ብዙ ግዜ ምንም ነገር ውስጥ ታግ እንዳታደርጉኝ ብዬ ጠይቄ ነበር፡፡ ግን ብዙ ሰዎች ከልጅነት ጨዋታ ገና ያልወጡ በመሆናቸው አልያም በውስጣቸው ያበበው የአምባገነንነት ስሜት ሊሰሙኝ አልቻሉም፡፡ እኔ ባዩሽ አበበ የማንም የፖለቲካ አባል ደጋፊም ተቃዋሚም አይደለሁም፡፡ በግሌ ያቀረብኩት አስተያየት ሁሉ ምንአልባት አንደዬ አንዱን ሌላ ግዜ ሌላውን ይነካ ይችላል፡፡ ይህ ማለት እኔ ያንንም ይህንንም አይደለሁም፡፡ ለመሆንም በጭራሽ ፍላጎት የለኝም፡፡ ኢትዮጲያ ውስጥ እንዳየሁት እና እንደተረዳሁት፤ የመንግስት ስራ አስፈጻሚ ብቻ ሳይሆን በህብረተሰብ ውስጥ ሙስና ያለእና የሚኖር ሊጠፋም የማይችል መሆኑን ተገንዝቤአለሁ፡፡ ምንም እንኩዋን ወያኔ ኢሕአዴግ 23 ዓመት በስልጣን ቢቆይም፤ ብቻውን ግን ሙስናን ከሕብረተሰቡ ውሥጥ አጠፋለሁ ማለት የማይቻል ሀቅ መሆኑንም ተገንዝቤአለሁ፡፡ በሌላ መልኩ ተቃዋሚም ቢመጣ እና ስልጣን ቢይዝ ይህንን ልቅ የሄደ የኖረ ሙስና ባህሪ ያስተካክላል ብዬ አላምንም፡፡ ይህንም ያደረገው እርስ በእርሳቸው የፖለቲከኞች መናናቅ እና ሁሉም እንዳገኘ በሚያደርገው የፕሮፖጋንዳ ወሬያቸው ነው፡፡ እንደእውነቱ ሙስና የመታው አገር ውስጥ፤ ለሴት ምንያህል አስቸጋሪ መሆኑን በእራሴ ሕይወት ተረድቻለሁ፡፡ ሙስና የመንግስት አካል የሆነ ስለፈለገው ብቻ ሳይሆን ፤ ከቁጥጥር ውጭ በሆነ የህብረተሰብ ባህሪ፤ ፈሪሀ እግዚአብሄር ማጣት እና ግድየለሽነት፤ የንዋይ ፍላጎት ማደግ ተጠያቂ ሊያደርገው ይገባል፡፡ ይህ ማለት ማንም የህብረተሰብ አካል ከቻለ ብዙ ነገሮችን በሙስና አጣሞ እራሱ ብቻ ተጠቃሚ የሚሆንበትን እና በማተርያል የሚያድግበትን ዘዴ ፈላጊ ሆኖአል፡፡
ልናየው የሚገባ
ለምሳሌ እኔ አንድ ወጣት ልጅ ቀበሌው ሊቀመንበር ጋር በመመሳጠር ለ9 አመት ያህል በራፌን ለጋራጅነት በመውሰድ ስራ እንዳልሰራ እንዳጣ እና እንድከስር ፤ ንብረት ይዠ እምበላው እስካጣ አድርገውኛል፡፡ ይህንንም የአካባቢው ህብረተሰብ በሙሉ እያወቀ ሳለቅስ እና ስሰቃይ ልጆቼን ስበትን ዝም ብሎ ሕብረተሰቡ የምለከት ነበር፡፡ ጭራሽ አበደች እያለ ከልጁ እና ከቀበሌው ስራ አስፈጻሚዎች ጋር በማበር ይሰድቡኝ ይዘልፉኝ ነበር፡፡ ስለዚህ ሙስናን የሚያቆመው ሕብረተሰብ እንጂ ፖሊስ ወይም ዳኛ ሊሆን አይገባውም፡፡ ብዙ የኢትዮጲያ ሙስና የሚካሄደው ግልጥ ባልሆነ መንገድ ነው፡፡ ለዚህ ህብረተሰባችን በቂ ለምድ አካብቶአል፡፡ የሚደብቅለት እራሱ ነውእና፡፡ ወይ እሱ ጥሩ ሰው፤ እሱዋ እየተባለ፡፤ የበላ መጋበዝ ያቅበታል፡፡ አንተ የፈራሃውን በረከት ከቤተመንግስት ወጥቶ እንዲያባርርልህ ትፈልጋለህ፡፡ ነውርን ነውር ለማለት የሚደፍር ባህሪ የለውም፡፡ ነውር የሚሰሩ ሰዎችን ህብረተሰቡ ሲተባበር ነበር የተመለከትኩት፡፡
ሕብረተሰቡ ከቀናው ሰው ጋር አብሮ የመጉዋዝ ባህሪ፤ ከየትም ያምጣው አንቱ ከተባለ አንቱ ነው፤ ሁሉም ሰጋጅ ነው፡፡ ህብረተሰቡ የጋራ ጥቅም የሆነው የባህሪ ለውጥ ለማሳየት የተቸገረ ነው፡፡ ሐብረተሰቡ እንደሌላው አካባቢ እርስ በእርሱ የመጠባበቅ ባህሪ ፤ መንግስትን እንደእራስ የማየት ባህሪ በጭራሽ ኖሮት አያውቅም፡፡ ወያኔ ኢሕአዴግ ባይፈልገውም ይህንን ባህሪ ግን በጭራሽ ሊያስቆም አይችልም፡፡ እንዴት ይህ አስቸጋሪ የሆነ ስልጣን አምሮት፤ እንደውነቱ በስልጣን መቆየት እንደፈለገ ነገሩ እኔን ያስቀኛል፡፡ እኔ በስልጣን ብሆን አንድ ቀንም ኢትዮጲያ ውስጥ ባለስልጣን ለመሆን ፍላጎት የለኝም፡፡ የዚህም ምክናያት ከጥንት ጀምሮ ህብረተሰቡ ለኢትዮጲያ መንግስት የባህሪ ተባባሪነት አልገነባም፡፡ ይህ የመንግስቱሀይለማርያም ችግርም ነበር፡፡ „ ቂጡን በሳንጃ“ ብለዋል፡፡ ሰውየው ከሄዱ በሁዋላ ደግሞ በመጡ ይላል፡፡ አይገባኝም፡፡
ኢትዮጲያን ማስተዳደር በጣም ከባድ እና አስቸጋሪ ነው፡፡ ማንም ከቻለ ሙስናን ይፈልጋል፡፡ በቃ እራሱ በይፋ ሙስና የገቡትን ሰዎች ቤት እየሄደ ድግሱን ይበላል ይጠጣል፡፡ ይህን ፈረንጅ አያደርገውም፡፡ እንግዲሕ የእያንዳንዱን ባለስልጣን ፎቶ በየቤታችን ለጠፈን ያስፈራሩልን እንደሁ አላውቅም፡፡ ነገም ዶ/ር ብርሃኑ ቢመጣ ያው ነው፡፡ በቃ ሕብረተሰቡ መንግስትን በባህሪ ለውጥ መደገፍ አይፈልግም፡፡ አማላጅ እና አንገት ማቅለስለስ፤ ፍርድ እና በማያገባው ገብቶ አድማ ይህ የአድርባይነት ስሜት የገነባ ነው፡፡ መጀመሪያ ሰው ከዚህ አዘቅት ውስጥ መውጣት አለበት፡፡
ሌላው
ልምሳሌ እኔን ታግ አታድርጉኝ፤ በጭራሽ ከምትሉት ነገር ጋር ግንኙነት የለኝምም ብዬ ታግ የሚያደርጉኝን በግልም በሚዲያም ባስተላልፍ ይህንን ቀጥለውበታል፡፡ ይህ ማስረጃነቱ ደግሞ ምንያህል በሕብረተሰቡ ውስጥ አምባገነንነት ሰርጦ እንደገባ የሚያስረዳ ነው፡፡ የግድ እንደእኔ አስቢ የሚለኝ ሰው አልፈልግም፡፡ ለእኔ ማንም ማንም የሚጠቅመኝ የለም፡፡ ሊጠቅመኝ የሚችለው፤ ሶስት ቀንም ቢሆን ስርአት ያለው አገር ማየት ነበር፡፡ ይህ ግን ዘወትር ባለጡንቻ የሚኖርበት አገር እሰየው በማለት ፖለቲከኞች ሁሉ ገዢውም ተቃዋሚውም ኢትዮጲያን ትናንት ገነት ነበረች አልያም ዛሬ እየተባበሉ መሙዋገት ሆኖአል፡፡ ለእኔ እይታ የኤትዮጲያ ገነትነት ጡንቻ ላለው፤ ገንዘብ መክፈል ለሚችል እና ነገርን በጉቦ አጣሞ ማስፈጸም ለሚችል ክፉ እና ደፋር ሰው ነው፡፡ ይህን አይነት ሰው እያደር የሚብስበት እንጂ የመጣ ቢመጣ ሊለውጠው የሚችል የለም፡፡ 23 አመት ሙሉ ወያኔ ላይወድቅ ነገር እርብርቦሽ ከማድረግ፤ 23 ዓመት ሙሉ የባህሪ ለውጥ ላይ የሰው ልጅ አተኩሮ በነበር፤ ኢትዮጲያ በተለወጠች ነበር፡፡
ግን ይህንን ባለጌ ባህሪ ለመለወጥ ቀርቶ ፤ ብልግና በውስጣችን አለ እንኩዋን ብሎ ደፍሮ ሊናገር የሚችል አልተፈጠረም፡፡ ስለዚህ እኛ ማለት በክርስቶስ ስም የምናገረው ነውርን ጎጆ አድርገን በውስጡ የምንኖር እንመስላላን፡፡ ትግሬ ወያኔ ወያኔ ቢል ለኪሱ ነው እንጂ ለወያኔ የሰሩለት ምንም ነገር ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡ ሌሎችም የወያኔ ፓርቲዎች ሁሉ እንደአብዛኛው ሕብረተሰብ ለኪሱ ነው፡፡ በቃ ሁሉም አንድን ገሎ መሸጋገር ብቻ ነው፡፡ ይህ ወያኔ ያመጣው ነው ብለን ደምድመናል፡፡ ስለዚህ ተቀብለነዋል፡፡ ግን ዛሬ ደፍሬ ልናገር፤ ይህ ወያኔ ሳይሆን ባህሪያችን ያመጣው ነው፡፡ ማንኛውም መንግስት የተባለ አካል አገር ቢረጋጋለት የሚደሰት ይመስለኛል፡፡ ግን ካለአጋዥ ማንም የትም አይደርስም፡፡ 23 አመትም በእርግጥም ብዙ ነው ፡፡ በዚህ ባህሪ ስራ መስራትም አልችልም ብሎ ወያኔ ቢደመድም እና ቢለቅ ከዛ በሁዋላ ያለውን ጉድ እናይ ነበር፡፡
ውሸት አፍንጫ ሲሞላ ያስነጥሳል እንዴ ? ብዬ ስገምተው፤ ስለኢትዮጲያ የሚባል ነገር ሳስበው ብዙ ነገር ያበቃልን በገዛ እጃችን እራሳችንን ለውንብድና ተግባር አሳልፈን የሰጠን ነን ብዬ እገምታለሁ፡፡ እራሱ እኔ በእራሴ የተገፋሁት ግፍ በህብረተሰቡ ውስጥ ውነት እውነት አለችእን ብዬ መገመት አላዳገተኝም፡፡
አንድ ነገር አለ፤ ሁሉንም የመንግስት ሰራተኛ መናቅ እና ገደል መክተት ጥሩ አይደለም፡፡ ግን አንድ ነገርነ አለ፤ እነዚህን ጥሩ የሚሰሩ ግን ለመደገፍ እንኩዋን 23 አመት ሙሉ አልቻልንም ነበር፡፡ ምክናያቱም፤ ወያኔ መውረድ አለበት ተብሎ ስለተገመተ፡፡ ወያኔም አልወረደ ሕብረተሰቡም ውስጥ መጥፎ ባህሪ እየሰረጠ ሄደ፡፡ በቃ የሰረቀን ሰው አዳናቂ፤ ጠበል አጣጭ ድግስ በይ የሆነ ሕብረተሰብ መካከል፡፡ እንኩዋን ወያኔ ተቃዋሚም ቢጨመር ማስተካከል አይቻልም፡፡ ማንም ኢትዮጲያን ማስተካከል አይችልም፡፡ ፈሪሃ እግዚአብሄር በምድሩ እንዲጠፋ ዘመኑ የንዋይ ሆኖአል እና፡፡ ለዚህ ነው „አይታ የማታውቀውን የሰው ጃኖ ለብሳ ፤ ነይ ተመለሽ ቢሉዋት ወዴት ተመልሳ „ያልኩት፡፡ ስለዚህ እኔን ታግ አታድርጉኝ፤ በብዙ ሰዎች ባህሪ ኢትዮጲያን ወዴት አቅጣጫ እየሄደች እንዳለች አውቃለሁ እና፡፡ ግን አንድ ነገር አለ፡፡ አንድም ተቃዋሚ ውጭ መትረፍ የለበትም፤ ምክናያቱም፤ ተቃዋሚ የለም ማለት በአገር ውስጥ መደነጋገር ይኖራል እና፡፡ ይህ ገዢ ፓርቲውን አይጠቅመውም፡፡ ሕብረተሰቡ ግን የለመደው ባህሪ ነው፡፡ የቻለ ዘዴ እየፈለገ ይኖራል ያልቻለ ያለቅሳል፡፡ ውሸት በውሸት፡፡ ሁሉ ነገር ውሸት፡፡ እግዚአብሄር ሆይ አንተስ ምን ትላለህ? „ የልባችሁን መሻት መርምሩ“ ባዩሽ