Sonntag, 8. Februar 2015

ሴትን ያልደበለቀው ትግል ወያኔን ማውረድ አልቻለም




ሴትን ያልደበለቀው ትግል ወያኔን ማውረድ አልቻለም

አንድ ወቅት ላይ በጀርመን በቪዝባድን መሰለኝ አቶ ልደቱ አያሌው መጥተው በወቅቱ ተስፋ ያደረጋቸው እና ይወዳቸው የነበረው ኢትዮጲያዊ አዳራሹን ሞልቶት  ነበር፡፡ እኔም እንደዘወትሩ ከምኖርበት ከተማ ተነስቼ እዛ ሄድኩ፡፡ ጥያቄም አቀረብኩላቸው፡፡ እሱም የኢትዮጲያን ሴቶች በተመለከተ ነበር፡፡ እድምተኛውም ሴት የሚባለውን ቃል ሲሰማ አጉመተመተ፡፡ ሁሉም መስማት የፈለገው ወያኔን ይጥልልናል ብለው ተስፋ ያደረጉትን ቃል ብቻ ነበር፡፡ አቶ ልደቱም እድምተኛውን ለማስደሰትም ጭምር መሰለኝ፤  ጥያቄዬን እንኩዋን ሳያስጨርሱ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው፤የእኔ እህት አሁን የሴቶች ጉዳይ ጊዜው አይደለምበማለት ወሽመጤን ቆረጡኝ፡፡ እሳቸውን ያደንቅ የነበረው ተስፈኛውም በጭብጨባ ቤቱን አደመቁት፡፡ የሴት ጉዳይ የሚፈልግ አልነበረም፡፡ ከዛም በሁዋላ በየአገሩ የኢትዮጲያ ሴቶች  ተሰደዱ፤ ሞትእና በአሰቃቂ ሁኔታ ሬፕ መደረጉም ቀጠለ፡፡ወያኔ ኢሕአዴግም እንደቸኮሉት የሚያወርደው አልተገኘም፡፡
                   ለነገሩ አቶ ልደቱን ለማንሳት ብዬ አይደለም፡፡ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ግን የሚሉት ምላሽ የሴት ጉዳይ ወቅቱ አሁን አይደለም ነበር፤ ቅድሚያ ወያኔን መጣል አለብን ሲሉ አዳምጥ ነበር፡፡ ወያኔ እስከሚወድቅ ግን ብዙ ሚሊዮን ሴት በሞራሉም በአካሉም በአይምሮውም ወደቀ፡፡ ሴት ከፍተኛ አዘቅት ውስጥ ወደቀች፡፡ ወያኔ ኢሕአዴግም ለሴት ጥሩ ነን ብዙ ሴት በሚኒስተሬ ውስጥ ሹሜአለሁ አለ፡፡ በጣት የሚቆጠሩትን ሴቶች ሰብስቦ የስልጣን ማቆያ ፕሮፖጋንዳ አደረገው፡፡ ብዙሀኑ ሴት በዚህ መልኩ ወኪል አጣ፡፡ ሴት እራሱዋን እንዳትጠብቅ ተቃዋሚም ጊዜው አሁን አይደለም እያለ በይክረም አስቀመጠው፡፡  ሴት እናት ናት ስለልጆቹዋ እንድትቆም ጉልበት መሆን የነበረበት የፖለቲካ ፓርቲ ነበር፡፡ ሴት ሚስት ናት፤ ስለባልዋ መጎዳት መቆም የነበረባት ቀዳሚይዋ እሱዋ ናት፡፡ ሴት በአገር ለመኩራት ቀዳሚዋ እሱዋ ነበረችእና አገሩዋን እንድትጠበቅ ሞራላዊ ድጋፍ ያስፈልጋት ነበር፡፡ ግና ሴትን በጉዋዳ ማየት የፈለገ አደባባዩን ብቻውን ይይዛል እና፤ በየሄድኩበት ለማቀርበው ጥያቄ ምላሽ ላገኝ ቀርቶ መሳቂያ እየሆንኩ እመለስ ነበር፡፡ የሚገርመው ግን ካለሴትም እርቆ መሄድ እንዳልተቻለ ማወቅ ያነሰው ወንድ መከበቤን ሳውቀው እኔም እስቅባቸው ነበር፡፡ ዛሬ ግን ከስንት ሞት እና እልቂት በሁዋላ ሴትን ጥሪ ማድረግ ተያዘ፡፡ እሰየው ይህም መቼም ተመስገን ነው፡፡ ለነገሩ ምሁር ሴቶች ሊፕስቲክ እና ጸጉር መቀጠልን ትተው፤ የምታለቅሰውን ሴት ወኪል ቢሆኑዋት መልካም ነው፡፡ ምክናያቱም ለፖለቲከኞቻችን የቀረቡት እነሱ ወረቀት ያላቸው ናቸውእና፤ ወረቀቱን በመስተዋት አስቀምጠው ጨርሻለሁ ከማለት ገና ያልጀመሩት ትግል ይጠበቅባቸዋል እና፤ ወደብዙሃኑ ይጠጉ፡፡ ለትግሉ ይበልጣሉ ለማለት ሳይሆን፤ የኢትዮጲያ ድምጽ ሰሚዎች ሁሉ የሚያምኑት አለባበሱንም ባሳመረ እና ትምህርታቸውን በጨረሱ ባለታይትል ሰው ስለሆነ ትምህርታቸውን እንድንገለገልበት ብቅ ይበሉ፡፡ እኔ ኢሕአዴግ ስልጣን ከያዘ ጀምሬ በየስብሰባው ስሄድ ዘወትር እጮህ ነበር፡፡ መቼም ብሶት ግዜ አይሰጥም እና፡፡ በዛን ወቅት ያየሁት ሴት የለም ለማለት ብደፍር ቅር አትሰኙብኝ፡፡ ይሁንእና ግን እኔ ምንም አይነት ታይትል ያልነበረኝ ሴት ስለሆንኩ ያዳመጠኝ ቀርቶብኝ ያልሳቀብኝ ባልኖረ በወደድኩ ነበር፡፡
                   በትግል ውሥጥ ብዙ ፍርሃት እና ብቸኝነት ውስጥ መሰበርም አለ፡፡ ሌላው የገረመኝ ፖለቲካሊ አክቲቭ የሆኑ ወንዶች እንኩዋን ሚስቶቻቸውን ይዘው አይመጡም ነበር፡፡ እኛ በየአደባባዩ የምንገኘው፤ ጩሆታችን እንደባለጌ እና እንደጋጥ ወጥ ያስቆጠረንን ግዜ አልዘነጋውም፡፡ እንዳውም በአደባባይ ብሶቱዋን የምታቀርብ ሴት እና የምትታገል ሴት እስከዛሬ ድረስ ወጥ እንኩዋን መስራት እንጀራ መጋገር የምትችል የማይመስላቸው ወንዶች ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ያም ሆነ ይህ ትግላቸውም አመርቂ ውጤት ሊያመጣበት ያልቻለበት ነገር ማጤን የፈለገ አልነበረም፡፡ እንዳውም ብዙዎች የሚያገቡዋቸው ሴቶች፤ ለማን ብለህ ነው ኑሮአችንን ትተን የምንታገለው እያሉ ይታገሉ የነበሩትን እንኩዋን ወንዶች ወደሁዋላ የሚያሸሹ ሴቶችን መረጡ፡፡  የሚገርመውም የሸመገሉ ሰዎችም ትንሽ ልጅ ማግባት ጀመሩ፡፡ ትግሉ ሁሉ የተኮላሸው በወንዶች በእራሳቸው ባልተለወጠ ባህል መሆኑን እንዲያውቁት ይገባል፡፡ ኢሕአዴግም የሴቶች ችግር ባላቸውን እንጀራ እንዲያስጋግርላቸው ስለመሰለው ትግሉን ባልና ሚስትን በማፋታት ተያያዘው፡፡ ወንዶችን ለይቶ መምታት ማኮላሸት መሆኑን ያልገባቸው ሴቶች እኩል ሆነናል ገብተህ ጋግረው በማለት እኩልነታቸውን እንዲያበስሩ ገዚው ፓርቲ አስደረገ፡፡ ባልና ሚስት ከተፋታ በሁዋላ፤ መኖሪያ ያጣቸው ሴት ወደአረብ አገር መሰደድ ጀመረች፡፡ ሁሉም ሆኖ ኢትዮጲያ ለጥቂት ተምሮ ወረቀጥ ላገኘ ሴቶች ሁነች፡፡ የሚገርመው፤ ዛሬ ደግሞ አባሮ ለኢሕአዴግ ቅርብ የሆነች ሴት በማግባት ሰላምን በማግኘት ተጠጋግቶ መኖርን ወንዱ መረጠ፡፡ በዚህ መልኩ ሴቶች ዛሬ እወረድንበት አዘቅት ላይ መገኘት ጀመርን፡፡ ሴትን ከትግል አለም ያባረረው ባህል አንድ ሴት ለአምስት ወንድ እስክትደፈር ድረስ ለወረበሎች ታልፈን ተሰጠን፡፡ ሴትን ያላዳመጠ አሞራ ይሆናልእና፡፡
ባዩሽ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen