ትዝታ
ያንን መገፋቱን ምንአልባት ብችለው
እስኪ መቀነቱን ስጡኝ ልታጠቀው
አገር አገር አሉኝ፤ አገር እንደለለኝ
በኔ እየደነሱ ሁሉን ቀምተውኝ
ስጡኝ መቀነቱን ወገቤን ላጥብቀው
አልቻል ያለውን ብሶት እንድችለው
ዳዊቴን ሰቀልኩት አልደግምህም ብዬ
እንዳያበላሸው ጠብ ሲል እንባዬ
ጎበዝ አቀብለኝ ያን መቀነቴን
ጠበቅ ላድርገው ናፋቂው አንጀቴን
እንዴት ነሕ በሉልኝ ያንን ላሊበላ
ጌታ ከፈቀደ አይዋለሁ ሁዋላ
ጊሸን ማሪያም ሂዱ እስኪ ንገሩዋት
ከርሜአለሁ እና ሄጄ ካየሁዋት
መቁዋሚያየን ስጡኝ ደግፍ ልበለው
የደሴን ሚካኤል በርቀት እንዳየው
ያለፍኩትን ሁሉ አልፎአል እንዳልለው
እየተካ እምቢአለ ቀኑ መናጢ ነው
ባዩሽ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen