Donnerstag, 26. Juni 2014

ተቃዋሚ ለታፈነው ህዝብ እንደፖለቲካ መሲሂ ሆኖ በናፍቆት ይጠበቃል፡፡





ተቃዋሚ ለታፈነው ህዝብ እንደፖለቲካ መሲሂ ሆኖ በናፍቆት ይጠበቃል፡፡

እንኩዋን ትክክል ሳይሰራእና ትክክልም ተሰርቶ ህዝብ በአገዛዙ ቢደሰትም፤ አንድ ብቻውን በስልጣን ለመቆየት የሚጥር ፓርቲ ትልቅ የታሪክ ስህተት እየሰራ መሆኑን መረዳት መቻል አለበት፡፡ አንድ ፓርቲ ብሎ ነገር የለም፡፡ አንድ ንጉስ እንጂ፡፡ ያም ሁዋላ ቀር ሆኖ ቀርቶል፡፡ አንድ ንጉስ አጥብቆ ቢይዝ ትንሽ ይሻላል፤ ስርአቱ እና የአገዛዝ የመጀመሪያው ደረጃ እንደዛ ሆኖ ባልሰለጠነው ዘመን ስለቀረበ፡፡ ንጉስም ሰው መሆኑን እያደር ሲታወቅ ግን በሁሉም አለም እየቀረ ሄድዋል፡፡ እዚህ ላይ እንዳንሳሳት፣ ዛሬ በኢይሮፕ ያሉ ነገስታቶች፤ ምንም አይነት የፖለቲካ የማዘዝ ሚና የላቸውም፡፡ ግን የኢይሮፕያን ነገስታቶች ላገራቸው በዘመናቸው ብዙ ጥሩ አስተዋጽኦ ስላደረጉ እንደ ሲንቦል ደመወዝ እየታሰበላቸው ይኖራሉ፡፡ ደመወዙም ህዝብ ከሚከፍለው ታክስ ነው፡፡ ጥሩ አድርገው ለአገራቸው የጣሉት ውለታ ዛሬ እንዲከበሩ ህዝብ እራሱ አምኖበታል፡፡ በዘመናቸው ግን መጥፎ ነገር አለንበረም ማለት አይደለም፡፡ ደግሞም አልሰሩም የተባሉት የሩሲያው ነገስታቶች አይሆኑ ሆነው እስከ ዘር ማንዘራቸው እንዲጠፉ ብዙ እርምጃዎች በተነሳው የህዝብ አመጽ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ „የቤት ቁዝምዝም እቃ ይፈጃል እንዲሉ ለህጻናት ልጆቻቸውም ቅጣቱ አልቀረም፡፡ በወቅቱ ራሽያ በአሰቃቂ እርሃብ እና መከራ ህዝቡዋ ወድቆ እነሱ የሞላቸው የተረፋቸው ነበር እና፡፡  እሱንም ለማስቀረት ንጉሶች ባሉበት አገር ሁሉ ከፍተኛ ሪቮሊሽን ተካሄዶአል፡፡
ዘወትር የምናየው ከአምባገነን በሁዋላ ደግሞ በጉሬላ ተዋጊዎች አምባገነን ሆኖ ይተካል፡፡ በተለይ አፍሪካ አካባቢ እንዲህ የተለመደ ነው፡፡ አምባገነንን ለማስለቀቅ የነበረው አማራጭ ይህ ብቻ ነው፡፡ አልያም በራሳቸው በከበባቸው መከላከያ  መገልበጥ፡፡ ንጉሶች ሲያገለግላቸው በነበረው ወታደራዊ ሀይል እዛው አጠገባቸው ባለው ስልጣን እንዲለቁ ቢደረግም፤ ወታደርን ግን መልሶ ለመጣል የግድ ለመብት የሚታገለው ቁጡው ሀይል አምርሮ በየጫካው ገብቶ ከዛም በሁዋላ ለስልጣን ይበቃል፡፡ ጫካም ከገቡ በሁዋላ ስምአውጥተው ብቅ ይላሉ፡፡  ወደአገር ሲገቡ ግን ስማቸው ሁሉ ለሕዝቡ ባይታዋር ስራቸውም የማይታመን ይሆኖአል፡፡ እንግዲሕ ህዝብ ተቀበለውም አልተቀበለውም ማሰብ ያለብን፤ ምንም እንኩዋን ምክናያት ይዘው ለትግል በየጫካው ቢሄዱም ዘመኑ ግን የአንድ ፓርቲ ዘመን መሆኑን መዘንጋታቸው መልሰው አምባገነንን ጥለው እራሳቸውም አምባገነን ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ ዛሬም የሙጥኝ ብሎ በብቸኝነት ስልጣንን መያዝ፤ በህዝብ እይታ ውለታ ሆኖ ተቆጥሮ፤ ይህን ያህል ዘመን ስለተዋጋ በስልጣን ይቆይ የሚል አይሆንም፡፡ ጭራሽ እንዲፈሩ የሚያደርጋቸው፤ ከአገር ሲወጡ ተንጠባጥበው እና ስም የለሽ ሆነው ከዛም እዛው ስም ስለሚሰይሙ „ገቡ“ ወይም „ገባች“ እየተባለ ይነገራል፡፡ ይህንን ዞሮ ማስታወስ ይገባል፡፡ እንደነገሩ  ደርግ ስልጣን ሲይዝ ወዲያውም ኢሕአፓ መሬት ላራሹ እያለ እና አትነሳም ወይ እያለ ከደርግ ጋር ተፋልሞ የሞተው ሞቶ የተረፈው ከአገር መውጣቱም ቢሰማ፤ ኢሕአፓ ግን ስልጣን ሊይዝ አልመጣም፡፡ ስንሰማ ግን ኢሕአፓ ተከፍሎ ግማሹም ከወያኔ ጋር ወግኖ ኢሕአዲግ ተብሎ ገባ ሲባል እኔ ለእራሴ በፖለቲካው ብዙም ችሎታ የለለኝ የተቀበልኩት ነገር ነበር ፡፡ ቢሆንም ግን ኢሕአዴግ የሚባለው ስም ወይም ወያኔ የሚባለው ስም ጫካ ከገቡ በሁዋላ የተመሰረተ በመሆኑ እራሱ ፓርቲውን እንደመጣብን እንጂ እንደመጣልን ሆኖ በሕዝብ እይታ ለመቀበል አስቸጋሪ ሁኔታ ሳይገጥመው አይቀርም ብዬ እገምታለሁ፡፡ደግሞ ስንት አመት ሊቆይ ነው  ብሎ አሳሳቢ ነገር በህዝብ አይምሮ ቀርጦ የቤት ስራ ከመስጠቱ ውጪ እነሱ ሰራን የሚሉትን ለማየት ህዝብ ተቸግሮአል፡፡ ምክናያቱም የሰው ልጅ ትልቁ ፈተናው አስተሳሰቡም መገደቡ ነው፡፡ ብዙ ግዜ አምባገነኖች ህዝብን የሚጫኑት ግንዛቤውን የሚያዳክም ነገር በማድረግ ነው፡፡ መካድ የለለበት ግን ተቃዋሚ ይከልከል ወይም ነጻ አይውጣ እንጂ ህብረተሰቡ ጋር ለመገናኘት አይችሉም ለማለት ሁኔታውን ሁሉ እያየነው ነው፡፡ ይህ በአለም ዙሪያ  ያለ ልምድ ነው፡፡ በዚሁ ሁኔታ ተቃዋሚ ለታፈነው ህዝብ እንደፖለቲካ መሲሂ ሆኖ በናፍቆት እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡ ስለዚህ ተቃዋሚ ያሸነፈበትም መንገድ እንዳለ በገሀድ እያየን ነው፡፡ እንዳውም የተከለከለን ነገር የበለጠ ተፈላጊ የሚያደርግበትእና፤ ተቃዋሚ የሚለውን ስም ገናና እንዲሆን ያደርገዋል፡፡  እንግዲህ የአንድ ፓርቲ ዘመን ማለፉን ደሞ ለመረዳት ለኢሕአዴግ 23 ዓመት የበቃውም አልመሰለኝም፡፡ እየተፈሩእና እየተሸነገሉ በስልጣን ዘመንን መጨመር ምን ያህል ለአየዕምሮአቸው እንደሚመቻቸው አይገባኝም፡፡
አሁን ጉዳዩ ማን ይበልጣል የሚለው ጥያቄ ያለውን ገዢ ፓርቲ አደጋ እንዲያኝዣብብበት ሊያደርገው የሚችለው፤ አንድም ተመቸኝ የሚል በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አለመኖሩ ነው፡፡ በሩ እንደተከረቸመባቸው ዘወትር እንሰማለን፡፡ ይህ ያልገባው ኢሕአዴግ ሕዝብን አምኖ መኖር ሳይሆን መከላከያውን አምኖ መኖር ለጊዜው የጠቀመው ይመስላል፡፡ ደግሞ ደጋግሜ የምናገረው ተቃዋሚ የማይፈቀድበት አገር፤ በገሃድ አምባገነንነትን ማወጅ እና እወቁኝ እኔ ጀግና ነኝ ብሎ ጣት የመቀሰር ያሕል ይሆኖአል፡፡ ምንአልባት ያለው ገዢ ፓርቲ፤ እውነትም ከመቆርቆር እኔ ነኝ የምሻለው ፤ ተቃዋሚ አይጠቅማችሁም ብሎ አስቦ ይሆናል፡፡ ያልተመቸው ህዝብ ግን ልምዱን እራሱ በእራሱ ማየት ይፈልጋል እንጂ፤  እይታው ታማኒነት ሊያሰጠው አይችልም፡፡  ፈሪ የማድረግ ነገርን ማድረግ ማወጅ የሚረዳው፤ ለጊዜው ማዘግየት አልያም ህዝብን በደፈናው በጭፍን እንዲጉዋዝ ሊያደርገው ይችላል እንጂ በእሱ ላይ ያለውን አመለካካት ሊለውጥ አይችልም፡፡ ለሕዝብ ምን ያህል የአስተሳሰብ ችሎታ እንዳለው እንዲረዳእና እራሱን እንዲገመግም እድል  ያልሰጠው ኢሕአዴግ፤ የእኔ አይምሮ ብቻ ነውእና የሚሰራው እኔ ላስብልህ ያለ ይመስላል፡፡ ይህ ፓርቲነት ሳይሆን ሕዝብ ስለማይችል እኔ ሞግዚት ልሁንለት የማለት ያህል ነው፡፡ የተቃዋሚን አለመርባትህዝብ እራሱ አይቶ ሊገመግም የሚችል ብቃት ይኖረዋል እና፡፡ ካልሆነም  አይ ኢሕአዴግ ይሻለኝ ነበር ሊልም ችል ይሆናል ብሎ ትንሽ እረገብ ማለት በተሸለ ነበር፡፡ የግሌ አስተሳሰብ፤  የተቃዋሚ ጋጋታ ለውጥ ያመጣል ብዬ ባላምንም ያለው ገዢ ፓርቲ ህዝብን ከእራሱ ጭምር አብሮ ገደል ለመክተት ጎዳና እንደጀመረ ሊረዳው አልቻለም፡፡ ወይም እያወቀ የፈለገ ይምጣ ያለ ይመስላል፡፡ እኔ ለእራሴ ይህ ጨዋታ አድካሚ ከመሆኑም በላይ ህብረተሰብን ሞኝ ያደረገ በመሆኑ እጅግ በጣም አዝናለሁ፡፡ ለኢሕአዴግ ቀላሉ መንገድ ተቃዋሚን ሁሉ መፍቀድ እና ህዝብ ጋር በግልጥ እንዲተዋወቁ ማድረግ ነበር፡፡ ይህ ግን አስፈርቶታል፡፡ ከገባም ጀምሮ ሁሉም ነገር የሚሽከረከረው በዚህ ተቃዋሚ በሚለው ቴማ ላይ በመሆኑ እኛም የተረጋጋ ህይወት መኖር አልቻልንም፡፡ ብዙዎች አስተሳሰባቸውን የሚገልጹት እንደእኔ፤ ፖለቲካው ላይ ተጽእኖ ለማድረግ ሀይል ወይም እውቀት ኖሮ ሳይሆን የአገሪቱ ሁኔታ አሳዣኝ ደረጃ ላይ በመገኘቱ እና እኛም ሰላምን በመመኘት ነው፡፡ እኔም ከእንግዲሕ ብዙም አስተያየቴን ከመሰንዘር እቆጠባለሁ፡፡ ምክናያቱም እዲንጋ ላይ ውሃ ማፍሰስ ስለሆነ ነው፡፡ ትክክልም ባይሆን አስተሳሰብን መስጠት ሊከበር ሲገባው ግን ኑሮአችን ምስቅልቅል እንዲል ይደረጋል፡፡ ከእንግዲህ እያንዳንዱ ስለእራሱ አስተሳሰብ ቢቆም መልካም ነው፡፡ እኔ አጼ ቴዎድሮስን ወይም በላይ ዘለቀን አልያም ደግሞ መለስ ዜናዊን ልሆን አልችልም፡፡ ይህን ስል ሁሉንም ማመሳሰሌ ሳይሆን ሁሉም ላመኑበት ነገር እስከሞት ተጉዘዋል እና፡፡ ይህ ሁኔታ ዛሬም ሰው ያንን የአንድ ሰው ጀብደኛነት እየጠበቀ መሄድ የማያዋጣ ነገር ነው፡፡ ሲበላሽ በአንድ ሰው መውቀስ፤ ደግሞ እንደገና ለለውጥ ድፍረትም አንድ ሰውን መጠበቅም ዘመኑ ለፈባቸው መሆኑን ተገንዝብን እያንዳንዱ ለሰላም እጁን አጣምሮ መቀመጥ የለበትም፡፡ እናውቃለን አድፍጦ መቀመጥ እና፤ ሁላም የለውጥ አፍ ሲከፈት አበባ እንዳየች ንብ ዙሪያውን መክበብ፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ አስተሳሰቡን ለውጦ ትግልን መካፈል አለበት፡፡ ለማንኛውም ሰው ተማረም አልተማረም፤ ደሃ ሆነም ሀብታም ሆነ፤ ሀይማኖት ይኑረው አይኑረው የኢትዮጲያ ፖለቲካ ወደፊት ልጆቹ የሚያድጉበትን አገር የሲስተሙን ጉዳይ በጋራ አይቶ ለተሸለ ዲሞክራሲ ቢንቀሳቀሱ ጥሩ ነው፡፡ በሌላው መልኩ የመጨረሻ አስተያየቴን የምሰጥበት ምክናያት ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት ከአዲስ አበባ ተነስቶ የወጣ መሆኑን ማንም ስለሚያውቀው ምንአልባት ታግሎ ስልጣን ቢይዝ ለህዝቡ ባይተዋር የሚሆን ባለመሆኑ ከኢሕአዴግ አገባብ የተለዬ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ስለዚህ ኢሕአዲግ ግንቦት 7 ስልጣን እንዳይዝ ከፈለገ፤ የሚቀጥለው ምርጫ ላይ ተቃዋሚዎች በግልጥ እንዲወዳደሩ ማባረሩን ማሳደዱን እና ማሰሩን ቢተው መልካም ነው እላለሁ፡፡ ህዝብን በራሱ የሚያስተዳድረውን መወሰን ግድ ሊለው ይገባል፡፡ እሱ በጠነከረ ቁጥር ህዝብም ጥላቻ እየገነባ ይሄዳል፡፡ የኢትዮጲያ ህዝብ ሞኝ አይደለምእና፡፡ ያም ሆነ ይህ በግልጽ የታዘብኩትን ለመናገር የኢትዮጲያ ህዝብ የበለጠው ክፍል፤ ምንአልባትም 80% ወይም ከዚያ በላይ አሁን ያለውን ገዢ ፓርቲ አይመርጠውም ብዬ ገምቻለሁ፡፡ ይህ የሚሆነው ግን አንዱ በከፍተኛ ግንዛቤ ሌላው ደግሞ በግል በደል እና ዘረኝነትን በምጥላት ይሆናል፡፡ እንግዲሕ ይህን ጽሁፌን ያቀረብኩት ለማበላለጥ ሳይሆን የእኔ የሴቱዋ እይታ ነው፡፡ ለዚህ ውድቀት 23 ዓመት ሙሉ ኢሕአዴግ ዝም ብሎ ቤተመንግስትን ከመጠበቅ እና ልማትን ብቻ ማውራት፤ በእያንዳንዱ ቤት ውስጥ ያለውን በደል፣ ህግ መጣመም እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ያደረሰውን መከራ ዞሮ ለማየት ግዜ አልነበረውም ነበርእና፡፡ ተቃዋሚ ግን ከሕዝብ ከአስተሳሰቡ ጋር ለመገናኘት በቂ ግዜ ወስዶአል፡፡ ሁሉም አቤቱታቸው ወደተቃዋሚ ነበር እና፡፡ ኢሕአዴግስ፤ የለለውን አለ ብለን እንድንቀበል አስገድዶናል አልያም ዘግቶናል፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ግን ኢሕአዴግ ላይ ያለው ከፍተኛ ጥላቻ፤ ህዝብን „የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው“ እንዲል ያደረገው ክፉ ስራ ተቃዋሚዎችን እና ህዝብን እንዳይገናኙ ፕሮግራማቸውን እንዳይለዋወጡ  የማፈን ስራ ጥቁር ነጥብ ጥሎ ያልፋል፡፡ ይህ ግንዛቤን የማያስጨብጥ ጭፍን አካሄድ ወጣቱ እና ችግሩ እንዳይገኛኝ በማድረጉ፤ ኢሕአዴግ   ወደፊት በሚመጣው ችግር እንደመሰረጥ ጣይ ሆኖ በወጣቱ አይምሮ ያልፋል፡፡ እኛም ትናንት ወጣት ነበርን እና፡፡ ላገናዘበው፡፡ በቸር ባዩሽ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen