትዮጲያን ይመግባል፡፡ ስለዚህ ሕዝብ ገጀራ ይዞ ይወጣል የሚል ካለ ኢትዮጲያን አያውቅም ማለት ነው፡፡ ይልቅስ ሁሉም
ፖለቲካውን መርመር ያድርግእና ምርጫው ላይ ደፋ ቀና ይበል፡፡ሌላው ሁሉ ለጊዜው አያዋጣም፡፡ በፖለቲካ ኩርፊያ የለም፡፡ አሜሪካ
እና ኢራን እንኩዋን መኩዋረፋችው ሊቀር ይችላል የሚባል ሽው የሚል ንፋስ ያመጣው ጨዋታ ሰማን፡፡ አያሳፍርም፤፤ ፖለቲካም እንዲህ
ሲሆን ነው የሚያምረው፡፡ ዮለቲከኞች ገቀራርቦ መስራት ነው፡፡ ከምርጫው በሁዋላ የሰላማዊ ትግል የሚለው
ነገር ሊያከትምለት እና ኢታማኒ ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ፡፡ አስተያየትሽን ነጻ ልቀቂው ካላችሁኝ፡፡ በነገራችን ላይ ነጻ መናገር
ብቻ ዋጋ የለውም ነጻ ንግግርን በአዳማጭም ህሊና ይወሰናል እና፡፡ በቸር ልበላችሁ
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen