Sonntag, 8. Februar 2015

የፌደራል ፖሊስ ጀብደኝነት ውርስ ነ



የፌደራል ፖሊስ ጀብደኝነት ውርስ ነው

ለነገሩ እኛ ኢትዮጲያውያኖች አንድ ብንሆን አለምን የሚያሰጋ ጉልበት ይኖረን ነበር፡፡ ለምን መሰላችሁ ሁሉም ጀብድ ስለሚወድ ነው አንደልቡ እያነሳ ሰላማዊ ሰልፍ አደረክ ብሎ የሚጠርዘው፡፡ ትግሬውም አማራውም ኦሮሞውም ሁሉም፤ ልቡ የአንበሳ ልብ ሆነብኝ፡፡ አባባሌ ፌድራል የሚባለው ከሁሉም ዘር ከሆነ ነው የምላችሁ፡፡ ታዲያ አንድ እንድንሆን ያልፈቀደ የፈራ ሀይል ያለ ይመስለኛል፡፡ እግዚአብሄር ይሆን? ታዲያ ዛሬ ለሁለት የተከፈለው፤ የገዢው ፓርቲ እና የተቃዋሚ ሁኔታ በቃ ተጠቂ እና አጥቂ ፈጥሮአል፡፡ ሁለቱ ግን አንድ ቢሆኑ ጉድ ያፈሉ ነበር፤ ደግሞ ሱማሌን ጁቡቲን ኬኒያን ……እያለ አፍሪካን አንድ ማድረግ የሚችል ይሆን ነበር፡፡ ስለዚህ እባብ የልቡን አይቶ እግር ነሳው እንዲሉ፡፡ ሌላ ቦታ መለማመድ ያልቻሉትን የማጥቃት የማስመለስ ዘመቻ በቃ እዛው መወጣት ሆነ፡፡ ታዲያ ሱማሌን ወይ ኬንያን አልያም ፈረንጅን በየት ያገኙታል፡፡ እዛው አገር ውስጥ ጀብዱኛነቱን፤ ይለማመድ እንጂ፡፡ በናታችሁ አሁን ይህ ተቃዋሚ ባይኖር ፖሊስ ምን ሰርቶ ይበላል፡፡ ሰላም በሰላም ቢሆን ማለቴ ነው፡፡ ተቃዋሚ እና ገዢው ፓርቲ ቢታረቁ፤ ፖሊስ ምን ሰርቶ ይበላል፡፡ አዎ ለፖሊሱ ስራ አይጣጣም ነበር፡፡ ለምሳሌ በመንደር የሚያውደለድሉ የሴት ጠላቶች፤ ሴት ላይ አሲድ የሚደፉ፤ የሚደፍሩ፤ ሬፕ የሚያደርጉ፤ ፌደራል ድምጥማጡን ያጠፉልን ነበር፡፡ በናታችሁ ለፖሊሶቹ እልክ ፖለቲከኞች ታረቁ እና፤ እስኪ ምን ሰርተው እንደሚበሉ እንይ፡፡


አንዳንዱ እማ ትንሽ ጣራ አልፎአል መሰል፡፡ ገዢው ፓርቲንም የተፈነተከውን ሰላማዊ ሰልፈኛ ሲያይ እንቅልፉን እንዲባትት  ያደርግበታል፡፡ ባይገርማችሁደም ሳይታይ ነው እንጂ መማታትብለው እንዳይቆጡዋቸው ፍሩልኝ፡፡ ፖለቲከኞች እርቅ ቢፈጥሩ፤  በቃ ፖሊስ ቅነሳ ይደረግ ነበር፡፡ የታክስ ገንዘባችንም ይቆጠብ ነበር፡፡ አሁን ግን ተቃዋሚ በዚህ ከቀጠለ፤ ገዢው ፓርቲ ፖሊሱን ማብዛት ግድ ሊለው ነው፡፡ ወይኔ የታክስ ገንዘባችን ማባከን እኮ ነው የያዝነው፡፡ እኔ ተቃዋሚን ብሆን ይህን ሰልፍ እርግፍ አድርጌ ትቼ፤ ፌድራል ምን እንደሚሰራ አይ ነበር፡፡ እኔ ያሳሰበኝ ግን ስለታክስ ስለገንዘባችን የምቆረቆረው፤ ጉራጌ ሁንኩ እንዴ በናታችሁ? እኔ ብቻ ሆንኩ እኮ የምወተውተው፡፡

የቀልዱ ቀልድ ነውእና ግን ጉራጌዎች መቼም ገንዘብ አያያዝን የሚያውቁ ናቸው፡፡ ትንሹዋን ማሳደግ የሚችሉ፡፡ ለምሳሌ የተዋጣለት ኢኮኖሚስት መሆንም ሊችሉ ይችላሉ፡፡ ብዙ ልምድም ከልጅነት ጀምሮ አካብተዋል እና፡፡ እንዳውም ገንዘብ ሚኒስተሩን እንዳለ ማድረግ ከጉራጌ ብሄር ነው፤ አዎ ጉራጌ፡፡ አማራእና ትግሬ አባካኝ ነው፡፡ በአበል ይጨርሱታል፡፡ ኦሮሞ ደግሞ በመዝናናት፡፡ በውነት በኢትዮጲያ ውስጥ ይቺን አለም ያወቀባት የኦሮሞ ብሄር ነው፡፡ በቃ መደሰት ይችሉበታል፡፡ ሌላውንም ብሄር ማስደሰት ይችላሉ፡፡ መሬታቸው ሀብታም ነው ሞልቶ፤  ስጋው ወተቱ፡፡ እሩዋጭ እንኩዋን የሚወጣው ከኦሮሞ ክልል ነው፡፡ በወተት ያደጉ፡፡  ዛሬማ ለብዙ የሰው አገሩም ተመችተዋል፡፡ ኢንቬስትሜንት በኢትዮጲያ ከተባለ፤ ታዲያ ደቡቡ እና ኦሮሚያ ክልል ነው መሬቱ የሚመች፡፡ በቃ እንግዲህ  ቁጠባ መማር አለብን፡፡ መዝናናትን መቀነስ፤ ደግሞ አላግባብ ፖሊስን የትም እየላኩ አበል አለማውጣት ነው፡፡ እንዳው ለራበው ትንሽ ቢተርፍ ብዬ ነው፡፡ ሆነ ይህ ሁላችሁም ኢትዮጲያውያኖች መሆናችሁ የሚያስታውቀው፤ ሁሉም አንበሳ በእጁ ባይዝም፤ ግና አንበሳ ልብ እንዳላችሁ ተቀበሉት፡፡ የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል፡፡ ሰላም ዋሉሉኝ፡፡ ባዩሽ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen